uz
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Kanalga Telegram’da o‘tish

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Ko'proq ko'rsatish
213
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-430 kun
Postlar arxiv
📌ጥያቄ 📌 ሴት ልጅ ወንዶች ባሉበት ግሩፕ ውስጥ ድምጵ ማሰማት ትችላለች ማለቴ ድምጷን በመቅዳት መልቀቅ ትችላለች⁉️ ✅መልስ ✅ በመጀመሪየ ደረጃ በኡለሞች መካከል ያለው ልዩነት በሴት ልጅ ድምፅ ላይ ያለው ነገር ነው። እሱም አመዛኙና በላጩ ንግግር ድምፅን ማጣፈጥና ማማለል እስከሌለበት ድረስ የአጅነቢ ሴት ድምፅ ዓውረት (ለአጂነቢ የተከለከለ ሀፍረት ነገር)  አይሆንም። ምክንያቱም አላህ በቁርአኑ እንደሚለው:— 🔵"እናንተ የነብዩ ሴቶች ሆይ ... ድምፃችሁን አታለስልሱ፣ ምክምያቱም በልቡ በሽታ ያለበት ሰው ይማረካልና።" ⚫️አህዛብ፣32 ✅ ስለዚህ አስፈላጊና የግድ ሆኖ ሲገኝና ውስጡ ማማለልና ማለስለስ ከሌለበት የአጅነቢ ሴትን ድምፅ መስማቱ የሚከለከልና ወንጀለኛ የሚያደርገው አይደለም። ለዚህም ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር ሴት ሶሀቦች መጥተው በዲን ጉዳይ ያላቸውን ጥያቄዎችና ቅሬታቸውን ያቀርቡ ነበር። 🚫ነገር ግን ይህም ሆኖ እያለ ሴት ልጅ #አዛን ማድረግ ፣ ወንዶችን #ማሰገድ ፣ ኹጥባ ማድረግ ፣ ሶላቷ ውስጥም ከኢማሙ ችግር ሲፈጠር ተስቢህ አትችልም። ምክንያቱም ድምጳን ማሰማቷ ፊትናና ሌሎች ችግሮችን እንዳይቀሰቅስ ስለሚፈራ ነው‼️ ⭕️ ከዚህም በመነሳት ወንዶች ያሉበት ግሩፕ ውስጥ ሴቷ ድምጷን ቀርፃ መላኳ የግድና በጣም አስፈላጊ ካለሆነ አይቻልም ፣ ለምሳሌ ዲናዊ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ መፃፍ ካልቻለችና መፃፍ ብትችልም ከፅሁፍ ይልቅ በድምፅ ይበልጥ ግልፅና የሚብራራ ይሆናል ተብሎ የሚታሰብ ከሆነ ከላይ እንደተገለፀው ድምጷን ሳታማልልና ሳታሳምር በኖርማል አነጋገር መናገር ትችላለች። ነገር ግን አሁንም ቢሆን በፅሁፍ መግለፅ የሚቻል ከሆን በድምፅ የሚከለከል ይሆናል። 📚የሳኡዲ የኢልም ጥናትና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth Fb.com/SecretsofTruth1

=UTF_8B4Yuo4Yi04Ym1IOGIjeGMheGKlSDhi4g==.mp32.05 MB

በደጋግ ቀደምቶች ዘመን ሴት ወንዶችን ታስተምር ነበርን ? 🏷በድጋሚ የተለቀቀ بسم الله الرحمن الرحيم وبه أستعين وصلاة ربي وسلامه على خير المرسلين وبعد. 🔸"ሴት ልጅ በድምጽ ሚዲያ ላይ መሳተፍ የለባትም" ሲባል ዓኢሻን رضي الله عنهما    ጨምሮ በርካታ ሴቶች ወንዶችን ያስተምሩ አልነበር?! እያሉ  በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሐቅና ባጢልን ለማቀላቀል የሚፈልጉና አላዋቂዎችንም የሚያደናብሩ ሰዎች አሉ 💥ዓኢሻም ትሁን ሌሎች አደባባይ ላይ ሙእሚኑም ሙናፊቁም ባለበትና ሁሉም ድምጻቸውን በሚሰሙበት መልኩ አልነበረም የሚያስተምሩት፣በቋሚነትም ወንዶችን አያስተምሩም ነበር፣ እቤታቸው ውስጥ ተቀምጠው እውቀትና መረጃ የሚፈልግ ሰው መጥቶ ሲጠይቃቸው ነበር የሚያስተምሩትና ጥያቄን የሚመልሱት   🔹ሴት ልጅ ሴቶችን እንኳ በአካል ለማስተማር እያለች በብዛት ከቤት መውጣት እንደሌለባት  ከዘመናችን ሊቃውንቶች  አልባኒን ጨምሮ ዑለሞች በግልጽ አስቀምጠዋል 🔸ሴት ወንድን ስታናግር ድምጿ የሚፈትን ከሆነ   አፏ ውስጥ ድምጿ የመፈተን ኀይሉን እንዲቀንስ የሚያደርግ ነገር ማድረግ እንደሚገባትም ኢማም አን`ነወዊይ ኪታቡል አዝካር ላይ እና ሌሎችም ጠቅሰዋል!   🔹ሴት ልጅ ሐጅና ዑምራ ላይ ተልቢያ (ለብይክ... ስትል)፣ እንዲሁም ተክቢር ስታደርግ፣ ወንድ ባለበት ሰላት ስትሰግድ ድምጿን ከፍ ማድረግ እንደሌለባት መላው የዲን ሊቃውንት ዘንድ የሚታወቅ ነገር ነው 🔸ሴት ልጅ እንደ ወንድ አዛን የማትለውና ኹጥባም የማታደርገው ለዚሁ ነው! 💥ዲኑ ይህን ሁሉ ከልክሏት ሳለ ሴት ልጅ ድምጿን እያሳመረች አንዳንዴም እየሳቀችና እየቀለደች ሚዲያ ላይ ትሳተፍ ይባላልን!!? 🔹ወንድና  ሴት ለሓጃ ( ለጉዳይ ወይም ለግዴታ ነገር) እንጂ መነጋገር የለባቸውም! ዝም ብሎ ያለ በቂ ምክንያት ማናገር አይገባም የተባለው ድምጿን መስማቱ የፊትና በር ስለሚከፍት ነው 🔸በተለይ ዘመናችን ፆታዊ ፈተና እጅግ በጣም የተስፋፋበት፣ ሙናፊቅና የቀልብ በሽታ ያለባቸው ሰዎችም የበዙበት ዘመን ነው 💥በእንዲህ ዓይነቱ ዘመንና ሁኔታ ላይ ሴት ልጅ በድምጽ (አልፎም በቪዲዮ) ሚዲያ ላይ ትሳተፍ ማለት የሚያስከትለውን መዘዝ ያለማስተዋል ወይም የግዴለሽነት ምልክት ነው! 🔹ሁሉንም ፆታዎች ማስተማር በመሰረቱ የወንዶች ኀላፊነት ነው ለዚህም ነው ነቢያት በሙሉ ወንዶች የነበሩት! ሆኖም ሴቶችም ለሴት ወገኖቻቸው ሸርጡ ተሟልቶ ማስተማር ይችላሉ 💥ግን ሚዲያ ላይ ወጥተው በድምጽ ያስተምሩ ጋዜጠኛ ሆነው ከወንድ ጋር ቃለ-ምልልስ ያድርጉ (አርት!) ላይ ይሳተፉ  ወዘተ ማለት በነቢዩ (ﷺ)ጎዳና ላይ አንገቱን ደፍቶ የሚጓዝ ሰው አስተሳሰብ የማይቀበለው ነገር ነው! ✍ ኡስታዘ አሕመድ ሼኽ  ኣደም 27/7/1439ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ 🔹🔸🔹🔸 በድምፅ ከታች ተለቋል። tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth Fb.com/SecretsofTruth1

