Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 321
Obunachilar
+224 soatlar
+87 kun
+15130 kun
Postlar arxiv
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት ፆታን መሰረት ባደረገ ጥቃት ላይ እንዲሁም የአካባቢያዊ እና ማህበራዊ ጥበቃን አስመልክቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ።
በመድረኩ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት (Gender-Based Violence) እና የአካባቢና ማህበራዊ ጥበቃ (Enviroment and Social safe guard) ጋር ተያይዞ በፕሮጀክቱ ቀጣይ ትግበራዎችና ተደራሽ የሚሆኑ ዝርዝር ተግባራት ላይ ለኮሌጁ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላት እንዲሁም የልህቀት ማዕከል ከሆኑት ሶስቱ ዲፓርትመንት ለተወጣጡ አሰልጣኝ መምህራን ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል::
በEASE ፕሮጀክት በትኩረት እንዲሰራባቸው ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል የስርዓተ-ፆታ እንዲሁም አካባቢያዊና ማህበራዊ ጥበቃ በዋነኛነት እንደሚጠቀሱ ያስታወሱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ እክለውም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ጋር በተመለከተ ፕሮጀክቱ የራሱ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ሂደት ያለው በመሆኑ ግንዛቤን ለመፍጠር እንዲሁም በቀጣይ በፕሮጀክቱ የሚሰሩ የሪኖቬሽን ስራዎች የአካባቢ ጥበቃን ባማከለ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆኑ በሚቻልበት አግባብ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት ይህ መድረክ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል::
በዕለቱ በነበረው መድረክ በቅድሚያ በEASE ፕሮጀክት ትግበራ የእስካሁን አፈፃፀምና በቀጣይ የሚከናውኑ ቁልፍ ተግባራትን አስመልክቶ የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ለተሳታፊዎች በዝርዝር ገለፆ አድርገዋል::
በመቀጠል በፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ሲፈጠሩ ጉዳዩ በሚስተናገድበት አግባብና ሪፖርት ከማድረግ ጀምሮ እስከ ሚሰጠው ውሳኔ ድረስ በፕሮጀክቱ ባህሪ መሰረት የተቀመጠውን የአሰራር ሂደት በዝርዝር ለተሳታፊዎች ግንዛቤ የሰጡት የEASE ፕሮጀክት የስርዓተ-ፆታና አካቶ ባለሙያ የሆኑት አቶ አዲስ አክሊሉ ሲሆኑ በተጨማሪም የፕሮጀክቱ የተለያዩ ትግበራዎች በሚከናወኑበት ወቅት የአካባቢና ማህበራዊ ጥበቃን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲከናወኑ በሚያመለክት ሁኔታ የተቀመጡ ዝርዝር ሂደቶችና ነጥቦች ላይም ሰፊ ገለፃን በመስጠት ለመድረኩ ተሳታፊዎች ግንዛቤ ፈጠረዋል::
በመጨረሻም በቀረቡ ጉዳዮች ላይ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ለቀጠይ የፕሮጀክቱ ትግበራ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችም የተገኙበት መድረክ ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
በተለያዩ ፕሮጀክቶች ለኮሌጁ የተሰጡ የተለያዩ ግብአቶች ከትምህርትና ስልጠናው በዘለለ ለኮሌጁ ገቢ የሚፈጥሩ ስራዎች ላይ እንዲውሉ መደረጉ የሚበረታታ ነው ተባለ፡፡
የ Skill Initiative For Africa(SIFA) ፕሮጀክት የICT የልህቀት ማእከል ግንባታንና የKFW ፕሮጀክትን የሚገመግም የባለሙያዎች ቡድን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡
በግምገማና ውይይት ሂደቱ ላይ በመገኘት እንግዶቹን የተቀበሉትና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት እና የኮሌጁን የተለያዩ ስራዎችን ያስጎበኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃድ ሲሆኑ በንግግራቸውም የSIFA ፕሮጀክት እንዲሁም የKFW ፕጀክቶች ለኮሌጁ ግብአትን ከማሟላት በዘለለ ለኮሌጁ የማሰልጠን ሂደቱን በዘመናዊ ማሰልጠኛዎች መስጠት እንድንችል አድርጎናል ያሉ ሲሆን የኮሌጁ ዲን አያይዘውም በኮሌጁ የሚተገበረው የSIFA ፕሮጀክት ወጣቶቻችን የሙያና የስራ ፈጣሪ የሚያደርግ ትልቅ ፕሮጀክት ነው፡፡ በፕጀክቱ አማካኝነት በኮሌጁ የሚገነባው የልህቀት ማእከል ከተማችንን ብሎም ሃገራችንን የICT ማእከል የሚያደርጋት ነው ብለዋል፡፡በመጨረሻም በኮሌጁና በKFW መካካል ያለው ግንኙነትም በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሌጁ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡
በግምገማና ውይይቱ ሂደቱ ወቅት የSIFA እና የKFW ፕሮጀክቶች እስካሁን የደረሰበት የፕሮጀክት አፈጻጸም በአቶ መሳይ ጥላሁንና በአቶ መሃመድ አወልጠሃ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በስተመጨረሻም በኮሌጁ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋወውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱና በሪፖርቱ መሰረትም ልኡክ ቡድኑ የመሩት ዶ/ር አየለ ግዛቸው እንዳሉት ኮሌጁ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለመሆን እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው በቀጣይ በኮሌጁ ውስጥ የሚገነባው የICT ልህቀት ማእከል ሲጠናቀቅ ደግሞ ለኮሌጁ ብሎም ለከተማው እንዲሁም ለሃገሪቱ የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም በተለይ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ለኮሌጁ የተሰጡ የተለያዩ ግብአቶች ከትምህርትና ስልጠናው እንዲሁም የበቃ የሰው ሃይል ከመፍጠር በዘለለ ለኮሌጁ ገቢ የሚፈጥሩ ስራዎች ላይ እንዲውሉ መደረጉ የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡ የልህቀት ማእከሉን ግንባታ በፍጥነት ተጀምሮ እንዲያልቅ አስፈላጊውን ስራ በKFW በኩል እንደሚደረግም ገልጸዋል ፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ የሚገኙ የግልና የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የአገልግሎት አሰጣጥ ለመገምገም ያለመ ድንገተኛ ሱፐርቪዥን ተካሄደ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚረዳ የኢንስፔክሽን ስራ መስራት ሲሆን በዛሬው ዕለትም በቢሮው ም/ኃላፊ እና በቴክኒክና ሙያ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የሚመራ ቡድን በአስተዳደሩ የግልና የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ድንገተኛ ምልከታ አድርጓል።
የድንገተኛ ምልከታ ዋንኛ አላማም ነባርና አዲስ ገቢ ሰልጣኞች በየኮሌጆቹ በስልጠና ላይ መሆናቸውን በተመሳሳይ የኮሌጅ አመራርና አሰልጣኝ መምህራን በስራ ገበታቸው ተገኝተው ለዜጋው ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥና በተጨማሪ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና አፈጻጸም ዙሪያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመመልከት ሲሆን መሰል ድንገተኛ ምልከታዎች በሁሉም ኮሌጆች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ለተመረጡ አሰልጣኝ መምህራን አቅም የሚገነባ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ፤
የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች በክህሎት ከሚቀስሙት ሙያ ተሰናስሎ “ETHICS AND CIVIC RESPONSIBILITY” ስልጠና ይወስዱ ዘንድ ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ለተመረጡ ስልጠናውን የሚሰጡ አሰልጣኝ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፤
በዚህም ስልጠና አእምሮን፣ ልብን እና እጅን በተግባር ማገናኘት የሚችሉ፤ ሁለንተናዊ ብቃትን የተላበሱ የአስተሳሰብ፤ የአመለካከት እና የስነ- ምግባር ባህሪ ለውጥ የሚያመጡ አሰልጣኝ መምህራንን ለማፍራት ሰው ተኮር ልል ክህሎትን መሰረት ያደረገ የዜግነት ኃላፊነትንና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ለማላበስ በሙያ ደረጃው ውስጥ የተካተቱትን ብቃት አሃዶች እና ኮርሶችን ያካተተ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፤
በመሆኑም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶበት እየሰራ ካለባቸው የክህሎት ልማት ጉዳዮች ውስጥ ወቅቱ የሚጠይቀን ሙያዊ ስነምግባር የተላበሰ ግልፅ አላማ እና ተልእኮ ያለው ትውልድ የማፍራት በመሆኑ አሰልጣኙ ሲበቃ ብቁ ሰልጣኞችን የማፍራት እድሉ ከፍተኛ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ገልፀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
🇪🇹✈️ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ከምን ይጀምራል?
