Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 330
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+97 kun
+8030 kun
Postlar arxiv
ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁ.1161/2011 ላይ ለገጠር ወረዳና ቀበሌ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፤
በዚህም መድረክ የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ የልማት ተነሺ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለራሳቸውና ለሌሎች በመፍጠር በዘላቂነት እራሳቸውን እንዴት ማቋቋም እንደሚገባቸው ገለጻ ተደርጓል፡፡
በመሆኑም የልማት ተነሺ የሚሆኑ ዜጎች ከዚህ በፊት የተከፈላቸውን ካሳ ዕሴት በማይጨምሩ ጉዳዮች ላይ በማዋል እራሳቸውንም ሆነ ሌላውን በዘላቂነት ሳይጠቅም ይባክን የነበረውን ሃብት በተቀናጀ አግባብ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠርና አሰራርን በመዘርጋት ዕሴት የሚፈጥር ይሆናል፡፡
ይህንንም ተፈጻሚ ለማድረግ በአስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት የሚገኘው ካሳ ክፍያና መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ከሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት፤ ከገጠር ወረዳና ቀበሌዎች፤ ከባንኮች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻዎችን ጋር በመሆን ይተገበራል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 16/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
'#ትንሿኢትዮጵያ' 🇪🇹 ድሬዳዋ
የኢትዮጵያ ኮደርስ ስልጠናን ለመተግበር የተከወኑ ቅድመ ዝግጅቶችን አስመልክቶ፥ የአስተዳደሩ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ፥ በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ለመሳካት እና ለአገር ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው በወቅቱ ተገልጿል።
ይህን ፕሮጀክት በዚህ ወር በድሬዳዋ ለመተግበር ቅድመ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የቴክኖሎጂ ስልጠናውን የሚወስዱ ወጣቶች ከሚያገኙት ዓለምአቀፍ የምስክር ወረቀት በተጨማሪ፥ በዘመኑ የዲጂታል ዓለም ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ስራ ፈጣሪ ለመሆን ያስችላቸዋል።
ለ3 ዓመታት በሚዘልቀው የኢትዮጵያ ኮደርስ ስልጠና ከ32 ሺህ በላይ የአስተዳደሩ ወጣቶች ተጠቃሚ ሲሆኑ፥ በዚህ ወር በሚጀምረው የኮዲንግ ስልጠና 8 ሺህ ወጣቶች ይሳተፋሉ።
ስልጠናው ወጣቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ሥራ ፈጣሪ ሆነው ለአገር ዕድገት ሚናቸውን እንዲወጡ መሠረታዊ ክህሎት ከማስጨበጡ ባሻገር፥ በአስተዳደሩ የሚገኙ 180 አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ዲጂታላይዝ በማድረግ፥ ድሬዳዋ ስማርት ሲቲ እንድትሆን ለተጀመረው ጥረት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
በአስተዳደራችን ለሚተገበረው የኢትዮጵያ ኮደርስ ስልጠና 20 የመማሪያ ክፍሎች እና 400 ኮምፒውተሮች የተዘጋጁ ሲሆን፥ ለፕሮጀክቱ መሳካት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እና ሁለቱ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም ሌሎችም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የድርሻቸውን ለመወጣት ተዘጋጅተዋል።
©️ Mayor Office - ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የውጭ አገር ሥራ ስምሪትና የሠራተኞች ደህንነት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት በድሬዳዋ አስተዳደር ከሴክተር ተቋማትና ከወረዳ አንድ ማዕከላት ለተወጣጡ የባለድርሻ አካላት ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ።
በመድረኩም ለባለድርሻ አካላት በሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና ለሥራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀል አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ህጋዊ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 1246/2013 ላይ በባለሙያዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
በዚህም ተሳታፊዎች አዋጆቹን በመረዳት በሰዎች የመነገድ፣ በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገወጥ መንገድ ለስራ ወደውጭ አገር መላክ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከቢሮው ጋር በቅንጅት ለመስራት መግባባት ተፈጥሯል፡፡ ፡፡
በማጠቃለያውም በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ (https://lmis.gov.et/auth) ሥራ ፈላጊው ህብረተሰብ እንዲመዘገብ እና ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 16/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአጫጭር ስልጠና ዘርፍ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚሰጡ ተቋማት የ2017 ዓ.ም በዝግጅት ምዕራፍ የትምህርትና ስልጠና ተቋማቱን አቅም ለመገንባት ያለመ የክትትልና ድጋፍ መርሃግብር ተካሄደ፤
በዚህም የድጋፍና ክትትል መርሃግብር የአጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት በዕቅድ መሠረት ስለመመራታቸው፤ በቂ የስልጠና ግብዓት ስለመኖሩ፤ የስልጠና ፍቃድ በተመለከተ በተሰጠው ፈቃድ ልክ እየሰሩ ስለ መሆናቸውና እንዲሁም የማሰልጠኛ ማንዋሎችና መሳሪያዎች በሚገባ መኖራቸውን ጨምሮ የአጠቃላይ ሰልጣኞችን መረጃ በማደራጀት እረገድ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከትና በቀጣይ በተከታታይ ድጋፍ የሚያገኙበትን አግባብ ለማመቻቸት ተችሏል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደም እንደተናገሩት ይህ የድጋፍና ክትትል ልክ መደበኛ ስልጠና እንደሚሰጡ ተቋማት ሁሉ አጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማትም ዜጎችን በማሰልጠን የሚያበቁ ናቸው ስለሆነም ትምህርትና ስልጠና ተቋማቱን አቅም ለመገንባትና በቅርበት በመከታተል መደገፍ አላማው አድርጎ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 15/2017 ዓ.ም

መስከረም 15/2016 ዓ.ም

Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
ማሳሰቢያ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተግባራዊ እያደረገ ያለው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መነሻና መዳረሻው የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፡፡
በዘርፉ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በተሰራው ጠንካራ የሪፎርም ሥራ በቴክኖሎጂ ጭምር በመታገዝ ህብረተሰቡን ካላስፈላጊ ወጪና እንግልት በመታደግ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ ሥራ አሁንም ተጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል፡፡
ነገር ግን ስምሪቱን በተመለከተ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስምና አርማ እንዲሁም የከፍተኛ አመራሩን ስምና ምስል ጭምር በመጠቀም የተለያዩ ማስታወቂያዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሕገወጦች በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሀሰተኛ መሆናቸው ታውቆ ሁሉም ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይዳረግ ጥንቃቄ እንዲያደረግ እናሳስባለን፡፡
የሥራ ስምሪቱን በተመለከተ አዳዲስ ነገሮች ሲኖሩ የተቋማችንን ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስርን ጨምሮ በሁሉም የሚደያ አማራጮች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
በሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልግ ማንኛው ሰው በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ (https://lmis.gov.et/auth) እንዲመዘገብ እና ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ
መስከረም 14/2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+9
ብቃት እና ክህሎትን በመላበስ አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር ሚችል አሽከርካሪን ለማፍራት ትኩረት ሰቶ እየሰራ እንሚገኝ የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ።
ኮሌጁ በማሽከርከር ሙያ ላይ ለሚገኙ አሽከርካሪዎች የመካኒክ አሽከርካሪ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
ስልጠናው በማሽከርከር ሙያ ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ያላቸውን ሞያዊ ክህሎት በማዳበር በሚያሽከረክሩ ጊዜ አደጋን ተከላክሎ እና የተሽከርካሪውን ፀባይ ተረድቶ ለማሽከርከር የሚያግዛቸውን መሰረታዊ ስልጠና ለመስጠት ታስቦ መዘጋጀቱ ነው የተጠቆመው።
በዚሁ ስልጠና ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን ኮሌጁ ከድሬደዋ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ባለስልጣን እውቅናን በመውሰድ በማሽከርከር ሙያ አዳዲስ አሽከርካሪዎችን ባማፍራት ላይ እንዳለ አስታውሰው ይህንኑ በማሳደግ በአዲስ አበባ ብቻ ይሰጥ የነበረውን የአሽከርካሪ መካኒክ ስልጠና በሙያው ላይ ለሚገኙ መንጃፍቃድ ለያዙ ሹፌሮች ሙያቸውን የሚያዳብሩበት እና ዘመን የፈጠረውን የማሽከርከር ጥበብ እና የተሽከርካሪዎች ባህሪን ሚረዱበት ቀድሞ የተማሩበትን ማስታወሻ እንዲሁም ቀለል ያሉ የተሽከርካሪ ብልሽቶችን በራሳቸው መጠገን ሚያስችላቸውን አቅም ሚፈጥሩበትን ሙያ ለማስተማር ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመው ሰልጣኞችም ክህሎቱን ባግባቡ በመጨበጥ ብቁ አሽከርካሪ ለመሆን እንዲተጉ መልእክት አስተላልፈዋል።
