LEARN TECH ||ethiopia ®
Kanalga Telegram’da o‘tish
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
Ko'proq ko'rsatish1 495
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-107 kun
-5530 kun
Postlar arxiv
ወይ ጥጋብ!
ተርባለች ብለው ሲያዝኑልሽ አይቼ
በአገልግሌ ሙሉ
አልጫና ቀዩን አንድ ላይ ፈትፍቼ
በቅመም በእንቁላል በደንብ አጣፍጬ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
እህል እስክትቀምሽ
አፌን አልሽር ብየ እኔም ተራብኩልሽ!
ታርዛለች ብለው ሲከፉ አየሁና
በሻንጣየ ሙሉ
አልባሳት ሞላሁት ቢሸፍን ገመና
ይሄን ኮተት ሁሉ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
ልብስ እስክደርቢ
ብርድ አልፈራ ብየ እኔም ታረዝኩልሽ!
ተጠምታለች ብለው ሲያሙልኝ ሰምቼ
በዕቃየ በሙሉ
በባልዲ በሀይላንድ በስኒ ሞልቼ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
አንጀትሽ እስኪርስ
ውሀ አልቀምስም ብየ እኔም ጥም ሞትኩልሽ!
አሁን በተራየ
በአካላቴ ሁሉ
በአይን በጆሮየ በነፍሴ እንደያዝኩት
ልቤን ረጋ በል እስክንደርስ እያልኩት
መልክተኛ አስትተሽ ራሴን አስላክሽኝ
መልስሽ ግን ይገርማል
ፍቅር እንኪ ብልሽ 'ጠግቤአለሁ' አልሽኝ
ወይ ጥጋብ!
የተራበ እህል
የተጠማ ውሀ
የበረደው ልብሱን እየደራረበ
ማባበል ተስኖት
ማስታገሻ ላጣው ይብላኝ ለጠገበ!😏
በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ታክሲ አድራሽ እንደሆነው በሕይወት ውስጥ የተሰገሰጉት ሰዎች ሁሉ አንድ የሚያደርሱህ ቦታ አላቸው እያንዳንዳቸው።
@abyssinianwisdom
ቀጣይ አመት "ምን አለ ያኔ ጀምሬ በነበር ኑሮ" ትላለህ።
ግዜ ይነጉዳል፤ መሄድን አያቆምም። ዛሬ አልፎ ትላንት ይሆናል፤ ነገም ደርሶ ዛሬ ይሆናል።
ጊዜ ሲያልፍ ከእነዚህ ሁለቱ አንዱን ትቶ ያልፋል:-
#1 ቁጭት
#2 ውጤት
ዛሬ ላይ ጠንክረህ ከሰራህ፣ በአግባቡ ከተጠከምክበት፤ ነገህ ያማረ እና የተመቸ ይሆናል። ዞረህ ስታየውም የውጤት አንጂ የጸጸት አይሆንም።
አሁን ስራ፤ ነገ ሲደርስ ምን አለ ትላንት በሰራሁ ከማለት ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። ነገም ሲደርስ ነገ እሰራለሁ እያልክ እድሜህን ትጨርሰዋለህና።
ዛሬ ስራ፣ ዛሬ ልፋ፣ አሁን ጀምር…
ቀጣይ አመት ህልምህ እውን ሆኖ ታገኘዋለህ።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አንዳንዴ ግን...አንዳንድ ሰዎች...ምን አይነት ሰዎች ናቸው...
የሆነ ቀን ላይ መሳቅ የማልችለው በእነሱ ነው።የሆነ ቀን ላይ ደስተኛ የማልሆነው በእነሱ ነው።የሆነ ቀን ላይም የምከፋው በእነሱ ነው።
ግን አንዳንዴ አንዳንድ ቀኖች ልዩ ቀኖች ናቸው።በእነዚው ሰዎች፦ መሳቅ የምችልባቸውና ደስተኛ የምሆንባቸው የተለዩ ቀኖች!
አንዳንድ ቀኖች......
@abyssinianwisdom
ፈረስ ያን ጉልበት ይዞ ከሱ የሚያንስ ለግልቢያ ይገራዋል፤ ምን አልባት ተፈጥሮ ለዛ ግልጋሎት ፈጥራው ወይስ የጋላቢው ጥበብ ይሆን ይህን ሁነት የፈጠረው?! ሰውንስ የሚጠምድ ሰውስ ጥበበኛ ሆኖ አልያ ተጠማጁ ለዝቦ በተመሳሳይ አቅም ውስጥ ከፍ እና ዝቅ የሚፈጠረው?!