Duʿāʾ for those who have been wronged: The best supplication that the one who is wronged may offer concerning the wrongdoer i
Duʿāʾ for those who have been wronged: The best supplication that the one who is wronged may offer concerning the wrongdoer is that which was narrated from the Prophet (ṣall Allahu ʿalayhi wa-’ālihi wa-sallam) by Jābīr who said: The Messenger of Allāh (ṣall Allahu ʿalayhi wa-’ālihi wa-sallam) used to say: «الَّلهُمّ أَصْلِحْ لِيْ سَمْعِي وَبَصَرِيْ ، وَاجْعَلْهُمَا الوَارِثَيْنِ مِنّي ، وَانصُرنِي عَلَى مَنْ ظَلَمَنِي ، وَأَرِنِي مِنْهُ ثَأْرِي» Allāhuma aṣliḥ lī samʿī wa baṣarī wa ajʿalhumā alwārithain minnī wa anṣurnī ʿalā min ẓalamanī wa arnī minhu thārī. O Allāh, correct my hearing and my sight, and allow me to retain them until I die. Lead me to victory over those who have done me injustice and allow me to see vengeance. [al-Buḵẖarī (rahimahullāh) in al-Adab al-Mufrad 1/226, Ṣaḥiḥ al-Albani (rahimahullāh) 1/421 and Anẓr al-Duʿāʾ at-Ṭabarānī (rahimahullāh), 426] tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth Fb.com/SecretsofTruth1

#Intro #Qur'an #Sheik_Fewzan

በሱጁደ ቲላዋ ጊዜ ኢማም ሆኖ ሚያሰግድ ሰው ማድረግ ያለበትን ጥንቃቄ 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

〽️ እውነትም አልኖረች እኛ ካሌለናት - ከጎኗ ከእውነት፤ በሷ እየኖርን - እኛ ካለደገፍናት፤ ሰውነታችን አምሮ - ካላሸበረቀንባት፤ እውነተኛ ካልሆንን - ተዘፍቀን በውሸት፤ መያዛችን አይቀርም - በአንድ ቀን ቁጭት፤ እየኖርን ሳለ - የመብረቅ ጋጋታ፤ አይናችን አንጋጠን - አምላኬ ይቅርታ፤ ይሀው አካላችን - በእውነት ተረታ፤ ምንም ብናስመስል - በደቂቃዎች ቆይታ፤ የምንሞት መስሎን - የያዘን ብዥታ፤ መፍራት ስንጀምር - የውሸታችን ኮታ፤ መቁጠርም ስንጀምር - የባጢላችን ብዛት፤ አውጥተን ስናሰላላስል - የውሸታችንን ይዘት፤ ለካስ ጎተራ ሞልቷል - የጥፋታችን ቅዠት፤ እውነትም አልኖርም በሚል - ከበቀለችበት ጠፋች፤  እኮ በኛ ጥፋት - በቅፅበት በረገገች፤ ከአፍንጫየ ውጡ ብላን - ጎራዋን ቀየረች፣ የሚናገራትን ፍልለጋ - ከውሸተኞች ራቀች። --- ለካስ ነገሩ - እንዲህ ነው፤ እኛ ነን ያልገባን - ሁኔታውን ያልተረዳነው፤ የእውነትን እውነት - እኛ ነን ያላወቅነው፤ ለካስ ወገኖቼ ነገሩ ወዲህ ነው፤ እውነት ቤት ስትሰራ - ውሸት ላግዝ ካለች፤ ጭቃ ከረገጠች - ሚስማር ካቀበለች፤ ቤቱም አልተሰራ - እውነትም አልኖረች ቤቱም አልተሰራ - እውነትም አልኖረች። ግጥም:- በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል https://t.me/SharpSwords1 www.youtube.com/@SharpSwords1 Twitter.com/SharpSwords1 tiktok.com/@sharpswords1 tiktok.com/@techmasterpage

ክፍል (101)፦ ዑለማዎችን ማጣጣል በማን ተጀመረ? ጉዳቱስ ምን ይመስላል? 🔎http://bit.ly/34botHF ክፍል (102)፦ አሕባሾች ያመጡት የእምነት/የዐቂዳ መዘዝ 🔎http://bit.ly/34dzR5O ክፍል (103)፦አሕባሾችና ኡማውን መከፋፈል    🔎 http://bit.ly/36rqtxe ክፍል (104)፦የአሕባሾች ረብሻ በዓለም ዙሪያ 🔎 http://bit.ly/2LK98Y6 ክፍል (105) ፦ የተሳሳቱና ችግሮችን ያስከተሉ የአሕባሾች ፈትዋና የፊቅህ ነጥቦች 🔎http://bit.ly/2YJOTzd ክፍል (106)፦ የተሳሳቱ ገንዘብና ኸምርን የሚመለከቱ የአሕባሾች ፈታዋ 🔎http://bit.ly/2YFrT4r ክፍል (107) :-ከሴቶችና ከአለባበሳቸው ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ የአሕባሾች ፈታዋ 🔎http://bit.ly/2WkQv17 ክፍል (108) ፦አሕባሾች የዑለማዎች ቅርስ ላይ ያስከተሏቸው መዘዞች 🔎http://bit.ly/2p69e4m ክፍል (109) ፦ አሕባሾች ደዕዋ ላይ ያስከተሉት መዘዝ 🔎http://bit.ly/33Vs2Cw ክፍል (110)፦ (የመጨረሻ ክፍል) አሕባሽ ሲጨመቅ 🔎http://bit.ly/2ሊR8lUTQ tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1