ስልጠናው 110 ሰአት የሚሸፍን ሲሆን በዚህም የህይወት ክህሎት ቀላል የተባሉ የተሽከርካሪ ጥገና እንደሁም ያለፉ ትምህርቶቻቸውን ከአዲሱ አጣምሮ ሚያስገነዝቡ ስልጠናዎች ተካተውበታል።
በስልጠናው በመጀመሪያ ዙር 43 ተማሪዎች እየተከታተሉ ሲሆን በቀጣይ ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ስልጠና እንዲያልፍ በአነስተኛ ዋጋ ክህሎቱ እንደሚሰጠው ከአስተባባሪዎቹ ለመረዳት ተችሏል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ለ2017 የትምህርት ዘመን ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የሚሆን የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ለአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስረከበ።
በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ክብርት ፈጡም መስጠፋ አማካኝነት ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ማለትም ደብተር ፣ ብዕር ፣ እርሳስ ለትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ለአቶ አቡበከር አዶሽ የድጋፍ ስጦታውን አስረክበዋል።
ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የሥራና ክህሎት ቢሮ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህም ውስጥ ለቅመ ደካማ ወገኖች ቤት እንደ አዲስ መስራት፣ ዝቅተኛ ደሞዝ ላላቸው የቢሮው ሰራተኞች ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የደም ልገሳ መርሃ ግብሮች መከናወናቸውን አስታውሰዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ በትምህርት ቢሮ በመገኘት ላደረጉት ድጋፍ የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ ምስጋናቸውን በራሳቸውና በቢሮው ስም ያቀረቀረቡ ሲሆን በዚህ ተግባር ላይ ሁሉም ተሳታፊ በመሆን ለትውልድ ግንባታ የላቀ ኃላፊነታችንን በመወጣት አሻራችንን እናሳርፍ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት (ዘገባ)
የትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት (ፎቶ)
መስከረም 10/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ለ2017 የትምህርት ዘመን ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የሚሆን የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ለአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስረከበ።
በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ክብርት ፈጡም መስጠፋ አማካኝነት ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ማለትም ደብተር ፣ ብዕር ፣ እርሳስ ለትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ለአቶ አቡበከር አዶሽ የድጋፍ ስጦታውን አስረክበዋል።
ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የሥራና ክህሎት ቢሮ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህም ውስጥ ለቅመ ደካማ ወገኖች ቤት እንደ አዲስ መስራት፣ ዝቅተኛ ደሞዝ ላላቸው የቢሮው ሰራተኞች ቀጥተኛ የጀንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የደም ልገሳ መርሃ ግብሮች መከናወናቸውን አስታውሰዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ በትምህርት ቢሮ በመገኘት ላደረጉት ድጋፍ የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ ምስጋናቸውን በራሳቸውና በቢሮው ስም ያቀረቀረቡ ሲሆን በዚህ ተግባር ላይ ሁሉም ተሳታፊ በመሆን ለትውልድ ግንባታ የላቀ ኃላፊነታችንን በመወጣት አሻራችንን እናሳርፍ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 10/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ
#የድሬዳዋ_አስተዳደር_የሥራና_ክህሎት_ቢሮ_አመራሮችና_ሠራተኞች_ደም_ለገሱ
የተለያዩ የማህበራዊ ኃላፊነቶችን በመወጣት የአስተዳደሩ ነዋሪ ተቋም መሆኑን በተግባር እያሳየ የሚገኘው ቢሮው በዛሬው ዕለትም አመራሩ እና ሠራተኛው በጋራ በመሆን የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡
ቢሮው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቢሮውን ማህበረሰብ በማስተባበር በተለይም በ2017 ሰባት የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በአዲስ አስገንብቶ ለማስረከብ የወሰደውን አገራዊ የመረዳዳትና የመተጋገዝ ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል።
በዚህም ቀድሞውን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ቢሮው በዛሬው ዕለትም በቢሮው ቅጥር ጊቢ በተካሄደ የደም ልገሳ መርሃግብር በተለያየ ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከሰብዓዊነት የመነጨ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 7/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