uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ግጥም

ግጥም

Kanalga Telegram’da o‘tish

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

Ko'proq ko'rsatish
5 640
Obunachilar
+324 soatlar
+267 kun
+11930 kun
Postlar arxiv
#ስልክ_ተደወለ ስልክ ተደወለ መላልሶ አቃጨለ        እኔ አነሳዋለሁ ብላ ሮጠች ሒሩት        እጮኛዋ መስሏት ይህች የኔ እኅት ስልኩ ጭርር ብሎ ሲደውል ቆየና እቴ ስታነሳው ዝም አለ እንደገና         ከዚያ እቴ አለች ማንን ፈላጊ ነው         ፍቀረኛዬ ይሆን አሁን የደወለው? ብላ ብትጠይቅ ወንድሜ እንዲህ አለ የለም የኔ ፍቅር ነች የኔዋ አምሳለ!         እማማም በተራ እነሱ አይደሉም         አለች ማኅበረተኞቼ ሳይሆኑ አይቀሩም አባቴም በፊናው የኔ ጓደኞች ናቸው የደወሉት ምን ሆነሻል አንች?         ብለው በጭቅጭቅ አፍ ላፍ ሲካፈቱ         ለኔ ነው ለኔ ነው ብለው ሲሟገቱ ያ! ያቃጨለው ስልክ መልሶ ጭጭ እስኪል ከጎረቤት ሔጄ የነበርኩ ስደውል         በጠቡ መሐከል በጣልቃ ገብቼ         እኔ ነኝ የደወልኩ አልኩኝ ዘመዶቼ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ደራሲ ታደለ ብጡል

#አዎ_ፍቅር_የለም በዝሙት ህሊና በክህደት እይታ በእምነት አልባ ቅኔ በጥቅመኞች ኩታ ከሆነ ልኬቱ የሚዛኑም ክብደት በእርግጥ ፍቅር የለም ሲረክስ ሰውነት ፍቅርን በፍቅር ለሚለካ ደግሞ የእውነት ፍቅር አለ ደጋግሞ ደጋግሞ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ኑዛዜ ቀበሮ ነኝ እኔ ዘመድ አልጠጋ አንደበቴ እሾህ ነው ሁሉን የሚወጋ      አውሬ ነኝ ተኩላ ነኝ ነገር አነፍናፊ      ስድ ነኝ ጠበኛ አጉል ተናዳፊ      ይሉኝታ የሌለኝ ሁሉን ነገር አጥፊ ዋሾ ነኝ ቀጠፊ እንዲሁም ሴሰኛ እርጉም ነኝ ክፉ ነኝ አጉል ቀናተኛ አፈጀሁ አረጀሁ በመሆን ምቀኛ      ነብር ነኝ ጭራቅ ነኝ የሰው ደም የምመጥ      አታልላለሁኝ ወዳጅ ዘመድ ሳልመርጥ      አምናለሁ በሰይጣን ከመላዕክት ይበልጥ እሰው ቤት እየዞርኩ ቅራሪ ሳጣራ ካንዱ ተቀብዪ ለሌላው ሳወራ ጨረስኩት ዕድሜዬን ቁምነገር ሳልሠራ      ክፋቴ ብዙ ነው አላውቅም ቁጥሩን      በግምት ይበልጣል ከአንድ ሚሊዮን      የኔ መጨረሻ ኧረ ምን ይሆን? ደከመኝ ታከተኝ መሆን ማን ዘራሽ እንዳልሰርቅ እንዳልገል ደግሞም አንዳልዋሽ አጣሁኝ መድኃኒት ኧረ የት ልሽሽ?      መልሱን የምታውቁ እኔን ያልሆናችሁ      ከእውነተኛው መንገድ ከቶ ያልራቃችሁ      አካፍሉኝ ምስጢሩን ለነፍስ ብላችሁ!          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ደራሲ ታደለ ብጡል

#አንድ_ነገር_አለ! አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ የተጋረደብን በጫጫታ ኩታ መረዳት ያልቻልነው የሰውነት ጥጉ ከፍታው ዝቅታው ውርደቱ ማዕረጉ በሀቅ ያልተቃኘ ያልገባን ግርታ አንድ ነገር አለ ያልታየን እውነታ ወደ ነፈሰበት የሚስብ አስልቶ ከሰውኛ ስሌት የሚጥል ጎትቶ መግነጢሳዊ ሀይል ለእኛ ያልታወቀን በዘር ዛር አዙሪት የሚያንቀጠቅጠን ያልታወቀን ህመም ያልታየን በሽታ አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ የግርግር ዓለም ረባሽ ውካታ የእራስ አቋም ነጥቆ በሰው የሚያስመራ ባልገባን በገባን ዘወትር የሚያስወራ እወነትን አስትቶ ከሀቅ የሚያጣላ በሆነ ባልሆነው ትውልድ የሚበላ ለማወቅ ያልጣርነው ሊገባን ያልቻለ ማየት ያልፈለግነው አንድ ነገር አለ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

