cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
530
Obunachilar
+124 soatlar
+87 kunlar
+5730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

          📖ዳግም ትንሣኤ       📖ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ? በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ሰሙነ ሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤን እንድናከብር ቀደም ሲል በዲዲስቅልያ ኋላም በፍትሐ ነገሥት ታዝዟል፡፡ “እስመ ሰሙነ ዐብይ ሰሙነ ሕማማት እንተ ትተልዋሄ ሰሙነ ትንሣኤ ወዘይትፈቀድ ከመ ናእምር እስመ ዘሐመ ናሁ ትንሣአ” ሲል ይገኛል፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 ፤ የሰሙነ ትንሣኤ መጨረሻው ስምንተኛው ቀን ዳግም ትንሣኤ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣው አንድ ጊዜ ነው፡፡ ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?      📖ዳግም ትንሣኤ የተባለበት ምክንያት፡- በአከባበር፥በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል፡፡ ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም “ፈጸምን አግብዓተ ግብር” ይባላሉ፡፡ “ፈጸምነ” የተባለበትም፤ ሰሙነ ትንሣኤ በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ “አግብዓተ ግብር” የተባለበትም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ… እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ ዮሐንስ 7፥4 በተጨማሪም የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡ ዳግመኛ ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ሳለ ደጁም ተዘግቶ ሳለ፥ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቁሞ እንዴት ሰነበታችሁ አስታረቅኋችሁ” አላቸው፡፡ ሁለት ሰዓት አሳልፎ ስለመጣ “እምድኅረ ሰሙነ” አለ እንጅ፥ በስምንተኛው ቀን ሲል ነው፡፡ በመጀመሪያው መገለጡ ያልተገኘው ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤውን አላመነም ነበርና፤ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ እጆቼንም እይ፤ እመን እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው፡፡ ቶማስም መለሰ “ጌታዬ አምላኬ ሆይ” አለ፡፡ መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤መቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ ሆይ “አለ፡፡ ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ ሕያዊት ሁና፤ (በሕይወት ትኖራለች)በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ያስቀምጧታል፡፡ በዓመት በዓመት በእምቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ፥ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች ዓመት አገልግሎ ያርፋል፤ እንዲሁ በዓመቱ የሚሾመውን ተራምዳ ትይዘዋለች፤ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡ ይህም የሚያስተምረን የጌታን ተአምራት፤ የሐዋርውን ሥልጣንና ብቃት ነው፡፡ጌታም ቶማስ ሆይ! ብታየኝ አመንክን? ሳያዩኝ የሚያምንብኝ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡ ዮሐ 21፥24–29 ለብርሀነ ትንሣኤው ያደረሰን አምላካችን፥ፍጻሜ ሕይወታችን በሃይማኖት የቀናን፤ በምግባር የጸናን ያድርገን! አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን ።አሜን 👇👇👇👇👇👇👇👇ሼር https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