አቡ
@abyssinianwisdom
የታላላቅ ሰዎች ታላላቅ አባባሎች፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
1. ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሳህበት ተመልሰህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ ካሰብክበት ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ፡፡
2. በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም የሚጠፋባቸው በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን ወንዶች ደግሞ በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡
3. መጀመሪያ ለራስህ ራስህ መሆን ስትጀምር ለማን ምን መሆን እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡
4. የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታው ሲጨምር የጓደኞቹን ብዛት ይቀንሳል፡፡
5. ዝቅተኛ እውቀት ባለህ ቁጥር የምትተኛው እንቅልፍ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
6. ጓደኛን አለማመን ከመካድ የከፋ ነው፡፡
7. የራስህን ትኩስ እንጀራ ለመጋገር ስትል የሌላውን ቂጣ አትርገጥ፡፡
8. አንዳንድ ሰዎች የሚወድቁት ሌሎችን በሁለት እግሮቻቸው ለመርገጥ ሲጣጣሩ ነው፡፡
9. ሰው ከጊዜ እና ከማጣት ብዙ ይማራል፡፡
10. አንዳንዴ ሽንፈትም ከድል የበለጠ ዋጋ አለው/ ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ ብዙ እውቀት አለ፡፡
11. ሠው የበለጠ እያገኘ በሄደ ቁጥር የበለጠ ስግብግብ እየሆነ ይሄዳል፡፡
12. ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡
13. የሰው ልጅ ከደስታው ይልቅ የሀዘኑን ጊዜያት መቁጠር ይወዳል፡፡
14. ባንኮች ዝናብ ሳይኖር ዣንጥላ ያበድሩህና መዝነብ ሲጀምር ግን ዣንጥላውን ይነጥቁሃል፡፡
15. አዋቂ ሆኖ ለመታየት የምናደርገው ጥረትና ከንቱ ድካም አላዋቂ አድርጎ ያስቀረናል።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
የስኬት መጀመሪያው የምትወደውን ነገር ማወቅ ነው። በመቀጠል የምትወደውን መስራት ነው። የምትወደውን ስራ እስካልሰራህ ድረስ ስኬታማ ነኝ ማለት አትችልም። ዓለም ቢያደንቅህ እንኳን በውስጥህ እርካታ አይኖርም። ስራህን የምትወደው ከሆነ በጥልቅ ጉጉት ታከናዉነዋለህ።
📓አእምሮዎን የመጠቀም ጥበብ
✍ አቤል ፀጋዬ
📚 @abyssinianwisdom
በህይወት እያለ አንዴ እንኳን ያልረዱት
በችግሩ ግዜ ከጎኑ የራቁት
መራቡን እያዩ የተሳለቁበት
ዛሬ እሱን ቢወስደው የማይቀርለት ሞት
ሁሉ ተሰብስበው መጡ ሊያለቅሱለት
ከመቃብሩ ላይ ሐውልት ሊሰሩለት
ጥሩ ሰው ነበረ ብለው ሊያወሩለት
ተዝካር ሙት አመቱን ሊያሰናዱለት
ግን ምንድን ሊጠቅመው
እንዲያው ምን ሊረባው
እስትንፋስ አይሰጠው ከሞት አይመልሰው
ሰው ሞቶ ከማልቀስ ደረትን ከመምታት
በሕይወት ሳለ ነው ሰው ሰውን መርዳት።
