uz
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Kanalga Telegram’da o‘tish

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Ko'proq ko'rsatish
213
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-430 kun
Postlar arxiv
ግርም ከሚሉኝ የሕይወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የእመት ዓኢሻ ነው፡፡ ግና በ18 ዓመቷ ነቢዩ ተለዩዋት፡፡ አሥር ዓመት እንኳን ከነቢዩ ጋር አልኖሩም፡፡ ዓኢሻ ገና በአፍላ ወጣትነቷ ነበር ያ
ግርም ከሚሉኝ የሕይወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የእመት ዓኢሻ ነው፡፡ ግና በ18 ዓመቷ ነቢዩ ተለዩዋት፡፡ አሥር ዓመት እንኳን ከነቢዩ ጋር አልኖሩም፡፡  ዓኢሻ ገና በአፍላ ወጣትነቷ ነበር ያዉም በእጅጉ የምትቀናባቸዉን ተወዳጅ ባለቤቷን ያጣችው፣ ልጅ አልነበራትም፡፡ የሚገርመው “ልጅ ይኖረኝ ዘንድ ዱዓ አድርጉልኝ” ብላ ነቢዩን ወትዉታለች የሚል ሐዲሥ አልተገኘም፡፡ ልብ በሉልኝ። ከርሣቸው ህልፈት በኋላ 47 ዓመታትን ብቻዋን ነው የኖረችው፡፡ አዎ ብቻዋን። አላህ ለዓኢሻ ልጅ ያልሰጣት ስለሚጠላት ነው የሚል ይኖር ይሆን?? አላህ ምንን ለምን እንደዳደረገ የሚያውቅ ጌታ ነው፣ አንችን ባርያዉን አይጠላም እሺ። እናታችን ዓኢሻ አላህ ልጅ ስላልሰጣት መፈጠሯን አልጠላችም፣ በአምላኳም አላማረረችም። እምነቷን አልቀየረችም። 'የኔስ ተለየ' አላማረረችም። የሷ ባልሆነው ልጅ 'ኡሙ ዐብደላህ' ተብላ እየተጠራች ሙሉ ሕይወቷን በዒባዳ፣ በዕውቀትና በጂሃድ አሳለፈች፡፡ ትላልቅ ሶሐቦች ከሷ ተምረዋል፣ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን ለብዙዎች ታስረዳ ነበር፡፡ ከዚህ ምን እንማራለን መሰለሽ ... ልጅ ስለጠፋ፣ ትዳር ስለጠፋ፣ ቤት መኪና ስለጠፋ … ሕይወት አትቆምም ትቀጥላለች፡፡ ዱንያ የፈተና ምድር ናት፣ እሷ ለማንም ሳታደላ ሁሉንም ትፈትናለች። ሃሳባችንን ሁሉ ተስፋ ሳንቆርጥ ለአላህ እንንገር፣ ለነገሮችም ከልክ በላይ አንጓጓ። ከሆነ ሆነ፣ ካልሆነ ፈሶብሩን ጀሚል .. ዉብ ትዕግስት ብቻ ነው ሚያዋጣው። ዓኢሻን የፈተነች ዱንያ እኛን ብትፈትን ምኑ ይገርማል። የሀብት ይሁን የልጅ፣ የትዳር ይሁን የሥራ ሪዝቅ አላህ ባለው ጊዜ ይመጣል ኢንሻአላህ አይቀርም። ሄደንበት ካልመጣና ከደከመን በራሱ ጊዜ ይምጣ እንተወው። አላህ የሚወደዉን ነገር ብቻ እንናገር።  ከሱ መልካም ነገር እንጠብቅ። ©ሙሃመድ ሰዒድ

سبحان الله ምንኛ ያማረ መልስ ነው ምንኛ ያማረ መጠጊያስ ነው !! Join:- YouTube.com/@SecretsofTruth tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/ReshadMuzemil

🔸: مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ 🔹:ከእርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ (20:55) ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

📌 የታላቁ የረመዷን ወር ሁለት ወራት ብቻ ቀሩት! 🔻 ረጀብ 🔻 ሸዕባን 🔸 አላህ በሰላም ከሚደርሱትና ፁመው ተቀባይነትን ከሚያገኙት ባሮቹ ያርገን🤲🤲
📌 የታላቁ የረመዷን ወር ሁለት ወራት ብቻ ቀሩት! 🔻 ረጀብ 🔻 ሸዕባን 🔸 አላህ በሰላም ከሚደርሱትና ፁመው ተቀባይነትን ከሚያገኙት ባሮቹ ያርገን🤲🤲