#በስተመጨረሻ_ይዘነው_የምንሄደው_ምንድን_ነው? 🥀ጠቢቡ ሰለሞን ሁሉን አየ ሁሉን አጣጣመ በስተመጨረሻ “ሁሉም ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ፤ ነፋስንም እንደመከተል ነው” ሲል ኑሮን ደመደመ። እንደኔ ሁሉም ከንቱ ነው ሲል ተስፋ ሊያስቆርጠን አይመስለኝም፤ ተስፋን ሊሰጠን እንጂ። ህይወታችን ከማንኛውም አለማዊ ሃብት፤ ከማንኛውም ዝና ከማንኛውም ክብር የላቀች መሆኗን ሲነግረን ይመስለኛል። ይህንን በቅጡ መረዳት ስለሚሳነን፤ በስተመጨረሻ ይዘናቸው በማንሄዳቸው አላፊ ነገሮችን ኑሮዋችንን እንበጠብጣለን። 🥀ኑሮ ማለት በውልደት እና በሞት መካከል ያለ የመሸጋገሪያ ጊዜ ነው። በድንገት ተጀምሮ በድንገት የሚቆም የመሸጋገሪያ ጊዜ። ጥቂቶች ይህንን የተረዱ ጊዜያቸውን አጣጥመው ይኖራሉ። አብዛኛዎቻችን ግን ዘላለም እንደሚኖር ሰው ተዘናግተን እንኖራለን። መልካም ነገር ሳናደርግባቸው በተራ ነገር የሚያልፉ ቀናቶች ከቆምንበት ህንጻ ስር እየተሸረፉ እንደሚወድቁ ጡቦች ይቆጠራሉ። ቀስ እያሉ ከከፍታው የሚያወርዱን። 🥀ሁሉም ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ ምክንያቱም ምንም ነገር በሞት ፊት ቆሞ ሞትን የሞጋፈጥ ነገር ስለሌለ። ይህን የተረዳ ሰው ትልቁን ቀንበር ከላዩ ላይ አወረደ ማለት ነው። የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ከልቡ ያደርጋል ምክንያቱም እድሉ አንደ ብቻ እንደሆነች ስለሚረዳ። እውነት ከሞት ፊት ቆሞ በቀልን የሚያስብ ማነው? ከመቃብሩ ላይ ቆሞ ገንዘቡ የሚያሳሳው ማነው? በከፈን ውስጥ ሆኖ የሚጠላውን ሰው የሚያስብ የሚቀና ማን ነው? በእርግጠኝነት ማንም። በሞት ፊት ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፤ የከንቱ ከንቱ። 🥀በስተመጨረሻ ይዘነው የምንሄድ ምንም ነገር የለም።ይልቅ የመሸጋገሪያ ጊዜያችንን መልካም እናድርገው። ተሰጥዖችንን እናበርክት፤ ማናችንም ያለተሰጥዖ አልተፈጠርንም። ተራ ሆነን መሞትን አንምረጥ። የራሳችንን አሻራ አኑረን፤ ነበሩ ለመባል ያብቃን። ሰለሞን ከንቱ ናቸው ያላቸው ነገሮች ህይወታችንን የሚያጨልሙና የምድር ቆይታችንን መራራ የሚያደርጉትን ነገሮች ነው። ህይወታችን ክቡር ናት፤ ከማንኛውም ነገሮች ሁሉ የከበረች የፈጣሪ ስጦታ። እኛ ግን በኪሳራ እየቸረቸርናት ነው። ፍቅር የሌላት ህይወት፤ እምነት የራቃት ህይወት፤ ሰላም የጎደላት ህይወት፤ ደስታ የሌለባት ህይወት ያለዋጋዋ የተሸጠች ናት። ምክንያቱም በዚህ ምድር የህይወታችንን ዋጋ የሚስተካከል አለማዊ ነገር ስለሌለ። 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

. ❤ልደታ ለማርያም❤ግንቦት ፩ እንኳን አደረሰን!!! 💟ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር: 💟እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ:ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ:አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን: 💟አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት: 💟እሱአም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም:ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው:: 💟እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቱአቹአል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው: 💟እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሱአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች: 💟ከዛም ፀንሳ በ9 ወሩአ ሴት ልጅ ወለደች:ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት:ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት:ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት:ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት;ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት:ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት:ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች:: 