uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 321
Obunachilar
+124 soatlar
+67 kun
+14830 kun
Postlar arxiv
"በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ብልጽግና ህብረት 3ኛ ዙር የብልፅግና ፓርቲ አባላት ስልጠና መካሄድ ጀመረ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 26/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

"ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽን በዘላቂነት እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል በአለም ለ38ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ37ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም ኤድስ ቀን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በፓናል ውይይት አከበሩ። በፓናል ውይይቱም የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን በመቆጣጠር ሂደት ተግዳሮቶችን በመለየት መቋቋም የሚያስችል የሚከሰቱትንም ቸግሮች መቅረፍ እንዲቻል ታላሚ ያደረገ ሲሆን ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በሃላፊነት መስራት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡ የኤች አይ ቪ ስርጭት አሁንም እጅግ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑንና ከዚህም ጋር በተያያዘ በበሽታው የሚፈጠረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና  ከፍተኛ መሆኑን ነው፤ በመሆኑም የፓናሉ ተሳታፊዎች በየአካባቢያቸው የሚመለከቷቸውን ለቫይረሱ ተጋላጭ የሚያደርጉ ጉዳዮችን አንስተዋል። በማጠቃለያውም ቢሮው በዋናነት ከወጣቶች ጋር የሚገናኝ እንደመሆኑ መጠን ተጋላጭነታቸውን በመቀነሱ ረገድ ከዋና ስራ ጎን ለጎን ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ መግባባት ተፈጥሯል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በብራንዲንግ እና አድቨርታይዚንግ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ 30 ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ተሰጠ፡፡ በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች በአስተዳደሩ የሚገኙና ምርታማነታቸው እንዲሁም ከፍተኛ የማደግ አቅም እንዳላቸው የተመሰከረላቸው ሲሆኑ ምርትና አገልግሎታቸውን በዘመናዊና በተሻለ አቀራረብ በማዘጋጀት በአገር ዓቀፍ አልፎም በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ እንዲጨብጡ አስችሏል፡፡ በዚህም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባህላቸውን እንዲያሳድጉና በዲጂታል ገበያው በተለይም ሉሲ ማርኬት ላይ ተቀላቅለው ተደራሽነታቸውን እንዲያሰፉ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሀ/ማርያም እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ አብራርተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በእጀ ወርቆች የተመረተ ልዩ ልዩ ቦርሳዎችን፣ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ታገኛላችሁ ምርቶቻችን 💼 በቆዳ ውጤቶች የተማሪ ቦርሳ፣የላፕቶፕ ቦርሳ፣የሴቶች ቦርሳ፣ዋሌት፣ቀበቶ 👗 በአልባሳት የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ጋውን፣የ ሰራተኞች ቱታ፣የባህል አልባሳት፣የስፖርት ቁምጣ እና ቲሸርት፣የህትመት ቲሸርቶች፣ስካርፕ እንዲሁም ዘመናዊ አልባሳትን በትእዛዝ እናመርታለን በቡድን ለሚመጡ ደንበኞች ልዩ ቅናሽ እናደርጋልን፡፡ጥራትና ቅልጥፍና መለያች ነው ይምጡ ይዘዙን አድራሻችን ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወደ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ 150 ሜትር ላይ እንገኛለን