ክፍል (47) ፦ አሕባሾች የአላህን ወደ ቅርቧ ሰማይ መውረድ ለማስተባበል የሚያነሷቸው ብዥታዎችና መልሶቻቸው 🔎http://bit.ly/2Pyawyg ክፍል (48) ፦የአላህ ንግግርና የአሕባሾችአቋምን   (ቁ-1) 🔎http://bit.ly/2Ead9RM ክፍል (49) ፦የአላህ ንግግርና የአሕባሾች አቋም  (ቁ-2) 🔎http://bit.ly/2E7xYx1 ክፍል (50) ፦"إنه لقول رسول كريم" ማለት ምን ማለት ነው? *እውነት ቁርኣን የጂብሪል ንግግር ለመሆኑ ማስረጃ ይሆናልን? 🔎http://bit.ly/34cYQGD ክፍል (51) ፦ የአላህ ንግግር በፊደልና በድምጽ ነው ወይስ..? 🔎http://bit.ly/38mtUXA ክፍል (52)፦ የአላህን ፊት የሚመለከቱ ጥቅሶችና አሕባሾች 🔎http://bit.ly/34bGupp ክፍል (53) ፦ ለአላህ እጅና እግር አለው? የአሕባሾችስ አቋም ምንድን ነው? 🔎http://bit.ly/36r2Gxm ክፍል (54)፦ አላህ ይቆጣል ማለት አሕባሾች ዘንድ ምን ማለት ነው? 🔎http://bit.ly/36oxcaV ክፍል (55) ፦ የሙእሚኖች  ኣኺራ ላይ አላህን ማየት እና የአሕባሾች አቋም 🔎http://bit.ly/2PFlTo2 ክፍል(56):-ኢማን ማለት አሕባሾች ዘንድ ምን ማለት ነው? 🔎http://bit.ly/2PDv0Wf. ክፍል (57) ፦ ደጋግ ቀደምቶች ዘንድ ኢማን ማለት ምን ማለት ነው? 🔎http://bit.ly/358rFVQ ክፍል (58) ፦ ኢማንና ሰላት 🔎http://bit.ly/2LM0vfI ክፍል (59) ፦ የኢማን መጨመርና መቀነስ አሕባሾችና አህል-አስሱና ዘንድ "ኢን'ሻ'አላህ ሙእሚን ነኝ" ማለትስ ይቻላል? 🔎http://bit.ly/2RIRGaC ክፍል (60) ፦ አሕባሾችና ሙስሊምን ማክፈር 🔎http://bit.ly/2LJU3Wu ክፍል (61) ፦ አሕባሾችና በቀደር ማመን እና እውነት አላህ ከሃዲያንን በክህደታቸው ላይ አግዟቸዋልን? 🔎http://bit.ly/2seSvgu ክፍል (62)፦ የሰሓባዎች ደረጃ አሕባሾች ዘንድ 🔎http://bit.ly/2P9v7dl ክፍል (63) ፦ ሁሉም ሰሓባዎች መወደድና መከበር እንዳለባቸው የሚያሳዩ የቁርኣና የሐዲሥ ማስረጃዎች ከቀደምት ዑለማዎች ንግግር ጋር 🔎http://bit.ly/38sPidU ክፍል (64) ፦ የምእምናን አጎት ሙዓዊያ (رضي الله عنهما)  በአሕባሾች እይታ 🔎http://bit.ly/36qGyTA ክፍል (65) ፦ ዐሊይና ሙዓዊያን رضي الله عنهما ምን ነበር ያጋጫቸው? ★የሌሎች ሰሓቦችስ ሚና ምን ነበር? 🔎http://bit.ly/2LL9P3u ክፍል (66) ፦ በዐሊይና በሙዓዊያ ጉዳይ ዙሪያ የዲን ሊቃውንት ምን አሉ? 🔎http://bit.ly/2RHXkK4 ክፍል (67) ፦ ቁርኣን፣ ነቢዩ፣ (ﷺ) ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው ስለ ሙዓዊያ ምን አሉ? የሙዓዊያ ትሩፋት 🔎 http://bit.ly/2LIQdNF ክፍል (68) ፦ የሙዓዊያ رضي الله عنهما ስነ ምግባርና ስብዕና 🔎http://bit.ly/2LLrgkt ክፍል (69) ፦ የሰሓባዎችን رضي الله عنهم ግጭት በተመለከተ የአህል-ስሱና አቋም ምንድን ነው? 🔎http://bit.ly/2slsHPD ክፍል (70) ፦ ቢድዓና አሕባሾች 🔎http://bit.ly/2RGLmAj ክፍል (71) ፦ ዲን ላይ ጥሩ ቢድዓ የሚባል ነገር አለን? 🔎http://bit.ly/36mA2gP ክፍል (72) ፦ "من سن في الإسلام سنةحسنة..." የሚለው ሐዲሥ እውነት የቢድዓ ጥሩ እንዳለ ማስረጃ ነውን? 🔎http://bit.ly/2sdLNrd ክፍል(73) ፦ የዑመር رضي الله عنه ("نعمت البدعة هذه") የሚለው ንግግራቸው እውነት የቢድዓ ጥሩ እንዳለ ማስረጃ ነውን? 🔎http://bit.ly/2rA4Sne ክፍል (74) ፦ ኢማሙ አሽሻፊዒይ ቢድዓን በተመለከተ አቋማቸው ምን ይመስላል? 🔎http://bit.ly/2E4EO6q ክፍል (75)፦ አሕባሾች የጥሩ ቢድዓ ምሳሌዎች ናቸው የሚሏቸው ነገሮችና መልሶቻቸው 🔎http://bit.ly/2YFfjSL ክፍል (76)፦መውሊድና አሕባሾች 🔎http://bit.ly/2sgW1ah ክፍል (77) ፦ የሶፊያ ጠሪቃ / መንገዶች እውነት መልካም ቢድዓ ናቸውን? 🔎http://bit.ly/2LKtT6m ክፍል (78) ፦ "ተወሱል" ማለት ምን ማለት ነው? የአሕባሾችስ አቋም ምንድነው? 🔎http://bit.ly/38vYG08 ክፍል (79) ፦ ለአሕባሾች የተሳሳተ ተወሱልና ለደሊሎቻቸው ምላሽ 🔎http://bit.ly/2rpSnLb ክፍል (80) ፦ አሕባሾች ለተሳሳተው ተወሱላቸው ማስረጃ የሚሏቸው 2 ነገሮች ምላሽ 🔎http://bit.ly/35cD86V ክፍል (81)፦ተበሩክ አሕባሾች ዘንድ እና እውነት የነቢዩ ጸጉር አሕባሾች ዘንድ አለን? 🔎http://bit.ly/2PzeE0V ክፍል (82) ፦ የአሕባሾች በመቃብርና በሼኻቸው ተበሩክ ማድረግ 🔎http://bit.ly/2YFhNk3 ክፍል (83)፦ የአሕባሾች መቃብር ላይ ድምበር ማለፍ 🔎http://bit.ly/38sEZGL ክፍል (84)፦ መቃብር ላይ መገምባት፣ለተበሩክ ብሎም ቀብርን መንካት በተመለከተ የዑለሞች አቋም ምን ይመስላል? 🔎http://bit.ly/2RHMnI9 ክፍል (85)፦ አሕባሾች ማንን ነው የሚከተሉት? 🔎http://bit.ly/2LGWqcM ክፍል (86) ፦ አሕባሾች ኢብኑ ተይሚያን ለምን ይጠላሉ? 🔎http://bit.ly/2RCZr1E ክፍል (87) ፦ ዐብደላህ አልሀረሪ የኢብኑ ተይሚያህ ታሪክ ላይ የፈጸማቸው ስህተቶች 🔎http://bit.ly/2qInilv ክፍል (88) ፦ በኢብኑ ተይሚያህ ዘመን የነበሩ ዑለሞች ስለሳቸው ምን አሉ? ዐብደላህ አልሀረሪስ?! 🔎http://bit.ly/34d80mv ክፍል (89)፦ እውነት ኢብኑ ተይሚየህ "አላህ አርሹ ላይ ተቀምጧል" ብለዋልን?! 🔎http://bit.ly/36sG8fo ክፍል (90)፦ አሕባሾች ለምን በሸይኽ ሙሐመድ አብዱል-ወሃብ ላይ ይቀጥፋሉ?! 🔎http://bit.ly/346WxVq ክፍል (91) ፦እውነት የሼኽ ሙሐመድ አብዱል-ወሃብ ወንድም የሳቸው ተቃዋሚ ነበረን? 🔎http://bit.ly/2RHChqY ክፍል (92) ፦ ስለ ሸይኽ ሙሐመድ አብዱል-ወሃብ በዘመኑ የነበሩ ሊቃውንት ምን አሉ? 🔎http://bit.ly/2E6GlZL ክፍል (93) ፦የአሕባሾች ቅጥፈት 🔎http://bit.ly/2RIU698 ክፍል (94) ፦የአሕባሾች ቅጥፈትና ግፍ 🔎http://bit.ly/2LM20uB ክፍል (95) ፦አሕባሾች ወሃቢያ የሚሏቸው ሰዎች ላይ የሚዋሹበት ምክንያት ምንድነው? 🔎http://bit.ly/2rstxub ክፍል (96)፦ ሽይኹል- ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ ማን ናቸው? 🔎http://bit.ly/36wpmfL ክፍል (97)፦ የሽይኹል- ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ እምነት (ዐቂዳ) ምን ይመስላል? 🔎http://bit.ly/2PCIK3E ክፍል(98) ፦ አሕባሾችን በተመለከተ የፈትዋና ኢስላማዊ ጥናቶች ቋሚ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫና ማብራሪያው 🔎http://bit.ly/2PcXtUb ክፍል (99) ፦ አሕባሾች ለቀደምት የዲን ዑለማዎች ያላቸው አመለካከት 🔎http://bit.ly/35ejJCq ክፍል (100)፦ አሕባሾች ለዘመናችን ታላላቅ ዑለማዎች ያላቸው አመለካከት 🔎http://bit.ly/2qJrcKX

