cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ @bewketuseyoum19 Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19 For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot Thank you!

Ko'proq ko'rsatish
Efiopiya77Амхара70Sport295
Advertising posts
128 678Obunachilar
-14924 soatlar
-9547 kunlar
-4 80630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Обуначиларнинг ўсиш даражаси

Ma'lumot yuklanmoqda...

ቀጣዩ ‘ስቴፕ” (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ቀነኒሳ አይነት ልእለ-ሰብ ሰዎችን ስታይ የእድሜ መገስገስ አያስፈራህም፤ እድሜ ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ብለህ ትፎክራለህ ፤ “ ቀነኒሳ አንበሳ “ ይላል ጀግና አሞጋሹ ጀግና ቴዲ አፍሮ፤ አንበሳ በምን እድሉ ነው ቀነኒሳን የሚስተካከለው ? አንድን አንበሳ በሀያ አመቱ በአጸደ ስጋ አታገኘውም፤ ካገኘኸው ጭርጭስ ብሎ፥ ጎብጦ ቁርበቱን እየላሰ ተኝቷል፤ ቀነኒሳ ግን በአርባ ሁለት አመቱ ማራቶን ያሸንፋል፤ ዋናው ጥያቄ- ለእድሜ ትገብራለህ ወይስ እድሜን ታስገብራለህ?” የሚል ነው፤ ርግጥ ነው እኔ በዚህ እድሜየ እንኳን ማራቶን ልሮጥ ውድድሩን በቲቪ ጨርሶ ለማየት ራሱ አቅምና ትግስት የለኝም፤ አንዳንድ ቀን፥ ከባለንጀሮቼ ጋር ኳስ ለማየት እቀመጣለሁ፤ በተቀመጥኩበት ሶፋ ላይ አራት ዙር ግልገል እንቅልፍ (ናፕ ) እተኛለሁ፤ በቀደም ከስንት ጊዜ በሁዋላ ጂም ሄድኩ፤ አሰልጣኙ ተቀብሎ ገና የስነልቦና ምክር እንኳ ሳይሰጠኝ “ ሀያ ጊዜ ቁጭ ብድግ ስራ “ አለኝ ፤” ቁጭ ማለቱ ላይ ችግር የለብኝም ብሮ ! ብድግ ማለቱ ላይ ግን እገዛህን እሻለሁ “ ብየው ፥ ትንሽ ወልመጥ ወልመጥ አልሁ ፤ ቀጠለና አስር ፑሽ አፕ አዘዘልኝ፤ አምስቱን ወገቡን እንደተመታ እባብ እየተቅመደምድሁ ሰራሁ፤ በተረፈች፥ ጉልበቴ ምንጣፉን እየሳምኩ ተነሳሁ፤ በመጨረሻ ሳልፈልግ ፥በርከክ ብየ ለወጫጫ ተራራ ሰገድሁ፤ ማጠቃለያው ላይ፥ አምስት ኪሎ ድምቤል አሸከመኝ፤ ከዚያ መስታውት ፊት ቆሜ ፥ ከክርኔ በላይ ያለውን ክንዴን ክፍል እየዳበስኩ ገመገምኩት፤ ብዙም ሳይቆይ አሰልጣኙ ከተፍ አለና፥ “አሁን አሟሙቀሀል፤ ቀጣዩ ስቴፕ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ” ሲል ጠየቀኝ፥ “ ቀጣዩ “ ስቴፕ”ማ ንቅሳት እሚሰሩ ሰዎችን ማፈላለግ ነው ዠለስ“ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
👍 14
ቤት ማንም ሳይኖር ብቻዬን ሳለሁኝ ስራ ጨራርሼ ፋታ እንዳገኘሁኝ ትንሽ መለስ ብዬ ትናንቴን ለማየት ያለፈው ዘመኔን ጥቂት ለመጎብኘት የትዝታን መዝገብ ጀመርኩኝ መቃኘት። እልፍ ደስታ ንፁህ ፍቅር  ሀሜት የለ እዛው ንግር የጨዋታው ለዛ ጥርስ የማያስከድን ልጅነት ይመስገን ያ መልካም ዘመን። ደሞ እሱ አልፎ ታድጎ ተጎርምሶ በንፁ ልቤ ላይ አለማወቅ ነግሶ መልካም ስሜ ሆኖ ከግብሬ ወርጄ ይሉኝታን ገድዬ ንቀትን ወልጄ ታዘብኩት እራሴን ወደኋላ ሂጄ። By ሳምሪ የዝኑ ልጅ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
🥰 13👍 11
#ቀይ_ወይስ_ጎመኔ ታስታውሺ እንደሆን ከወር ምናምኔ እስከሆነ ለታ ካሁን ብዙ ሳይርቅ የአይኔ እንባ መቋጠር የመተከዝ ጠኔ ከኔ ብዙ ሲልቅ ከጎኔ ቁጭ ብለሽ ባደረግሺው ሹራብ የአይኔን ስታብሽ ከጎኔ ቁጭ ብለሽ ከጎንህ ነኝ እያልሽ ልቤ ሲሆን ልብሽ እኔን ትዝ ይለኛል! ታስታውሺ እንደሆን "ምን ሆንክብኝ" ብለሽ መዳፌን ካንቺ መዳፍ ስታገጣጥሚው "ያልፋል እኮ" እያልሽ የያዝሺውን መዳፍ ደጋግመሽ ስትስሚው የተከዳን ልቤን ልታክሚ መተሽ በሽታ ሆንሽብኝ ፍቅር ሚሉት ነገር ከልቤ ላይ ተክለሽ። አላውቅም ያንቺኑ...እኔን ትዝ ይለኛል! ከእጆቼ መዳፍ የጨበጥኳቸውን በአይኖችሽ እያየሽ "ምንድን ነው" ያልሽኝን 'አላውቀውም' ያልኩሽ የምድር ተፈጥሮ የማይመስሉ ፍጥረት በእጄ አንጠልጥዬ "ምንድን ነው" ያልሽኝን 'አላውቀውም' ያልኩሽ እውነቴን መሰለሽ! ገፁን ያጣ አበባ ለአመታት ያህል ቤቴ ያኖርኩትን ከአመታት በፊት የአመታት ፍቅርን የገለፅኩበትን ታድያ ከቆምኩበት ብቻዬን የቀረው ብቻዬን የኖርኩት አበባ ነው ያልኩት ደማካሴ መስሎ ገፁን ያስቀየርኩት ለምን ይመስልሻል! መለየት ያቃተሽ ቀለምና ህብሩ ይዤው የነበረው እንደው ለመሆኑ አበቦች ነበሩ! ምክንያቱን እወቂ... ጠብቀኝ ያለችኝ አንዲት የሴት ጉብል እየጠበኩ ሳለሁ ድንገት ስልኬ ጠራ አነሳሁት ተኩራርቼ ፍቅሬ ነቻ "ምነው ቆየሽ" ከማለቴ....