Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Kanalga Telegram’da o‘tish
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
Ko'proq ko'rsatish213
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-430 kun
Postlar arxiv
🇵🇸 ንፅዎችን አደራ
I love you ብየ - አላበዛም ጣጣ፤
በጣም እወዳችኋለሁ - ነብሴ እስኪወጣ፤
ውስጤ ቢያመኝም - አይኔ ቢመረቅዝ፤
ለእናንተ ያለኝ ፍቅር - መቼም አይቀዘቅዝ፤
ባገኝም እበላለሁ - ባጣም ተበድሬ፤
ክፉ አይካችሁ - ሞቼም ተቀብሬ፤
ወሰላሙ አለይኩም - ፍቅሬን በስንኝ፤
እስቲ ልጀምር - ኢብኑ ሙዘሚል ነኝ።
የረህማን የአላህ - እውቀት ለግሳቸው፤
ለማህበረሰቡ የሚጠቅም - ለሀገር የሚተርፋቸው፤
ጀባሩ ያአዚዝ - ሲሳይ ለግሳቸው፤
የድሆችን ሀዘን - እንባ የሚያብስላቸው፤
በተውሒዱም ቀጥ - በሱና አፅናቸው፤
በሀቁ ጎዳና እንጂ - እባክህ አትግደላቸው።
እነሱ ናቸው - ምሳሌ የፍቅር፤
ባለ ንፁህ ልብ - ሰውን የሚቀይር፤
እውነት ነው ልባቸው - ሐቅን የሚያፈቅር፤
በቃ ፍቅር ነው - የንፁህነታቸው ሚስጥር
ዝግ ሆኖ አያውቅም - የመልካምነታቸው በር፤
የወንድምነት ቁጣ - ክፋት መስሏችሁ
ተቀይማችሁም እንደሆን - እኔ አስከፍቻችሁ፤
ሰብሬው ከሆነ - መልካሙን ልባችሁ፤
አውፍ በሉኝ እንደው - ለአላህ ብላችሁ፤
ይቅር በሉኝ እንደው - ለአላህ ብላችሁ።
ምኞቴ ብዙ ነበር - ጊዜም አልፈቅድ አለ፤
ሰዓቱ ጉድ ሰራኝ - ገና ነኝ እያለ፤
እሁድን ስጠብቅ - ሰኞ ከተፍ አለ፤
ማክሰኞ ብትዘገይስ - አረ እንደው ምን አለ⁉️፤
ለካ! ሞዴል እየጠበቅኩ - ሚኒስትሪ ደረሰ፤
ቀን ተፈራረቀ - ወሩ ተጋመሰ፤
ወር ቀረን ስንል - ሳምንቱ ተደረመሰ፤
ጊዜም እንደ ቤት - ተሰርቶ ፈረሰ፤
እናም ይህ ጊዜ - ፈረሰና ሊለያየን፤
ሚኒስትሪ ደርሶ - ሰኔ 4 ነው አሉን፤
በሩ ተንኳኳ - ደርሶ የቁርጡ ቀን፤
ቀኑም አልቆም አለ - መያዝም አልቻልን፤
እባክህ ብንለው - እሱም ዝም አለን፤
ብዙ እናወጋ ነበር - ትንሽ ቢጠብቀን፤
ምን እናድርግ ታዲያ - አማራጭ አልሰጠን⁉️
በቀ❗️ እመካከራለሁ - ከጌታዬ ጋራ
መጥፎን አርቅላቸው - ከሚቀማመጡበት ስፍራ
ወዳጅ አበርክትላቸው - አላህን የሚፈራ፤
ሰውን የሚያከብር - የማያውቅ ጎራ፤
ህይወቷቸው ይመር - ኑሮአቸውም ይብራ፤
እባክህ የአላህ - ተማሪዎቼን አደራ፤
እባክህ የአላህ - ንፁዎችን አደራ።
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
▭▬▬▭▭▬▬▭▭▬▭▬▭▬▭▬
⭕️ ማስታወሻነቱ: ለ2016 ዓ.ል ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎቼ (ለወንድም እህቶቼ) ይሁን❗️
══════════════
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇
➊ t.me/AndalusGrade7and8
❷ t.me/AcademicEducations
➌ t.me/BasicComputer_Skills
➍ t.me/AndalusGrade5and6
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ዝግጅት የምሁራን ኮሚቴ አዋቅሮ ሰፋ ያለ ጥናት ሲያስጠና ቆይቷል። ኮሚቴው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎችን በዘጠኝ ዐብይ አጀንዳዎችና በ47 ንዑሳን አጀንዳዎች ቀንብቦ በማጠናቀር ለኮሚሸኑ ያቀረበ ሲሆን፣ የ47ቱ ንዑሳን አጀንዳዎችን ይዘት በዚህ ገጽ በተከታታይ እናቀርባለን።
