cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

B-POEMS

Ecclesiastes 12 (አማ) - መክብብ 1: የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ብንኖር በዚህ ቻናል ላይ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች ፣ የተለያዩ ጽሑፎች ይቀርባሉ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
774
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-47 kunlar
-2130 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
[ግንቦት 11 የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል] ✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. በአክሱም ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡ ❤ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡ ♥ “ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ” ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡ ♥ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፡- “ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” (ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው) ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት፣ በማለት "አርያም" በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡ ♥ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡ ♥ ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም፦ ፩ኛ) ድጓ ፪ኛ) ጾመ ድጓ ፫ኛ) ምዕራፍ ፬ኛ) ዝማሬ ፭ኛ)መዋሥዕት ናቸው፡፡ ♥ እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ፣ በዕዝል፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ “ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ” ይላል፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡ ♥ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን “የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡ ♥ “ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን” ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ። ❤ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ” (በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር) ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡ ♥ በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡ ♥ ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት፦ “ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር... ” (ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል” ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት ጌታ በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡ ♥ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ፦ “ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ” (የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል) በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡ ♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ፡- “ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤ ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ”፡፡ (የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን፤ እናንተም ይኽነን ሊቅ አወድሱት። ✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
1040Loading...
02
https://youtu.be/gB1Z2OBR4KQ?si=x9DgIeWrL__Bo8NS
1230Loading...
03
"ዮም ፍሰሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም" ዘማሪ ፍቃዱ አማረ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
2420Loading...
04
“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ቅዱስ ያሬድ)
2291Loading...
05
https://youtu.be/VY5WNF2fIn0?si=xxPQcSG4DJ8pb-vE
2430Loading...
06
ሉቃ 24:5 " ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ "ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም ። እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል!
2892Loading...
07
እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት አደረሳችሁ
2583Loading...
08
ሐሙስ 1.ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል። 2.ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። 3. የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። 4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። 5. የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። 🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCmahlet👈                  👉@EOTCmahlet👈 👉@EOTCmahlet👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹       @EOTCmahlet     #Join & share
2113Loading...
09
Media files
2211Loading...
10
+ አንዲት ዘለላ እምባ   + ቅዱሱን መጽሐፍ ለማንበብ ፈልጌ በድንገት ብገልጠው ፣ አየዋት ያቺን ሴት የጌታዬን እግር በእንባዋ ስታጥበው ፣ ምናለ እሷን ብሆን ብዬ ተመኘሁኝ ፣ ለበደሌ ጸጸት እምባንም ላጣሁኝ ፣ ወለል ብሎ ታየኝ ያጠፋሁት ጥፋት ፣ ግልጥልጥ አለልኝ የበደሌም ክፋት ፣ ከዛም በመቀጠል አንድዬ ፈጣሪን እንዲህ ስል ጠየኩት ፣ እባክህን ስጠኝ አንዲት ዘለላ እምባ ፣ ለሰራሁት ስራ ለኀጢአቴ ላምባ ፣ የበደሌን ብዛት የኀጢአቴን ክፋት በማልቀስ ልግለጸው ፣ ፍቀድልኝና ከእግርህ ወድቄ በእምባዬ ልጠበው ፣ በዛውም ይታየኝ የጥፋቴ ብዛት ፣ ደግሜ እንዳልሰራው እንዲያድርብኝ ጸጸት ፣ ከሰጠኸኝ መክሊት አንዱን እምባ አድርገው ፣ ጽድቅን አትርፌበት ነፍሴን አድኜበት ላንተው ልመልሰው ፣ ✍ ብሩክ መለሰ @orthopoems @orthopoems @orthopoems
2874Loading...