አዘነበች ዶፉን ዶፉን ምናምንቴ ያልመጣም ቃል ሌላ ፈልግ ነበር ቃሏ መድረሻዋ ይታወቃል ይኸው ከዛ ወዲ ለፍቅራችን ብዬ የገዛሁላትን ቀያይ አበባዎች አስቀመጥኩ በክብር እንዳይረጋገጡ በሷ እንደቆረጥኩ ቀለም ህብራቸውን እነሱም ለወጡ። ቀያይ የመሰሉት ገረጡብኝ በጊዜ ላይ ጎመን ሆነ ቀለማቸው የኔ ስቃይ የኔ ጉዳት ህመሜ ነው ህመማቸው ርዕስ ...... ቀይ ወይም ጎመኔ ይበልዛል ቀዩ ቀለም የተመታን እንደሆነ ይጠቋቁራል አረንጓዴው የደረቀ እንደሆነ ያሳዝናል የኔ ህይወት ባንዱ ክዳት ባንዱ ፍቅር እየተኮነነ አላፈቅርም ያልኩት አፈቀርኩኝ ዳግም ልቤ እስኪጠፋ ተረቱ ሆድ ነበር እንዴት ልቤ ሰፋ ልክ እንደ አበቦቹ ቀይ እንደነበሩት ደረቁ ሲባሉ ቀለም ህብራቸውን ለተቀያየሩት እኔም እንደነሱ ተካዳሁ ባልኩ ቀን ከሌላ ፍቅር ጋር ፍቅር አሳወቀን ቀይ ነበርኩ አሁን ደግሞ አረንጓዴ ከዛ ደግሞ ጥቁር ይቀጥላል ህብረ ቀለም ያለቀ ይመስላል የሚያልቅ ግን የለም ዮኒ ኣታን @yonatozz 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
👍 22 2
አድነኝ😔 (ታደሰ ደምሴ) አድነኝ... ገላ ከቅጠል ቀለለ የትም ሲረግፍእየዋለ😌 አድነኝ... "በእረኛው እየተበላ፣ ያለቀው ስንቱ መንጋ ነው?" እንዳልል ማንስ ሊሰፍረው! አድነኝ... ሲያሻው አለቃ ሊበላኝ፣ ሲፈልግ ሊመነዝረኝ፣ ምድር ላይ እቃኔን አለሁ፣ ኑረት ኮንትራት ሆኖብኝ መሬት ንጉስን አትከስም፣ አንተእንጂ የምታስጥለኝ። አድነኝ... ከብዙ ሰይፍና ጎመድ ከብዙ የጥይት ባሩድ እኔእንደሁ ገልአፈር እንጂ፣ የለኝም የብረት ሃዲድ። አድነኝ ከጅራፍ እጆች አድነኝ ከጭራቅ ጥፍሮች ለበድኔ ከማሱት ገደል ብረት አሎሎ ሸክፈህ፣ "ኑር" የሚል ፊርማህን ትከል። ፈውሰኝ ከነፍሴም ቁስል፣ እጠበኝ ከስጋየ እድፍ ሞትም እርስቴ ነውና፣ በእረፍቴ ሰይፍህ እንዳታርፍ። አድነኝ... አድነኝ... ሳር ቅጠሉ ሁሉ  ሞቴን ሲደግሰው ማዳንህን ብቻነው ካንተ ዘንድ የምሻው አድነኝ...። 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
14👍 9
በአለም ውጥንቅጥ ሀሳቤ ቢበተን መኖር ዳገት ሆኖ ጉልበቴ ቢፈተን ክፉ መሰናክል መንገዴን የሚያስት ወጥመድ በየቦታው ቢተክልብኝ ጠላት ጉልበቴ ነው ስምሽ ለዳገቱ መውጫ ከለላ ነው ምልጃሽ ከወጥመድ ማምለጫ አምላክ ቀድሶሻል ከሁሉም አብልጦ ካንቺ ይወለድ ዘንድ በስጋ ተገልጦ ቀድሞ ያየኝ ጌታ ሳልፈጠር በፊት አንቺን አስቀረልኝ እንዳገኝ መድኃኒት ህመም ለጠናበት ለተራበው ጎኔ የሰማይ መና