እንዲህ ናት ዱንያ‼
==============
✍ «ልክ በአሁኗ ሰዓት ነገ ማታ ለሐጅ በረራ የነበራቸዉን የአንድ ትልቅ ሰው መቃብር እየቆፈርን ነው። ድንገት ነው ሕልፈታቸው።
ዱንያ እንዲህ ናት።
እኛ ብዙ እናስባለን፣ እናቅዳለን፤
አላህም የራሱ መሻት አለው፣
የሚሆነው ግን አላህ የሻው ብቻ ነው።
ለሐጅ ቲኬት ቆረጥክ ማለት ሄድክ ማለት አይደለም ።
ከቆረጥከው ቲኬት የአኺራ ጥሪ ቲኬት ቀድሞ ሊመጣ ይችላል ።
ለዚህም ነው ሞትን ልክ የሆነ አገር ሊሄድ ብሎ ቲኬት ቆርጦ እንደሚጠባበቅ ሰው ሁሌም ዝግጁ ሆነን መጠበቅ የሚገባን።
ሰው ከንቱ!!»
©: ሙሐመድ ሰይድ
ፈለስጢናውያን ወንድሞቻችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ልብ አድሚ ከመሆኑ አልፎ ምንም ማድረግ ባለመቻልህ የሚሰማህ ስሜት ልብን ይቆራርጣል።
ሆኖም ግን በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ዓይነት ፅሑፎችንም ሆኑ በአንደበት የሚነገሩ ንግግሮችን መጠንቀቅ የግድ ነው።
أرضيت يا رب؟
ጌታ ሆይ! የሆነውን (ጠላት እየሰራ ያለውን) ወደህ ነው?
ወይም
ጌታ ሆይ! አሁንስ? ወደድክ (ደስ አለህ)?
ማንኛውም ዓይነት ትርጉም ይታሰብበት ከአላህ ﷻ ጋር ስነ-ምግባርን መላበስ የግድ ነው።
ዑለማዎች ከአላህ ﷻ ጋር ሊኖረን ስለሚገባ ስነ-ምግባር ሲጠቅሱ "አላህ ﷻ ለምን እንዲህ አደረገ?" ተብሎ አይጠየቅም፤ ስርዓት አይደለም።
መጠየቅ ያለበት "ከዚህ ተግባር በስተጀርባ ያለው የአላህ ጥበብ (حكمة) ምንድነው?" ተብሎ ነው መጠየቅ ያለበት።
ምክንያቱም አላህ ራሱን በቁርኣን ሲገልፅ
{ لَا یُسۡـَٔلُ عَمَّا یَفۡعَلُ وَهُمۡ یُسۡـَٔلُونَ }
"ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ፡፡" ብሎ ነው የገለፀው።
ብዙ ግፎች በኛ፣ በቤተሰቦቻችን፣ በሃገራችን፣ ሌላ ቦታ ባሉ ሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ ይደርሱ ይሆናል ነገር ግን ከጌታችን ጋር ያለውን ስነ-ምግባር እና የአላህን ልቅና መርሳት ብሎም በሱ ድንበር ማለፍ ተገቢ አይደለም።
ደግሞም አላህ ዘንጊ አይደለም
{ وَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱللَّهَ غَـٰفِلًا عَمَّا یَعۡمَلُ ٱلظَّـٰلِمُونَۚ إِنَّمَا یُؤَخِّرُهُمۡ لِیَوۡمࣲ تَشۡخَصُ فِیهِ ٱلۡأَبۡصَـٰرُ }
"አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡"
ጌታዬ ድረስላቸው 🤲
فوائد الصلاة على النبي
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
الشيخ ابن عثيمين رحمه اللهበጁምዓ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ…
ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾
“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”
📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1531
✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