11
#ዕረቡ በማቴዎስና በማርቆስ ወንጌል መሠረት በዚህ እለት ሦስት ነገሮች ተደርገዋል። 1. የካህናት አለቆች ጸሀፍትና ፈሪሳውያን በጌታ ላይ ተማክረዋል ሊያስገድሉትም ወስነዋ። 2. ጌታችን በስምኦን ዘለምጽ ቤት ተገኝቶ አንዲት ሴት(ማርያም እንተ ዕፍረት) ዋጋው የከበረ የአልባስጥሮስ ሽቱ ቀብታዋለች። 3. ይሁዳ ጌታን ለመሸጥ ወደ ጸሀፍት ካህናት ጋር በመሄድ ተዋውሏል። በአይሁድ ዘንድ 72 አባላት የነበሩት ሸንጎ ነበር። "ሲናድርየም " ይባላል።አብዛኛዎቹ ሰዱቃውያን ሲሆኑ ጥቂቶቹ ጸሀፎችና ፈሪሳውያን ነበሩ። የተሰበሰቡትና ጌታን እንዴት እንደሚይዙት የተማከሩት በካህናቱ አለቃ በቀያፋ ግቢ ነበር። በዚ ጊዜ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የነበረው ያስቆሮቱ ይሁዳ ወደ ስብሰባው በመሄድ "ምን ትሰጡኛላችሁ እኔ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ" በማለት ጌታን ለመሸጥ ተዋዋለ።ይህን ያደረገው በስምኦን ዘለምጽ ቤት እያሉ አንዲት ሴት ጌታን የከበረ ሽቱ ስትቀባው ለድሀ አዛኝ በመምሰል "ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር "ሲል ጌታ የልቡን መሻት አውቆ ስለተቃወመው አኩርፎ ሄዶ ተዋውሎ በ30 ብር የተስማማ። ከዛም ሊያስገድሉት ወስነዋል። እንዲሁም ሐሙስ በአል ስለነበር በአሉን አክብረው ውለው ማታ ላይ አስይዘው አርብ ጠዋት ሸንጎ ሊያቆሙት ተስማምተው ተለያዩ (ማቴ 26÷3.. ማር 14÷1-11 ሉቃ 22÷1-6) በዚህ እለት በቤተክርስቲያን የሚሰበከው ምስባክ - አንድ ሰአት መዝ 83÷5 - ሦስት ሰአት መዝ 41÷6 - ስድስት ሰአት መዝ 41÷5 - ዘጠኝ ሰአት መዝ 83÷2 - አስራ አንድ ሰአት መዝ 6÷2 © ተግባራዊ ክርስትና
1642Loading...
12
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ማክሠኞ በዚህ ዕለት አምላካችን ለጥያቄዎች በሙሉ መልስ የሰጠበት እና በስፋት ያስተማራቸው ትምህርቶች የሚታሰቡበት ዕለት ነው። ፩. የጥያቄ ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት አምላካችን ስለ ሥልጣኑ በካህናት አለቆችና በሕዝብ አለቆች"በምን ሥልጣንህ እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?"(ሉቃ፳:፩-፵፩) የሚል ጥያቄ ለፈተና የተጠየቀበት ዕለት በመሆኑ የጥያቄ ቀን ትባላለች፡፡ ጥያቄዎቹ በቁጥር አምስት ናቸው። እነዚህም:- ፩. ሥልጣኑን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፪) ለክፋት የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄውን በጥያቄ መልሶታል። ፪. በወይን አትክልት መስሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል። (ሉቃ፳:፱)ይህ ምሳሌ በቀጥታ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝ ተረድተውም ነበር። ፫. ግብርን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፳፪) ይህንንም በድንቅ ጥበቡ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብሎ መልሶላቸዋል። ፬. ትንሣኤ ሙታንን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፴፫) ከጋብቻ ጋር በተገናኘ ምድራዊ አስተሳሰብ ሰማያዊውን ኑሮ አውርደው ለጠየቁት ለሰዱቃውያን ከሞት በኋላ እንደ መላእክት ያለን ኑሮ የመኖር ዕድል እንዳለው የሰው ልጅ መልሶላቸዋል። ፭. ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ለምን ይሉታል የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።(ሉቃ፳:፵፩) መልስ ላጡበት ጥያቄ ራሱ በመመለስ እርሱ የዳዊት ጌታ መሆኑን አስተምሯቸዋል። ፪. የትምህርት ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት ደቀ መዛሙርቱን ሰፊ ትምህርትን ስለ መጨረሻው ዘመን ምልክቶች አስተምሯቸዋልና የትምህርት ቀን ተብላ ትጠራለች። (ሉቃ፳:፵፬-፵፯) ያስተማራቸው ትምህርቶች ፩. የአምልኮ መልክ ካላቸው ተጠንቀቁ ፪. ታይታን ከሚወዱ ተጠንቀቁ ፫. ለራሳቸው ክብርን ከሚሰጡ ተጠንቀቁ ፬. የባልቴቶችን ገንዘብ ከሚበሉ ተጠንቀቁ ፭. በምክንያት ጸሎት ከሚያረዝሙ ተጠንቀቁ ሌላው በግብረ ሕማማት ካህናት በዚህች ዕለት ስለሚያከናውኗቸው ስራዎች እንዲህ ተብሎ ተገልጿል:-"ከዚህ በኋላ በከበረች ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ከሌሊቱ መጀመሪያው ሰዓት ካህናት ይሰብሰቡ። ተዘከሮ እግዚኦ የሚለውን የዳዊት መዝሙር ወአሰሰልኩ ዕለተ እስከሚለው ድረስ ጸልዩ። ውዳሴ ማርያምም የቀዳሚትን ይድገሙ።" ግብረ ሕማማት (ገጽ፪፻፴፪) የመዝሙረ ዳዊት ምንባባት በ፩ ሰዓት (መዝ፴፬:፬-፭) በ፫ ሰዓት (መዝ፻፲፰:፻፶፬) በ፮ ሰዓት (መዝ፲፯:፲፯) በ፱ ሰዓት (መዝ፳፬:፩) በ፲፩ ሰዓት (መዝ፵፬:፮) @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
1874Loading...