O Allah, bless our Prophet Muhammad, peace be upon him
O Allah, bless our Prophet Muhammad, peace be upon him

⭕️ // ከትዝብቴ ማህደር // 🔰 ኋላ ቀርነት ሰዎችን ዱንያዊ በሆነ ጉዳይ ከሸሪዓ ጋር አያይዘን በምንመክራቸውና በምንገስፃቸው ወቅት እኛን «ኋላ ቀር» አመለካከት ያለው ሰው አድርገው ሊቆጥሩን ይችላሉ‼️ወይም በተግሳፁ ሊሸማቀቁ፣ ሊሳለቁ አሊያም ሊያፍሩ ይችላሉ። .... .... ይሄኔ ሊከፋን፣ ልናዝን፣ ልንናደድ አሊያም ልንበሳጭ እንችላለን። ነገር ግን እኛ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር እኛ ለአላህ ብቻ ብለን ከመጥፎ ስንከልክልና በጥሩ ስናዝ ምንዳውን (አጅሩን) ከአላህ እናገኘዋለን። ኢንሻአላህ!! ግዴለም፤ ነገሮችን በአዕምሯችን እንደፈለግን ማድረግ ሳይሆን በሸሪዓ ሚዛን በመመዘናችን «ኋላ ቀር ናችሁ» ብሎ የሚያስብ ተውት እያሰበ ይኑር። ግዴለም፤ ለአላህ ብለን ሸሪዓዊ ምክርን ስንመክራቸው ካፌዙና ካላገጡ ተዋቸው ያላግጡ ውጤታቸውን ከአላህ ያገኙታል። አዎ እኛ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል፦ ከውድቀት መማር ብልህነት፣ ደካሞችን መርዳት ጠንካራነት፣ ለሰዎች መጨነቅ አዛኝነት፣ ሰዎችን ማክበር አዋቂነት፣ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅነት እንዲሁም ለአላህ ብሎ ሰዎችን በጥሩ ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል የሁሉም ኃላፊነት አድርገን መልካም የሆኑ ማንነቶችን ተንከባክበንና ኮትኩተን ማሳደግ ይኖርብናል። ...... ... እኛ ላይ የሚሰነዘሩ ወቀሳዎች፣ ዛቻዎች ወይም ትችቶች ከምንሰራው መልካም ነገር ሊያርቁን ሳይሆን ይበልጥ እንደ ብረት ሀዲድ ጠንካራ ሊያደርጉን ነው የሚገባው። ለአላህ ብሎ መልካም ነገርን የሚፈፅም ሰው ለምንስ ሲል ተስፋ ይቆርጣል!? አጀሩን የሚከፍለን አላህ አይደለን⁉️ አዎ ለአላህ ብለን፣ ከሱ ምንዳን ፈልገን ስራዎችን ስንሰራ ለተስፋ-ቢስነት ምክንያት አይኖረንም፤ ሊኖረንም አይገባም‼️ ውድ እህት ወንድሞች ሆይ! ▬ ለአላህ ብላችሁ ሰዎችን ስትመክሩ፣ ስትገስፁ ትችት ወቀሳ አስተናግዳችሁ ይሆናል። ግን አብሽሩ አጅሩን ከአላህ ታገኙታላችሁ ኢንሻአላህ!! ተስፋ ሳትቆርጡ ሰዎችን መርዳት መደገፍ፣ በጥሩ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከላችሁን አታቁሙ። አላህ አቅሙንም ሶብሩንም እንዲሰጣችሁ ዱዓ አድርጉ!! በአላህ ፍቃድ የስራችሁን ፍሬ ከአላህ ታገኙታላችሁ። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ► ለአላህ ብላችሁ ዱንያዊ በሆነ ጉዳይም ሆነ አኺራ በሆነ ነገር ላይ ሰዎችን በሸሪዓ ህግጋቶች የምትመክሩና የምትገስፁ እህት ወንድሞቼ ለአላህ ብየ እወዳችኋለሁ!! እነዛ ይወቁ ሸሪዓ ˝ኋላ-ቀር አይደለም˝ ፤ ኋላ-ቀሮቹና የማንጠቅም እርባና-ቢሶች «ሸሪዓን ኋላ-ቀር» ነው ብለን የምናስብ ሰዎች ነን!! ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ቀን:- ህዳር 21/2016 አ.ል [Dec 1/2023 G.C] Join:- YouTube.com/@SecretsofTruth tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/ReshadMuzemil