📱፦ https://bit.ly/486xnrS
📱፦ https://bit.ly/41zEZkk
📱፦ https://bit.ly/4arMbTx
📱፦ https://bit.ly/41tIUPv
📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh
ኢቲቪ ሙስሊሙ ተወክሏል የሚለውን ለማሳየት የአንድን አማኢም የለበሱ አባት ፎቶ ጎላ አድርጎ አቅርቦልናል።
ከ2000 ተሳታፊ ውስጥ 100 መሙላታቸው የሚያጠራጥሩ ተሳታፊዎች እያሉ፤ በእኩል ቁጥር የተወከልን ይመስል ዘገባው ላይ ደብለቅ ያደርጓቸዋል። ከፊትም ያስቀምጧቸዋል። ከጀርባ ግን ሺዎች ሌሎች አሏቸው።
ሞኝህን ፈልግ አባቴ!
በተኩላ ዘመን በግ አይደለንም‼
መጅሊሱንና ፕሬዝዳንቱን አድንቁልኝ‼
=========================
(«መብታችንን ተቀማን ብለን እንደወትሮው አንገታችንን ደፍተን አንቀመጥም!» ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ)
||
✍ የፌዴራሉ መጅሊስ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽነጀ ሙስሊሙን አግልሎ እየሄደበት ያለውን መንገድ ቀድሞ ነቅቶበታል። መንቃት ብቻ ሳይሆን እንዲያስተካክል ወትውቷል። በግል በማናገር ካደረገው ጥረት ባሻገር በይፋዊ ደብዳቤም ባለፈ አሳውቋል።
እነሆ ዛሬም የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከሃሩን ሚዲያ ጋር የነበራቸው ቆይታ ሃሩን ሚዲያ በዚህ ጽሑፍ አቅርቦታል።
«ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሀጅ ኢብራሂም መልእክት አስተላለፉ።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የዘመናት የታሪክ ጠባሳ አለባቸው በዚሁ የተነሳ የሀገራዊ ምክክር ሲነሳ ቀድሞ የተደሰተው ሙስሊም ማህበረሰብ መሆኑን እንደተቋም ኮሚሽኑ በአዋጅ ሲቋቋም ቢሯቸው በመገኘት "የእንኳን ደስ አላችሁ" መልዕክት ያስተላለፈው በቀዳሚነት መጅሊሱ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ተናግረዋል።የሀገራዊ ምክክር ሂደት ከተጀመረበት ባለፉት ሁለት አመታት ሙስሊምን ማህበረሰብ በተመለከተ እንደ ተቋም ከኮሚሹኑ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች ማድረጋቸውን አንስተዋል።
...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ለምክክር ሒደት የሚቀርቡ የሀገሪቱን ሙስሊሞች አጀንዳዎች በተመለከተ ታላላቅ ምሁራንን ፤ኡለማኦች፣ የታሪክ ባለሙያዎች፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰውችና ሌሎች አካላት በማካተት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች በ9 አጀንዳዎች ተካተው፣በ47 ጥያቄ ቀርቦ የካቲት ወር ላይ ለኮሚሽኑ ማቅረቡን ሼኽ ሀጂ ለሀሩን ሚዲያ ገልፀዋል።የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታ በሚያደርግበት ወቅት ሙስሊሙ በሚመጥን ልክ አለማካተቱን በፌዴራል መጅሊሱ ስር ካሉት የክልል እና ከተማ አስተዳደር መጅሊሶች ካቀረቡት ቅሬታ መረዳታቸውን አያይዘው ገልፀው ነገር ግን ቁጥሩን በትክክል የሚያስቀምጥ መረጃ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል።
...