"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ: «የአሕባሾች እምነት፤ በሚዛን ላይ!» «عقيدة فرقة الأحباش» በሚል ርዕስ፤በተከታታይ 110 ክፍሎች በዛዱል መዓድ የትምህርት መድረክ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ሲሰጥ የነበረው ወሳኝ የዐቂዳ ትምህርት የአሕባሾችንና የሌሎችን መሰል የተሳሳተ ዐቂዳ ያላቸው አንጃዎችን ምንነት በስፋትና፣  በመረጃ  የቀረበበት ትምህርት ሲሆን ይህም ትምህርት  በቅርቡ በአላህ ፈቃድ ወደ መፅሃፍ ተቀይሮ  ለአንባብያን የሚደርስ መሆኑን እንገልፃለን 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 🔸 ሙሉ ትምህርቱን  ለማግኜት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ  🔎http://bit.ly/36rMgVn 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ክፍል (1) ፦  የአሕባሾ እምነት በሚዛን ላይ (መግቢያ) 🔎http://bit.ly/36rSJzQ ክፍል (2) ፦ የአሕባሽ እምነት መችና በማን ተመሰረተ? 🔎http://bit.ly/38tYcb6 ክፍል (3) ፦ አብደላህ አል ሀረሪ በኢትዩጵያ ቆይታው ምን አደረገ? 🔎http://bit.ly/36nUAFx ክፍል (4) ፦ አብደላህ አል ሀረሪ ሊባኖስን ለምን መረጠ? ወሀቢና ሱፊይ ምን ማለት ነዉ? 🔎http://bit.ly/2scyVSa ክፍል (5) ፦ አብደላህ አል ሀረሪና መፅሀፎቹ 🔎http://bit.ly/35b3LZX ክፍል (6) ፦ የአሕባሽ እምነት እንዴት ተመሰረተ? ለምንስ አሕባሽ ተባሉ? 🔎http://bit.ly/38sho91 ክፍል (7) ፦ አሕባሾች አለም ላይ ያላቸዉ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? 🔎http://bit.ly/2Pb7np3 ክፍል (8) ፦ የአሕባሾች ዋና አላማ ምንድን ነዉ? ከጀርባቸዉስ ማን ነዉ ያለዉ? 🔎http://bit.ly/38BGJO2 ክፍል (9) ፦ አሕባሽና አላህን ማወቅ 🔎http://bit.ly/2LGjB7e ክፍል (10)፦ የመጀመርያው የሰዉ ልጆች ግዴታ ምንድን ነዉ? 🔎http://bit.ly/35bl50L ክፍል (11)፦ ተዉሒድ በአሕባሾች ዘንድ   🔎http://bit.ly/2t6XCjk ክፍል (12) ፦ እዉነት ተሒሂድን ለሶስት ከፍሎ ማየት ቢድዓ ነዉ? 🔎http://bit.ly/2rywJUQ ክፍል (13) ፦የጀነት ቁልፍ የሆነችዋን ላኢላሀ ኢለላህ አሕባሾች ምን ብሎ ነዉ የሚተረጉሙት? 🔎 http://bit.ly/2E8GAne ክፍል(14) ፦ ዒባዳ አሕባሾች ዘንድ ምን ማለት ነው? 🔎http://goo.gl/0KaeqN ክፍል (15)፦ ዱዓ በኢስላምና በአሕባሾች ዘንድ ያለው ቦታ 🔎https://goo.gl/vXpYvz ክፍል (16)፦ ቀደምት ዑለሞች ዱዓን አስመልክተው  ምን አሉ? አሕባሾችስ ዱዓን ከዒባዳ ያስወጡበት ምክንያት ምንድነው? 🔎https://goo.gl/3ZPL0I ክፍል (17) ፦ አሕባሾች የሞቱ ወሊዬችንና ሷሊሆችን መለመንና መጣራት ይቻላል ብለዉ ለሚያቀርቧቸዉ ማስረጃዎች በሚዛን ላይ 🔎https://goo.gl/o9R7mH ክፍል (18) ፦ እዉነት አሕባሾች እንደሚሉት ወሊዮችንና ነቢያቶችን እርዳታ መጠየቅና ኢስቲዐና ማድረግ ይቻላልን? 🔎https://goo.gl/Fk9aXS ክፍል (19)፦ አሕባሾችና ኢስቲጛሣ(ሙታንን መጣራት)" 🔎https://goo.gl/WD8Ebe ክፍል (20) ፦ "አሕባሾች ሙታንን መጣራት (ኢስቲጛሣ)  ይቻላል" ብለው ለሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች ምላሽ 🔎https://goo.gl/mZykAW ክፍል (21)፦ "አንዳንድ ሰዎች ሙታንን ተጣርተው ያሰቡት መሳከቱ ድርጊታቸው ትክክል የመሆኑ ምልክት ነውን?" 🔎https://goo.gl/bTYv1m ክፍል (22) ፦ አሕባሾችና በፍጡራን (በሙታን) መጠበቅ 🔎https://goo.gl/zq1UyZ ክፍል (23)፦ በተለምዶ ከሰው ልጆች የማይጠየቅን ነገር መኽሉቅን(ፍጡርን) መጠየቅ እንዴት ይታያል? 🔎https://goo.gl/LPx2kn ክፍል (24)፦ በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-1) 🔎https://goo.gl/smOuBJ ክፍል (25) ፦በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-2) 🔎https://goo.gl/dtqbFL ክፍል(26)፦ በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-3) ወልዮች ላይ ድንበር ማለፍ 🔎https://goo.gl/UpHWNZ ክፍል (27) ፦ በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-4) 🔎https://goo.gl/i7xcsp ክፍል (28) ፦ የሺርክ አስከፊነትና ከአደጋው የመዳኛ መንገዶች 🔎https://goo.gl/apPAEy ክፍል (29) ፦ አሕባሾችና የአላህ ባህሪያት 🔎https://goo.gl/Zh33Tw ክፍል (30) ፦ እውነት የአላህ ባህሪያት 13 ብቻ ናቸውን? በዚህ ዙሪያስ ደጋግ ቀደምቶች ምን ብለዋል? 🔎 https://goo.gl/G3uuhw ክፍል (31) ፦ የአላህ ባህሪያት ዱሮ ሆነዉ ያበቁ ናቸዉ ወይስ ...? 🔎http://bit.ly/2P9P43B ክፍል (32) ፦ አላህ ራሱ ከፍጡራኖች ሁሉ በላይ መሆኑና የአሕባሾች አቋም      (ቁ-1) 🔎http://bit.ly/2PCBNjj ክፍል (33) ፦ አላህ ራሱ ከፍጡራኖች ሁሉ በላይ መሆኑና የአሕባሾች አቋም      (ቁ- 2) 🔎http://bit.ly/34aEUEn ክፍል (34)፦ አላህ የት ነው ብሎ መጠየቅ እንዴት ይታያል? 🔎http://bit.ly/2E3bv4a ክፍል (35)፦ የአላህን እላይ መሆን የሚያሳዩ የሐዲሥ ማስረጃዎችና የቀደምት ዑለማዎች አቋም 🔎http://bit.ly/2E5hntV ክፍል (36)፦ የአላህ ከዓርሽ በላይ መሆንና የአሕባሾች አቋም 🔎http://bit.ly/2si7ING ክፍል (37) ፦ ኢስተዋ የሚለውን ቃል የቋንቋ ሊቃውንት ምን ብለው ተረጉሙት? 🔎http://bit.ly/2PwK8Vu ክፍል (38)፦ አሕባሾች "ወሕይን" እየተዉ ተናጋሪውና ምንጩ የማይታወቅን "ግጥም" ማስረጃ ያደርጋሉ 🔎http://bit.ly/2YCddTs ክፍል (39)፦ የአላህ ከአርሽ በላይ መሆን የሚያሳየዉ የኢማሙ ማሊክ ንግግርና የአሕባሾች ሽሽት 🔎http://bit.ly/2RHooJs ክፍል (40)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን የሚያሳዩ ጥቂት የሰሓባና የታቢዒዮች ንግግር 🔎http://bit.ly/2PMbPtN ክፍል (41) ፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን በተመለከተ ደጋግ ቀደምቶች ምን አሉ? 🔎http://bit.ly/2PBf86F ክፍል ( 42)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን በተመለከተ ኢማም አቡ ሐኒፋና ኢማሙ ማሊክ ምን አሉ? 🔎http://bit.ly/2Pywz86 ክፍል (4 3)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን በተመለከተ ኢማሙ አሽሻፊዒና ኢማሙ አሕመድ ምን አሉ? 🔎http://bit.ly/2E6yiMv ክፍል (44) ፦ አሕባሾች የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን ለማስተባበል የሚጠቀሟቸው ቃላቶች الله موجود بلا مكان❌ 🔎http://bit.ly/2RJf07U ክፍል አርባ (45)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን የተመለከተ ማጠቃለያ ትምህርት 💥ለብዥታዎች መልስ የሚሰጥበት 💥የአላህን ስምና ባህሪ በተመለከተ ጠቃሚ ምክሮች የተለገሱበት ትምህርት 🔎http://bit.ly/2YElaaN ክፍል  (46)፦የአላህ  በየሌሊቱ ወደ ቅርቧ ሰማይ መውረድና የአሕባሾች አቋም 🔎http://bit.ly/2rpKoOd