@henila31
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ታላቁ አሌክሳንደር
ታላቁ አሌክሳንደር በህይወት ዘመኑ ብዙ መንግስታትንና ሀገሮችን በቁጥጥሩ ስር ያደረገ ጀግና ንጉስ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ብዙ ሀገራትን ድል አድርጎ ወደሃገሩ እየተመለሰ ሳለ በጣም አመመዉ፡፡
ጄኔራሎቹና የኔ የሚላቸዉ ቁልፍ ሰዎችም እንዲያርፍና ህክምና እንዲከታተል ማድረግ ጀመሩ፡፡ ነገር ግን የሱ ህመም ከቀን ወደቀን እየባሰና ወደሞት አፋፍ እየቀረበ መጣ፡፡
አንድ ቀን ግን ህመሙ እጅግ ከብዶ በመምጣቱ አሌክሳንደር እንደማይድን አዉቆታል፡፡ ጄነራሎቹን ሁሉ አስጠርቶ ኑዛዜ መናዘዝ ጀመረ... “ስሙኝ...ከደቂቃ በኋላ ወደማልመለስበት እሄዳለሁ ነገር ግን ስሞት ሶስት ነገሮች እንድታደርጉልኝ እፈልጋለሁ አላቸዉ፡፡
• የመጀመሪያዉ የመቃብር ሳጥኔ እኔን ሲያክሙኝ የነበሩ ዶክተሮች ብቻ ተሸክመዉ ወስደዉ እንዲቀብሩኝ
• ሁለተኛዉ ወደ መቀበሪያዬ ቦታ የሚወስደዉ መንገድ በወርቅና በከበረ ድንጋይ እንዲሰራ
• ሶስተኛዉ ደግሞ ሁለቱም እጆቼ ከመቃብር ሳጥኑ ዉጪ እንዲታዩ አዝዣለሁ
ብሎ የመጨረሻዎቹን ትንፋሾች መሳብ ጀመረ፡፡ የንግግሩን ግራ አጋቢነት የከበቡት ዶክተሮችና አገልጋዬች ባይረዱትም ንጉስ ነዉና ሁሉም ዝም ብለዉ እሺታቸዉን ገለፁ፡፡
ነገር ግን በዚህ ግራ የገባዉ የቅርቡ ጀነራል ንጉሱን እንደምንም ብሎ ጠየቀዉ“ንጉስ ሆይ ሶስቱ ኑዛዜህ አልገባኝምና እባክህ ቢቻልህ ምን ማለት እንደሆነ ብትነግረኝ?” ንጉሱም እንዲህ አለዉ “ሁሉም ሰዉ እንዲያዉቅልኝ የምፈልገዉ ሶስት ወሳኝ ነገር አለ፡፡
ልክ እንደመጀመሪያዉ ኑዛዜ ሰዉ የፈለገዉን ያህል ህክምናና እንክብካቤ ቢደረግለት ከሞት አያመልጥም፡፡ ሁሉም ዶክተሮች ሞትን አሸንፈዉ ህመምተኛዉን ሰዉ ሊያስጥሉት ፈፅሞ አይችሉም!
እንዲያዉ ለጊዜዉ ይሞክራሉ እንጂ ዞሮ ዞሮ ሁሉም ወደሞት ነዉ! ሁለተኛዉ ደግሞ በህይወት ዘመኔ ስዳክርለትና ስደክምለት የኖርኩት ሃብት አሁን ይዤዉ መሄድ አልችልም፡፡
ገንዘብንና ሀብትን እያሳደዱ መኖር ከንቱና ባዶ የማይጠቅም መሆኑን ተረዳሁ፡፡
ሶስተኛዉ ደግሞ ወደዚህ አለም ስመጣ በባዶዬ መጥቻለዉ፣ ስሄድም እንዲሁ በባዶዬ! ምንም ሳልይዝ እጄ ባዶ እንደሆነ ነዉ፡፡
የእናንተም እጣ እንዲሁ ነዉ በባዶህ እንደመጣህ ድምቡሎ ሳትይዝ በባዶህ ትመለሳለህ” አለዉ፡፡
ከወደዱት ይድረስ ለሚወዱት
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ስቲቨን ጆብስ እና ስቲቨን ዎዝኒያክ ምንም የቢዝነስ እውቀት የሌላቸው፤ትምህርትም ያልወሰዱ፤ሀብት በደረሰበት ደርሰው የማያውቁ ሰዎች ቢሆኑም የApple Computer Company ለማቋቋምና የኮምፒውተር ቢዝነስ ለመስራት ተስፋ ሰነቁ።
ወቅቱ በ1976 ሲሆን ያኔ በጣም ብዙ ሰው ኮምፒውተርን ያውም ለቤቱ ለመግዛት ፈፅሞ የሚያስብበት ጊዜ አነበርም።ጆብስና ዎዝኒያክ ግን አንድ የጭነት መኪና እና ሁለት የሂሳብ መስሪያ ማሽኖችን ሸጠው የቋጠሯትን 1,300 ዶላር ለApple Computer Company መክፈቻ አዋሏት(ድርጅቱ የተከፈተው ደግሞ በጆብስ የቤት የመኪና ማቆሚያ ውስጥ ነበረ) እውነት ለመናገር በስኬታቸው ላይ የተጋረጡባቸው ነገሮች እጅግ የበዙ ነበሩ።