የሙስሊሙን አጀንዳዎች እና የተሳታፊ ልየታ ሂደቱን በተመለከተ መጅሊሱ ፕሬዚደንቱ የሚመራ የመጅሊሱን ስራ አስኪያጅ እና የህግ ክፍሉን ያካተተ ልዑክ ከኮሚሽኑ አመራሮች ጋር ከሰሞኑ የፊትለፊት ውይይት ማድረጋቸውን አንስተው ተፈፃሚነቱን እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል።ለመሆኑ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሙስሊሙን ቅሬታ ጆሮዳባ ብሎ የሚቀጥል ከሆነስ የመጅሊሱ አቋም ምን ይሆናል?በሚል ከሀሩን ሚዲያ ጋዜጠኛ ከማል ኑርዬ ለተነሳላቸው ጥያቄ
"እንደዛ ይሆናል ብለን አናምንም ነገር ግን እኛ እንደትላንቱ መብታችንን ተቀማን ብለን አንገታችንን ደፍተን ዝም አንልም በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ትግላችንን እንቀጥላለን ብለዋል።ሙስሊሙ ማህበረሰብ በያለበት በሰላማዊ መንገድ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ሀገሩን እንድገነባ አንድነቱን እንድጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
...
¤ሀሩን ሚዲያ ከፌዴራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ጋር ያደረገውን ቆይታ በነገው ዕለት ወደናንተ ያደርሳል!»
...
©ሀሩን ሚዲያ
||
t.me/MuradTadesse
ጥያቄ
በቀን ውስጥ በሆነ ሰዓት እንኳን ቁርዓንን አንብበሃል?
ካልሆነ ግን👇
★ በራስህ ላይ አልቅስ!
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓
@tolehaahmed
┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
ለሌሎች ሼር የሚያደርግን አካል
አላህ ይዘንለት❕
🤲 ኢላሂ !
በውዴታቸው ቅን የሆኑ የዲን ወንድሞችን ለግሰን!
ዑመር ኢብኑል ኸጣብ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ብለዋል፡-
"ከእስልምና ቀጥሎ ከጥሩ ወንድም በላይ ምንም አይነት በላጭ ነገር አልተሰጠም።"
ቁወቱ አል–ቁሉብ - (178/2)
ኢማም አሽ– ሻፊኢይ - አላህ ይዘንላቸውና፡-
“ከወንድማማቾችን ጋር አብሮ ማሳለፍ የሚያክል ደስታ የለም፣ ወንድሞቻችን መለያየት የሚያክል ሐዘን የለም።
ሹዐቡል ኢማን - (504/6))
NEWS | The Sun will be directly above the Ka'bah tomorrow (27th May 2024) at 12:18 PM (Makkah time). During the minute anyone who sees in the direction of the Sun will be perfectly aligned with the Qibla.
በትናንሽ ስህተቶች ብቻ ለም እንበሻሸቃለን⁉️
እስቲ ትላንት አብረን ያሳለፍነውን ጊዜ እናስበው!
እስቲ ትላንት በጥሩ ሁኔታ ተጎራብተን የኖርነባቸውን አመታቶች ቆም ብለን እናስባቸው።
ለምን በትንሽ ስህተቱ ወንድማችንን እንራቀው!?
ለምን በትንሽ ስህተቷ እህታችንን እንራቃት!?
የራቅናቸውን ሰዎች እንደ ነጭ ወረቀት ብናስባቸው፤ ይህ ነጭ ወረቀት መሬት ወደቀ እንበል። ወረቀቱ ይዞ የተነሳው አቧራ ትንሽ ነው (የቆሸሸው የወረቀቱ ክፍል ኢምንት ነው)።
ያ! የቀረው ወይም አቧራ ያልነካው ቦታ ሁሉ እኛ የጠላነው ሰው ጥሩ ጎኑ ነው። የሱ ስህተት ደግሞ ያቺ ትንሿ አቧራ የነካት ቦታ ብቻ ናት።
ታዲያ ለዚህች ኢምንት ነገር ብለን ያሳለፍናቸውን በጎ ነገራቶችን በሙሉ ለምን እንርሳቸው⁉️
ለምንስ በዚህች ትንሽ ስህተቱ ብቻ እንበሻሸቅ?