👍 አርሽን ከመፍጠሩ በፊት... ይድረስ ለአህባሽ ወገኖቻችን 🎙 በሼኽ ኢልያስ አህመድ tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1

3⃣አላህ ከአርሽ በላይ ለመሆኑ ተቆጥሮ ከማያልቀው መረጃ በጥቂቱ ...ክፍል ሶስት ============================   አላህ ከአርሽ በላይ ነው ስንል ከበቂ ማስረጃ ጋር ነው!! ማስረጃዎችንም እንደጀመርኩላችሁ ዛሬም ቀጣይ ክፍል ኢማሙ ሃፊዝ አቡ ኑዓይም እንዲህ ይላሉ፦ ( وأجمعوا أن الله فوق سمواته ، عال على عرشه ، مستو عليه ، لا مستولٍ عليه كما تقول الجهمية إنه بكل مكان …).     አላህ ከሰማትና ከአርሽ በላይ በመሆኑ ኡለማዎች ሁሉ ተስማምተዋል ። ልክ ጀህምያዎች አላህ አርሽ ተቆጣጠሮታል ያለው ሁሉም ቦታ ነው እንደሚሉት አይደለም...    እናንተ የጀህምያ ፍልፈሎች(ስድብ አይደለም) አያችሁ የናንተ አቂዳ ከማን ጋር እንደሚመሳሰል? አሁንም አቡ ኑዓይምም ወሃብያ ነበር? አቡ ሙጢዕ ፊቅሁል አክበር በሚለው ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ ፦ እኔ አቡ ሃኒፋን እንዲህ ብዬ ጠየኳቸው ጌታዬ ከሰመይ በላይ ይሁን ምድር ይሁን አላውቅም  ስለሚል ሰው ምን ይላሉ ብዬ ጠየኳቸው እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱልኝ ' ይህ ሰው ከፍሯል ምክንያቱም አላህ እንዲህ ይላል  الرحمن على العرش استوى የአላህ አርሽ ደሞ ከሰባቱም ሰመያት በላይ ነው። ' ከዛም እንዲህ አልኳቸው እሺ ሰውየው አላህ ከአርሽ በላይ ነው ነገር ግን አርሽ ከሰመያት በላይ ይሁን በምድር አላውቅም ይላል አልኳቸው እሳቸውም እንዲህ አሉኝ ' ይህ ሰው አርሽ ከሰመያት በላይ መሆኑን ከካደ ከፍሯል። ምክንያቱም ከፍ ያለው አላህ ከበላይ ሁሉ እላይ ነው ። አላህ ከላይ ሆኖ ነው ወደ ላይ የሚለመነው ከታች ሆኖ አይደለም።'አሉኝ" وقال أبو مطيع البلخي في كتاب "الفقه الأكبر": سألت أبا حنيفة عمن يقول لا أعرف ربي في السماء أو  في الأرض، قال: كفر؛ لأن الله يقول: { الرحمن على العرش استوى }(طه:5)، وعرشه فوق سبع سمواته، فقلت: إنه يقول على العرش، ولكن لا أدرى العرش في السماء أو في الأرض، فقال: إنه إذا أنكر أنه في السماء كفر، لأنه تعالى في أعلى عليين، وأنه يُدعى من أعلى لا من أسفل ".      ያ አዩሃል አህባሽ ወተብሊጎች ወሱፊያ... ታድያ አቡ ሃኒፋም ወሃብያ ናቸው ማለት ነው? ወይ የናንተ ሚዛን ይገርማል ብቻ! እና አሁንም አልጠገባችሁም? አሁንም ትንሽ የመመለስና የመቶበት ፍላጎቱ አላደረባችሁም?     ውድ ተከታታዮች እንሸ አላህ የአላህ ፍቃድ ከሆነ በሶስት ተከታታይ ክፍል ከኡለሞች ንግግር ከባህሩ ውስጥ የቀረበኝን ጨልፌ በፅሁፍ ልኬላቹሃለሁ። ዊትር ስለሞላ የኡለሞችን ለግዜው በዚህ እገታውና የአላህ ፍቃድ ከሆነ ቀጣይ ክፍሎች ከሃዲስ እንቀጥላለን ከዛ ወደ ቁርዓን እንሄዳለን!!ከዛ ለሎጂክ ሹብሃቸው ወደ ሎጂክ እንሄዳለን ተከታተሉኝ...ሰዎችን ከመጥፎ ሹብሃ ለማራቅ ሁላችሁም ሼር ማድረጉን አትርሱት!! ✍ወንድማችሁ ጅብሪል ሱልጣን