ይሁን እንጂ እነዚህ ልጅ-እግር የስራ ፈጣሪዎች ራዕይ ነበራቸው፤ሊያሳኩና እውን ሊያደርጉ የሚፈልጉትን ነገርም በትክክልና ጠንቅቀው አውቀውታል።"ማን ነው ኮምፒውተርን ለተወሰኑ ድርጅቶችና ሎቢስቶች ብቻ ያደረገው? በማለት በድፍረት ጠየቁ።"ኮምፒውተር አዕምሮ መሳፈሪያ ብስክሌት እንዲሆን እናደርገዋለን።በቀላልና በትንሽ ዋጋ የሚገኙ ኮምፒውተሮች በየሰው ቤት ላይ እንዲገኙ ማድረግ አላማችን ነው"!" አሉ።
የApple Computer Company መስራቾች አላማቸውን ገና ከመጀመሪያው ጀመሮ በሚገባ አራምደዋል፤በቻሉት አጋጣሚ ሁሉ አሳውቀውታል። ራዕያቸውን የሚረዱ ሰዎችን ቀጠሩና ከትርፉ አጋሯቸው። ራዕያቸውን ኖሩበት፣ አወሩት፣ ተገበሩትም። ሕይወታቸውም አደረጉት።ቢዝነስ ነውና አባጣ ጎርባጣው ሲመጣባቸው አከፋፋዮች "አይ አንፈልግም አታምጡብን" ሲሉ አምራቾች ደግሞ "አረ በቃ ይብቃችሁ !" ሲሏቸው ለመሸነፍና ለማቆም ፈፅሞ አልፈለጉም።
ድንቅ ጥረታቸው ያለ ፍሬ አልቀረም! አለም ቀስ በቀስ እነሱ የፈለጉበት አይነት ንቃተ ህሊና ላይ ደረሰላቸው።ገና በጀመሩ በስድስት አመታት ውስጥ በአመት 650,000 የግል ኮምፒውተሮችን ሸጡ።ዎዝኒያክና ጆብስ በርግጥም ከነበሩበት ዘመን ቀድመው ማሰብ የቻሉ ታታሪ መሪዎች ነበሩ።
የሆነው ሆኖ ግን አመራር ስኬታማ እንዲሆን የሚያስፈልገው ነገር የግለሰቡ በትክክል ራሱንና ማንነቱን በቅድሚያ ማወቅ፤አለማውን በተብራራ መንገድ መግለፅ እና ከዚያ አስቦበት በተግባር ማዋል ነው።
📚 @abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ትንሿን ጠብቅ !
በህይወት ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥሩት ትናንሽ ነገሮች ናቸው፤ ዝሆን ገጭቶት የሞተ ሰው ታውቃላችሁ? በትንሿ የወባ ትንኝ ግን ተነክሶ የሞተስ ። ታዲያ እንደ ቀላል የምታየው ቸልተኛ ፀባይህ ምን እንደሚያሳጣህ የምታውቀው ዘግይተህ ነው።
በቀን ውስጥ አደርጋለው ያልከውን ሳታደርግ ቀጣዩን ቀን አትጀምር! አለዛ ከነገ ላይ እየሰረክ ነው፤ ስንፍናን ማሸነፍ ቀንህን ከማሳመር ነው የሚጀምረው።
የተባረከ ቀን ተመኘን🙏
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
🐕 ቅብጥብጡ_ውሻ 🐕
የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡
በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡
የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡
የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡
ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡
ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . .
ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት ፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡
ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ!
ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
✍️ ከማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘሁት
💚💛❤️ 📖 💚💛❤️
ጥንታዊ ግሪካውያን ጸሐፍቶችና ፈላስፎች ስለኢትዮጵያውያን ምን ይላሉ? (Part 1)
1. "የኢትዮጵያ ወንዶች፤ ከወንዶች ኹሉ በጣም ቆንጆዎች ናቸው።" - ሄሮዶተስ
2. "ኢትዮጵያውያን ወንዶች፤ ከዓለም ወንዶች ኹሉ ረጃጅም እና ቆንጆዎች ናቸው ይባላል።" - ዲዮዶረስ ሲኩለስ
3. "ኢትዮጵያውያን አማልክትን በማምለክና መስዋዕት በማቅረብ የመጀመሪያዎቹ ናቸው።" - ሆሜር (ነበርን ?? )🫵
4. "ኢትዮጵያውያን ኹል ጊዜ መልከ መልካሞችና ውብ ፀጉር ያላቸው ናቸው።" - አርስቶትል
5. "ኢትዮጵያውያን የጥንት የዘር ግንድ አላቸው፣ ጥበባቸውም ከሌላው ሕዝብ የላቀ ነው።" - ማኔቶ ☑️
6. "ኢትዮጵያውያን በጣም አስተዋይ ሕዝቦች ናቸው፤ ስለ አስትሮኖሚ እና ፍልስፍና ያላቸው ግንዛቤ የላቀ ነው።" - ስትራቦ
7. "ኢትዮጵያውያን ከሀገሮች ሁሉ የበለጠ ሃይማኖተኛ ናቸው፤ ለአምላካቸው ታላቅ ክብር አላቸው." - ፕሉታርች
8. "ኢትዮጵያውያን በኪነጥበብ እና በሳይንስ ኹሉ የላቀ ችሎታ ያላቸው ከፍተኛ ባህል እና እውቀት ያላቸው ሕዝቦች ናቸው." - ፕሊኒ ሽማግሌ
9. "ኢትዮጵያውያን ልዩ የሆነ የፍትሕ ስሜት ያላቸው እና በፍትሃዊነት እና በገለልተኝነት ይታወቃሉ." - ሉቺያን
10. "ኢትዮጵያውያን በጣም ጤነኛ ህዝቦች ናቸው ረጅም ዕድሜም ይኖራሉ።" - ሂፖክራተስ
11. "ኢትዮጵያውያን በግብርና የተካኑና ብዙ ሰብሎች አሏቸው።" - ዜኖፎን
12. "ኢትዮጵያውያን በጣም ሙዚቃ የሚወዱ ህዝቦች ናቸው፤ ታላቅ የዳንስ ፍቅር አላቸው." - ፒንዳር ( የጭፈራችን ነገርማ ፓ አወ አይነገርም 🤭)
13. "ኢትዮጵያውያን የተከበሩ ህዝቦች ናቸው፤ ታላቅ ክብርም አላቸው." - አሴሉስ
14. "ኢትዮጵያውያን በጦርነት ላይ ደፋር ናቸው፤ በድፍረታቸውም ስመ-ጥር ናቸው።" - ዩሪፒድስ
15. "ኢትዮጵያውያን ለትውፊት ትልቅ ክብር ስላላቸው በትውፊታቸውም ኩራት ይሰማቸዋል።" - ቱሲዳይድስ
16. "ኢትዮጵያውያን ለሕግ ትልቅ ክብር ያላቸው ጥበበኛ፤ ፍትሃዊ ህዝቦች ናቸው." - ፕሉታርች
17. "ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ባህል ያላቸው፤ የግጥም እና የስነ-ጽሁፍ ፍቅር ያላቸው ህዝቦች ናቸው." - ሶፎክለስ
18. "ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ማኅበረሰባዊ ሕዝቦች ናቸው፤ በእንግዳ ተቀባይነት ይታወቃሉ።" - ሄሮዶተስ
19. "ኢትዮጵያውያን ጥልቅ መንፈሳዊ ሰዎች ናቸው፤ ታላቅ የመለኮት ፍቅር አላቸው." - ሲሴሮ
20. "ኢትዮጵያውያን በታላቅ ኢንደስትሪ ውስጥ ያሉ ህዝቦች ናቸው፤ በብዙ የእጅ ስራዎች የተካኑ ናቸው።" - ሆሜር
