uz
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Kanalga Telegram’da o‘tish

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Ko'proq ko'rsatish
213
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-430 kun
Postlar arxiv
ጠቃሚ ዱዓእ! ከዓዒሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ: እንዲህ ትላለች፦ ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ በማለት ይህን ዱዓእ ያደርጉ ነበር፦ ﴿اللَّهُمَّ إنِّي أَعُوذُ بكَ مِن شَرِّ ما عَمِلْتُ، وَشَرِّ ما لَمْ أَعْمَلْ﴾ “አላህ ሆይ! ከፈፀምኩት ነገር ክፋት። ካልፈፀምኩትም ነገር ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2716 ©️ ©️

አንዳዴ ሰዎች በክፉ አቅደዉ በወረወሩህ ጉድጓ ጌታህ አንስቶ ከእነሱ በላይ ከፍ ያደርገሃል። እነሱ የመጨረሻዉ ነው በቃ አብቅቶለታል ብለው በማሰብ ሲወረውሩህ፤ አዛኙ ጌታህ ግን ያን ጉዞ የስኬትህ ጅም
አንዳዴ ሰዎች በክፉ አቅደዉ በወረወሩህ ጉድጓ ጌታህ አንስቶ ከእነሱ በላይ ከፍ ያደርገሃል። እነሱ የመጨረሻዉ ነው በቃ አብቅቶለታል ብለው በማሰብ ሲወረውሩህ፤ አዛኙ ጌታህ ግን ያን ጉዞ የስኬትህ ጅምር ያደርገዋል‼️ ▬ መገፋትህን ብዙም አትጥላዉ! መገፋት ጥሩ  ነዉ። ወተት ተገፍቶ ይረጋና አናት ላይ ይወጣል ይላሉ የሃገሬ  ሰዎች! ©️

"ሒጃባችሁን ካላወለቃችሁ ፈተና ላይ አትቀመጡም!" - ዶክተር ዘላለም  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ትምህርት መምህር ነው :: በዛሬው እለት 2ኛ አመት ተማሪዎችን final exam ይፈትን ዘንድ በገባበት ሒጃቢስቶችን ወይ ሂጃባችሁን አውልቁ ወይ ደግሞ ክላሱን ለቃችሁ ውጡ በማለት በእብሪት ተናግሯል :: የአንዲት እህትንም ሒጃብ ለማውለቅ ሙከራ አድርጓል :: ልትወጣ ስትል ተመለሺ ብሎ ተመልሳ ብትፈተንም እሷ ላይና ሌሎች ሒጃቢስቶች ላይ በሙሉ ፈርሟል ::    ድፍረት ነው ! ጋጠ ወጥነት ነው ! ሙስሊም ጠልነት ነው ! ጉዳዩን ጀመዓው ይዞ እስከ ጥግ ድረስ ይሄዳል :: መድረስ እስካለብን እንደርሳለን :: ሁላችሁም በንቃት ተከታተሉ ::    በሒጃባችን ላይ የሚሰነዘርን ምንም ነገር አንታገስም ! በየክላሳችሁ በሀይማኖታችን ላይ የሚቀረሹ መምህራን ካሉ በአላህ ይሁንባችሁ አትታገሷቸው :: በሚገባቸው ቋንቋ አናግሯቸው :: ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎ

ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ብለዋል፡- "ስትሳሳት የሚመሩህ፣ መንገድ ስትስት የሚጠቁሙህ፣ ከረሳህ የሚያስታውሱህ፣ የማታውቅ ከሆንክ የሚያስተምሩህን ጥሩ ሰዎችን መጎዳኘት ላይ ጥረት አድርግ።” (ሸርሕ አል-ቡኻሪይ /ኢብኑ ዑሰይሚን 62/1)

Night falls and Makkah begins to shine.
Night falls and Makkah begins to shine.