2⃣አላህ ከአርሽ በላይ ለመሆኑ ተቆጥሮ ከማያልቀው መረጃ በጥቂቱ ...ክፍል ሁለት =============================    👌ማሳሰቢያ፦   ባለፈውም ክፍል ላይ ይሁን በዚህም ክፍል እንሸ አላህ በቀጣይም ክፍሎች አመታትን አስልቼ ስያስቀምጥ 1 በሂጅራ አቆጣጠር ነው ። 2 ደሞ እስከ አሁን ሳይሆን እስከ ሙሃመድ ኢብን አብድል ወሃብ ውልደት ድረስ እስካለው ነው። በተጨማሪም በፅሁፉ ላይ አብድል ወሃብ ብቻ ካልኩ የፈለኩበት ሙሃመድ ኢብን አብድል ወሃብን ነው። ለሁሉም አሊም ረሂመሁላህ ብዬ ያልፃፍኩት ፅሁፉን ለማሳጠር ነው እናንተ ስታነቡ በሉ።     ጀምር ኢማሙ አል-አውዛዒይ     የሞቱት 157 ዐመተ ሂጅራ ነው እንግዲህ ይህ ማለት ሙሃመድ ኢብን አብድል ወሃብ የተወለደው ይህ ኢማም ከሞቱ ከ958 አመት ቦሃላ ነው የተወለዱት እና ይህ አሊም እንዲህ ይላሉ፦ ( كنا والتابعون متوافرون نقول : إن الله تعالى فوق عرشه ، ونؤمن بما وردت به السنة )   "እኛ ታቢዕይኖች በደንብ እያሉ ' ከፍ ያለው አላህ ከአርሹ በላይ ነው ያለው እንዲሁም ሱና ይዛው በመጣችው ሁሉ እናምናለን' እንል ነበር።"    ተመልከቱ እንግዲህ አዩሃል አህባሽ ወረባሽ ወሱፊያ ወዓሽዓሪያ... እንግዲህ በናንተ calculator machine ኢማሙ አውዛዒይም ወሃቡያ ነበሩ? ጭንቅላትህን አሰራው ወንድ ጋሼ    ኢማሙ ኡስማን ኢብኑ ሰዒድ አድ-ዳረሚይ    የሞቱት በ280 አመተ ሂጅራ ነው ይህም ማለት እኚህ አሊም ከሞቱ ከ835 አመት ቦሃላ ነው ሙሃመድ ኢብን አብድል ወሃብ የተወለዱት... እና በቢሽር አል ሚሪሲይ ላይ ረድ ስያደርጉ እንዲህ ይላሉ (اتفقت الكلمة من المسلمين أن الله تعالى فوق عرشه ، فوق سماواته ).    የሙሉ ሙስሊሞች አቋም አላህ ከሰመያት በላይ ከአርሹ በላይ በመሆኑ ተስማምቷል።   አያችሁ እናንተ መጤዎች የዛኔ በተከበረው ክፍለ ዘመን እንደናንተ አይነቱ ከዲን፣ ከሰሃባዎች መንገድ ያፈነገጠ ከመምጣቱ በፊት ሁሉም ሙስሊሞች አቋማቸው አንድ ነበር ... ቦሃላ ላይ እንደናንተ አይነቱ የዲን ግንዛቤ የሌለው የነብዩን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም መንገድ የመከተል ፍላጎቱ 0% የደረሰ ...በገገማው ብቻ ነብዩ እወዳለሁ የሚል ሲመጣ ነው እንደናንተ አይነት ኹረፋቶችና ባጢሎች ሰርገው የገቡት። ስለዚህ በናንተ ሂሳብ ይህም አሊም ወሃቢያ ነበሩ?? ኢማሙ ቁተይባ ቢን ሰዒድ  የሞቱት በ240 አመተ ሂጅራ ነው ይህም ማለት  አብድል ወሃም የተወለደው እኚህ አሊም ከሞቱ ከ875 አመት ቦሃላ ነው... እና እንዲህ ይላሉ ፦ ( هذا قول الأئمة في الإسلام وأهل السنة والجماعة : نعرف ربنا عز وجل في السماء السابعة على عرشه ، كما قال ( الرحمن على العرش استوى )   ይህ የኢስላም አሊሞችና የአህሉ ሱና ወልጀመዓ አቋም ነው። ጎታችን አላህ ከሰመያት በላይ ከአርሹ በላይ መሆኑን እናውቃለን። ልክ እራሱም እንዲህ እንዳለው الرحمن على العرش استوى    አየህ አንተ አህባሽ ፣ ሱፊያ ፣ ተብሊግ ፣ አሻዒራ...ይህቺን አንቀፅ አላህ ከአርሽ በላይ ለመሆኑ እንደ ማስረጃነት ይጠቀሟት የነበሩት እነ ማን እንደሆኑ? ዝም ብለህ አፍህ እንደመጣልህ በማታውቀው ነገር ወሃብያ! እያልክ አትዘላብድ ውሃ ይብላህና ...! እንግዲህ አሁንም በናንተ ሂሳብ ከአብድል ወሃብ በፊትም ወሃብያ የምትሉት ነበር ማለት ነው!! ወይስ የዛኔ የአብድል ወሃብ መንፈስ ነበር? (እንዲህ ካላችሁ አብድል ወሃብን ከሚገባው በላይ ሰቅላቹታል ማለት ነው)። አቡ ዙርዐተ አር-ራዚ እኚህ አሊም ካላወቃቹሃቸው የኢማሙ ሙስሊም ሸይኽ ናቸው ኢማሙ ሙስሊ ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ "ሃዲሶቹን ከፃፍኩ ቦሃላ ለአቡ ዙርዐተ ራዚ አቀርብላቸውና ስለ ሃዲሶቹ እንዲሁም ስለሰነዶቹ አስተያየታቸውን ይመግሱኝ ነበር!"(ምናልባት ንግግሩ ቃል በቃል አይደለም) እኚህ አሊም እንግዲህ ለዛ ሊቅ ቢባል ለምያንሰው ለሙስሊም አስተያየት ከሰጡ ምን አይነት አሊም መሆናቸውን መገመት የሚከብዳችሁ አይመስለኝም እናማ ይህ አሊም እና በተመሳሳይ አቡ ሃቲምም (ስለአቡ ሃቲም ትልቅነት አለም ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ነው ) የሞቱት (አቡዙርዓተ ራዚ) 264 አመተ ሂጅራ ነው። ይህም ማለት አብድል ወሃብ የተወለዱት እኚህ አሊም ከሞቱ ከ851 አመት ቦሃላ ነው ... እናም እንዲህ ይላሉ ፦ (أدركنا العلماء في جميع الأمصار ، فكان مذهبهم أن الله على عرشه بائن من خلقه ، كما وصف نفسه ، بلا كيف ، أحاط بكل شيء علما ) በተለያዩ ሃገራት ትላልቅ ኡለማዎችን አግኝተናል ። ያገኘናቸውም አሊሞች መዝሃባቸው አላህ ከአርሹ በላይ ነው እራሱ እንደገለፀልንም ከፍጡራኑ ተነጥሎ ያለ ከይፊያ እና ሁሉንም ነገር በእውቀቱ አካቧል።    ተመልከቱልኝማ እንግዲህ አብድል ወሃብና ወሃብያዎች የማንን አቋም እያራመዱ እንደሆነ! አዩሃል አህባሽ ወአፍራኹል የሁድ ወተላሚዝሁም መዝሃባችሁ እና አካሄዳችሁ ከማን ጋር እየተጋጨ እንደሆነ እየተረዳችሁልኝ ነው? ተከተሉኝማ፦ ኢማሙ አብድል በር ሃፊዝ አልመግሪብ የሞቱን በ 463 ዐመተ ሂጅራ ነው ይህም ማለት አብድል ወሃብ የተወለደው እኚህ አሊም ከሞቱ ከ652 አመት ቦሃላ ነው ማለት ነው እና ይህ አሊም ተምሂድ በሚባለው ኪታባቸው አላህ ወደ ዱንያው ሰማይ ይወርዳል የሚለውን ሃዲስ ስያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦ … وفيه دليل على أن الله عز وجل في السماء على العرش من فوق سبع سموات ، كما قالت الجماعة ، وهو من حجتهم على المعتزلة والجهمية في قولهم : إن الله عز وجل في كل مكان وليس على العرش . و الدليل على صحه ما قاله أهل الحق في ذلك : قول الله عز وجل ( الرحمن على العرش استوى …) انتهى    ሃዲሱ በብዙ አቅጣጫ የመጣ ሃዲስ ነው በዚህ ሃዲስ አብዝሃኛዎቹ ኡለማዎች እንዳሉትም አላህ ከሰባቱም ሰመያት በላይ ከአርሹ በላይ ለመሆኑ ማስረጃ አለው።ይህ ደሞ አላህ ከአርሽ በላይ አይደለም ሁሉም ቦታ ነው ያለው በሚሉት በሙዕተዚላዎችና በጀህሚያዎች ላይ የሚያመጡትም ማስረጃቸውም ነው።  እንግዲህ እነኚህ(ከአርሽ በላይ ነው ያሉት) የሃቅ ባለቤቶች ላሉት ንግግራቸው ትክክለኝነት ማስረጃው እንዲህ የሚለው ያአላህ ቃል ነው الرحمن على العرش استوى እንግዚህ እናንተ ወሃብያ የሚባል virus የያዛቹ አህሉል ኹራፋቶች የወሃብዮች እምነት የማን እምነት እንደሆነ እያያችሁልኝ ነው? ቀጥል... ይቀጥላል...    በአህባሾችና በመሰሎቻቸው ጥመት ለተዘፈቁት እንዲደርሳቸው ሼር አድርጉት ✍ወንድማችሁ ጅብሪል ሱልጣን