💟ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆተረላቸውምና አልተፃፈም:ይህቺም ሃና በስራት በቅጣት አደገች:ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት:: 💟እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ:ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ: 💟ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ:እያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ:አትናቀኝ:ፀሎተን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ:ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:ሃናም በበኩሉአ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች: 💟እንዲ ብለው ስይዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቹአ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኅኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች: 💟እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን:ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው: 💟ከዚያም በሁአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግንተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት: 💟ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው:ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ:የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው:7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው:ምልአቱ:ስፍሃቱ:ርቀቱ:ልእልናው:ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: 💟ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱአ ንጽህናዋ:ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቱአ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሱአ ነው:ይህንኑም ራእይ ያዩት ሃምሌ 30 ዕለት ነው:: 💟እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን:ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም:ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ: 💟ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሱአን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች(በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና): 💟እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ:ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት:የሃናም የአጎቱአ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቹአ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት: 💟እርሱአም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት:አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን:እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማሁአቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሱአ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ:: ❤""እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::"" 💟እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም የተወለደችበት እለት በአባት እናቱአ ቤት ፍስሃ ደስታ ተደረገበት ቤቱንም ብርሃን መላው በስምንተኛውም ቀን ""ማርያም"" ብለው አወጡላት::