#ዱኒያ... ጊዜያዊ መኖሪያ እንጂ ዘላለማዊ መኖሪያ አይደለችም። ለዱኒያ ብዙ አትድከምላት፣ ብዙ አታስብላት፣ ብዙም አትጨነቅላት:: ➞ ….ይልቅ ለአኺራህ ድከም፣ ለአኺራህ አስብ፣ ለአኺራህ ተጨነቅ፣ ለአኺራህ ስራ። ባለህና በምታገኘዉ ነገር ሁሌም ደስተኛ ሁን። ⭕️ እመነኝ! ጭንቀትህ ለዱኒያ ሳይሆን ለአኺራ መሆን ሲጀምር የውስጥ ደስታ ሰላምና መረጋጋት ታገኛለህ፡፡❗️   ▮ለዚህች ብልጭልጭና ጊዚያዊ አለም ቅንጣት ታክል ሳትጨነቅ ለነገዉ የአኺራ ህወትህ እንዲያምርልህ ወደ ጌታህ አልቅስ። ➽ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦  "ሀሳቡና ጭንቁ ዱኒያ የሆነ ሰው አላህ ጉዳዩን ይበታትንበታል። ድህነቱን በአይኑ መሀል ያደርግበታል።ከዱኒያ የተወሰነለትን እንጂ አያገኝም። ⭕️ ሀሳቡና ጭንቀቱ አኼራ የሆነ መብቃቃትን በልቡ ያደርግለታል። ጉዳዩን ይሰበስብለታል። ዱኒያ የግዷን ወደሱ ትመጣለታለች።" (ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 950) ያረብ መጨረሻዬን አሳምርልኝ🤲

▮የምትጠይቅ ከሆነ አላህን ብቻ ጠይቅ፤ እገዛም ካስፈለገህ በአላህ ብቻ ታገዝ❗️ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰልም) http://Ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/Reshad
▮የምትጠይቅ ከሆነ አላህን ብቻ ጠይቅ፤ እገዛም ካስፈለገህ በአላህ ብቻ ታገዝ❗️ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰልም) http://Ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/ReshadMuzemil

#The_truth_is_with_the_evidences قال العلامة ابن عثيمين رحمه الله، " الحق ما قام الدليل عليه وليس الحق فيما عمله الناس " [الف
#The_truth_is_with_the_evidences قال العلامة ابن عثيمين رحمه الله، " الحق ما قام الدليل عليه وليس الحق فيما عمله الناس " [الفتاوى 7/367]📔 Shaykh ibn ‘Uthaymīn (may Allāh have mercy on him) said, “The truth is what the proof is established upon, and the truth is not in what the people do.” [Al-Fatāwā 7/367]📔 translation: The_Authentic_Sunnah

Pictures: Salat Ul Istisqa ( Rain seeking prayers) led by Sheikh Hameed in Masjid An Nabawi, Madinah today.
+7
Pictures: Salat Ul Istisqa ( Rain seeking prayers) led by Sheikh Hameed in Masjid An Nabawi, Madinah today.

Pictures: Jummah led by Sheikh Qasim in Masjid An Nabawi, Madinah today.
+3
Pictures: Jummah led by Sheikh Qasim in Masjid An Nabawi, Madinah today.

አቡበከር አልወርራቅ አልበልኺይ እንዲህ ይላሉ፦ “የረጀብ ወር የአዝመራ ወር ነው፣ የሻዕባን ወር ውሃ የምናጠጣበት ወር ሲሆን የረመዳን ወር ደግሞ የአጨዳ ወር ነው።” 📚( لطائف المعارف/ص٢
አቡበከር አልወርራቅ አልበልኺይ እንዲህ ይላሉ፦ “የረጀብ ወር የአዝመራ ወር ነው፣ የሻዕባን ወር ውሃ የምናጠጣበት ወር ሲሆን የረመዳን ወር ደግሞ የአጨዳ ወር ነው።” 📚( لطائف المعارف/ص٢٣٤ )