ኤስ.ኦ.ኤስ ወጣቶችን በተለያዩ ፕሮጀክቶች በማቀፍ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሊተገብር ነው ። ግሪን ግሮውዝ - ወጣቱን ለብሩህ መፃሄ ማብቃት("Green Growth - Empowering Youth for a green future") የተባለውን ፕሮጀክት ስራ ለማስጀመር ኤስ ኦ ኤስ ( sos ) ህጻናት መንደር ከባድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። ግሪን ግሮውዝ ከ 2ሺ400 በላይ ወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በፕሮጀክት ውይይቱ ላይ እንደገለጹት እንደ ግሪን ግሮውዝ ያሉ በተለይ ወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች እንደ አስተዳደር ከፍተኛ የሆነውን የወጣት ሥራ አጥነት ቁጥር የሚያቃለሉ ናቸው። ኤስ ኦ ኤስ ህፃናት መንደር ከዚህ በፊትም መሰል ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ከቢሮው ጋር መስራታቸውን አስታውሰው አሁንም ቢሮው በፕሮጀክቱ የሚታቀፉትን ከ 2ሺ 4 መቶ በላይ ወጣቶችን በቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በሞያና በክህሎት በማስልጠን የስራ ምችችት በማድረግ ከsos ( ኤስ ኦ ኤስ ) ህጻናት መንደር ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ። የኤስ ኦ ኤስ (sos) ህጻናት መንደር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ የፕሮጀክቶች አስተባባሪ አቶ ሚካኤል ስንታየሁ እንደገለጹት ወጣቶችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ በማድረግ መጪ ጊዜያቸውን ብሩህ ለማድረግ የሚተገበረው ፕሮጀክት ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ነው። ፕሮጀክቱንም ተግባራዊ ለማድረግ ቀደም ሲል ከባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያና የትብብር ፊርማ መፈራረም መቻሉን ጠቁመዋል። ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወጣቶች መካከል 60 በመቶው ሴቶች እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን አካል ጉዳተኞች ደግሞ 5 በመቶ የተጠቃሚነት ድርሻ እንደሚኖራቸው ነው የታወቀው። በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ ከዚህ በፊት በጥናት የተሰሩ ፕሮጀክቶች ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ©️ DireTvአማርኛ | ህዳር 25 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ

“ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ሶስተኛ ዙር የድሬዳዋ አስተዳደር አፈጻጸም በፌደራል የሱፐርቪዥን ቡድን ተገመገመ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት በስሩ ከምገኙ የወረዳ አንድ ማዕከላት ከሚያስተባብሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የሶስተኛ ዙር በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ ከፌደራል በመጡ የሱፐርቪዥን ቡድን የተመላከቱ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመንቀስ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም መድረክ ላይ ፕሮጀክቱ ባለፉት አመታት እንደ አስተዳደር ያስገኘውን ጠቀሜታ ከጅምሩ ሰልጣኞች በስልጠና ላይ ሆነው ከአመለካከት አንስቶ በኢንደስትሪዎች ተመድበው በሥራ ላይ ልምምድ እያደረጉ እስከሚገኝበት አሁናዊ ሁኔታ ወጣቶቹ እያሳዩ የሚገኙትን ለውጥ ቤተሰብ የመሰከረለት በሚሰሩበት ኢንደስትሪም በሥራ ላይ ልምምዱ ቋሚ ቅጥር እየፈጸሙ መሆኑ የሚያበረታታ መሆኑን የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡ በተያያዘ ወጣቶቹ የአቻ ለአቻ ውይይቶችንና መሰረታዊ የአይ.ሲ.ቲ እንዲሁም የህይወት ክህሎትና የሥራ አፈላለግ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የተደረገ መሆኑና ጥቂት የታዩ የመጠነ ማቋረጥ አዝማሚያዎችን ከኢንደስትሪዎቹ ጋር ተናቦና ተቀራርቦ ከፌደራል በተዘረጋው የድጋፍና ክትትል ስርዓት የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ከዚህ በላይ ለማሳደግና ለማጠናቀቅ አቅጣጫዎች ተቀምጠው ወደ ስራ መገባቱ ታውቋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 24/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የ2018 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ሰልጣኞች ቅበላ በመንግስትና በግል ኮሌጆች ላይ የትምህርት ማስረጃ ጥራትና አግባብነት የማረጋገጥ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ፤ በዚህም በየአመቱ በአስተዳደሩ የሚገኙ ሁሉም የግልና የመንግስት ኮሌጆች የሰልጣኝ ቅበላ ሲያካሂዱ በተላለፈላቸው የአሰራር መመሪያ ማከናወኛ መሰረት ሲሆን ከዚህ በተለየ ኮሌጆች ለራሳቸው በሚያመቻቸው