አላህ ከአርሽ በላይ ለመሆኑ ተቆጥሮ ከማያልቀው መረጃ በጥቂቱ ... ============================    መጀመሪያ ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት አንድ ጉድ ልንገራችሁ አላህ ከአርሽ በላይ ነው ያሉት ወሃብያዎች ናቸው ይሉናል። ወሃብያ ማለት ደሞ የሙሃመድ ኢብን አብድል ወሃብ ተከታይ ማለት ነው በነሱ አባባል... በዚህ አባባል ደሞ አንድ ነገር እንረዳለን እሱም፦ አላህ ከአርሽ በላይ ነው ማለት የተጀመረው በሙሃመድ ኢብን አብድል ወሃብ ግዜ አንስቶ ነው ማለት ነው። ወይም ደሞ በሌላ አባባል አላህ ከአርሽ በላይ ነው ያለ ወሃብያ ነው ማለት ነው። እሺ ወደ መረጃችን እንግባ    ሙሃመድ ኢብን አብድል ወሃብ መች ሞተ ለመሆኑ?    አቡል ሁሰይን ሙሃመድ ኢብኑ አብድል ወሃብ 1206 አመተ ሂጅራ ነው የሞተው። የተወለደው 1115 ነው። እንግዲህ እንደ አህባሾች ግንዛቤ ከሆነ ከዚህ በፊት አላህ ከአርሽ በላይ ነው ያለ አንድም አሊም ዬለም ማለት ነው ። እሺ እስቲ የኡለማዎችን ንግግር ከነ አመታቸው እንመልከት ። ምናልባት አህባሾች ብዙውን የቁርዓን ማስረጃ ሲሰጣቸው ተዕዊል በማድረግ ወይም ብዙ ትርጉም አለው ስለዚህ ይህ ትርጉም ደሞ ለአላህ አይገባም ይላሉ። በተለይ ብዙ ግዜ استوى የምትለዋን استولى በማለት ይታወቃሉ ስለዚህ የማመጣላችሁ መረጃ አንድ ትርጉም ያለውን ብቻ ነው። አረብኛውንም አያይዤ አቀርብላቹሃለው ከሰሃባዎች ንግግር እንጀምራለን፦ 1 እውቁ ሰሃቢይ አብደላህ ኢብኑ አባስ አንድ ቀን አኢሻ ስትሞት ወደሷ ገባና እንዲህም አላት፦ አንቺ ከነብዩ ምስቶች ውስጥ የተወደድሺው ነበርሽ ነብዩ ደሞ ጥሩን እንጂ አይወዱም(አንቺም ጥሩ ነሽ አተስቢ) አላህም የአንቺን ንፁህነት ከሰባቱም ሰማይ በላይ ሆኖ አውርዷል። كنت أحب نساء رسول الله صلى الله عليه وسلم ولم يكن يحب إلا طيباً وأنزل براءتك منفوق سبع سماوات   أخرجه الدارمي في الرد على الجهمية بسند حسن  . አብደላህ ኢብኑ አባስ እንዲህም ማለታቸውን አላለካኢ ዘግበውታል ። እንግዲህ ተመልከቱ አብደሏህ ኢብኑ አባስ ማለት ሰሃባ ናቸው እሳቸው ደሞ የነበሩት በነብዩ ዘመን ነው ይህንን ደሞ የተናገቁት "ቁሩኑል ሙፈደላህ" ወይም ነብዩ በላጭ ክፍለ ዘመን ወይም ግዜ ብለው በመሰከሩለት ዘመን ነው። እንግዲህ በዚህ ሰአት ደሞ ሙሃመድ ኢብኑ አብድል ወሃብ አልነበረም ገና ሊወለድም አልታሰበም...ታድያ አብደላህ ኢብኑ አባስም ወሃብያ ነበር ማለት ነዋ? ከምንም በላይ ግን አንድ ነገራችሁ ደስ ይለኛል እናንተ አህባሾች እሱም ፦ እኛን እናነውራለን ብላችሁ ከሰሃባዎች ጋር የምትጨምሩን ነገር !! ወሊላሂል ሃምድ ወላሂ እኛም አላማችን ነብዩንና ሰሃባዎችን መከተል ነው ... ይህንን አላማችንን ደሞ በወዳጃችንም በጠላታችንም ምስክርነትን ስናገኝ ምንኛ ያስደስታል እናንተዬ ?? ሁለተኛው ማስረጃ ደሞ ፦ ይህን የአላህን ቃል አስመልክቶ ኢብኑ አባስ፦ ( ثُمَّ لآتِيَنَّهُمْ مِنْ بَيْنِأَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَنْ شَمَائِلِهِمْ وَلاتَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ) ሰይጣን ከሰው ልጆች ከፊታቸው ኮሃላቸው ከቀኛቸው ከግራቸው እመጣቸዋለሁ ሲል ነገር ግን ከበላያቸው እመጣቸዋለሁ አላለም ያላለበትም ምክንያት ከበላያቸው አላህ መኖሩን ያውቃልና لم يستطع أن يقول من فوقهم ؛ علم أن الله من فوقهم  رواه اللالكائي في شرح أصول السنة بسند حسن. እንግዲህ አብደላህ ኢብኑ አባስ ሰሃባ ናቸው ታድያ እሳቸው ሙሃመድ ኢብኑ አብድል ወሃብን ተከታይ ነበሩ ማለት ነው ¡? አታፍሩም እኮ አው ትሉ ይሆናል...¡? 3, የምዕመናን እናት ዘይነብ ቢንት ጀህሽ (የነብዩ ምስት ነች) በነብዩ በሌላ ምስቶች እንዲህ እያለች ትፎክርባቸው ነበር፦ زوجكن أهاليكن وزوجني الله تعالى من فوق سبع سماوات  أخرجه البخاري  . እናንተን ቤተሰቦቻችሁ ናቸው የዳሩዋችሁ። እኔን ግን አላህ ነው ከሰባቱ ሰመያት በላይ ሆኖ ያዳረኝ። ቡኻሪ ዘግበውታል። እንግዲህ የነብዩም ምስት ወሃብያ ነች ማለት ነው ¡ የዘገቡት ቡኻሪስ? 4, እውቁ ሰሃቢይ አብደላህ ኢብኑ መስኡድ እንዲህ ይላሉ፦ العرش فوق الماء والله فوق العرش لا يخفى عليه شيء من أعمالكم . أخرجه البيهقي في الأسماء والصفات بسند حسن. አርሽ በውሃ ላይ ነው አላህ ደሞ ከአርሽ በላይ ነው። ከምትሰሩት ስራ በሱ ምንም አይደበቅበትም። በይሃቂይ ጥሩ በሆነ ሰነድ ዘግበውታል። እንግዲህ አብደላህ ኢብኑ መስኡድም ወሃቢያ ነበሩ ማለት ነው ¡ የሰሃባዎችን መንገድ በመከተላችን ምክንያት ስማችንን ወዳንተ ስም (ወደ አል ወሃብ) ላስጠጋህልን ጌታ ስፍር ቁጥር የሌለው ምስጋና ይገባህ!! እንሸ አላህ ይቀጥላል... (ሌላ ግዜ የለቀኩት ተጨምሮበት ድጋሚ የተፖሰተ እንሸ አላህ ቀጣይ ክፍል በሰሞኑ...) ✍ወንድማችሁ ጅብሪል ሱልጣን