ሆንሽ ፈዋሼ መድህኔ የህወትን ሀሩር የምከለልብሽ የነፍሴ እርጋታ ማረፊያ ነው ጥላሽ ወጀቡን ልሻገር ባንቺ ተደግፌ ድካሜ ይወገድ ከጥላሽ አርፌ ጎድሎ የነበረው ሙሉ ሆኗል ዛሬ ምንም አላጣሁም ላንቺ ተናግሬ የጌታዬ እናት ለኔም እመቤቴ መመኪያዬ አይኔ ፍቅር ነሽ ህይወቴ ደጓ አዛኚቱ አንቺን የተጠጋ ከልጅሽ ይወርሳል የሰማዩን ዋጋ ይመስገን ፈጣሪ የነ ዳዊት አባት ቤቴን ሞልቶልኛል ባንቺ አማልጅነት እራሱ መስርቶ እናቴ ሆይ ያለሽ ልጄ ሆይ ምትይው አምላክሽን አቅፈሽ የቸርነት አባት የዘላለም ቅዱስ መንበረ ፀባዖት ለአርያም ንጉስ ለናሬቱ ኢየሱስ ታምሩ ለማያልቅ መንበር የሆንሽለት ምንጭ ነሽ የማይደርቅ ዳግም እንዳልራብ ነፍሴ ኤንዳትጠማ ከማይደርቀው ምንጭሽ አጠጪኝ እማማ Aናን 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
21👍 8🥰 3
👄አፍና ልብ❤️ 🙅‍♂ አፌን አትመኝው አንዳንዴ ይዋሻል 🤥 በመግደርደር ብዛት እውነትን ያሸሻል ❤️ ልቤ ግን ሞኝ ነው ትንሽ ብትቀርቢው             ሁሉም ይታይሻል 💓ከሌላ አብልጦ አንቺን እንደሚወድ          በደንብ ይነግርሻል።❤️‍🔥 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
👍 17🥰 6
/ይቀጥላል ፍቅር/ ሳላገኝሽ በፊት ሳትሆኚ በቅርቤ በገሃድም ሳይሆን ሳለሽ በአሳቤ፤ የዛኔ የሆንኩት አንቺን ላገኝ ብዬ ሙሾ ያስወረደኝ ያስባለኝ እዬዬ፤ ያ ፍቅርሽ ብዙ ጉድ ያሳየኝ ጊዜው ደርሶ ዛሬ ካንቺ ቢያቆራኘኝ፤ አጣጥሜ በቅጡ ሳልቀምሰው ልኖር ካንቺ ቤቴን ሳልቀልሰው፤ በጅምሩ በፍቅራችን ንጋት የመውደድን ፅዋ አብረን ሳንጋት፤ " ዛሬላይ" እስክረሳው ያንቺ ወደኔ መምጣት እስክል ድረስ ለምን አፈቀርኳት፤ አርጎኝ የነበረው ላንቺ እንድረታ ሰከን ያላረገኝ እንዳላስብ ላፍታ፤ የከለለኝ እሱ እንዳላይ ጋርዶብኝ ፍቅርሽ አይደለም ሆይ ያረገኝ ባንቺሞኝ፤ ግን የሚገርመው የኔ ፅኑ አቋም ይቀጥላል ፍቅር እንዴት ባንቺ ሊቆም: #መሳይ ግርማ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
🥰 7👍 6🔥 1
ታብ ታብ  አደለም  እየገባችው  ክሌም ማረግ ነው  ቤተሠቦች    166.99$በ1ቀንን ከታች ሊንክ  አለ  ተመዝገቡ ታብ ታብ  አደለም  እየገባችው  ክሌም ማረግ ነው  ቤተሠቦች    166.99$በ1ቀንን ከታች ሊንክ  አለ  ተመዝገቡ 👇👇👇👇 Click Here
Hammasini ko'rsatish...
