Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 329
Obunachilar
+324 soatlar
+87 kun
+8330 kun
Postlar arxiv
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በ2017 ዓ.ም በኮሌጁ ሊሰሩ በታቀዱ ቴክኖሎጂዎች ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ::
በመድረኩ አሰልጣኝ መምህራን በበጀት አመቱ ሊሰሯቸው ያቀዷቸውን የቴክኖሎጂ አርዕስቶች ለጥናትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ክፍል በግልና ቡድን ባስገቡት መሰረት ስለሚሰሩት ቴክኖሎጂ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል::
በተጨማሪም በዕለቱ በቀረቡት የቴክኖሎጂ አርዕስቶች ላይ ከሚመለከታቸው ዲፓርትመንቶች እና ከክፍሉ ባለሙያዎች እንዲሁም አሰልጣኝ መምህራን ጋር በመሆን ከማህበራዊ ጠቀሜታ፣ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ፣ከአካባቢ ደህንነት እና ከቴክኖሎጂ አንጻር ገንቢ አስተያየት ተሰጥቶባቸው ወደ ቀጣይ ስራ እንዲገቡም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ በ2017 ዓ.ም በአስተዳዳር ደረጃ ለሚደረገው የቴክኖሎጂ ውድድር በሁሉም ወረዳዎች በኢንተርፕራይዝ የተመዘገቡ ሆነው የቴክኖሎጂ ስራ ያላቸውና ለመወዳደር የሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች እስከ ህዳር 20/2017 ዓ.ም ድረስ ቴክኖሎጂ ክፍል በአካል በመቅረብ ምዝገባ እንድታደርጉ እያሳወቅን የመ/ቤቱ አድራሻ ቢ-ካፒታል ሆቴል ጎን መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ
#ዜና | በሀገራችን የተንሰራፋውን ስራ አጥነት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አጫጭር ስልጠናዎች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።
#Diretv አማርኛ ጥቅምት 24/2017
የአሰሊሶ ክላስተር በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ላሰለጠናቸው ወጣቶች እውቅና ሰጥቷል።
ስልጠናው በምግብና በምግብ ነክ እንዲሁም በእንጨት ስራና በሌሎችም ሞያ ላይ ያተኮረ ሲሆን ያገኙትም የሞያ ስልጠና ለሶስት ወራት ያህል በአግባቡ በመውሰድ ላጠናቀቁ ለሰላሳ ወጣቶችም እውቅና ተሰጥቷል።
የአሰሊሶ ክላስተር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዲ አብደላ ስራ አጥነትን በሀገራችን ለመቀነስ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች የሚሰጡ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን ገልፀው ታዲያ በተለያዩ ጊዜዎች በምችችት የሚመጡ አጭጭር ስልጠናዎችን ወጣቶች እንዲጠቀሙበት ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዛሬ በአሰሊሶ ክላስተር የወሰዱትን ስልጠና አጠናቀው እውቅና የተሰጣቸው ሰልጣኞች ወደ ስራ ለማሰማራት ሁኔታዎችን የማመቻቸት ስራዎች እንደሚሰሩም የገለጹት አቶ አብዲ ይህም ለሌሎች ወጣቶች መነቃቃት የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም ይህን የአጭር ጊዜ ስልጠና እንዲያገኙ ከክላስተሩ ጋር በትብብር የሰሩትን አካላት ማለትም ወሊፍ በጎ አድራጎት ፣ የሥራና ክህሎት ቢሮን አመስግነዋል።
የአጭር ጊዜ ስልጠናውን የወሰዱ ወጣቶችም በቀሰሙት የሞያ ትምህርት ራሳቸው ለመለወጥ ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
©️ Dire Tv አማርኛ
በድሬዳዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚሰሩ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ሰራተኞች ህጋዊነት የሚያረጋግጥ የቁጥጥር ስራ መሰራቱ ተገለጸ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት በአስተዳደሩ በሚገኙ ኢንደስትሪዎችና የግል ድርጅቶች ውስጥ በተለያዩ የሥራ መደብ ላይ ተቀጥረው የሚሠሩ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ቁጥጥር አደረገ።
በዚህም መሰረት በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ህጉን ተከትለው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ማረጋገጥ ዋና አላማው ያደረገው ይህ ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአግባቡ ተፈጻሚነት፤ ወቅቱን ጠብቆ የታደሰ የመኖሪያ ፈቃድ መኖሩን፤ የፓስፖርት እና የስራ ፈቃድ እንዳላቸው፤ ለአገራችን ዜጎች በተገቢ መልኩ የእውቀት ሽግግር እያደረጉ መሆኑን እንዲሁም በሚሰሩበት ክልል/አስተዳደር ላይ የሥራ ግብር እየከፈሉ መሆኑን የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል፡፡
የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፉን የሚመሩት አቶ መሀመድ ኢብራሂም ዜጎች ወደ ውጭ አገራት በመሄድ የመስራት መብት እንዳላቸው ሁሉ የውጭ አገራት ዜጎችም ወደ አገራችን በመምጣት በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ የመሥራት መብት እንዳላቸውና ሲሰሩ ሀገሪቱ ባጸደቀቻቸው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት ተገቢውን ፎርማሊቲ እንዲያሟሉ የሚጠበቅ(የሚገደዱ) መሆኑን ገልጸዋል፤
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት እቅድ እና የዝግጁነት ምዕራፍ አፈፃፀም ሪፖርት በተመለከተ የኮሌጁ ማህበረሰብ በተገኘበት የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ በቅድሚያ በኮሌጁ የዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን በዋነኛነትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የሆነውን የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት እውቅና ያገኘበትን የላቀ ትግበራ ያከናወነበት ምዕራፍም ነበር::