አንገብጋቢ እውነታ…❗️ ▫️ዱዓ ለችግር ጊዜ ና ለጭንቅ መገላገያ መንገድ ብቻ የምናደርገው መሆን የለበትም። ◾️ይህች ዱንያ የፈተና አለም ነች ። እኛም ወደሷ  የመጣንበት  ምክንያት ለ አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ አምልኮን ለመፈፀም ነው ። ስለዚህ ዱአ የምናደርገው  አላህን ለመገዛትም መሆን ይኖርበታል   ። ረሱልም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፦ "الدعاء هو العبادة " " ዱዓ እሱ ልሹ አምልኮት ነው " ▫️ ለአላህም ትክክለኛ ባሪያ መሆን  ከፈለክ ይህን ነገር በቀንም በማታም  ሁሌም አስታውሰው ...... ◾️አላህን በ ልቅናው ፣ በውበቱ ፣ በታላቅነቱ ፣ በሀያልነቱ ፣ በችሮታው እና በለጋሽነቱ ተዋወቀው ። ይህም እዝነቱን ተስፋ በማድረግ ፤ ትሩፋቱን በመፈለግና  ቅጣቱን  በመፍራት  እንድትገዛው ይረዳሃል። ✔️  ዱዓ የምታደርገው ጌታህ እንድትጠይቀው ስለሚፈልግና እሱም ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ኢባዳ ስለሆነ  ነው ። ✔️ዱዓ የምታደረገው  አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ሊጠየቅና ሊለመን የሚገባው ጌታ ስለሆነ ነው ። ✔️ዱዓ የምታደርገው የአላህን á‰˝áˆŽá‰ł ፈልገህና áŠĽáˆąáŠ• ለማመስገን ፣ ለማላቅና   በብቸኝነት ለመገዛት መሆን አለበት ። 🔘ለአላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ያለህን ተገዢነት ማረጋገጥን አላማህ አድርግ ። ዱዓን á‹¨áˆŤáˆľáˆ…ን የግል ፍላጎት ማሟያ ብቻ አደርገህ እንዳታስበው ። እንዲሁም ለሆነ ጥበብ ምክንያት አላህ ምላሹን ያዘገየበህን ጥያቄህ አላህን ከመለመን ሊከለክልህ አይገባም ። 🔘በአላህ እዝነት ፣ ጥበብ ፣ ፍትሐዊነትና ለጋሽነት ያለህ እምነት ሕይወትህን በአጠቃላይ የሚሞላ መሆን አለበት እንጂ ለጊዜያዊ ፍላጎትና ዱንያዊ አላማዎችህ ለማሳካት  ብቻ መሆነ የለበትም። ▫️ሕይወት áˆ˛á‰Łáˆ የዚህችን አጭር ሀያት ዱንያ ብቻ አደርገህ እንዳታስብ ። ሕይወት ሲባል ከዚህ ጠባብ ትርጉም እጅጉኑ የሰፋ ሲሆን የቀብርንና የ አኼራን ሃያት አጠቃሎ ይይዛል። ◾️ስለሆነም በሁሉም የሕይወትህ ክፍል ዘላቂን ደስታን የምታገኘው የዱንያ ሀያትህ ብቻ ስለተሟላልህ እንዳልሆነ ማስታወስ ይኖርብሃል። ምክንያቱም ዱንያ አንተ ሳትፈልጋትም ልትመጣለህም ትችላለች ወይም አላህ ከተወሰኑ ትሩፋቶቿ   ከልክሎህ ላንተው ለ አኺራህ ሊያስቀምጥልህ á‹­á‰˝áˆ‹áˆá˘ አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ቸር መሆኑን አትዘንጋ  ። ጠያቂውን አይመልስም። ወይ በጠየቀው ዱአ ሊመጣበት ያለን ችግር  ይመልስለታል ። አልያም ደግሞ ለአኼራው ያስቀምጥለታል ። ✔️ስናጠቃለለውም ዘላለማዊ የሆነን ደስታ የሚፈልግ ሰው  የባርነትን ደጃፍ ያንኳኳ !!! ፅሁፍ✍ : ፈውዝ ቢንት አበዱለጢፍ ኩርዲ ትርጉም : ቢንት አብደላህ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 https://ummalife.com/ReshadMuzemil ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        ©️ Toleha Ahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛

⇢ ሙሳ አለይሂ አሰላም መድየን ሲደርስ ቤትም ፣ ስራም ፣ ሚስትም አልነበረውም ። መልካምን ሾል ሰርቶ  ዘወር አለና እጁን ወደ ሰማይ ከፍ አደረገ :   { رَبِّ إِنِّى لِمَآ أَنزَلْتَ إِلَىَّ مِنْ خَيْرٍۢ فَقِيرٌ} «ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ» አለ፡፡ 【 አል - ቀሰስ  24】 የዚያ ቀን ፀሃይ ሳትገባ ነበር ቤትም ስራም ሚስትም ያገኘው ። ሰበቡን አድርስ…! በጌታህ ላይም ተመካ … ! በእርግጥም ጣፋጭ ፍሬዎችን ትቀጥፋለህ 🌸🍃 አላህ ይወፍቀን! ⛅️⛅️⛅️ መልካም ንጋት ⛅️⛅️⛅️ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 https://ummalife.com/ReshadMuzemil ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        ©️ Toleha Ahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛

🔰 አላህን መታዘዝ ► ጌታችንን መታዘዝ እላይ ያደርሰናል። እሩቅ እንኳን ብንሆን ቅርብ ያደርገናል❗️ ● መልካምነታችን ብዙ ቦታ ይሰራጫል። በሄድንበት ሁሉ መልካም ይገጥመናል! ➢ አላህ ለሚያውቀው ጥበብ መጥፎ የሆነ ነገር ቢገጥመን እኳን መወጣጫ መሰላሉን ያበጅልናል! ▮ምድር ላይ ተከብረን እንኖርበታለን፤ በሰራነው ስራም ምስጉን እንሆናለን❗️ https://ummalife.com/ReshadMuzemil

🔰 ሶብር ያስፈልጋል ከእኛ የሚጠበቀው በመልካም እሳቤ (ንያ) ጥረት ማድረግ ነው። ጥረታችንን እጥፍ ድርብ አድርጎ ወደ ስኬት መቀየሩ የአላህ ነው! ► ለመልካም ጥረታችን ምንዳውን የሚመነዳንም (አጅሩን የሚከፍለንም) አላህ ነው። ⭕️ ስለዚህ ነገሮች ምንም ያህል ቢከብዱን፣ ሰዎች ባይረዱን፣ ሰዎች ስለእኛ የማይሆን ነገር ቢያስቡም...... ሶብር ያስፈልገናል ማለት ነው! ► ጥረታችን፣ ልፋታችንን አላህ በእዝነቱ በብዙ እጥፍ አባዝቶ አጅሩን የሚሰጠን እሱ (አላህ) ነውና ተስፋ አንቆርጥም። ► የምንሰራው ነገር ለአላህ ብለን እስከሆነ ድረስ ተስፋም መቁረጥም አይገባንም። ❌ ተስፋ የሚቆርጡ ደካሞች ብቻ ናቸው❗️ ወንድማችሁ:- ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

የተጠርጣሪው ማንነት የሚያሳይ ተጨማሪ ፎቶ! የደበቃችሁ አካላት በራሳችሁ ላይ እየፈረዳችሁ መሆኑን እወቁት። አጋልጡ! ማንኛውም መረጃ ያላችሁ፦ 011-1-11-01-11 ላይ ወይም በነፃ የስልክ መስመር
+1
የተጠርጣሪው ማንነት የሚያሳይ ተጨማሪ ፎቶ! የደበቃችሁ አካላት በራሳችሁ ላይ እየፈረዳችሁ መሆኑን እወቁት። አጋልጡ! ማንኛውም መረጃ ያላችሁ፦ 011-1-11-01-11 ላይ ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ ደውሉ። ★ በተገኘበት እንዲያዝና ሁሉም ሲያየው እንዲያውቀውና ጥቆማ እንዲሰጥ ማንነቱን የሚያሳዩ ፎቶዎችን በሁሉም ሚዲያዎች እናሰራጭ። የሸይኻችን ግፍ ተዳፍኖ አይቀርም በአላህ ፈቃድ። ሁላችንም ፎቶውን በተለያዩ ገፆች በማሰራጨት እንረባረብ።