13
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ሰኞ ፩. መርገመ በለስ (በለስ የተረገመችበት) ዕለት ነው። አንድምታ፡ ወንጌሉ እና ግብረ ሕማማቱ ላይ እንደተገለጸው ☞በለስ የቤተ እስራኤል እና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌ ናቸው ፡፡ ጌታችን ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ፤ አላገኘም፡፡ ስለዚህም እስራኤል ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡ ☞በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት "ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም፡፡" በማለት ፈጸማት ፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት ፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡ ☞በለስ ኃጢአት ናት ፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ "በአንቺ ፍሬ አይገኝ" ማለቱም "በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር" ማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በአምላካችን እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ ፪. አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተከናወነበት ዕለት ነው። ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት" ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፣ ገርፎም አስወጣቸው...'' እንዲል። (ማቴ ፳፩፡፲፫) ምስጢሩ :- ☞ቤተመቅደስ የሆንን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም በማለት ሊቃውንት ይገልጹታል። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
1932Loading...
14
https://youtu.be/okaGVdbrlgU?si=n5mqQO_Ey6FjLhfL
1900Loading...
15
፬. በሰሙነ  ሕማማት  ዕለተ  ዐርብ የስቅለቱ  መታሰቢያ  ነው፦  ምእመናኑ  በሰሙነ  ሕማማት  የሰሩትን  ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱን  በወይራ  ቅጠል  ትከሻቸውን  እየጠበጠቡ  ቀን  ከሰገዱት  ስግደት  በተጨማሪ  ሌላ  ስግደት  ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ  ምሳሌ ነው፡፡  ጥብጠባው የሚደረግለት  ሰው በህማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቁጥር ከፍ እያለ እንዲል ያደርጋል፡፡ ፭. አክፍሎት፡-  በሰሙነ  ሕማማት  ዕለተ  ዐርብ  ከስግደት  በኋላ  ምእመናን  በየቤታቸው  ጥቂት  ነገር  ለቁመተ  ሥጋ ቀምሰው  እስከ  እሁድ  /የትንሳኤ  በዓል/  ይሰነብታሉ፡፡  ይህ  አክፍሎት  ይባላል፡፡  ከዓርብ  እስከ  ቅዳሜ  ሌሊት  ለእሁድ አጥቢያ  ማክፈል  የብዙዎች  ነው፡፡  አንዳንዶች  ግን  ከሐሙስ  ጀምረው  ያከፍላሉ፡፡  ይህም  እመቤታቸን  ያዕቆብ  እና ዩሐንስ  የጌታን  ትንሳኤ  ሳናይ  እህል  ውኃ  አንቀምስም  ብለው  እስከ  ትንሳኤ  መቆየታቸውን  ተከትሎ  የመጣ  ትውፊት ነው፡፡ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ዕለት የሚካሄደው የሰሙነ ሕማማት የጸሎት ሥርዓት እንደሚከተለው በምስል ቀርቧል: @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
1702Loading...