21. "ኢትዮጵያውያን በጣዕም እና በቅንጦት የታወቁ ህዝቦች ናቸው." - ፕሉታርች
22. "ኢትዮጵያውያን ታላቅ የነጻነት ፍቅር ስላላቸው ራሳቸውን የቻሉ ናቸው።" - አርስቶትል
23. "ኢትዮጵያውያን በጣም ሃይማኖተኛ ሰዎች ናቸው፤ ለቅዱሳን ታላቅ ፍቅር አላቸው." - ፕላቶ ❤️
24. "ኢትዮጵያውያን በጣም የሰለጠኑ ህዝብ ናቸው፤ ታላቅ የመማር ፍቅር አላቸው." - ሉቺያን
25. "ኢትዮጵያውያን ታላቅ ድፍረት ያላቸው፤ በጀግንነታቸው የሚታወቁ ህዝቦች ናቸው." - ፕሉታርች
26. "ኢትዮጵያውያን ታላቅ ክብር ያላቸውና በሚያውቁት ኹሉ የተከበሩ ህዝቦች ናቸው." - ሆሜር
27. "ኢትዮጵያውያን ጥልቅ መንፈሳዊ ሰዎች ናቸውና ታላቅ የመለኮት ፍቅር አላቸው." - ፒንዳር
28. "ኢትዮጵያውያን ታላቅ ክብር ያላቸውና በጸጋቸው እና በመልካምነታቸው የሚታወቁ ህዝቦች ናቸው." - ሶፎክለስ
29. "ኢትዮጵያውያን ታላቅ ውበት ያላቸው እና በሚያዩአቸው ሁሉ የሚደነቁ ህዝቦች ናቸው." - ዩሪፒድስ
30. " 'ኢትዮጵያውያን ከሁሉም ሰዎች ሁሉ የመጀመሪያዎቹ ነበሩ' ለዚህ አባባል ማስረጃዎች ግልጽ ነው..... ከአማልክት ተዋልደዋል፣ ፍልስፍናና ጥበብን ፈልስፈዋል።" - ዲዮዶረስ ሲኩለስ ( የገባው አለ?🤔 ..)
31. "የኢትዮጵያ ባህሎችና የኢትዮጵያ ንጉሥ በብዙ አጎራባች ህዝቦች ላይ አገዛዙ በሁሉም ዘንድ እጅግ የተመሰገነ ነው።" - ሄሮዶተስ
32. "እነዚህ ኢትዮጵያውያን በጣም ቆንጆ እና ከሰው ሁሉ ረጃጅም ነበሩ።" - ሄሮዶተስ
33. "ከሁሉም የተዋበች እና የሰለጠነች ሀገር ኢትዮጵያ ናት" - ኢሶቅራጥስ
34. "ፍትሃዊነታቸው ፈጽሞ የማይበላሽባቸው ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው " - ሆሜር
35. "ኢትዮጵያውያን ሴቶች በዓለም ላይ በጣም ቆንጆ ናቸው ተብሏል።" - ስትራቦ
36. "ኢትዮጵያውያን የላቀ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው." - ፕሊኒ
37. "ኢትዮጵያውያን በቁመትና በውበት ይበልጡናል።" - ፊሎስትራተስ
38. "አማልክትን ያከበሩ እና ሳይንሶችን ያገኙት የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው" - የአሌክሳንደሪያው ክሌመንት
ይቀጥላል ......
🔹እኛ የዛሬዎቹስስ?
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አንቺን እንዲሰጠኝ
አንቺን እንዲሰጠኝ ፈጣሪን ለመንኩኝ
አንቺን እንዲሰጠኝ
በፀሎት በረታሁ ሱባኤም ገባሁኝ
አንቺን እንዲሰጠኝ
ግሸን ሄጄ ጠየኩ ዝቋላም አለቀስኩ
ዋልድባ አልቀረኝ ኢቲሣም ረገጥኩ
አንቺን እንዲሰጠኝ
ፆም መፆም ጀመርኩኝ
ቅዳሴም ለመድኩኝ
አንቺን እንዲሰጠኝ ጌታዬን ለመንኩት
ግን በዚህ ሂደት ውስጥ....