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

1
💟ስለምን ማርያም ብለው አወጡላት ቢሉ:እነሆ በዚ አለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን "ማር" ነው:በገነትም በህይወት የተዘጋጁ ጻድቃን ቅዱሳን "ያም" የሚባል ምግብ አላቸው :: 💟ከዚ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ ስለዚህ "ማርያም" ብለው አወጡላት::የእመቤታችን ማርያም ስም ተነቦ ሳይተረጎም ይቀር ዘንድ አይገባምና:- ❤""ማ"" ማለት ማህደረ መለኮት: ❤""ር"" ማለት ርግብየ ይቤላ: ❤""ያ"" ማለት ያንቀዓዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት: ❤""ም"" ማለት ምስሃል ወምስጋድ ወምስትሥራየ ኃጥያት ማለት ነው:: 💟አንድም "ማርያም" ማለት ልዩ ከጣዖት:ክብርት እምፍጥረታት:ንጽህት እምሃጥያት:መልክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው:ዳግመኛም "ማርያም" ማለት ተፈስሂ ቤተ ይሁዳ ወተሃሠዪ ቤተ እስራኤል ማለት ነው:: 💟አንድም "ማርያም" ማለት መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው:ይህስ እንዴት ነው ቢሉ:እነሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሱአም በፍቅሩአ: 💟በጣዕመ ፍቅሩአ የሰውን ሁሉ ኃጥያት:ክፋት ፍቃ ከልጁአ ከወዳጁአ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ስለዚህ መርህ ለመንግስተ ሰማያት አሉአት::አንድም ማርያም ማለት ሰረገላ ፀሃይ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሄር ወሰብእ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ውብህት(ስጥውት) ማለት ነው:: ❤በዚህ በግንቦት አንድ ቀን እመቤታችን አለምን ልታስምር ከቅድስት ሃና እና ከቅዱስ እያቄም በብዙ ልመና ተገኘች:: ❤የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሩአ ጣዕሙአ በረከቱአ ረድኤቱአ አማላጅነቱአ በእውነት በኛ አማላጅነቱአን በምናምን ልጆቹአ ላይ ይደርብን:: 👇👇👇👇👇👇share join https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

“ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤”   — ሮሜ 6፥5 ✨እንኳን ደስ አላችሁ ሞትን ድል አድርጎ ጌታችን ተነስቷል✨ ✝ ለመላው ✝ የክርስትና ✝ እምነት ✝ ተከታዮች ✝ በሙሉ ✝ እንኳን ✝ ለትንሳኤ    ✝ በዓል ✝ አደረሳችሁ ✝ 👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

👍 1
#ቅዲሜ 1. ቀዳም ስኡር ይህች ዕለት (የተሻረችው ቅዳሜ) ትባላለች ምክንያቱም እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በሰንበት እለት የግልም ሆነ የአዋጅ ጾም በፍጹም አይጾምም። ውጉዝም ነው። ነገር ግን በዚህች የሕማማት ቅዳሜ ይህ ሥርአት ይሻራል ይጾማልም።ስለዚህ የተሻረችው ቅዳሜ ተባለች። በዚህ እለት የሚጾምበት ምክንያት እናቱ እናታችን ድንግል ማርያምና ቅዱሱ ሐዋርያ ዮሐንስ የጌታን ሞት አይተው እስከትንሳኤው ምግብን አልቀመሱም ነበር።ያን መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ከቻልን ከአርብ ጀምሮ ከከበደን ደግሞ ከቅዳሜ ጀምሮ ቀኑን ሙሉና እስከሌሊቱ 9:00 እናከፍላለን እንጾማለን። 2. ለምለም ቅዳሜ ትባላለች ምክንያቱም በዚህ እለት ጠዋት በቤተክርስቲያን ካህናት ለሕዝበ ምእመናን ለምለም ቀጤማን ያድላሉ።ምእመናንም ይህን ቀጤማ በጭንቅላታችን እናስራለን። ይህም ምስጢር "ለኔ ሰላምን ልትሰጠኝ አንተ የእሾህ አክሊል ደፋህ እኔን ልታነግሰኝ አንተ ተንገላታህ የክብር አክሊል ልታረግልኝ የሾህ አክሊል አረክ " ስንል ነው። 