16
🩸 ሰሙነ ሕማማት 🩸   ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዕለተ ትንሣኤ በፊት  ያለውን ሳምንት "ሰሙነ ሕማማት" በማለት ታከብረዋለች። "ሕማማት" የሚለው ቃል "ሐመ"  ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን የዚህ ስያሜ  መነሻም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው፣ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርበት  ከአዳም እስከ ክርስቶስ የነበረው የዓመተ ፍዳ  የዓመተ ኩነኔ ወቅትም የሚታሰብበት ስለሆነ "ሰሙነ ሕማማት" ተብሏል።   በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምእመናን  በነግህ፣ በሠልስት፣ በቀትር፣ በተሰዓትና በሠርክ  ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ስለ ጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማተ መስቀል  የሚያዘክረውን  ምዕራፍ  ከቅዱሳት  መጻሕፍት በማንበብና  በመጸለይ  ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ፤ ቅዱስ  ያሬድ በመጨረሻው  ሳምንት በየዕለቱ በጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ  ላይ  የተፈጸመውን  ነገረ  መስቀል  በተመለከተ  ያዘጋጀውን  መዝሙር  ይዘምራሉ፤  አብዝተው  ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡   ጌታችንና  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ሕማማትን መቀበሉ ስለምን ነው ቢሉ፡- ☞ፍቅሩን  ለመግለጽ፡-  ለፍጥረቱ  ይልቁንም  ለሰው  ልጆች ያለውን  ፍቅሩን  ይገልጽ  ዘንድ(ዮሐ  ፫÷፲፮)  ምንም  በደል ሳይኖርበት  ነፍሱን  አሳልፎ ሰጠ(ዮሐ  ፲፭÷፲፫) ☞የኃጢአትን ፍዳ ከባድነት ለማሳየት፡- እርሱ  ጻድቅና ንጹህ ሆኖ ሳለ ሰውን ወዶ ይህን ያህል  መከራ ከተቀበለ ሰው ኃጢአት በመሥራት  ቢመላለስ  የኃጢአትን  ውጤት  ከባድነት  ያስተምረናል፡፡  ራሱ  ጌታችንም  ከጲላጦስ  ግቢ እስከ ቀራንዮ አደባባይ መስቀል ተሸክሞ ሲንገላታ  ላለቀሱለት የኢየሩሳሌም  እናቶች  <<በእርጥብ  እንጨት የሚያደርጉ ከሆነ በደረቀውስ እንዴት ይሆን>> በማለት ገልጾለታል፡፡ (ሉቃ  ፳፫÷፳፪) ☞ቤዛ ለመሆን፡- በኦሪት ዘመን ሰዎች  ለሠሩት  ኃጢአት ኃጢአታቸውን  ለማስተሰርይ  ነውር  የሌለበትን  በግ  ቤዛ እንዲሆናቸው መስዋዕት ያቀርቡ ነበር ይህ ግን ከአዳም የተሰወረውን ኃጢአት ማስቀረት ስላልቻሉ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሁኖ መጣ <<እነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ>>(ዮሐ ፪÷፳፮) ☞እርግማናችንን  ለማስቀረት፡-  <<በእንጨት  የሚሰቀል  ሁሉ  የተረገመ  ነው  ተብሎ  ተጽፏልና  ክርስቶስ  ስለ እኛ እርግማን  ሆኖ  ከሕግ  እርግማን  ዋጀን>>(ገላ  ፫÷፲፫)    በማለት  ቅዱስ  ጳውሎስ  እንደጻፈው  እርግማናችንን  ተሸክሞ ሕማማትን  መቀበሉ  የቀድሞው  ኃጢአት  ምንም  ያህል  ከባድ  ቢሆን  በታላቅ  መስዋዕትነት  እንዳስቀረልን ሊያስተምረን ነው፡፡ (ዘዳ  ፳፩÷፳፫) ☞የድኅነታችንን ክቡርነት /ውድነት/ ሊያስረዳን ፡- ድኅነታችንን  የእግዚአብሔር ልጅ ደሙን እስኪያፈስለት ድረስ እጅግ ውድ መሆኑን ሊያስተምረን፡፡ (ራዕ ፭÷፱) @Ethiopian_Orthodox   ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም  ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡  በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት : ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው:: በመስቀል መባረክ፣ ማማተብ፣ መሳቅ፣ መሳሳም፣ ከሴት ጋር መገናኘት(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 593)፣ ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ:: በዚህ ሳምንት ለሞተ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም፣ ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም:: "እግዚአብሔር ይፍታህ" አይባልም(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 600)፤ ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው:: የግዝት በዓላት(12፣21 እና 29) እንኳ ይሰገድባቸዋል:: የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው:: ምግቡም ቆሎ ዳቦ የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው፤ መጠጡም ንጹህ ውኃ ነው:: ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው።(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 578)    ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም። ጸሎቱ ውዳሴማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ መልክአ ሕማማትና መዝሙረ ዳዊት ናቸው። የቅዱሳን መልክአ መልክእ አይጸለይም። ስናጠቃልለው የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ፡ 1.  እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል፣ መሳሳም 2.  ሩካቤ ሥጋ ማድረግ 3.  መስቀል ማሳለም እና መሳለም 4.  ክርስትና ማስነሣት 5.  ለሙታን ፍትሐት ማድረግ 6.  ክህነት መስጠት 7.  የላመ የጣመ ምግብ መመገብ 8.  መሳቅ መጫወት መጨፈር 9.  አብዝቶ ጠግቦ መመገብ 10. መስከር ወዘተ ናቸው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሣዕና ይከናወናሉ፡፡ @Ethiopian_Orthodox የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች: ፩.  