ለማንኛውም የእውነት ከልባችን ለሃይማኖታችን የምንቆረቆር ከሆነ ቅስም ሰባሪ ሰሞንኛ ስሜት ሲከሰት ብቻ ሳይሆን ሁሌም ለዲን አስተማሪዎች በቂ ትኩረትና እንክብካቤ እንስጥ። በዙሪያችን ወይም በአካባቢያ
ለማንኛውም የእውነት ከልባችን ለሃይማኖታችን የምንቆረቆር ከሆነ ቅስም ሰባሪ ሰሞንኛ ስሜት ሲከሰት ብቻ ሳይሆን ሁሌም ለዲን አስተማሪዎች በቂ ትኩረትና እንክብካቤ እንስጥ። በዙሪያችን ወይም በአካባቢያችን ወይም የትም ቢሆኑ የምናውቃቸውን መሻይኾች፣ ዱዓቶች፣ ኢማሞች፣ ሙአዚኖች፣ የመስጂድ ጥበቃዎችና የፅዳት ሰራተኞች ጭምር በማገዝ ላይ እንረባረብ። ምናልባት በዚህ ሰዓት መታከሚያ ወይም ቤተሰብ ማሳከሚያ ያጡ ስንት ይኖሩ ይሆን? የእለት ጉርስ የተቸገሩስ? የቤት ኪራይ ያጨናነቃቸውስ? የመስጂድ ኮሚቴዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ ሃላፊነት የሚሰማችሁ ወይም ማስተባበር የምትችሉ ሁሉ ክፍተት ያለበትን እያጤናችሁ የድርሻችሁን ተወጡ። አላህ ይሁነን። ©️ Ibnu Munewor

ታላቁ ዓሊም እንዲህ እንተደፉ ቀሩ⁉️ ኪታባቸውን እንደያዙ፣ ከጀርባ በአንድ አረመኔ በተተኮሰባቸው ሽጉጥ ተመተው፣ ለየቲሙ ልጃቸው የገዙት ዳቦ በደማቸው ተለውሶ፣ በዚያ ጨለማ እንዲህ ተደፉ። ዒልም ተ
ታላቁ ዓሊም እንዲህ እንተደፉ ቀሩ⁉️ ኪታባቸውን እንደያዙ፣ ከጀርባ በአንድ አረመኔ በተተኮሰባቸው ሽጉጥ ተመተው፣ ለየቲሙ ልጃቸው የገዙት ዳቦ በደማቸው ተለውሶ፣ በዚያ ጨለማ እንዲህ ተደፉ። ዒልም ተደፋ! የሸይኽ ዐብዱ ያሲን ሞት ልጆቻቸውን ብቻ አይደለም የቲም ያደረገው፤ መላው የሰፈሩ ሰውም የቲም ሆኗል። የሰበሰቡትን ጀማዓህ ጨለማ ላይ ነው ጥለውት የሄዱት። የሰፈሩ ሙስሊም ውስጡ ደምቷል። አላህ ይዘንላቸው። እንዲህ በግፍ ለገደላቸውም አላህ የሚገባውን ፍርድ ይስጠው። || ©️ Murad Tadesse