⭕️ ከትዝብቴ ማህደር 🔰 መልካምነት በአላዋቂነት ሲፈተን ........... ➽ እነሱ ለራሳቸው አይጨነቁም «እሱ ግን ይጠበብላቸዋል»❗️ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ➞ እነሱ ለራሳቸው አይጨነቁም «እሱ ግን ይጠበብላቸዋል»❗️ ➞ እነሱ ለህይወታቸው አያስቡም «እሱ ግን መስዋዕትነት ይከፍልላቸዋል»❗️ ➞ እነሱ በህይወታቸው እያፌዙ ወደ ቁልቁል ለመውረድ ይሯሯጣሉ «እሱ ግን ቁልቁል እንዳይወርዱ የተቻለውን ያደርጋል»❗️ ምላሽ ሳይፈልጉ ለአላህ ብቻ ብሎ ሰውን መርዳት። ግን እጅግ በጣም ፈታኝና ደካማ ሰው የማይችለው ነገር ነው። አዎ ሰዎች ራሳቸውን እየጎዱ ከአጠገባቸው ያለ መልካም አሳቢ ደግሞ ጉዳትን ይከላከልላቸዋል። ይህን የሚያደርገው የአላህ ፍራቻ ልቡ ላይ ያለ ሰው ብቻና ብቻ ነው። ይህን የሚያደርገው ያ ሰው ነው “እውነተኛ የአላህ ባሪያ (ኢባዱራህማን)” የሆነ❗️ በርግጥም ያ ሰው እድለኛ ነው “እውነተኛ የአላህ ባሪያ የሆነ”። በርግጥም ያ ሰው የስኬት ተምሳሌት ነው “ሰዎችን ለአላህ ብሎ የሚረዳ” ! ምንም እኳን ወቀሳው፣ ዛቻው፣ ትችቱ ቢበዛበትም ► እየተጠላ እሱ ግን «ይወዳል»❗️ ► እየተገፋ እሱ ግን «አለሁኝ ይላል»❗️ ► ሰዎች እያሾፉበት እሱ ግን «ለአኺራው ጥረት ያደርጋል»❗️ ► ሰዎች ጅል ምንም ነገር የማያውቅ ሞኝ አድርገው ያስቡታል እሱ ግን «ያወቃትን ያስተምራል፣ ባወቀው ለመስራት ጥረት ያደርጋል»❗️ ► የሚናገረውን ነገር ብዙዎች ባይሰሙትም እሱ ግን «ሀቅ ከመናገር ወደኋላ አይልም»❗️ ▮እንደዚህ ያለ ሰው መሆን ከባድ ነው፤ ነገር ግን የውስጥ ፍላጎት ካለንና የአላህ ፍራቻ ልባችን ላይ ካለ፤ የሚቻልም ነው‼️ o እንደራሳችን ቆጥረን ስለሌሎች ስንጨነቅ ፣ o ዉለታን ሳንፈልግ ለጌታችን ብለን ስናገለግል፣ o ሰው ሲንቀን እኛ ግን ስናከብር o ምላሽ ሳንጠብቅ ለአላህ ብለን መስጠት ስንጀምር ይሄኔ ልባችን ላይ የመልካምነት ቡቃያ 🌱 እያደገ ይሄዳል። ⇒ ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህነት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን። ⇒ እውነታው ግን ለአላህ ብሎ ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤ ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ⁉ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል https://t.me/SharpSwords1 tiktok.com/@sharpswords1 ✔️ ummalife.com/ReshadMuzemil 👉 ለሐሳብ፣ አስታያየት፣ ጥቆማ፣ ለትኛውም ጥያቄና ድጋፍ ለመጠየቅ 👇👇👇 ✔️ t.me/ReshadMuzemil

🍃🍃🍃ጥቆማ🍃🍃🍃 🌿 ቅን መሆን ባትችል ቅንቅን አትሁን!! 🍃አላህ አይፈራም" ብላችሁ በምትገምቱት ሰው ላይ ቢሆን እንኳ አላህን ፍሩ!! 🌿ሸይጣን ልባችሁ ላይ ባኖረው ጥቁር ጥላቻ እና እውነቱን በተቃረነ ጥርጣሬ ተነስታችሁእከሌ እንዲህ ነው እያላችሁ የከፊል ወንድሞችን ስም ለማጠልሸትና ለማሳቀቅ የሚቋምጣችሁ ወንድሞች ወላሂ ከባዱን ቀን አስታውሱ!! 🌿ክፉ ነው ብላችሁ በምታስቡት ሰው ላይ ቢሆን እንኳ በምታልፉት ድንበርና በምትቀጥፉት ቀጠፋ ትጠየቃላችሁ።!! 🌿የዐይን ጥቅሻና የልብ ሚስጥር የሚያውቀው አላህ እንጂ አንተ አይደለህም?! ወንድሜ ተረጋጋ ሁሉንም አውቃለሁ አትበል!! 🍃በእውቀትህና በልክህ ላይ ሆነ አውራ?!   🌿 አማርኛ ወደ ቀኝ እያነበብክህ ወደ ግራ የምትተረጉመው ኸረ ተው ተመከር?!    🍃 አንተ እንዳይከፋህ ተብሎ ግን ልክ ተከፍሎት ፈትዋ ሲጠየቅ ቀድሞ ምን ብየ ልስጥህ እንደ ሚለው በላተኛ እኔ የምለውን በል በቀደድኩት ፍሰሱ አትበል!! ©️ Via copy