አለመሳሳም ፡- ከላይ እንዳየነው በሰሙነ  ሕማማት  የኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  እምነት  ተከታዮች መስቀል  እንደማይሳለሙት  ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን  ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ  አልሰመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ  እንስቀለው ፤እንግደለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡  በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ ፪. ሕፅበተ  እግር፡- ጌታ በፍጹም ትህትና  የደቀ  መዛሙርቱን  እግር  ያጠበበት፣  ከሐዋርያት  ጋር  ግብር  የገባበትና የክርስትና  ህይወት  ማሕተም የሆነውን  ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት  ነው። ጸሎተ ሐሙስ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ  ዕለተ  እናንተ  ለወንድማችሁ  እንዲሁ  አድርጎ  ለማለት  የደቀ  መዛሙርቱን  እግር  በማጠቡ  ምክንያት  የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ፫. ጉልባን እና ቄጠማ ፡- ጉልባን ከባቄላ ክክ፣  ከስንዴ  ወይንም  ከተፈተገ  ገብስ  ጋር  አንድ  ላይ  ተቀቅሎ  የሚዘጋጀና የጸሎት  ሐመስ  እለት  የሚበላ  ንፍሮ  ነው፡፡  የጉልባን  ትውፊት  እስራኤላውያን  ከግብጽ  ተሰደው  በሚነጡበት  ጊዜ በችኮላ  ስለነበር  አቡክተው  ጋግረው  መብላት  ያለመቻላቸውን  ሁኔታ  ያመለክታል፡፡  ያን  ጊዜ  ያልቦካው  ሊጥ  እያጋገሩ ቂጣ  መብላት  ንፎሮም  ቀቅለው  ስንቅ  መያዝ  ተግባራቸው  ነበር፡፡  ይህን  ለማሰብ  በሰሙነ  ሕማማት  ቂጣና  ጉልባን በማዘጋጀት በዓል ይታሰባል፡፡ [በጸሎተ ሐሙስ ዕለት በስፋት የምናየው ይሆናል።] ቄጠማ (ቀጤማ)፡-  በቀዳም  ስዑር  ቀሳውስቱን  ዲያቆናቱ  ቃጭል  /ቃለ  አዋዲ/  እየመቱ  "ገብረ  ሰላመ  በመስቀሉ ትንሳኤሁ  አግሃደ" የሚለውን  ያሬዳዊ  ዜማ  በመዘመር  ጌታ  በመስቀሉ  ሰላምን  እንደሰጠ  እና  ትንሳኤውንም እንደገለጠልን  በማብሰር  ቄጤማውን  ለምእመናን  ይሰጣሉ፡፡  ምእመኑም  ለቤተ  ክርስቲን  አገልግሎት  የሚውል  ገጸ በረከት  ያቀርባሉ  ቀጤማውንም  በራሳቸው  ያስራሉ፡፡  ይህም  አይሁድ  ጌታችንን  እያሰቃዩ  ሊሰቅሉት  ባሉ  ጊዜ  የእሾህ አክሊል  ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ  እለት  ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለምዕመናን ትልቅ ብስራት ነው።
1483Loading...
[ግንቦት 11 የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል] ✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. በአክሱም ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡ ❤ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡ ♥ “ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ” ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡ ♥ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፡- “ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” (ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው) ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት፣ በማለት "አርያም" በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡ ♥ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡ ♥ ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም፦ ፩ኛ) ድጓ ፪ኛ) ጾመ ድጓ ፫ኛ) ምዕራፍ ፬ኛ) ዝማሬ ፭ኛ)መዋሥዕት ናቸው፡፡ ♥ እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ፣ በዕዝል፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ “ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ” ይላል፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡ ♥ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን “የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡ ♥ “ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን” ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ። ❤ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ” (በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር) ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡ ♥ በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡ ♥ ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት፦ “ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር... ” (ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል” ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት ጌታ በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡ ♥ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ፦ “ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ” (የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል) በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡ ♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ፡- “ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤ ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ”፡፡ (የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡ የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን፤ እናንተም ይኽነን ሊቅ አወድሱት። ✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
Hammasini ko'rsatish...
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

Hammasini ko'rsatish...

👍 2
"ዮም ፍሰሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም" ዘማሪ ፍቃዱ አማረ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Hammasini ko'rsatish...
“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ቅዱስ ያሬድ)
Hammasini ko'rsatish...
1
Hammasini ko'rsatish...

ሉቃ 24:5 " ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ "ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም ። እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል!
Hammasini ko'rsatish...
🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት አደረሳችሁ
Hammasini ko'rsatish...
Repost from ያሬዳውያን