Narrated Hisham's father: Aisha said, "I went to Abu Bakr (during his fatal illness) and he asked me, 'In how many garments was the Prophet () shrouded?' She replied, 'In three Suhuliya pieces of white cloth of cotton, and there was neither a shirt nor a turban among them.' Abu Bakr further asked her, 'On which day did the Prophet () die?' She replied, 'He died on Monday.' He asked, 'What is today?' She replied, 'Today is Monday.' He said, 'I hope I shall die sometime between this morning and tonight.' Then he looked at a garment that he was wearing during his illness and it had some stains of saffron. Then he said, 'Wash this garment of mine and add two more garments and shroud me in them.' I said, 'This is worn out.' He said, 'A living person has more right to wear new clothes than a dead one; the shroud is only for the body's pus.' He did not die till it was the night of Tuesday and was buried before the morning." "حَدَّثَنَا مُعَلَّى بْنُ أَسَدٍ، حَدَّثَنَا وُهَيْبٌ، عَنْ هِشَامٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ دَخَلْتُ عَلَى أَبِي بَكْرٍ ـ رضى الله عنه ـ فَقَالَ فِي كَمْ كَفَّنْتُمُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَتْ فِي ثَلاَثَةِ أَثْوَابٍ بِيضٍ سَحُولِيَّةٍ، لَيْسَ فِيهَا قَمِيصٌ وَلاَ عِمَامَةٌ‏.‏ وَقَالَ لَهَا فِي أَىِّ يَوْمٍ تُوُفِّيَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَتْ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ‏.‏ قَالَ فَأَىُّ يَوْمٍ هَذَا قَالَتْ يَوْمُ الاِثْنَيْنِ‏.‏ قَالَ أَرْجُو فِيمَا بَيْنِي وَبَيْنَ اللَّيْلِ‏.‏ فَنَظَرَ إِلَى ثَوْبٍ عَلَيْهِ كَانَ يُمَرَّضُ فِيهِ، بِهِ رَدْعٌ مِنْ زَعْفَرَانٍ  فَقَالَ اغْسِلُوا ثَوْبِي هَذَا، وَزِيدُوا عَلَيْهِ ثَوْبَيْنِ فَكَفِّنُونِي فِيهَا‏.‏ قُلْتُ إِنَّ هَذَا خَلَقٌ‏.‏ قَالَ إِنَّ الْحَىَّ أَحَقُّ بِالْجَدِيدِ مِنَ الْمَيِّتِ، إِنَّمَا هُوَ لِلْمُهْلَةِ‏.‏ فَلَمْ يُتَوَفَّ حَتَّى أَمْسَى مِنْ لَيْلَةِ الثُّلاَثَاءِ وَدُفِنَ قَبْلَ أَنْ يُصْبِحَ‏.‏" Sahih al-Bukhari, 1387 In-Book Reference: Book 23, Hadith 139 Join:- YouTube.com/@SecretsofTruth tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/ReshadMuzemil