👍 8
ሰባት ሆነን ነበር ትምርት ቤት የምንሄደው አንለያይም። እናጠናለን አቅማችን ፥ ኑሯችን ፥ ጥረታችን ተመሳሳይ ነበር። ማትሪክ ደረሰ ፤ አጠናን ተፈተንን ፤ ፕሪፕ ስንገባ ምን እንደምንመርጥ እቅዳችን አውጠነጠንን ፤ ውጤት ከብዙ ጥበቃ በሆላ ወጣ ተባለ ፤ ልንቀበል ሄድን... ሁሉም አለፉ ከኔ በቀር። ከውጤት መልስ አብርያቸው ነበርኩ እንደልባቸው ድላቸውን እንዳያጣጥሙ አደረኳቸው። ጓደኞቼ ፣የሰፈሩ ሰዎች፣ የጓደኞቼ ቤተሰቦቾ አይዞህ አሉኝ አዘኑልኝ። ውጤቴን ለቤተሰቦቼ አሳየኋቸው እቤት እከሌስ እከሌስ እንዴት ሆነ ሲሉኝ ከኔ በቀር ሁሉም አልፈዋል አልኳቸው። ለመጀመርያ ግዜ ከቤት መውጣት ደበረኝ። አለመርባት ስሜት ተሰማኝ.. እድል የለኝም አልኩ.. ምን አለ ሞቼ ብሆን አልኩ.. ድብርት አከሳኝ። አብሮ አደጎቼ ጋ መሆን አልፈለኩም ነበር። ኋላ የምቀር መሰለኝ ....የሆንኩትን የገጠመኝን ቀላል እንደሆነ የሚያሳምነኝ አንድም አላገኘሁም። መውደቅን ፥ ማነስን ፥ ብቻዬን ተጋፈጥኩት። እናቴ ብቻ ናት የራሱ ጉዳይ አንተ ብቻ ደና ሁንልኝ ያለቺኝ ዋናው ጤና ነው የሚቀጥለው ታሻሽላለህ አለቺኝ። ደግሜ መፈተን እንደማልችል አልገባትም ነበር። . . . አጎቴ ገራዥ ነበረው እሱ ጋ መዋል ጀመርኩ። የማታ Auto mechanic መማር ጀመርኩ። ጎበዝ ባለሙያ ሆንኩኝ። practically እወቀቱን ሳየው ስለምውል theory ቀለለኝ። ከክፍሉ አንደኛ እየወጣሁ ስራ ቦታም ጎበዝ መካንኪ ሆንኩኝ። ብቻ መቆም ለመድኩኝ ብቻ መውደቅ ምን ምን እንደሚል ጌታዬ አስተማረኝ የወደቀ ሰው እንዴት እንደሚፅናና ተማርኩኝ መውደቅ ሁሉ መውደቅ እንዳይደለ ተማርኩ ዛሬ ሃብታም ነኝ። የመኪና 'spare part' አስመጪ እና ላኪ ሆኛለሁ። ጌታ ኋላ የቀረን ግምባር ቀደም ማድረግ እንደሚችል ፤ በሁሉም ሰው የታዘነለትን ፥ በሁሉም ዘንድ የሚያኮራበት ሰው ማድረግ እንደሚችል አይቻለሁ። ያኔ ብቻዬን ስሆን የተሰማኝ ውድቀት የወለደልኝ ጥንካሬ እና ብስለት ዛሬ ድረስ ስንቴ አሻግሮኛል...! አንዳንዴ ተለይቶ የመውደቅ መጨረሻ ድልም ሊሆን ይቻላል!! © Adhanom Mitiku 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
👍 70 19👏 1
ናፍቀሽኛል ጊዜ ይሮጣል አሉ ጊዜ ይበራል አሉ አንደዚ በማለት ሚያወራ ሰው ሁሉ ምናለ ቢያስረዱኝ ይህንን ከቻሉ : : ለኔ ጊዜው አይሮጥም በፍፁም አይበርም እንደው ይባስ ብሎ መቁጠሩንም ትቷል ካንቺ ከራቅኩ ወዲህ ቀኑ አመት ሆኗል እናም ርዝማኔው አሁንስ ከብዶኛል የውነቴን ነው ምልሽ በጣም ናፍቀሽኛል : : ሀልጊዜም ቢሆን አንቺን ነው ማስብሽ ከራሴ በላይ ነው እኔ የምወድሽ በደስታ ቆዪልኝ በአካል እስካገኝሽ:: 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Hammasini ko'rsatish...
👍 17🥰 2👏 1