3. ቅዱስ ቅዳሜ ትባላለች ቅዱስ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ሥነ ፍጥረታትን ፈጥሮ ጨርሶ ያረፈባትና የቀደሳት ስትሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ስለሰው ልጅ ሲል በቤዛነት ያደረገውን የማዳን ሥራ ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር አረፈ፥ በነፍሱም ወደ ሲኦል ወርዶ በሲኦል ለ5500 ዘመናት ሲሰቃዩ የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ ወደ ዘላለም ረፍት ወስዷቸዋልና ይህች እለት ቅዱስ የሆነች ልዩ እለት ትባላለች። የሰሙነ ሕማማት ተከታታይ ጽሑፋችንን በዚሁ አጠናቀናል ዛሬ ሌሊት በቤቱ እንገናኝ ሰላም ሁኑ ! ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ join 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

👍 1
+ የሚያምር እግር + በጸሎተ ሐሙስ ልብን የሚሰውር አንድ ነገር ተፈጽሞ አለፈ፡፡ ይህም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር የማጠቡ ነገር ነው፡፡ የሰውን የቆሸሸ እግር እያሸ የሚያጥብ አምላክ ፣ የተማሪዎቹን እግር የሚያጥብ መምህር ፣ የባሪያዎቹን እግር የሚያጸዳ ጌታ ማየት እንዴት ያስጨንቃል? እስቲ ለአንድ አፍታ ወደዚያ ቤት በሕሊናችን ተጉዘን እንግባና ጌታን እግር ሲያጥብ አብረን እንመልከተው፡፡ የአምስተኛው ክፍለ ዘመን ባለቅኔ የቅዱስ ኤፍሬም ተማሪ ሶርያዊው ቄርሎና በመንፈስ ሆኖ ያንን ቤት በዓይነ ሕሊናው እንዲህ ቃኝቶት ነበር ፦ ‘ጌታ ውኃ ቀዳና መታጠቢያውን ተሸከመ፡፡ የማበሻ ጨርቅ ያዘና ታጠቀ፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ፡፡ ሕሊናዬን አንዳች ነገር ሲወጋው ተሰማኝ ዕንባዬም ፈሰሰ፡፡ በፍርሃት ፊቴን ሸፈንኩ ዓይኖቼንም በመሳቀቅ ዞር አደረግሁ፡፡ ሲያጥባቸው ለማየት አቅም የለኝምና ብወጣ ተመኘሁ’ ይላል፡፡ (Hymns of Cyrillona, On The Washing of the feet, Gorgias Press pg 72)እውነትም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጎንብሶ ማጠብ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ ጌታችን ሐሙስ ዕለት ያደረገውን ነገር መጥምቁ ዮሐንስ ቢያይ ኖሮ ምን ይል ይሆን? ጌታ ሊጠመቅ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ ዮሐንስ ‘አንተ እንዴት ልትጠመቅ ወደ እኔ ትመጣለህ?’ ብሎ አልነበር? መጥምቁ ዮሐንስ ሆይ ና ተመልከት! በአንተ በባሪያው እጅ ሊጠመቅ ሲመጣ ስለ ትሕትናው የተደነቅህበት ጌታ ዛሬ ደግሞ አጥምቁኝ ከማለት አልፎ የባሪያዎቹን እግር ሲያጥብ አጎንብሶ ታየ፡፡ አንተ ‘የጫማውን ጠፍር ተጎንብሼ ልፈታ አይገባኝም’ ያልክለት ጌታ አጎንብሶ የሐዋርያቱን ጫማ ሲፈታና እግራቸውን ሲያጥብ ብታይ ምን ትል ይሆን? በዮርዳኖስ ዳር ‘አንተ እንዴት ልትጠመቅ ወደ እኔ ትመጣለህ?’ ያልከውን ጌታ ቅዱስ ጴጥሮስ ‘አንተ እንዴት የእኔን እግር ታጥባለህ?’ ሲለው ተመልከት! በእርግጥ በዮርዳኖስ ወንዝ ከታየው ትሕትና የበለጠ ትሕትና በዚያች የመታጠቢያ ውኃ ውስጥ ታየ፡፡ ውኃ በተሞላ በአንድ ማስታጠቢያ ውስጥ የፍጡር እግርና የፈጣሪ እጅ አንድ ላይ ሆነው የታዩበትን ያን ቅጽበት እጅግ ታላቅ ትሕትና ተማርንበት፡፡ ፍጡር ፈጣሪውን ሲያጠምቀው ከማየት በላይ ፈጣሪ የፍጡርን እግር ሲያጥብ ማየት ድንጋይ ልባችንን የሚሰብር ቅጽበት ነው፡፡ ከመጥምቁ ዮሐንስ በፊት የነበሩት ነቢያትስ ይህንን ቢያዩ እንዴት ይደነቁ ይሆን? ኢሳይያስ ሆይ ‘ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ሆኖ አየሁት’ ያልክለት ጌታ ዝቅ ባለ መቀመጫ ላይ ቁጭ ብሎ የአሳ አጥማጆችን እግር ሲያጥብ ተመልከተው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ሆይ ‘እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን’ ብለህ የዘመርክለት ጌታ እግር እያጠበ ነው፡፡ የሚገርመው እግር ከማጠቡ በፊትም ውኃ አስቀረበ አይልም ምክንያቱም ውኃውን የቀዳውም እርሱ ራሱ ነበረ፡፡ አብርሃም ለእንግዶቹ እንዳለው ‘ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ’ ብሎ ውኃ አላስቀዳም፡፡(ዘፍ. 18፡4) ራሱ ውኃውን ቀድቶ በመታጠቢያው ሞልቶ የባሪያዎቹን እግር አጠበ፡፡ ለነገሩ በትሕትና የተጠመቀበትን የዮርዳኖስን ወንዝስ ቢሆን በውኃ የሞላው እርሱ አልነበረምን? ጴጥሮስ ተጨነቀ ፤ ‘ጌታ ሆይ አንተ እንዴት የእኔን እግር ታጥባለህ?’ አለና ተከላከለ፡፡ የጴጥሮስ ጭንቀት ብዙ ነገር ከማሰብ የመነጨ ነው፡፡ ‘ኪሩቤል በፊትህ ግርማ እንዳይቃጠል ፈርተው በፊትህ ሲቆሙ በክንፎቻቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ፡፡ ታዲያ እኔ እጠብልኝ ብዬ እንዴት ደፍሬ እግሬን እሠጥሃለሁ? ሱራፌል የልብስህን ጫፍ የማይነኩህ ጌታ የእኔን እግር እንዴት ታጥባለህ? በባሕር ላይ በአንተ ትእዛዝ የተራመድሁት አይበቃኝም? እንዴት እግርህን ልጠብህ ትለኛለህ? ይህንን ዕዳ እንዴ እሸከመዋለሁ?’ የሚል ጽኑ ጭንቀት ያዘለ ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታ ግን ዕውር ባበራባቸው እጆቹ እግር አጠበባቸው፡፡ ሸክላ ሠሪው አጎንብሶ የሸክላውን እግር አጠበ፡፡ ሰውን ከምድር አፈር የፈጠረው አምላክ ትቢያውን በክብር አስቀምጦ እግሩን አጠበው፡፡ ጌታችን ያጠበው ከሰዓታት በኋላ እግሬ አውጪኝ ብለው ጥለውት የሚሸሹትን የደቀ መዛሙርቱን እግሮች ነበረ፡፡ ለአንድ ሰዓት እንኳን አብረውት ሊተጉ የማይችሉትን ተማሪዎቹን እግር አጠበ፡፡ ጥለውት እንደሚሔዱ እያወቀ ‘ንጹሐን ናችሁ’ ብሎ አወደሳቸው፡፡ ‘ወደ አብ እንደሚሔድ አውቆ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው’ እንደሚል ምድር ላይ በቀረችው ጊዜ ያልከፈለው የፍቅር ዕዳ እንዲኖርበት አልፈለገምና ጊዜውን ለመውደድ ተጠቀመበት፡፡ የሚወዳቸውን ደቀ መዛሙርት እግራቸውን አጥቦ በፍቅር ተሰናበታቸው፡፡ ጌታ ሆይ የእኔንስ እግር የምታጥበው መቼ ነው? በእውነት በምድር ላይ ከእኔ እግር በላይ የቆሸሸ አለ? ያልረገጥሁት የኃጢአት ጭቃ ፣ ያልነካሁት የበደል ቆሻሻ እንደሌለ አታውቅምን? ‘በክፉዎች ምክር የሔደ’ እግሬን የማታጸዳው ለምንድን ነው? (መዝ. 1፡2) ‘የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም’ ብለህ የለምን? እውነት ነው ፤ እግሬን ከኃጢአት ከከለከልክልኝ ሌላውን አካሌን ማዳንህም አይደል? አጥብቀህ ከምትጠላቸው ነገሮች መካከል አንዱ የሆነውን ‘ወደ ክፉ የሚሮጥ እግሬን’ የማታጥብልኝ ለምንድን ነው? (ምሳ. 6፡18) እባክህን እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ፡፡ በእርግጥ የሐዋርያትን የቆሸሸ እግር በውኃ እንዳጠብከው አስበን አደነቅን እንጂ በማግሥቱ ደግሞ የዓለምን ኃጢአት በደምህ አጥበሃል፡፡ ከዳንሁ በኋላ የቆሰልሁትን ፣ ከታጠብኩ በኋላ ያደፍሁትን እኔን በከበረ ሥጋና ደምህ ከኃጢአቴ እድፍ ታጥበኝ ዘንድ ነው ልመናዬ፡፡ በጌታ እጅ የታጠበው የሐዋርያት እግር እንዴት የታደለ ነው? በእሱ ስለታጠበ ዓለምን ዞሮ ወንጌል ለማዳረስ የቻለ እግር ሆነ፡፡ ጌታ ያላጠበው እግር ወንጌል ለዓለም አያደርስም፡፡ ባልታጠበ እግራችን ብንዞር እኛ እንጂ ወንጌል ዓለምን አይዞርም፡፡ ስለዚህ ሐዋርያ ሊሆን የሚሻ ሁሉ ጌታ ሆይ እግሬን እጠብልኝ ብሎ መለመን አለበት፡፡ ወንጌሉም ‘የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ’ ይላልና ክርስቶስ ደቀ መዝሙሩ ሊሆኑ ለሚወዱ ሁሉ እግራቸውን ማጠቡን አሁንም አያቋርጥም፡፡ ጌታ ያጠበው እግር ምን ይሆናል ካልከኝ ‘የሚያምር እግር ይሆናል’ እልሃለሁ፡፡ ሐዋርያት እግራቸው እጅግ ያምር ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ በእግሩ እብጠት የማይንቀሳቀሰው ቅዱስ ያዕቆብ ሳይቀር እግሩ ያማረ ነበር፡፡ ምክንያቱም ‘መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው?’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡ ሮሜ 10፡15 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሚያዝያ 24 2016 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም ፤ ፳ኤል 👇👇👇👇👇👇👇👇share join https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