በተጨማሪም በዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት እንደ ተቋም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ከዋና ስራ ሂደቶች ጀምሮ እስከ ፈፃሚው ድረስ የጠራ እቅድ ዝግጅት የተከናወነበት ወቅት ሲሆን እንዲሁም የአረንጏዴ አሻራ፣የደም ልገሳን ጨምሮ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስና መሰል ትግበራዎችም በዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት እንደተከናወኑ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ሪፖርት ቀርቧል::
በመጨረሻም የ2017 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ለኮሌጁ ማህበረሰብ የቀረበ ሲሆን የቀረበውን እቅድ መነሻ በማድረግም ከመድረኩ ተሳታፊዎች ሀሳብ ተሰቶበት ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጎበታል::
በማጠቃለያውም በተጠናቀቀው በጀት አመት የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማስቀጠል እንዲሁም በ2017 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ተገልፆ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም
#ዜና በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች መቀበል መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፤
በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች ምዝገባ መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በዛሬው ዕለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮው አዳዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲገቡ በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በአስተዳደሩ 6 የግል እና 2 የመንግስት ኮሌጆች ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት አዋጭ የትምህርት ዘርፎችን የመለየት በተለይም አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ሀገር አቀፍ እና አለምቀፍን የሚያስተሳስሩ የዲጂታላይዜሽን ስልጠናዎችን ጨምሮ ስለሚሰጥ ሰልጣኞች አውቅና እና ብቃት ካላው ኮሌጆች ጋር ተገናገኝተው ዘርፉን መምረጥ እንደሚገባም ነው ኃላፊዋ ያብራሩት፡፡
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በደረጃ 3 እና 4 ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የመቀበል አዝማሚያዎች እንዳሉ አንስተው በተያዘው በጀት አመት ሁሉም የግል እና የመንግስት ኮሌጆች ደረጃ 1 እና 2 ተቀብለው ምዝገባ እንዲያካሂዱም ነው ያሳሰቡት፡፡
ኃላፊዋ አያይዘውም ቢሮው እንደ ከዚህ ቀደሙ በአስተዳደር ደረጃ በደማቁ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሳምንት(TVT Week) ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸውንና የዘርፉን ገጽታ ለመገንባት የሚያስችሉ በተጨባጭ የተሰሩ ስራዎችን ህብረተሰቡ እንዲመለከታቸው የማስተዋወቅ እና ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶጨ ጀማል አደም ሰልጣኝ ተማሪዎች የሥራ ዕድል ፈጠራን በክህሎት በመታጀብ የተመቻቸውን ዕድል ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመምጣት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
©️ DGC ጥቅምት 20/2017
#ዜና በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች መቀበል መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፤
በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በ2017 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገቡ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁንና ኮሌጆች ምዝገባ መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በዛሬው ዕለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮው አዳዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲገቡ በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በአስተዳደሩ 6 የግል እና 2 የመንግስት ኮሌጆች ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት አዋጭ የትምህርት ዘርፎችን የመለየት በተለይም አስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ሀገር አቀፍ እና አለምቀፍን የሚያስተሳስሩ የዲጂታላይዜሽን ስልጠናዎችን ጨምሮ ስለሚሰጥ ሰልጣኞች አውቅና እና ብቃት ካላው ኮሌጆች ጋር ተገናገኝተው ዘርፉን መምረጥ እንደሚገባም ነው ኃላፊዋ ያብራሩት፡፡
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በደረጃ 3 እና 4 ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የመቀበል አዝማሚያዎች እንዳሉ አንስተው በተያዘው በጀት አመት ሁሉም የግል እና የመንግስት ኮሌጆች ደረጃ 1 እና 2 ተቀብለው ምዝገባ እንዲያካሂዱም ነው ያሳሰቡት፡፡
ኃላፊዋ አያይዘውም ቢሮው እንደ ከዚህ ቀደሙ በአስተዳደር ደረጃ በደማቁ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሳምንት(TVT Week) ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸውንና የዘርፉን ገጽታ ለመገንባት የሚያስችሉ በተጨባጭ የተሰሩ ስራዎችን ህብረተሰቡ እንዲመለከታቸው የማስተዋወቅ እና ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ኃላፊዋ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