የእህት ወንድሞችህን ስቃይ እያየህ እጅህን ከፍ አድርገህ ያ አላህ ማለት እንዴት ተሳነህ?! ቀልብህ ማዘን ውስጥህስ መናጥ እንዴት አቃተው?! ስለነሱ መስማትስ ስለለምን ትሰለቻለህ?! ልጆችህ የስጋ እ
የእህት ወንድሞችህን ስቃይ እያየህ እጅህን ከፍ አድርገህ ያ አላህ ማለት እንዴት ተሳነህ?! ቀልብህ ማዘን ውስጥህስ መናጥ እንዴት አቃተው?! ስለነሱ መስማትስ ስለለምን ትሰለቻለህ?! ልጆችህ የስጋ እህት ወንድሞችህ ቢሆኑ ሊሰማህ የሚችለው ህመም ስለፈለስጢኖችም ሲሆን ይሰማህ! አላህ ይርዳቸው

〽️ እውነትም አልኖረች እኛ ካሌለናት - ከጎኗ ከእውነት፤ በሷ እየኖርን - እኛ ካልደገፍናት፤ ሰውነታችን አምሮ - ካላሸበረቀንባት፤ እውነተኛ ካልሆንን - ተዘፍቀን በውሸት፤ መያዛችን አይቀርም - በ
〽️ እውነትም አልኖረች እኛ ካሌለናት - ከጎኗ ከእውነት፤ በሷ እየኖርን - እኛ ካልደገፍናት፤ ሰውነታችን አምሮ - ካላሸበረቀንባት፤ እውነተኛ ካልሆንን - ተዘፍቀን በውሸት፤ መያዛችን አይቀርም - በአንድ ቀን ቁጭት፤ እየኖርን ሳለ - የመብረቅ ጋጋታ፤ አይናችን አንጋጠን - አምላኬ ይቅርታ፤ ይሀው አካላችን - በእውነት ተረታ፤ ምንም ብናስመስል - በደቂቃዎች ቆይታ፤ የምንሞት መስሎን - የያዘን ብዥታ፤ መፍራት ስንጀምር - የውሸታችን ኮታ፤ መቁጠር ስንጀምር - የባጢላችን ብዛት፤ አውጥተን ስናሰላላስል - የውሸታችንን ይዘት፤ ለካስ ጎተራ ሞልቷል - የጥፋታችን ቅዠት፤ እውነትም አልኖርም በሚል - ከበቀለችበት ጠፋች፤  እኮ በኛ ጥፋት - በቅፅበት በረገገች፤ ከአፍንጫየ ውጡ ብላን - ጎራዋን ቀየረች፣ የሚናገራትን ፍልለጋ - ከውሸተኞች ራቀች። --- ለካስ ነገሩ - እንዲህ ነው፤ እኛ ነን ያልገባን - ሁኔታውን ያልተረዳነው፤ የእውነትን እውነት - እኛ ነን ያላወቅነው፤ ለካስ ወገኖቼ ነገሩ ወዲህ ነው፤ እውነት ቤት ስትሰራ - ውሸት ላግዝ ካለች፤ ጭቃ ከረገጠች - ሚስማር ካቀበለች፤ ቤቱም አልተሰራ - እውነትም አልኖረች ቤቱም አልተሰራ - እውነትም አልኖረች። ግጥም:- በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል https://t.me/SharpSwords1 Twitter.com/SharpSwords1 tiktok.com/@sharpswords1 ✔️ ummalife.com/ReshadMuzemil ✔️ t.me/ReshadMuzemil

#ረሱል (ﷺ) ላይ ድንበር ከማለፍ ተጠንቀቅ! ከዑመር ኢብኑል ኽጣብ (رضيﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لا تُطْرُونِي كما أَطْرَتِ النَّصارى ابْنَ مَرْيَمَ؛ فإنَّما أَنا عَبْدُهُ، فَقُولوا: عبدُ اللَّهِ وَرَسُولُهُ.﴾ “ክርስትያኖች በመርየም ልጅ በኢሳ ላይ ድንበር እንዳለፉት በኔ ላይ ድንበር አትለፉ (ከፍ ከፍ አታድርጉኝ) እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ። የአላህ ባሪያና መልዕክተኛ በሉኝ።”