ኪታባቸውን ተንተርሰው ወደቁ ❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️ በሳኡዲ የሸህ ኡሰይሚን ደረሳ የነበሩ፤ሱደይስን ተጅሪድ ያቀሩ  ታላቁ ዓሊም ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በርካቶችን እያስተማሩ ነበር። አሁን አስኮ በድር መስጅድ ኸጢብ ከመሆናቸው በፊት አፍንጮ በር የሚገኘው አቅሷ መስጅድ ያቀሩ እንደነበር የሚታወቁት በነሲሀ ቲቪም ሲያስተምሩ ይታወቃሉ። ትናንት ምሽት ኪታባቸውን ተንተርሰው ለልጃቸው  የገዙትን ዳቦ በትነው የወደቁበት ቦታ ላይ የዳቦው ፌስታል በደም ጨቅይቶ አየነው። ከጀርባቸው ሲመቱ አይነ በሲሩን አረቡን ቤቱ እየሸኙት ነበር። ወደ አረቡ ቤት አቅንተን  የሆነው ሁሉ ሲቃ እየተናነቀው አጫወተን።  አረቡ እንደነገረን ከመግሪብ እስከ ኢሻ ተፍሲር ሲያቀሩ አመሹ። ለዚያውም ሱረቱል ዙመርን ሲያብራሩ አመሹ። ሁሌም እንደሚያደርጉት መስጅድ በር ላይ ሲዋክ የሚሸጠውን አይነ በሲሩን አረቡን ለመሸት ጠበቁት። አረቡ ሁሌ እንደሚያደርገው «ኡስታዝ  አይጠብቁኝ ይሂዱ» ይላቸዋል። እሳቸው እሽ አይሉም።  ከኢሻ በኋላ ለአረቡ ምርኩዝ ናቸው። እንጀራ አይበላም ለሚሉት ለልጃቸው  ዳቦ ገዝተው አረቡን ቤቱ እየመሩ አስገብተው ነው ወደቤታቸው የሚገቡት። ትናንትም አይነ በሲሩን አረቡን እየመሩ ወደቤታቸው ሲሄዱ መታጠፊያ አሳቻ ቦታ ላይ ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ሽጉጥ ከጀርባቸው በኩል ተመተው የወደቁ ሲሆን በወቅቱ አረቡም ራሱን ስቶ አብሮ ወድቆ ነበር። በተመቱበት ሰዓት በአካባቢው መብራት ጠፍቶ እንደነበርና ከወደቁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መብራት መምጣቱን የአካባቢው ሰዎች ነግረውናል። እዳ ያስጭንቃቸው እንደነበር እና በሽማግሌዎችም የተሰጣቸው ጊዜ አጭር በመሆኑ ያሳስባቸው እንደነበር የተወሰነውን ተበድረው ከፍለው ቀሪውን ለመክፈል ቤታቸውን ለመሸጥ እንዳሰቡ ነገር ግን የበድር መስጅድ ጀመዓዎች ቤቱ ከመሸጡ በፊት ትላንት ፈጅር ላይ ለመስጅድ ጀመአ ዛሬ እሁድ ገቢ ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ እንደነበር ነገሩን። እናንተ የአላህ ባሮች ኢማማችንን ሸኻችንን ከየቲም ልጆቻቸው ጋር እና ከእዳቸው ጋር ለኛ ትተው ተገድለዋል። ከቀብራቸው በፊት እዳ ለመክፈል እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኮሚቴዎች አካውንት የከፈቱና የገለጹ ስለሆነ ፖሊስ ገዳዩን አጣርቶ ለህዝብ ይፋ እስኪያደርግ የመስጅድ ኢማም እንደመሆናቸው መጠን መጅሊስ በቅርብ ርቀት ዜናው ከተሰማበት አንስቶ ከሚመለከተው አካል ጋር ሲከታተል እንደነበረው ሁሉ ማህበረሰቡም ደግሞ እዳውን እንዲከፍል  ጥሪ ቀርቧል። የኢማማችን ባለቤት በቅርብ ጊዜ ወደ አኸራ የተሻገሩ በመሆኑ የቤቱ አስተዳዳሪ አባት ሸይኽ አላህ ይዘንላቸው ያለውን ክፍተት እንሙላ። አስተባባሪ ኮሚቴ ስም የተከፈለ የሂሳብ አካውንት ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የአካውንት ስም:- ጀሚል ሁሴን ፣ ሲሩ ሀሰን እና አብዱ ዑስማን  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000592716309

«ነፍሴ በ እጁ በሆነው ጌታ ይሁንብኝ! በሰዎች ላይ ገዳይ በምን ጉዳይ እንደገደለ፣ሟች በምን ምክኒያት እንደተገደለ የማይታወቅበት ዘመን ይመጣል!» ―ሸይኽ ዐብዱ ያሲን'ን አላህ ማረፊያቸውን ጀነት ያ
«ነፍሴ በ እጁ በሆነው ጌታ ይሁንብኝ! በሰዎች ላይ ገዳይ በምን ጉዳይ እንደገደለ፣ሟች በምን ምክኒያት እንደተገደለ የማይታወቅበት ዘመን ይመጣል!» ―ሸይኽ ዐብዱ ያሲን'ን አላህ ማረፊያቸውን ጀነት ያድርግላቸው!

አለም ብትጠፋ የተሻለ ነው! ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿والَّذي نفسي بيدِهِ لقَتلُ مؤمنٍ أعظمُ عندَ اللَّهِ من زوالِ الدُّنيا﴾ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው እ
አለም ብትጠፋ የተሻለ ነው! ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿والَّذي نفسي بيدِهِ لقَتلُ مؤمنٍ أعظمُ عندَ اللَّهِ من زوالِ الدُّنيا﴾ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! አንድን አማኝ ከመግደል ይህቺ አለም ብትጠፋ አላህ ዘንድ የላቀ (የተሻለ) ነው።” 📚 ነሳዒ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 3997

« እኔ ዱዓውን የማድረግ ሀሳብ ነው ያለብኝ፤ ዱዓውን የማሳካት ጭቀት የለብኝም» እሱ የአላህ ነው❗️ ኢማሙ ሻፊዒይ