ለምንስ እዚህ ግባ በማይባል ስህተት እንገፋፋለን፣ እንባላለን፣ እንጎሻሸማለን⁉️
ያን ትንሽ አቧራ ከማየት አቧራ ያልነካውን ትልቁን ቦታ ብናይስ? ግዴላችሁም በቃ ለሰው ልጅ ፍቅር እንስጥ፤ በማይረባ ነገር አንበሻሸቅ።
ለሰው ልጅ ፍቅርህንና አክብሮትህን የምትሰጠው ደግሞ ከገንዘብህ ወይም ከዕድሜህ ሳይሆን ከንፁህ ልብህ ነው!!
ግን ብዙዎቻችን ፍቅርን ከገነዘባችንና ከዕድሜያችን ቀንሰን የምንሰጥ ይመስለንና ለሰው ልጅ.......
ፍቅርን፣ አክብሮትን፣ ታማኝነትን፣ ሐቀኝነትን፣ ይቅር ባይነትን፣ መርዳትንና መደገፍን፣ መቻቻልን፣ ምክርንና ተግሳፅን እንሰስታለን፤ አረ አንደውም ይባስ ብለን እንደ አውሬ ለብቻችን መኖርን እንመርጣለን።
⇒ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፤ የዋህነትና ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?
- እየተጠሉ መወደድ፤
- እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤
- በጥላቻ መንፈስ እየታዩ ፍቅርን መስጠት
- እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል።
⛔ ትዕግስት እንደ ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደ ማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው።
⇒ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን።
ደግነት ማለት ማየት ለማይችሉ አይን፤ መስማት ለማይችሉ ጆሮ ሆኖ የሚያገለግል መሣሪያ መሆኑን ማን በነገረን!!!
ደግነት የሚጀመረው ደግሞ በልባችን ስንመራ፣
o እንደራሳችን ቆጥረን ስለሌሎች ስንጨነቅ፣
o ዉለታን ሳንፈልግ ስናገለግል፣
o ሰው ስንቀን እኛ ግን ስናከብር
o ምላሽ ሳንጠብቅ መስጠት ስንጀምር ነው።
ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህንት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን። እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤
ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ⁉
⇒ ግዴላችሁም ወንድምና እህቶቼ እስቲ ብንበደልም ይቅርታ እንጠይቅ ምክንያቱም ይቅርታ ለአዕምሮ ነፃነትን፣ ለልብ እርካታን፣ ለመላው ሰውነታችን ደግሞ ደስታን ይሰጣል።
ታዲያ ነፃነት፣ እርካታንና ደስታን ማይፈልግ አለን⁉
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
⭕️ በመጨረሻም የምላችሁ ነገር ቢኖር፦
❝ጊዜ የሳለ ጎራዴ ነው❞ ይላሉ አረቦች❗️
አዎ! ጊዜ የሳለ ጎራዴ ነው፤ ካልተጠቀምንበት ይቆርጠናል!!
እናም በዚህ ጎራዴ በሆነው ጊዜያችን ከመባላትና ከመጠላላት ይልቅ አብረን ተዋደን፣ ተከባብረን፣ ተደጋግፈን፣ አንዳችን አንዳችንን መክረን ወይም ገስፀን በሰላምና በፍቅር እንኑር። ካልሆነ ግን በጥላቻና በተንኮል ያሳለፍነው ጊዜ እራሳችንን ቆርጦ ይጥለናል።
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ለአስታያየት: t.me/ReshadMuzemil
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
Telegram: t.me/SharpSwords1
Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1
YouTube: youtube.com/@SharpSwords1
Instagram: Instagram.com/sharp_swords1
Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