አንቺን ረስቼ ፈጣሪን ወደድኩት🥰
@henila31
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
Repost from LEARN TECH ||ethiopia ®
ወድ የቻናላችን ቤተሰቦች አድስ የተከፈተውን ጉሩፓችን ይቀላቀሉ
https://t.me/abyssinian_wisdom
የበየነ በግ
(በእውቀቱ ስዩም)
በየነ አሜሪካን አገር በፊላደልፊያ ጠቅላይ ግዛት የሚኖር ጉዋደኛየ ነው፤ በየነ አሜሪካን እየጠሉ አሜሪካ ውስጥ ከሚኖሩ ዲያስፖራዎች አንዱ ነው፤ “አሜሪካን የሚዘውሯት እፍኝ አማይሞሉ አይሁድ ናቸው “ ብሎ ይከራከራል::
በአገሩ ህግ መሰረት ዜጎች ቤታቸው በግ ገዝተው አያርዱም፤ በግ ካማራቸው በግ ገዝተው ቄራ ወስደው ያሳርዳሉ፤ ከዚያ ስጋውን አስጭነው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ::
በየነ ግን ይሄ ህግ አልተዋጠለትም፤ ባንዱ ፋሲካ ዋዜማ ግድንግድ በግ ገዝቶ የተከራየው አፓርታማ በር ፊትለፊት አሰረው፤ በግየው እሪሪሪሪሪሪሪረ ብሎ መጮህ ጀመረ፤ የህንጻው ነዋሪዎች ከየመስኮታቸው ብቅ እያሉ “ ድምጹን ትንሽ ትቀንስልናለህ በዲ?” እያሉ በየነን ተማጠኑት፤ በየነ ወደ ህንጻው ነዋሪዎች አንጋጦ እያየ” በአሜሪካ ህገ- መንግስት ሰዎች ደስታ የመፈለግ መብት እንዳላቸው ተደንግጓል! ለእኔ በአመት በአል ቀን፥ ከበግ ስጋ በላይ ደስታ እሚሰጠኝ ድምጹ ነው” እያለ አጠር ያለ ማብራርያ ሰጠ::
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ ፖሊስ በሳይረን አካባቢውን ድብልቅልቅ እያደረገ ከች አለ፤ አንዲት መከካለኛ አምቡላንስ እየተበለጨለጨች ተከትለዋለች::
ፖሊሱ ከአፓርታማው ፊትለፊት ቆሞ በማይክራፎን ,“ እጅህን ከፍ አድርገህ ውጣ” ብሎ አዘዘው: :
“ምን በድየ ነው?” አለ በየነ
“አካባቢውን በበግ ድምጽ ረብሸሀል! “
“ አሁን የኔ ጉፋያ በግ ድምጥ አንተ ከምትነዳው መኪና ድምጥ በላይ ረብሾ ነው ? እንዲያው ነገር ፍለጋ ነው እንጂ!” በየነ አልተረታም::
ፖሊሱ ወደ አምቡላንሱ ተመለከተ፤ አምቡላንሱ እዚህ ድረስ መጥቶ ባዶውን መመለስ እንደሌለበት አሰበ::
“ እጅህ ላይ ያለውን መሬት አስቀምጥ “ አለ ፖሊሱ
“ እጄ ላይ ምንም የለም ኦፊሰር” አለ በየነ::
“ትዛዜን እማትቀበል ከሆነ ለሚደርስብህ ነገር ሀላፊነት አልወስድም” ፖሊሱ አምባረቀ::
“ ከእጮኛየ ካደረገችልኝ ቀለበት በቀር እጄ ላይ ምንም የለም “ በየነ ተከራከረ:
:
“ ጭራሽ አንተን በእጮኝነት እምትቀበል ሴት አለች?” አለ ፖሊሱ በሹፈት እየሳቀ::
“ ህ! ድንበር ያለፍህ አልመሰለህም ጌታው ! ምንም ቢሆን አበሻ ነኝ! ደሜ ይፈላል” አለና በየነ እጅጌውን ከፍ ከፍ ማድረግ ጀመረ::
ፖሊሱ በየነን በጠረባ ጥሎ ፥ እጁን ከሰበረው በሁዋላ አምቡላንሱ ውስጥ ጫነው ::
ሶስት ቀን ታስሮ ተለቀቀ::
ቤቱ ሄጄ “ አይዞህ ! “ እያልሁል ላጽናናው ስሞክር የመለሰልኝን አልረሳውም::