Remember for daily checkin

#ሐዘኔ_ከበደ አፈር ፈጭተን ስናድግ እዚያ እኛ መንደር ገደብ ባልነበረው ተሳስረን በፍቅር እጅ ለጅ ተያይዘን ስንሸረሸር ምን ብለሽኝ ነበር? ምን ብዬሽ ነበር?          በዛፎች ከለላ አዝግመን ስንሔድ          የአበቦች ሽታ መዓዛው ሲያውድ          እንኳን ጠላትና ሲቀና ዘመድ          ተጋብተን ለመኖር ወልደን ለመክበድ ምኞት ሕልማችንን ያኔ ያቀድነውን ልንፈጽም ካልቻልን ቃል የገባነውን ዛሬ ቀዝቀዝ ካለ ያ ሁሉ ፍቅራችን በጣም ያሳዝናል ሰዎች መሆናችን          በወፎች ጫጫታ ልቤ ተመስጦ          ያንችም ልብ እንደኔ ኔው በሃሳብ ተውጦ          በፍቅር ትኩሳት አካላችን ቀልጦ          ጉድ እንዳልተባለ ሚሥጥሩ ተገልጦ የጋለው ፍቀራችን ዛሬ ከበረደ ደንዳናው ልባችን ለመናድ ከራደ ፍቅርን ያመነ ሰው መሆኑን ያበደ በእውን ተረዳሁት ሐዘኔ ከበደ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ   ✍ ደራሲ ታደለ ብጡል

#ከራስህ_ተስማማ ስትናገር ፎካሪ ዝም ስትል ፈሪ ዓለም ስም አታጣ ለአንተ ስታወጣ ክፉም ጥሩም ስራ ዝም በልም አውራ ስም ትሰጥሃለች እንዲህ ነው እያለች አንተ እርሷን አተስማ ከእራስህ ተስማማ ዛሬ ከላይ ሰቅላ ነገ ለምታወርድ ከሰውነት ክብርህ አንተ ብቻ አትውረድ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ወድቄ_ተሰበርኩ አተኩሮ ሲያየኝ ቀዝቃዛ መሰልኩት አፈፍ ቢያረገኝ እጁን ቀዘቀዝኩት        ሽንጤን ጨበጥ አርጎ አንገቴን አቅንቶ        ዓይን ዓይኔን እያዬ አፍ ከንፈሬን ከፍቶ ሳም-ላስ ቢያደርገኝ ዕውነት ቀዝቃዛ ነኝ የሱ ከንፈር መሞቅ እኔን ግን ገረመኝ        ከዚህማ ወዲያ ምኑ ይጠየቃል        ቃናዬ ተስማምቶት ምራቄን ይውጣል ደጋግሞ ሲስመኝ ሲመጠኝ ሲልሰኝ ሰውነቴ ሲቀል አቅም ሳጣ ተሰማኝ        ፍላጎት ምኞቱ ሞልቶለት ሲረካ        ገልበጥ ቀና አድርጎ ገላዬን ሲነካ ድንገት ሳያስበው ገፍተር ሲያደርገኝ ወድቄ ተሰበርኩ የመጠጥ ጠርሙስ ነኝ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ደራሲ ታደለ ብጡል

#ከዛሬ_ላይ_ጣለን በሰቀቀን ዜማ በብሶት ተሰልቶ ፣ የእድሜ ቁጥር ገደብ ሳንኖረው ሞልቶ ፣ የኖርን የመሰለን እድሜያችን የራቀ፣ በጭንቀት ተባዝቶ ሳይኖር አለቀ!!! በስጋም አልደላን በነፍስም አልታደልን፤ የህይወት አዙሪት ከዛሬ ላይ ጣለን።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ናፍቆት መለሎ ቁመናሽ ቀጭን ወገብሽ ኮራ ያለ ዳሌሽ ጉች ጉች ጡትሽ ኧረ እንዴት ከረሙ አንችስ ደህና ነሽ?        እኔ በበኩሌ በጣም ደህና ነኝ        ግን ለደብዳቤዬ መልስ ሳላገኝ        ባነቺ ናፍቆት ብቻ ሞቼ እንዳትቀብሩኝ ቢሮዬ ስገባ ስብሰባ ስቀመጥ አሳቤ ኮብሎ ወዳንቺ ዘንድ ሲሮጥ ሥጋቴ በዛና ጀመርኩኝ መደንገጥ        በሰው በደብዳቤ የላክሁት መልዕክት        ደርሶሽ ነው ዝም ያልሽው ወይስ ረሱት        እኔ እምሰቃየው በዝናሽ መጥፋት ከፋም ተናግሬሽ በነገር መሐል አስቀይሜሽ ከሆንኩ ፈጽሜ በደል ባይሆን ለይቅርታሽ ካሳውን ልክፈል         ይቅር ግድ የለኝም ያለፈውስ ይለፍ         በሽታ እንዳይዘኝ አብጄም እንዳልከንፍ         ለዚች ለደብዳቤ ቶሎ መልስሽ ይጻፍ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ደራሲ ታደለ ብጡል

