cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ East Gurage Zone Justice Department

+251904202912

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
522
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+87 kunlar
+1930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ከባድ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጥቷል ድርጊቱ የተከሰተው በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ ውስጥ ሲሆን ተከሳሽ አቶ ከበበው ጣሰው በቡኢ ከተማ ልዩ ስሙ ቄራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በቀን 28-08-2015 አ.ም ሟች አቶ ፈቀደ አታሎን ከኪሴ ገንዘብ አውጥተሀል በሚል ምክንያት በዱላ እና በመጥረቢያ ጭንቅላቱን ጨምሮ የተለያየ የሰውነት ክፍሉ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ አቃቢ ህግ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቶ ሲከራከር አቃቢ ህግ ምስክር አሰምቶ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱ ስለመፈፀሙ በማስረዳቱ ተከላከል ቢባልም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የመከላከል መብቱ ታልፎ በቀን 17-07-2016 በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ጥፋተኛ ብሎታል። በተከሳሽ በኩል አራት የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት በ15 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል። የእለቱ የመምሪያው መልእክት፦ ተከሳሽ ጥቂት ሴኮንዶች መረጋጋት ባለመቻሉ የሰው ህይወት አጥፍቷል ፣ የራሱን ቀሪ ህይወትም በማረምያ እንዲያሳልፍ ሆኗል። መላው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ማህበረሰብ የወንጀልን አስከፊነት በመረዳት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን ከስሜት በፀዳና ህግን ባከበረ መልኩ እንዲሆን ለማሳሰብ እንወዳለን። https://www.facebook.com/61552754727232/posts/pfbid02WMd7kTwGBmUjZUfGHeYUj1kWR5c2xokzv3APyaXiBMPMDUdUWRGaSxPmUuJQMbrjl/
Hammasini ko'rsatish...
New COM Regulations
Hammasini ko'rsatish...
የፌዴራል_ሰነዶች_ማረጋገጫና_ምዝገባ_አገልግሎት_543.pdf4.62 KB
544_የደን_ልማት_ጥበቃና_አጠቃቀም_የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት_ደንብ.pdf6.64 MB
542_ብሔራዊ_የእንስሳት_ጤና_ጥበቃ_ኢንስቲትዩት_ማቋቋሚያ_ደንብ_ማሻሻያ.pdf7.16 KB
ቀብድ እና ቅድመ ክፍያ ቀብድ (Earnest) ➡️ ቀብድ ማለት ውል ሲፈጸም የሚመለስ ወይም ከሽያጩ ገንዘብ (ከዋጋዉ) ላይ የሚታሰብ ገንዘብ ነው። ➡️ ተዋዋዮየች ቀብድ የተቀባበሉ እንደሆነ በመካከላቸው የሽያጭ ውል መኖሩን የሚያረጋግጥ ሲሆን ሻጭ ስምምነት ላይ በተደረሰዉ ዋጋ መሰረት ለመሸጥ ገዥም በዚያዉ ዋጋና የውል አፈጻጸም መሰረት ለመግዛት የጸና አቋም እንዳላው (ሁለቱም ወገኖቸ ቁርጠኛ መሆናቸዉን) የሚያረጋግጥ ነዉ፡፡  ቀብድ መሰጠቱ በማያከራክር ሁኔታ ውል መደረጉን እንደሚያረጋግጥ በፍትሀብሔር ሕጋችን በቁጥር 1883 ስር በግልጽ ተደንግጓል። ➡️ ቀብድ የመቀባበል ውጤት:- ውሉ የማይፈጸም ከሆነ የቀብዱን ገንዘብ የከፈለዉ ወገን የሰጠውን ገንዘብ ለሌላኛው ወገን በመተው ወይም በመልቀቅ ውሉን ለመሰረዝ መብት የሚያገኝበት ሲሆን ቀብድ ተቀባዩ የገንዘቡን እጥፍ በመክፈል ውሉን ለመሰረዝ መብት የሚያገኝበትን ውጤት የሚያስከትል ነዉ፡፡ ቅድመ ክፍያ ➡️ በፍትሀብሔር ሕጋችን ቅድመ ክፍያን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የለም ማለት ባይቻልም ቅድመ ክፍያ በመክፈል የተፈጸመ ዉል በሚመለከት ልክ እንደ ቀብድ ራሱን የቻለ ክፍል ተሰጥቶት የቅድመ ክፍያ ምንነትና የሚያስከትለዉን ዉጤት የሚመለከት አንቀጽ በፍትሀብሔር ሕጋችን በግልጽ አልተደነገገም፡፡ ➡️ ቅድመ ክፍያ ማለት ውል ሲፈጸም ከሽያጩ ገንዘብ (ዋጋ) ላይ የሚታሰብ ከዋጋዉ ላይ በከፊል በቅድሚያ የተከፈለ ገንዘብ ነዉ፡፡ ➡️ ቅድመ ክፍያ ከቀብድ የሚለየው ከሽያጩ ዋጋ ላይ በከፊል ቅድመ ክፍያ በመክፈል የተደረገ ውል ገንዘብ ከፋዩ(ገዥ) በውሉ መሰረት ቀሪ ገንዘብ በመክፈል ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ውል በሚሰረዝበት ጊዜ ከዋጋው ላይ በቅድሚያ የተከፈለዉን ገንዘብ እንዲያስቀር ለሻጭ የፍትሀብሔር ሕጋችን መብት አይሰጠዉም። ➡️ በመሆኑም የተከፈለዉ ገንዘብ ቅድመ ከፍያ መሆኑ ከተረጋገጠ ውል ሲሰረዝ ገንዘብ ከፋዩ ገንዘቡን መልሶ የመዉሰድ መብት ያለዉ ሲሆን ገንዘብ ተቀባዩም የተቀበለዉን ገንዘብ የመመለስ ግዳታ ይኖርበታል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
" የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቃ አዋጅ " ምን ይዟል ? የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ናቸው ፡- 1. መስከረም አንድ ቀን የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል 2. የካቲት ሃያ ሶስት ቀን የአድዋ ድል በዓል 3. ሚያዚያ ሃያ ሶስት ቀን የዓለም የሠራተኞች (የላብአደሮች) ቀን 4. ሚያዚያ ሃያ ሰባት ቀን የአርበኞች (የድል) ቀን በዓል በተጠቀሱት ብሔራዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ይሆናሉ፡፡ የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ናቸው ፡- 1. የካቲት አስራ ሁለት ቀን የሰማዕታት ቀን 2. ሕዳር ሃያ ዘጠኝ ቀን የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊነት (የብሔር ብሔረሰቦች) ቀን በተጠቀሱት ብሔራዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናሉ፡፡ የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት ናቸው ፡- 1. መስከረም አስራ ሰባት ቀን የመስቀል በዓል 2. በየአራት አመቱ የሚመጣው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ታህሳስ ሃያ ዘጠኝ ቀን የሚውለው የገና ወይም የልደት በዓል 3. ጥር አስራ አንድ ቀን የጥምቀት በዓል 4. የስቅለት በዓል 5. የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል 6. የኢድ-አልአድሃ (አረፋ) በዓል 7. የመውሊድ በዓል 8. የኢድ አልፈጥር በዓል በተጠቀሱት ኃይማኖታዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ይሆናሉ። ይህ ገና ረቂቅ አዋጅ ሲሆን ገና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አልጸደቀም። ረቂቅ አዋጁ በም/ቤት ሲጸድቅና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ነው የጸና የሚሆነው።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
የታክስ_አስተዳደራዊ_ቅጣት_አነሳስ_መመሪያ_ረቂቅ_መመሪያ.pdf4.97 KB
ሰነድ ለማረጋገጥ የሚረዳ ማብራሪያ.pdf6.11 KB
👍 2
➡ቼክ ለማስከፈል ስለሚቀርብ ክስ  💦                                                                                  ✴ አንድ ሰው በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ የጻፈ ከሆነ በወንጀል ሕግ ቁጥር 693 መሠረት በቼክ ማጭበርበር ወንጀል የሚቀጣ ሲሆን ድርጊቱ ሆን ተብሎ ወይም በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ የተፈጸመ ከሆነ ቅጣቱ ከአስር አመት የማይበልጥ እስራት ሲሆን ድርጊቱ በቸልተኝነት ከተፈጸመ ደግሞ ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት ነው፡፡ ✴ በመሆኑም ክፍያ ቼኩን የሰጠው ሰው በወንጀል የሚቀጣ ሲሆን ነገር ግን ቼክ የተሰጠው ሰው በቼኩ ላይ የተገለጸውን ገንዘብ እንዲከፈለው ለመጠየቅ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ክስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ✴ ቼክ ለማስከፈል የሚቀርብ ክስ እንደ ሌሌች መደበኛ ክሶች የመቀርብ ሳይሆን በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርአት ሕጉ መሠረት በአጭር ሥነ-ሥርአት የሚታይ ነው፡፡ ✴ ስለዚህ ቼክ ይከፈለኝ በማለት በአጭር ሥነ-ሥርአት የሚቀርብ ሰው ተከሳሹ የተለየ መከራከሪያ እስካላቀረበ ድረስ ቼኩን ባለ ሂሳቡ መጻፉ ተረጋግጦ እንዲከፈለው የሚወሰን ነው። አለኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች የማያያዝ ግዴታ እንደለበት እንደተጠበቀ ሆኖ። ✴➡ ይርጋ ✴ እንዲከፈል ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተሉት 6 (ስድስት) ወራት ውስጥ እንዲከፈል ባንክ መቅረብ እንዳለበት ህጉ ያስገድዳል። ✴ በደረቅ ቼክ ምክንያት ለፍትሐብሄር ክስ በቼክ የሚገደዱ ሰዎች ላይ ቼኩን የተቀበለው ሰው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩን ለክፍያ ባንክ ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ እስከ (6) ስድስት ወር ድረስ ነው፡፡ በመሆኑም ቼክ የተቀበለ ሰው፣ ቼክ ሰጪው ላይ የፍትሀ-ብሄር ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በ 1 (አንድ) ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ለወንጀል ክስ ግን ስድስት ወር ብቻ ነው።
Hammasini ko'rsatish...