ይህ የእርሶዎም ጥያቄ ከሆነ ይህንን በጥንቃቄ ያስተውሉ!
👉ትክክለኛ መረጃ ያግኙ ℹ️
✅ህጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፣ ህጋዊ ሥምምነት የተደረገባቸው የመዳረሻ ሀገራት፣ ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዝርዝር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በቂ መረጃ ማግኘት፣
✅ስምሪቱ ከለመዱት የሥራ ባህል፣ ቋንቋ፣ ስርዓትና ወግን ጨምሮ በበርካታ ጉዳች እንግዳ ነገር ወደሚገጥምዎ ማህበረሰብ የሚያስገባዎ በመሆኑ በስነ-ልቦና እና በክህሎት ራስዎን ማዘጋጀት ይኖርብዎታል፣
👉በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ መመዝገብ 💻
✅የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ዋናው መግቢያ በር ነው፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም (https://lmis.gov.et) በስርዓቱ ላይ መመዝገብ ይኖርቦታል፣
✅ምዝገባውን በሁለት መልኩ ማከናወን ይችላሉ፡፡ በእጅ ስልክዎ ካሉበት ሆነውና ማስፈንጠሪያውን በመጠቀም በራስዎ ያለማንም የሰው እርዳታ መመዝገብ ችላሉ፡፡ አልያም አቅራቢያዎ በሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በመሄድ በባለሙያዎች እገዛ ምዝገባውን ማድረግ ይጠበቅብዎታል፣
✅ምዝገባውን እንዳጠናቀቁ በእጅ ስልክዎ በሚደርስዎ መልክት መሰረት በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የእጅ፣ የፊት እና የአይን አሻራ (የባዮሜትሪክስ) መረጃ መስጠት ይኖርብዎታል፡፡ በዚህ ወቅት የሚፈልጉት ሥራ የሀገር ውስጥ ወይም የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መሆኑን ለይቶ ማሳወቅ ያስፈልጋል፣
✅ይህን ምዝገባ እንዳጠናቀቁ ባለ ስምንት አሀዝ የሰራተኛ መለያ ቁጥር በእጅ ስልክዎ ይደርስዎታል፣
👉ሙያዊ ስልጠና መውሰድ🎓
✅በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ በቂ እውቀትና ክህሎትን ብቻ ሳሆን ለሥራው ቅልጥፍና ዘመኑ ያፈራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ተያያዥ ጉዳችን ማወቅና አጠቃቀሙንም በበቂ ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም በቂ የሙያ ስልጠና ማግኘትን ይጠይቃል፣
✅በአቅራቢያ በሚገኙ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆችና እውቅና በተሰጣቸው የግል ማሰልጠና ማዕከላት ስልጠናውን ማግኘት ይችላሉ፣
✅ስልጠናውን እንዳጠናቀቁም የሙያ ብቃት ምዘና መውሰድ ይኖርብዎታል፣
👉ህጋዊ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ጋር አስፈላጊውን ሂደት መጨረስ🤝
✅ስልጠናዎን በምዘና እንዳጠናቀቁ ሙሉ የስልጠናና የብቃት ምዘና መረጃዎ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወዳለማው የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በቀጥታ ይገባል፣
✅በሰው ሰራሽ አስተውሎት በሚታገዘው በዚህ ስርዓት ሥራ ፈላጊውን ከሠራተኛ ፈላጊው ጋር ወደሚያገናኙ ኤጀንሲዎች አውቶሜትድ በሆነ መልኩ ድልድል ይደረጋል፣
✅ በዚህም መሰረት ኤጀንሲው ለጉዞ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ያደርጋል
👉የቅድመ ጉዞ ስምሪት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና✈️
✅ይህ ስልጠና ስለሚሄዱበት ሀገር ባህል፣ ሕግ፣ ሃይማኖት፣ ስለ ሥራ ውልዎ እና ስለ መብትና ግዴታዎ የሚሰጥ ሥልጠና ነው። ይህንን ሥልጠና መውሰድዎ መብትዎን ብቻ ሳይሆን ግዴታውንም አውቀው በስነ-ልቦና ተዘጋጅተው እንዲሄዱ ያደርግዎታል፡፡
📣ማሳሰቢያ
✅የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አቋራጭ መንገድ የለውም!
✅ህጋዊ ያልሆነ የሥራ ስምሪት ላልተገባ ወጪና እንግልት ከመዳረጉም በላይ ህይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ የጨለማ መንገድ ነው!
✅ስምሪቱን የተመለከተ መረጃ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅች እና በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ መዋቅር ቢሮዎች ብቻ ያግኙ
✅ ለማንኛውም አስተያየትና ጥቆማ 9138 ነፃ የሥልክ መስመር ይጠቀሙ
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
በድሬዳዋ አስተዳደር በገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ አርሶና አርብቶ አደሮችን በተለያዩ የገቢ አማራጮች በማሳተፍ ምርትና ምርታማነታቸውን በዘላቂነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት(LLRP) ጋር በመተባበር በድሬዳዋ አስተዳደር በዋሄል ክላስተር ሀሎቡሳ ገጠር ቀበሌ ለሚገኙ አርሶና አርብቶ አደሮች 150 ያህል ፍየሎች ድጋፍ ተደርጓል።
በድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደተናገሩት በድሬዳዋ አስተዳደር በገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ አርሶና አርብቶ አደሮችን በተለያዩ የገቢ አማራጮች በማሳተፍ ምርትና ምርታማነታቸውን በዘላቂነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው መሰል የእርባታ ፍየሎች ድጋፍ በቅርቡ ለ13 ማህበራት እንደሚደረግ ገልፀዋል።
አቶ ሮቤል አክለውም በበጀት አመቱ በጥቅሉ ለ42 ኢንተርፕራይዞች መሰል ድጋፎችን ለማድረግ መታቀዱንም አስታውቀዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና፣ውሐ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢህሳም ሁሴን በበኩላቸው ፕሮጀክታቸው የገጠሩን ማህበረሰብ ከጠባቂነት በማላቀቅ ኑሮውን የሚያሻሽሉ ተግባራትን አቅዶ እየተገበረ መሆኑን ገልፀው አሁን በዋሄል ክላስተር በሀሎቡሳ ቀበሌ ለሚገኙ 3 ማህበራት 150 ያህል ፍየሎች ድጋፍ መበርከቱን ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አልዪ በበኩላቸው በአስተዳደሩ ከከተማው ባሻገር በአራቱም የገጠር ክላስተሮች የሚገኙ 15 ኢንተርፕራይዞች ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀው በዚህም ማህበረሰቡ ዘላቂ ገቢ እንዲኖረው እንደሚያስችለው አብራርተዋል።
በሀሎቡሳ ቀበሌ የሚገኙት ኢንተርፕራይዞች አባላት የሆኑትና ድጋፉ የተደረገላቸው አርሶና አርብቶ አደሮች በወቅቱ ባጋሩን ሀሳብ እንዳሉት ቢሮውና ፕሮጀክቱ ባደረጉላቸው የቤት እንስሳት ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው በዚህም ከእርሻ ስራቸው ጎንለጎን በአማራጭ ገቢ መስገኛ መሳተፋቸው ኑሯቸውን እንደሚደግፍላቸው ገልፀዋል፤ ለዚህም አመስግነዋል።
©️ DireTvአማርኛ | ታህሳስ 09 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
Repost from E-LMIS - ብቁ
🌏✈️ውጪ ሀገር/UAE የመስራት ህልም አሎት?
🚀በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት በተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል። አሁንም በዚሁ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ወደተባበሩት አረብ ኤምሬትስ/UAE/ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች የሰው ሃይል ይፈለጋል።
📌የኮንትራት ቆይታ:ሁለት አመት
📌ተፈላጊ ፃታ:ወንድ
🚧የሞያ ዘርፎች:-
1.Construction Laborers (የኮንስትራክሽን ሰራተኛ / ረዳት)
2.Mason(ግንበኛ)
3.እስቲል ፊክሰር (ፌራዩ)
4.Shuttering Carperter (አናፂ)
5. Delivery Boy (ሞተረኛ)
6. Walkers (እግረኛ ተላላኪ)
7. Plumber (የቧንቧ ሰራተኛ)
8. Electrician (የኤሌክትሪክ ሰራተኛ)
9. Scaffholders (የብረት መወጣጫ ባለሞያ)
10. Ductmen (የቬንትሌሽን ባለሞያ)
11. Supervisors and Foreman
12. Timekeepers (የሰራተኛ ሰአት ተቆጣጣሪ)
13. Camp Boss Assistant (የካምፑ አለቃ ተጠሪ)
☝️በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች ለመወዳደር https://forms.lmis.gov.et/triple-one-uae/ በመግባት ፓስፓርት፣ የሰራተኛ መለያ ቁጥር/Labor id/፣ የነዋሪነት መታወቂያ እና አስፈላጊ መረጃዎችን በማስገባት ከታህሳስ 08 እስከ ታህሳስ 14 2018 መወዳደር ይቻላል።
💰የትኬት፣ የጤና ምርመራ እና ቪዛ በአመልካቾች የሚሸፍኑ ወጪዎች መሆኑን እንገልፃለን። ሌሎች በስራ ቆይታ ላይ የሚያስፈልጉ የመኖርያ ቤት፣የማብሰያ ክፍልእና ከነማብሰያ እቃዎች፣ኢንሹራንስ እና የህክምና ወጪ በአሰሪው የሚሸፈኑ ወጪዎች ይሆናል።
በ9138 ነጻ የጥሪ ማእከል ይደውሉ።
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ከሶስተኛ ዙር ትግበራ የተሻለ አፈፃፀም እየተመዘገበ መሆኑ ተገለፀ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት በስሩ ከሚገኙ የወረዳ የአንድ ማዕከል አስተባባሪ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ' ፕሮጀክት የሦስተኛው ዙር አጠቃላይ የስራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች ትግበራ የ 5 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቷል።
በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በተለይ የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍን በማሻሻል በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
'ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ' ከመጀመሪያውና ከሁለተኛው ዙር የስራ አፈፃፀም ተሞክሮ እየተወሰደ ክፍተቶች እየተሞሉ በሦስተኛው ዙር የፕሮጀክቱ አፈፃፀሙ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩ የሁሉም ወረዳዎች የሦስተኛው ዙር 'ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ 'ፕሮጀክት የስራ ቅጥር አፈፃፀም እና አጠቃላይ የስራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች ትግበራ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
#DireTvአማርኛ | ታህሳስ 08 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ለአሰሪና ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ።
በመድረኩም ከተለያዩ የአስተዳደሩ ኢንዱስትሪዎች ለተወጣጡ አሰሪና ሰራተኞች በሁለትዮሽ ማህበራዊ ምክክር ዝርጋታ እና በአሰሪና ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
በዚህም አዋጁን በመረዳት የአሰሪውንና ሰራተኛውን ግንዛቤ ማሳደግ ዓላማው አድርጎ ከዚህ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪውን ሰላም በማረጋገጥ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚኖሩ አለመግባባቶችን በመቀነስ የስራ ክርክሮችን በምክክር መፍታት የሚያስችላቸው ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