አህባሽና ጉዷ! ሶሂህ የሆነ የማያወላዳ ከረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም መምጣቱ በተረጋገጠ የሀዲስ ዘገባ "አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑ" ሲደርሳቸው እርምጃቸው ሀዲሱን አለመቀበል መሆኑን በግልፅ ተናግረዋል። ረሱልን (ሰ.ዓ.ወ) ሙጀሲም ናቸው ላለማለት ያላቸው የመጨረሻው ምርጫ ሀዲሱን መመለስ በመሆኑ ነው!! የቁርአንን እና የሀዲስን ቀጥተኛ አስተምህሮ "ከአዕምሮ ጋር ይጋጫል" በሚል ላለመቀበል የሚሄዱበትን የተህሪፍ አካሄድ ያስተዋለ ሰው እምነታቸው ምንኛ የተሳሳተ መሆኑን ይረዳል። ከሰሀባዎችና ከታቢዒዮች የተነገሩ እውነታዎችን ሁሉ በተልካሻ ምክንያቶች ከመቀበል ይሰናከላሉ!! ስለ ጌታቸው በቁርአንና ሀዲስ መሰረት ያመኑትን ሰዎች "ሀሸዊያ፣ ሙጀሲም፣ ወሀቢያ..." የሚል ቅፅላ ስም በመስጠት ከሰዎች ሊያርቁ ይታገላሉ" እውነታው ግን የእምነታቸው መነሻ አእምሮ መሆኑና ከአእምሮ ጋር የተጋጨ ነገር ሁሉ - ቁርአንና ትክክለኛ ሀዲስም ቢሆን- ስለማይቀበሉ መሆኑ ነው። የቁርአን ዟሂሩ ኩፍር ያስተምራል ከሚልህ ጠሞ አጥማሚ አህባሽ ለምን እንደምናስጠነቅቅህ ተገለጠልህ?? ወዳጄ!! ኪታብና ሱናን ይዘህ ልትጠም አትችልም። ለአእምሯቸው ፍላጎቷን እየመገቡ የሚኖሩትን ትተህ ጌታችን አጥብቀን እንይዘው ዘንድ የላከልንን ቁርአንና ሱናን በሰለፎች አረዳድ መሰረት ጨምድደህ ያዝ!! የወቃሾች ወቀሳ እንዳይሸነግልህ!!! tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1

የአህባሽን እምነት ተመልከት!!! -------- ዲን ከሰለፎች ብቻ የሚወሰድ አይደለም ይላሉ! ለምን??? የሰለፎች የቁርአን ትንታኔ የነሱን ቁርአንን አጣሞ መተርጎም አካሄዳቸውን ስለሚያንኮታኩትባቸው ነው!!! ኢስተዋ ሰለፎች እንደፈሰሩት ዓላ ወርተፈዓ ነው። ቡኻሪ ሰሂሃቸው ላይ አስቀምጠውታል። ኢስተውላ ብለው የፈሰሩት ሙዕተዚላዎችን መንገድ የተከተለው አህባሽ ግን ግራ ሲገባው ዲን ከሰለፎች ብቻ አይወሰድም እያሉ ነው!! ሰዎችዬ ወደ ኪታብና ሱና በሰለፎች አረዳድ መመለስን የመሰለ መንገድ የለም!! ከሰሀባና ታቢዒዮች የተሻልኩ ነኝ ከሚል ገልቱ አመለካከት እንጠበቅ ዘንድ!! tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1