ፍትሕ የማግኘት መብት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት ፍትሕ የማግኘት መብትን አስመልክቶ በአንቀጽ 37(1) መሠረት "ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው፡፡" በማለት ደንግጓል፡፡ ፍትሕ የማግኘት መብት ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37(1) በተጨማሪ በሌሎች የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች እና ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀቸቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ጭምር እውቅናና ጥበቃ የተሰጠው መብት ነው፡፡ ፍትሕ የማግኘት መብት በአለም አቀፍ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ሰነድ አንቀጽ 14፣ በሁሉን አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ አንቀጽ 8 እንዲሁም በሌሎች ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ስምምነቶች እውቅና የተሰጠው ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ በማብራርያ ቁጥር 13 ፍትሕ የማግኘት መብት ይዘትና አተገባበርን አስመልክቶ ሰፊ ትንተና ሰጥቷል፡፡ በማብራርያው መሠረት የሰዎች ፍትሕ የማግኘት መብት ተረጋግጧል ለማለት የሚቻለው ነጻና ገለልተኛ፣ ብቁ፣ ሁሉንም በእኩልነት የሚያይ፣ ተደራሽ የሆነ የፍትሕ አካል አንድን ጉዳይ በማቅረብ ውሳኔ ማግኘት ሲችሉ ነው፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥትም ነጻና ገልተኛ ፍ/ቤቶች እንዲቋቋሙ፣ እኩልነት እንዲሰፍን፣ የፍትሕ ተደራሽነት እንዲዳብር እና ተከራካሪ ወገኞች አለን የሚሉትን ማስረጃ የማቅረብ መብታቸው እንደሚጠይቅ ደንግጓል፡፡ ፍትሕ የማግኘት መብት ዋና ዓላማም ዜጎች በመካከላቸው የሚያጋጥማቸውን አለመግባባት በፍርድ ሊወሰን የሚችል እስከሆነ ድረስ በሕግ ስልጣን ለተሰጣቸው ውሳኔ ሰጪ አካላት በማቅረብ ውሳኔ እንዲያገኙ ለማስቻል ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብታቸውን ማስከበር የሚችሉት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ብቻ ሳይሆን በሕግ የዳኝነት ስልጣን በተሰጣቸው ተቋማት ጭምር በመቅረብ ነው፡፡ በዚህም ዜጎች በፍርድ ሊወሰኑ የሚችሉ ጉዳዮቻቸውን ለአስተዳደር ፍርድ ቤቶች፣ ለግልግል ዳኝነት ተቋማት፣ ለሃይማኖትና ባህል ፍርድ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች የዳኝነት ስልጣን ለተሰጣቸው አካላት የማቅረብ ሕገ መንግሥታዊ መብት አላቸው፡፡ በግልግል ዳኝነት፣ በባህልና ሃይማኖታዊ ፍርድ ቤቶች የመዳኘት መብት በተከራካሪዎቹ ወገኖች ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ከዚህ በፊት በሰጠው የውሳኔ ሃሳብ በሃይማኖታዊ ፍርድ ቤት ለመዳኘት ፈቃዳቸውን ባልሰጡ ተከራካሪዎች የሚሰጥ ውሳኔ ፈቃዱን ባልሰጠው ተከራካሪ ወገን ተፈጻሚነት እንደማይኖረው ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ተከራካሪ ወገኖች በፈቃደኝነት ጉዳያቸውን ከፍርድ ቤት ውጪ ባሉ የዳኝነት አካላት ለመጨረስ ሲስማሙ ፍርድ ቤቶች የተከራካሪዎቹ ፈቃድ በመጋፋት ጉዳዩን መርምረው ውሳኔ የመስጠት ስልጣን እንደማይኖራቸውም ግንዛቤ መውሰድ የሚቻል ነው፡፡ በሌላ በኩል ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸውን በግልግል ዳኝነት በፈቃደኝነት ለመጨረስ ከተስማሙ በኋላ ተዋዋይ ወገኖች የመረጡት የግልግል ዳኝነት ተቋም ህልውናው ያከተመ ከሆነ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ክርክሩን የማስቀጠል ግዴታ እንዳለባቸው ውሳኔ ከተሰጠባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው ፍትሕ የማግኘት መብት ሌላው ገጽታ ሊሆን የሚችለው ፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው አካላት አንድን ጉዳይ መርምረው ውሳኔ ወይም ፍርድ መስጠት የሚችሉት ጉዳዩ በፍርድ ሊወሰን የሚችል ጉዳይ ሲሆን ነው፡፡ በፍርድ ሊወሰኑ የማይችሉ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች ስልጣን የሚያገኙት የአስተዳደር ውሳኔዎችን በመከለስ ረገድ ነው፡፡ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ የአስተዳደር ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ውሳኔውን በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ የሚያቀርብበት አግባብ እና ምክንያቶች በስራ ላይ ባለው የአስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ በዝርዝር ተደንግጓል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር አካላት በቀን ተቀን ስራዎቻቸው ሊወስኗቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ጣልቃ ባለመግባት በአስተዳደር አካሉ እና በፍርድ ቤቶች መካከል ያለው የስልጣን ክፍፍል መርህ ያከብራሉ፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በ5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ አመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 የሚቀርበው መቃወሚያ ከዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብት ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም እንዳለበት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ለውሳኔው መነሻ የሆነው ጉዳይ አመልካቾች በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ይዞታቸውን ተጠሪ ቤት በመስራት ለ20 ዓመት እንዲጠቀምበት ውል ፈጽመዋል፡፡ አመልካቾች ተጠሪ ያልከፈላቸውን የ18 ዓመት የኪራይ ክፍያ ለማስከፈል ክስ አቅርበው፣ የጠየቁት ዳኝነት በይርጋ ቀሪ ተደርጎባቸው ነበር፡፡ በመቀጠል አመልካቾች ተጠሪ በውሉ መሠረት በይዞታው ለ20 ዓመት የተገለገሉ በመሆኑ ይዞታውን ለቀው ያስረክቡን በማለት ያቀረቡት ክስ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁ.5 ተቀባይነት የለውም ተብለዋል፡፡ ምክር ቤቱም ከዚህ በፊት በአመልካቾች የቀረበው ክስ ያልተከፈላቸው ኪራይ ለማስከፈል ሆኖ አሁን የቀረበው ክስ ይዞታቸውን ለመረከብ ሆኖ እያለ ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ ማድረጉ ተጠሪ አለአግባብ በይዞታው ላይ እንዲጠቀሙ እድል የሚሰጥና የአመልካቾች ክስ የማቅረብ መብት የሚጥስ ነው ሲል በመወሰን የአመልካቾች የመከራከር መብት እንዲከበር ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ ፅ/ቤት!!!
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በቆንጨራ በመምታት የሰው ህይወት እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጥቷል ጉዳዩ የተከሰተው በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ ሰሜን ዲዳ ቀበሌ ልዩ ስፍራው መንዲቶ ወርካ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በቀን 02-12-2012 ዓ.ም ሲሆን ሟች ከሰሜን ዲዳ ወደ ባቲ ፉጦ እየተጓዘ ባለበት ተከሳሽ ቀድሞ ከተቀጡ ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ከበቆሎ ማሳ በመውጣት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የሟች ጭንቅላትና ፊት በቆንጮራ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡ ከዚ ቀደም ግብረ አበሮቹ ተከሰው ጥፋተኛ ተብለው በተቀጡበት ክስ ተከሳሽ ድልበቶ አላሮ በመጥፋቱ ምክንያት ጉዳዩ በሌለበት ታይቶ ውሳኔ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ተከሳሹ በሌለሁበት የተወሰነው ፍርድ በድጋሚ ይታይልኝ በማለት አቤቱታ አቅርቦ ፍ/ቤቱም ተገቢነቱን መዝኖ በሌለበት የተሠጠውን ፍርድ በድጋሚ እንዲታይ አድርጓል። ክሱን እንዲያስረዱ ቀርበው የተሰሙት የአቃቢ ህግ ምስክሮች ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀሙ በማስረዳታቸው ፍርድ ቤቱ ተከላከል ብሎታል፡፡ ተከሳሽም የመከላከያ ማስረጃ አስቀርቦ ያሰማ ቢሆንም የአቃቢ ህግን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ ጥፋተኛ ብሎታል፡፡ በተከሳሽ በኩል ከቀረቡት አምስት የቅጣት ማቅለያ መካከል ሶስቱን ተቀብሎ ከነበረበት እርከን 38 ወደ እርከን 35 ዝቅ በማድረግ በቀን 12-09-2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያርማል ማህበረሰቡንም ያስተምራል ያለውን በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 3👏 1