መንገድ ከተቀመጠላቸው መመሪያ ውጪ በሚገባ ባልተፈተሸና ባልተረጋገጠ ሀሰተኛ ማስረጃ ሰልጣኝ ከተቀበሉ በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያት የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በወቅቱ ለማረምና ለመቆጣጠር የትምህርት ማስረጃ ጥራትና አግባብነት የማረጋገጥ ሥራ የሚከናወን ይሆናል፡፡ በዋናነት ኤጀንሲው ባለው ስልጣንና በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ኮሌጆቹ ከመነሻው በወረደላቸው የቅበላ መመሪያ መሰረት ምዝገባ ማከናወናቸውን የማረጋገጥና ሰልጣኞች ያቀረቧቸው የትምህርት ማስረጃዎች ትክክለኛውን ከሀሰተኛው በመለየት ቅበላው በየደረጃው መቁረጫ ነጥብ መሆኑን ፈትሾ በሚገኙ ክፍተቶችና ከመመሪያ ውጪ በሆኑ አካሄዶች ላይ ፈጣንና አግባብነት ያለው የማስተካከያና የእርምት ስራዎችን ለመስራት አላማው አድርጎ የሚሰራ መሆኑ ታውቋል፡፡ በመሆኑም በመንግስትና በግል ኮሌጆች በ2018 ዓ/ም በአገር አቀፍ ደረጃ በተላለፈው የመቁረጫ ነጥብ መሠረት የ2018 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ሰልጣኞች ቅበላ ላይ የትምህርት ማስረጃ ጥራትና አግባብነት ትክክለኛ መሆኑን በማረጋገጥ በተሰጣቸው ህጋዊ የማሰልጠን ፈቃድ ብቻ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰልጣኞችን በሞያ መስኩና ደረጃ መቀበላቸውን በተቀመጠው የቴ/ሙ/ት/ስ የስልጠና ጥራት ስታንዳርድ መሰረት መሆኑን በማስጠበቅና በማረጋገጥ ተቋማት ህግና ደንብን በሚገባ አክብረው እንዲሰሩ ኤጀንሲው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በመቆጣጠር በህግ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት እንዲወጣ ያስችለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 24/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንድ ጀምበር ለ30 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ አስጀመሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንድ ጀምበር ለ30 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄን አስጀመሩ። ከንቲባዋ በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት፥ የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ዛሬ የምንገነባው ትውልድ በክህሎትና በዕውቀት የበለጸገና ችግር ፈቺ እንዲሆን እየተጋን ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ በአንድ ጀምበር ለ30 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ መርሐ ግብር የዚህ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም ወጣቶች ከዛሬ ጀምሮ በከተማ ግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በንግድ፣ በአገልግሎትና በአምራች ዘርፎች ስራ ይጀምራሉ ነው ያሉት። በመዲናዋ የሚፈጠረው የስራ ዕድል ፈጠራ የስራ ገበያው በሚፈልገው ልክ እንዲሆን ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ከንቲባዋ ለወጣቶቹ የስራ መሳሪያ ስጦታዎችን ያበረከቱ ሲሆን፥ በቀጣይም በሚሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሚሊዮን ማቴዎስ በበኩላቸው፥ በመዲናዋ የስራ አጥነትን ለመቀነስና ለስራ ዕድል ፈጠራ ያሉ ጸጋዎችን በጥናት በመለየት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በ2017 በጀት ዓመት ለ366 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን አስታውሰው፥ በ2018 ባለፉት አራት ወራት ብቻ ለ158 ሺህ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል። በመዲናዋ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የብድርና የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ለማመቻቸት ከተማ አስተዳደሩ እየሰራበት እንደሚገኝም ነው የተናገሩት። በመዲናዋ ለክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰው፥ በ14 የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ወጣቶችን በማሰልጠን የስራ ዕድል እየተፈጠረ ይገኛል ብለዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የመርሐ ግብሩ ተጠቃሚ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)