“ ጌታን ገርፈው ለመስቀል የደፈሩ ሰዎች እኔን ከንዴን ቀልጠመው፥ ሶስት ቀን አሰሩኝ ብየ አላዝንም”
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
የበየነ በግ
(በእውቀቱ ስዩም)
በየነ አሜሪካን አገር በፊላደልፊያ ጠቅላይ ግዛት የሚኖር ጉዋደኛየ ነው፤ በየነ አሜሪካን እየጠሉ አሜሪካ ውስጥ ከሚኖሩ ዲያስፖራዎች አንዱ ነው፤ “አሜሪካን የሚዘውሯት እፍኝ አማይሞሉ አይሁድ ናቸው “ ብሎ ይከራከራል::
በአገሩ ህግ መሰረት ዜጎች ቤታቸው በግ ገዝተው አያርዱም፤ በግ ካማራቸው በግ ገዝተው ቄራ ወስደው ያሳርዳሉ፤ ከዚያ ስጋውን አስጭነው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ::
በየነ ግን ይሄ ህግ አልተዋጠለትም፤ ባንዱ ፋሲካ ዋዜማ ግድንግድ በግ ገዝቶ የተከራየው አፓርታማ በር ፊትለፊት አሰረው፤ በግየው እሪሪሪሪሪሪሪረ ብሎ መጮህ ጀመረ፤ የህንጻው ነዋሪዎች ከየመስኮታቸው ብቅ እያሉ “ ድምጹን ትንሽ ትቀንስልናለህ በዲ?” እያሉ በየነን ተማጠኑት፤ በየነ ወደ ህንጻው ነዋሪዎች አንጋጦ እያየ” በአሜሪካ ህገ- መንግስት ሰዎች ደስታ የመፈለግ መብት እንዳላቸው ተደንግጓል! ለእኔ በአመት በአል ቀን፥ ከበግ ስጋ በላይ ደስታ እሚሰጠኝ ድምጹ ነው” እያለ አጠር ያለ ማብራርያ ሰጠ::
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ ፖሊስ በሳይረን አካባቢውን ድብልቅልቅ እያደረገ ከች አለ፤ አንዲት መከካለኛ አምቡላንስ እየተበለጨለጨች ተከትለዋለች::
ፖሊሱ ከአፓርታማው ፊትለፊት ቆሞ በማይክራፎን ,“ እጅህን ከፍ አድርገህ ውጣ” ብሎ አዘዘው: :
“ምን በድየ ነው?” አለ በየነ
“አካባቢውን በበግ ድምጽ ረብሸሀል! “
“ አሁን የኔ ጉፋያ በግ ድምጥ አንተ ከምትነዳው መኪና ድምጥ በላይ ረብሾ ነው ? እንዲያው ነገር ፍለጋ ነው እንጂ!” በየነ አልተረታም::
ፖሊሱ ወደ አምቡላንሱ ተመለከተ፤ አምቡላንሱ እዚህ ድረስ መጥቶ ባዶውን መመለስ እንደሌለበት አሰበ::
“ እጅህ ላይ ያለውን መሬት አስቀምጥ “ አለ ፖሊሱ
“ እጄ ላይ ምንም የለም ኦፊሰር” አለ በየነ::
“ትዛዜን እማትቀበል ከሆነ ለሚደርስብህ ነገር ሀላፊነት አልወስድም” ፖሊሱ አምባረቀ::
“ ከእጮኛየ ካደረገችልኝ ቀለበት በቀር እጄ ላይ ምንም የለም “ በየነ ተከራከረ:
:
“ ጭራሽ አንተን በእጮኝነት እምትቀበል ሴት አለች?” አለ ፖሊሱ በሹፈት እየሳቀ::
“ ህ! ድንበር ያለፍህ አልመሰለህም ጌታው ! ምንም ቢሆን አበሻ ነኝ! ደሜ ይፈላል” አለና በየነ እጅጌውን ከፍ ከፍ ማድረግ ጀመረ::
ፖሊሱ በየነን በጠረባ ጥሎ ፥ እጁን ከሰበረው በሁዋላ አምቡላንሱ ውስጥ ጫነው ::
ሶስት ቀን ታስሮ ተለቀቀ::
ቤቱ ሄጄ “ አይዞህ ! “ እያልሁል ላጽናናው ስሞክር የመለሰልኝን አልረሳውም::
“ ጌታን ገርፈው ለመስቀል የደፈሩ ሰዎች እኔን ከንዴን ቀልጠመው፥ ሶስት ቀን አሰሩኝ ብየ አላዝንም”
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