#የሌቦች_እቁብ!! ሌቦች ተሰባስበው እቁብ መሰረቱ ሰብሳቢ ለመምረጥ እጅግ ተሟገቱ ማንስ ማንን ይመን የመንታፊ መንጋ አንድ ታማኝ ጠፍቶ አስመሳይ ቢንጋጋ ውሸታም በጋራ እድር ቢመሰርት መኖሩም ውሸት ነው መሞቱም የሐሰት ሀይማኖት ቢበዛ በስም ተለያይቶ አማኝ ሳይኖርበት የስም አሜን በዝቶ በምላስ ማሞገስ በልብ ግን መርከስ በማስመሰል ዜማ የውሸት መደገስ ባልዘነበ ዝናብ በዘር ጎርፍ መበስበስ በግም ፖለቲካ ቅዱሱ ሰው ሲረክስ እንዴት ኢትዮጵያችን እንደጥንቱ ትንገስ ቆመን እያወደስን የነበረው ሲፈርስ         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ገንዘብ ድሀ ከሀብታም ሰው የሚለይበት በገንዘብ መሆኑ እውነት ነው ውሸት?     እውነት ይሆን ውሸት እንደዚህ መባሉ     ገንዘብ ከመሰብሰብ መበተን መቅለሉ እውነት ይሆን ውሸት ደሀው ሰው ሲራብ የሀብታም ፍላጎት መቆጠብ ከምግብ      እውነት ይሆን ውሸት ዕዳ ከሌለበት      ድሀ ሰው ካብታሙ እኩል የሆነበት እንዲያው በደፈናው የሆነውን ሆኖ ምነው ገንዘብ ቢኖር ከሁሉም ተዋስኖ         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ    ✍ደራሲ ታደለ ብጡል

#ፍቅርን_ባይተካም ይታሰር ቀለበት ቃልን ያስታውሳል ፍቅርን ባይተካም አጥፊን ይታዘባል ፍቅርን ጠፍሮ አስሮ ባይጠብቅም የጎደለን እምነት ሰፍሮ ባይመልስም ይታሰር ቀለበት አጥፊን ያሳቅቃል በወለቀ ቁጥር ህሊናን ይከሳል ሐይል ባይኖረውም ክህደትን ለማስቆም አንደበት አውጥቶ ለፍርድ ባያቀርብም ቃል እያስታወሰ አጥፊን እንዲቀጣ ከቦርሳና ከኪስ ሲገባ ሲወጣ ህሊናን አድምቶ በደልን ይናገር ይደረግ ቀለበት ከጣት ላይ ይታሰር         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#ፍቅር_ወረተኛ ፍቅር እንደሞት ጥላ በድን አደረገኝ አጥንቴን ሰበረው ከቶ አዝለፈለፈኝ ፍቅር በአበባው መዓዛው ጣፈጠኝ አሁን ግን ጠውልጎ ሽታው አሰለቸኝ         የፍቅር ክፋቱ ትዝታ ነው ሲሉ         አላመንኩም ነበር ውሸት በመምሰሉ         አሁን ግን አወቅሁት ይሰማኛል ቁስሉ         የነደፈኝ መርዙ የወጋኝ ሾተሉ ይህ ጣፋጭ እንደማር መራር እንደኮሶ ልፍስፍስ እንደጥጥ ጥብቅ ከምሰሶ ዛሬ ህይወት አለው ነገ ይቀራል ፈርሶ ፍቅርን አትመኑት ቢታይ ድርብ ለብሶ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ      ✍ደራሲ ታደለ ብጡል

#የተቃርኖ_ሕግ ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#Tearline (1$ price in premarket 🔥) ✅|| tearline ይባላል። ይህ ኤርድሮፕ ብዙ ተጠቃሚ የለውም። ✅|| ለዛም በpre market ለአንድ የtearline ቶከን እስከ 1$ ዋጋ ደርሰዋል። 😱 ✅|| በ Gate.io exchange ዋሌት የፕሪማርኬቱ ዋጋ መመልከት ትችላላችሁ። ✅|| ሊስት የሚደረግበት ጊዜ በቅርቡ ነው ተብሏል። እጅግ ቀላል ነው። ሙሉ አሰራሩ አሳያችኋለሁ። በርግጥ ከባድ ነገር የለውም። ለጊዜው ታስኮችን እየሰራችሁ ጠብቁኝ። ከታች ባለው ሊንክ ጀምሩት 🏃‍♂ https://t.me/TearlineAI_Bot/app?startapp=8m9IQBTh_0

It is Very big expected Airdrop by this month give attention and do it more

#ችግር ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት        ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው        ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ደራሲ ታደለ ብጡል

Nodepay Download Nodepay App Download & Login ሁሉንም ታስክ ጨርሱ 600ፖይንት ይሰጣቿል ክሌም አድርጉ Browser ላይ ማይም ማድረግ ለተቸገራቹ በ Android App ስለጀመረ አውርዳቹ ከፍታቹ ማስቀመጥ ብቻ ነው። Join 👉 Start

ዓለም ቅንዝረኛ ብዙ ባል አግብታ ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ ✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