ጉልባን ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡ ምንጭ፡- ስምዐ ተዋሕዶ (ልዩ ዕትም ዘሰሙነ ሕማማት) እንበለ ደዌ ወሕማም፥ እንበለ ጻማ ወድካም፥ ያብፀሓነ አመ ከመ ዮም። 👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል‼ 1. አክሊለ ሦክ (ወደ 70 የሚደርስ ራስ ቅሉ ላይ የተተከለ የብረት እሾኽ የያዘ ዘውድ ወይም አክሊል)። 2. ተኰርዖተ ርእስ (ራሱን በዘንግ ወይም በዱላ መመታቱ/መቀጥቀጡ)። 3. ተጸፍኦ መልታሕት (ጉንጩን ወይም ፊቱን በጥፊና በቦክስ መመታቱ)። 4. ሰትየ ሐሞት (ተጠማሁ ብሎ ስለ ውሃ ፋንታ መራራ ሐሞትን መጠጣቱ)። 5. ወሪቀ ምራቅ (በፊቱ በአካሉ ላይ በንቀትና በጥላቻ በመሳለቅ በመዘባበት ፊቱ ላይ ምራቅ መትፋታቸው)። 6. ተቀስፎ ዘባን (6,666 ጊዜ የሾለ አጥንትና ብረት በታሰረበት ጅራፍ መገረፉ)። 7. ተአስሮ ድኅሪት (የፍጥኝ ወደኋላ መታሰሩ ...በአፍ ጢሙ መደፋቱ)። 8. ፀዊረ ጒንደ ዕፀ መስቀል (የሚሰቀልበትን የእንጨት መስቀል መሸከሙ)። 9. ሳዶር (ቀኝ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር)። 10. አላዶር (ግራ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር)። 11. ዳናት (ቀኝ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር)። 12. አዴራ (ግራ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 13. ሮዳስ (ደረቱ ከመስቀሉ ጋር እንዲጣበቅ ከታሰረበት ሽቦ ጋር ልቡ ላይ የተቸነከረ...) አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እሊህ ናቸው ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያሉ በመቁጠር መናገር ነው እንጂ የመከራው ብዛት የስቃዩ ጽናት በቁጥር የሚገለጽ ሆኖ አይደለም!!! ጌታ ሆይ! ሕማምህ ይፈውሰን ዘንድ ቁስልህ እንዲሰማን ማስተዋልን ስጠን ‼ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም አሜን! ምንጭ ፦ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇share https://t.me/othodox12
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

👍 1
E). Gaaffiii waa'ee du'a ka'umsaa Saaduqoonni (gartuu Yihuudotaa du'aa ka'umsatti hin amanne) Gooftaa gaafatan. (Maat.22:23-33). F). Gaaffii waa'ee abboommiiwwanii irratti Farisoonni Gooftaa gaafatan! (Maat. 22:34-40). G). Gooftaan waa'ee Masihii abdachiifame sanaa Fariisota gaafachuu isaa. (Maat. 22:41-xum). H). Gooftaan uummanni barumsa (raacatii) Barsiisota seeraa fi Fariisota kana irraa akka of eeggachuu qaban dubbachuu isaa. (Maat. 23: 1-27). J). Gooftaan adabbii gartuu Yihuudotaa kana irra gahuuf jiru dubbachuu isaa fi Iyyerusaalemiif bo'uu isaa. (Maat. 23:29-xum). K). Gooftaan waa'ee bara dhumaa, mallattoolee bara dhumaa fi dhufaatii Isaa lammaffaa barsiisuu isaa. (Maat Boq 24 guutuu isaa). L). Mootummaa Waaqayyoof maal qabannee akka qophaa'uu qabnuu fi akkasuma Makliitii nutti kennameen firii buusnee argamuu akka qabnu (Maat.25:1-30) M). Murtoo bara dhumaa sana (Maat. 25:31-Xum). ►Egaa kana hunda booda ture ifatti Gooftaa irratti himata banuu fi isa fannisuuf marii kan jalqaban! 🙏Waaqayyo, dhibee fi dhukkubbii; dheebuu fi dadhabbii tokko malee akkuma har’aan nu gahe guyyaa du’aa ka’umsa isaatiin nagaa fi gammachuun nu haa gahu. Ameen!🙏 👇👇👇👇👇👇👇share join godha https://t.me/othodox12 👆👆👆👆👆👆👆👆share godha.
Hammasini ko'rsatish...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .