cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

Reklama postlari
5 226
Obunachilar
-924 soatlar
-567 kunlar
-20330 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ሹመኞችን ለሚጠቁም ጉርሻ የሚያሰጥ መመሪያ ሊወጣ ነው የአዲስ አበባ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሃብታቸውን በትክክል ያላስመዘገቡ የመንግሥት ሹመኞችን ለሚጠቁም ጉርሻ መስጠት የሚያስችል መመሪያ እያወጣሁ ነው ብሏል። ኮሚሽኑ እንደገለፀው ከሆነ መመሪያው ለጠቋሚዎች ከሚገኘው ሀብት 25 በመቶ ድርሻ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው። ይህም በሃብት ምዝገባ ሂደት ላይ የሚፈጸም ሙስናን ለመከላከል አጋዥ እንደሚሆን ታምኖበታል።(Arada_Fm)
1611Loading...
02
Addis Ababa’s Vital Registration Embraces Telebirr The Addis Ababa Civil Registration & Residency Service Agency (CRRSA) is transitioning to a cashless system accepting payments only through telebirr starting next year. Read More Source: shegahq @Ethiopianbusinessdaily
2140Loading...
03
የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ለግሉ ዘርፍ የሀገር ቤት የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ በሩን ከፍቷል። የግል አየር ትራንስፖርት እንዲሰጡ የተጋበዙት ድርጅቶች እየሰጡት ካሉት የቻርተር በረራ በተጨማሪ መደበኛ የመንገደኞች እና የጭነት በረራ አገልግሎት እንዲሰጡ ነው የተፈቀደላቸው። ይህ ፍቃድ መሰጠቱ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ያሳድጋል፣ ምርትና አገልግሎትን ከ አንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ለማሸጋገር ይረዳል፣ ቱሪዝምን ያሳድጋል ያለው ባለስልጣኑ ነው። የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ከዚህ በተጨማሪም ይህ ፍቃድ መሰጠቱ የአውሮፕላን የበረራ አገልግሎት ዋጋንም ይቀንሳል ገና ብዙ ያልተነካ ዘርፍ ነው ብሏል። ሸገር በዚህ ጉዳይ የጠየቃቸው የአቢሲንያ በረራ ድርጅት ሀላፊና መስራች ካፒቴን ሰለሞን ግዛው መፈቀዱ በጎ ቢሆንም ቀድሞ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ብለዋል፡፡ ካፒቴን ሰለሞን በ ሐገር ውስጥ የአውሮፕላን ጥገና ለማድረግ አይቻልም ይህን ለማድረግ ወደ ውጭ እንበራለን ይህ ደግሞ ከፍተኛ ወጪና የሀገርም ሀብት ያባክናል ብለዋል፡፡ ባንኮች ይህ ቢዝነስ ወደ ፊት እንዲራመድ ማገዝ አይችሉም አቅምና ብቃትም የላቸውም ብለው ነግረውናል፡፡ አውሮፕላን ለመግዛትና መለዋወጫውን ለማምጣትም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ ካፒቴን ሰለሞን ይህን አገልግሎት በሀገር ውስጥ እየሰጡ የውጭ ምንዛሪውን ማካካስ የሚቻልበት መንገድ የለም ማለታቸውን አስረድተዋል፡፡ የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ይህን ፍቃድ መጀመሩ በጎ ሆኖ ሳል ጎን ለጎን መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ተብሏል፡፡ በኢትዮዽያ የግል የቻርተርና አቬዬሽን ሞያ የሚሰጡ ድርጅቶች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡(ተህቦ ንጉሴ)
2190Loading...
04
አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞችን የሚቆጣጠሩ ካሜራዎች በየወረዳዎች ሊገጠሙ ነው👏 አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞችን የሚቆጣጠሩ ካሜራዎች ዛሬ በየክፍለ ከተሞች እንደሚሰራጩ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ። ይህም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ደንበኞች ላይ እንግልት የሚፈፅሙ ሰራተኞችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል። ኤጀንሲው በ11 ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር ሲያደርግ እንደቆየና አሁን ደግሞ በ119 ወረዳዎች የካሜራ ቁጥጥር ስራ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል። ኤጀንሲው ለአራዳ ኤፍ ኤም እንደገለፀው የካሜራዎቹ ግዢ ተጠናቆ ዛሬ በየክፍለ ከተሞች ይሰራጫሉ። ይህም ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ለመፍጠር እንዲሁም ክፍለ ከተሞች የየራሳቸውን ወረዳዎች መመልከት የሚችሉበት ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚረዳ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የደንበኞችን እንግልት ይቀንሳሉ የተባሉና ምስልን እንዲሁም ንግግርን የሚቆጣጠሩት ካሜራዎች ገጠማ በሁለት ሳምንት ይጠናቀቃል ተብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ ደረጃ ያለውን የደንበኛ መጉላላት ለመቀነስ ተቋሙ መታወቂያ ሲታተምና በክፍለ ከተማ ያለውን የፅህፈት ቤት አገልግሎቶች ሂደት በካሜራ ሲቆጣጠር መቆየቱ ይታወቃል። (አራዳ ኤፍ ኤም)
1630Loading...
05
ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ደረጃ መዘጋጀቱ ተነገረ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስትም አስገዳጅነት ወደ ሀገር ቤት በብዛት እየገቡ ለሚገኙት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የደረጃ መለኪያ መስፈር መዘጋጀቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በርካታ ባለሙያዎች ወደሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወኪል አልባ ናቸዉ ከሚለዉ ጀምሮ ካለ መለኪያ መስፈርት የሚገቡ መሆናቸውን ሲናገሩ ይደመጣል። የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በምን ደረጃ ላይ መገኘት አለባቸዉ የሚለዉን የሚመዝን ደረጃ ማዘጋጀቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ሰምቷል። በተጨማሪም የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑም ተገልጿል። በሌላ በኩል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሀይል መሙያ ማዕከላት የአተገባበር መመሪያ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሀይል መሙያ ማዕከላትን መላዉ ኢትዮጵያን የሚሸፍን ለማድረግ የቅድመ አዋጭነት ጥናት መደረጉንም ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሀይል መሙያ ለመገንባት ለሚያቅዱ ባለሃብቶችም ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የፕሮጀክት እቅድ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ይፋ አድረወገዋል። በአሁኑ ወቅትም ለ 162 የኤሌክትሪክ መኪና አስመጪዎች ፈቃድ መሰጠቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ዳጉ_ጆርናል
1550Loading...
06
#ማስታወሻ " የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ? ➡️ የመኖሪያ ቤት አከራዮች #በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ መጨመር #አይችሉም። ➡️ አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪ አካል #በዓመት_አንድ_ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው። ➡️ ማንኛውም የቤት ኪራይ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ 1 ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል። ➡️ የቤት ኪራይ ውል ዘመን #ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው። ➡️ አከራዮች #ከ2_ወር_የቤቱ_ኪራይ_በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም። ➡️ የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው #የመያዝ_ግዴታ አለባቸው። ➡️ ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት። ➡️ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል #ከሁለት_ዓመት ሊያንስ አይችልም። NB. በአዋጁ መሠረት " ተቆጣጣሪው አካል ፣ ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡ More : https://t.me/tikvahethiopia/86580?single #Ethiopia #የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥርና_አስተዳደር_አዋጅ @onestopetnews
1980Loading...
07
ከዛሬ ግንቦት 28 /2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተወሰኗል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየጊዜው እየተከለሰ ሥራ ላይ እንዲውል ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ከዛሬ ግንቦት 28/2016 ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑ ተነግሯል፡፡
2150Loading...
08
የሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንትና የንግድ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። 79 አባላትን ያካተተው ልዑካን ቡድን፣ ከተለያዩ የሳዑዲ ዓረቢያ ታዋቂ ኩባንያዎች የተውጣጡ ባለሃብቶችንና የአገሪቱን ንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ያቀፈ እንደኾነ ሚንስቴሩ ገልጧል። ልዑካን ቡድኑ በሦስት ቀናት ቆይታው፣ በአዲስ አበባ በሚካሄድ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ይሳተፋል፤ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንም ይጎበኛል ተብሏል። ሚንስቴሩ፣ የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በኹለቱ አገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋትና የኹለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ እንደኾነ ገልጧል።
2180Loading...
09
በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡ በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል። ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል። ቤት አከራዮች ፦ ➡️ ህጋዊ የምዝገባ ውል ለመፈጸም ወደ ወረዳ ጽ/ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት ቤቱ የራሳቸው ስለመሆኑ ወይንም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ተከራዮች ፦ ➡️ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም ሌላ ህጋዊ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው። በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም ይችላሉ። Source: tikvahethiopia
2191Loading...
10
አዲስ አበባን ጨምሮ ክልሎች የቤት ኪራይ መመሪያ እና ደንቦችን አዘጋጀተው ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ ክልሎች እና ከተሞች አዲሱን የቤት ኪራይ መመሪያ እና ደንቦችን አዘጋጀተው ወደ ስራ መግባታቸው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ፤ አዋጁ አከራይና ተከራዩ በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህን አዋጅ ለመተግበር የአፈፃፀም መመሪያ እና ደንብ ተዘጋጀቶ ወደ ስራ መግባቱን ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ በሚቀጥለው ወር ወደ ስራ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌሎቹም ይህን ይተገብራሉ ብለዋል፡፡ አዋጁ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር በተከራይም ሆነ በአከራይ በኩል ለሚነሱ ቅሬታዎች ምላሽ የሚሰጥ ኮሜቴ የተጠቆመ ሲሆን ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡ አዋጁ በአከራይና ተከራይ መካከል ያለውን ብዥታ ግልፅ የሚያደርግ እና ሁለቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል በመሆኑ ለአተገባበሩ ሁሉም የራሱን አስተዋፅኦ አንዲያደርግ ተጠይቋል፡፡ መናኸሪያ ሬዲዮ
2770Loading...
11
ከአፍሪካ በየአመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚተመን ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ እንደሚወጣ አዲስ ሪፖርት አመለከተ ከአፍሪካ ሀገራት በየአመቱ በ10 ቢሊዮን ዶላር የሚተመን ወርቅ በህገወጥ መንገድ እንደሚወጣ እና አብዛኛው የህገወጥ ወርቅ ንግድ መዳረሻ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መሆኑን አዲስ ሪፖርት አመለከተ። መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ያደረገው ስዊስሳይድ የተሰኘው የእርዳታ እና ልማት ቡድን ባወጣው በዚህ ሪፖርት በ2022 ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወይም ከ435 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚገመት ወርቅ ከአህጉሪቱ በህገወጥ መንገድ መውጣቱ ተመላክቷል። ሪፖርቱ ከአፍሪካ የሚወጣው የህገወጥ የወርቅ ንግድ ዋና መዳረሻ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ቱርክ እና ስዊዘርላንድ መሆናቸውን ሲያመለክት የአህጉሪቱን የወርቅ ንግድ ተዋናዮች ላይ ጫና በመፍጠር የአቅርቦት ሰንሰለቶችን የበለጠ ግልፅ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል። Source: tikvahethmagazine
3020Loading...
12
ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ስራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በመንገድ ኮሪደር ልማት እና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። በዚሁ መሰረት፡- ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ መንገዶች ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የልማት ስራው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 እስከ ንጋቱ 12:30 ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።
2901Loading...
13
በቅርብ የፀደቀዉ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተገልጿል። የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባሳለፍነው ወር ያፀደቀዉን የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ረቂቅ አዋጅ ቀልጣፋና አመቺ የንግድ ከባቢ ሁኔታን ለመፍጠር የሚያስችል እንደሆነ ተናግሯል ። የወጪ ንግድ አፈጻጸምን በማሳደግ የገቢ ንግድ እቃዎችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት እቅም ለመፍጠር የሚያስችል ነዉ የተባለለት የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ ከግንቦት ወር ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን ጀምሯል ። በኢትዮጵያ እስካሁን ተግባራዊ የተደረገውን  የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሥርዓት ዲዛይን እና ትግበራ  ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሥርዓት በማሳደግ የኢኮኖሚውን መስፋፋት እና ተፅእኖ ፈጣሪነት ከፍ ለማድረግ አዋጁ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ነዉ የተገለፀው ። Capital
2510Loading...
14
#Daily_Tips THE HISTORY OF PENS by Andrew Wilson You don’t always realise how important pens are in our daily lives. Often, they’re sitting in convenient places in our houses for when we quickly scramble to find a pen and paper. They are also generally personalised with engraving or printed with company logos or branding, often a cheap plastic pen, but sometimes, a nice metal pen that can be refilled and kept. The breakthrough of pens changed lives and allowed people to be able to communicate and write for future generations. Pens have been around for thousands of years with the first pen used in 3200 BC. Have you ever wondered how we went from using a bamboo reed pen to the ballpoint pen we use today? Jump into our time machine to find out where and when the first pens were created. Read More Source: Executivepensdirect @Ethiopianbusinessdaily
2850Loading...
15
#Tigray ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት አገልግሎት መስጠት የጀመረው በመቐለ ከተማና አከባቢዋ ነው። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ አገልግሎት መስጠት ስለመጀመሩ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በ2 ምዕራፎች 16 የትግራይ ከተሞች የ4G እንዲሁም የ5G የሞባይል ዳታ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብሏል። #TikvahEthiopiaFamilyMekelle @tikvahethiopia            
2490Loading...
16
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የ 27 በመቶ የአክሲዮን ድርሻቸውን ከህግ አግባብ ዉጪ ወስዶብኛል ያሉት ግለሰብ ግዙፉን ድርጅት ከ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ክስ መስርተዉበታል ወ/ሮ ዘዉድነሽ ጌታሁን የተባሉት ከሳሽ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ልዩ ችሎት ባቀረብት ክስ ቢ.ጄ.አይ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል ማህበርን የካስቴል ግሩፕ ዋና ባለድርሻ ከሆኑት ሚስተር ካስትል ጋር በመሆን እንዲመሰረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። ካፒታል በተመለከተው በዚህ የክስ ማስረጃ ዝርዝር ላይ እንደተብራራው ግምቱ ብር 8,283,000  የቢ.ጄ.አይ.ኢትዮጵያ 27% ድርሻ ላይ የባለቤትነት ክስ እና ያልተከፋፈለ የትርፍ ክፍፍል በድርሻቸዉ ልክ እንዲከፈል እንዲወሰንላቸዉ ችሎቱን ጠይቀዋል ። ባለቤትነት ድርሻዬ በህገወጥ መንገድ ተወስዶብኛል ያሉት ወ/ሮ ዘዉድነሽ ጌታሁን የአክሲዮን ባለቤትነቴ እንዲመለስልኝ፤ ወደ ማህበር እንድመለስ እና ያልተከፈለኝ የትርፍ ድርሻ ሂሳብ ተጣርቶ በድርሻዬ ልክ እንዲከፈለኝ  በማለት ነዉ ክስ ማቅረባቸው ለማወቅ የተቻለው ። ካፒታል
2711Loading...
17
ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ እና ድሬ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎቶችን በጋራ ጀመሩ 👉ካቻ ከድሬ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ጋር በመተባበር የደሞዝ መዳረሻ እና የባጃጅ ብድር አገልግሎትም አስጀምሯል ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በአጋርነት አዲስ የዲጂታል ብድርና ቁጠባ አገልግሎቶችን የብሔራዊ ባንክ እውቅና አግኝተው አስጀምረዋል፡፡ የድሬ ማይክሮ ፋናንስ አ.ማ ቦርድ አባል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ጽጌረዳ ክፍሌ፤ እንዲህ አይነት በማይክሮፋይናንስ እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል የሚደረግ ትብብር መንግስት በ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፎች እውን ለማድረግ አቅዶ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራበት እና አበረታች ውጤት እየታየበት ያለውን ጉዞ የሚደግፍ እና የሚያሳልጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም እንዲህ አይነት ትብብሮች አነስተኛ ገቢ ያላቸውን እንዲሁም በተለመደው የባንክ አገልግሎት አሰጣጥ ከፋይናንስ አገልግሎቶች ተገልለው የነበሩ በርካታ የህብረተሰቡን ክፍሎች ተጠቃሚ ከማድረጉም ባሻገር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት ያለውን ጠቀሜታ አጉልቶ እንደሚያሳይም ተናግረዋል። (menahriaradio)
3390Loading...
18
ኢትዮጵያ እንጀራን ወደ ውጭ ሃገራት በመላክ በዓመት ከ30 እስከ 40 ሚሊየን ዶላር ገቢ ታገኛለች ተባለ። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢትዮ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል ሊካሄድ መሆኑን በዓምራች ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት የምግብ እና መጠጥ ምርምር ልማት ማዕከል የምግብ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሀብታሙ ታዬ ገልፀዋል። የፈስቲቫሉ አዘጋጆች ኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦቿን ለቱሪዝም ክፍት በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት እንደምትችል ተናግረዋል። እንደ እንጀራ እና ቆሎ ያሉ ባህላዊ ምግቦችን ጨምሮ ቅመማ ቅመሞችም ወደ ው እየተላኩ ገቢ እያስገኙ መሆኑም ተገልጿል። በመሆኑም ፌስቲቫሉ በምግብ እና መጠጥ ዘርፉ ሀገሪቱ ያላትን የቱሪዝም አቅም ለማወቅ ብሎም የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ታምኖበታል። ፌስቲቫሉ ከሰኔ 5 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በዓምራች ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት የምግብ እና መጠጥ ምርምር ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኢቨንት እንዲሁም ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው።(Arada_Fm)
3310Loading...
19
የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ በመጪዎቹ ሁለት ወራት ወደ ማምረት ይገባል የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በቀጣይ ሁለት ወራት ወደ ማምረት እንደሚገባ ተገለጸ። የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኘ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ በሀገሪቱ በሲሚንቶ ምርት፣ አቅርቦትና ግብይት ከፍተቶች ይታያሉ፡፡ ይህም ምርት እጥረት የሚፈጥረው ክፍተት በርካታ ተያያዥ ችግሮችንም የሚያስከትል ነው። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ወደ ማምረት እንደሚገባ ገልጸው፤ ይህም አሁን ያለውን የሀገሪቱን የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት እስከ 40 በመቶ የሚሸፍን እንደሚሆን ተናግረዋል። ፋብሪካው የመጀመሪያውን ምእራፍ ሲያጠናቅቅ ሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቶን፤ እንዲሁም ሁለተኛው ምእራፍ ሲጠናቀቅ አጠቃላይ በዓመት ስድስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርት መሆኑንም ገልጸዋል። (ኢ ፕ ድ)
3404Loading...
20
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሴራሊዮን ፍሪታውን ከተማ በረራ ጀመረ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፥ አየር መንገዱ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ መዳረሻውን በየጊዜው እያሰፋ ነው። በተለይም ደግሞ አየር መንገዱ የፓን አፍሪካን እሳቤ በማንገብ የአፍሪካ ሃገራትን እርስ በርስ ለማስተሳሰር እየተጋ መሆኑን ነው የገለጹት። በዛሬው እለትም በረራ የጀመረባት ፍሪታውን ከተማ ለአየር መንገዱ በአፍሪካ 64ኛ መዳረሻው መሆኗን ጠቁመዋል። ዛሬ ወደ ሴራሊዮን የተጀመረው ይህ በረራ በሳምንት 3 ጊዜ የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 136 ዓለም አቀፍና 22 የሃገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት።
3260Loading...
21
ኢትዮ ቴሌኮም ከ400 በላይ ከተሞች የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉን አስታወቀ ኢትዮ ቴሌኮም በሀገሪቱ ከ400 በላይ ከተሞች የአራተኛ ትውልድ (4 ጂ) ኤል ቲ ኢ አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉን አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም ለጣቢያችን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው 77 የሚሆኑ የሀገሪቱ ከተሞች አዲስ የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አስጀምሯል። በአጠቃላይ የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ የሀገሪቱ ከተሞች ብዛትም 417 ደርሷል ነው ያለው። በቀጣይም የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዕቅድ ይዞ እያከናወናቸው ያሉ የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከተሞች አገልግሎቱን በስፋት ተደራሽ አደርጋለሁ ብሏል። (Arada_Fm)
2970Loading...
22
EthiopiaDebt As part of the Homegrown Economic Reform Program, policymakers target enhanced macroeconomic stability and encourage private sector involvement. Major creditors include the World Bank’s International Development Association (IDA). The federal government has established the Ethiopian Investment Holding (EIH) and a Capital Market to diversify funding sources and reduce reliance on external debt. These measures, however, have not entirely alleviated the burden on the economy. Read More Source: Addisfortune @Ethiopianbusinessdaily
2730Loading...
23
በኢትዮጵያ በዘረመልና ተያያዥ ባህላዊ እውቀቶች ላይ የፈጠራ ስራ ያበረከቱ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት ማግኘት ሊጀምሩ መሆኑ ተገልጿል። የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) አባል ሀገራት እ.ኤ.አ ከሜይ 13-24 በጀኔቭ ባካሄዱት ዲፕሎማቲክ ኮንፍረንስ በአእምሯዊ ንብረት ፣ በዘረመል (Genetic) ሀብቶች እና በተዛማጅ ባህላዊ እውቀት መብት ጥበቃ ላይ የተመሰረተ አዲስ ዓለምአቀፍ ስምምነትን በተባበረ ድምፅ አጽድቀዋል፡፡ ኢትዮጵያም በድርድር ሂደቶቹ ከመሳተፍ ባሻገር ካላት ሰፊ የዘረመል ሃብቷ እና ባህላዊ እውቀቷ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያስችላትን አቋም በመያዝ የስምምነት ሰነዱን ፈርማለች። ይህ ስምምነት በጄኔቲክ ሃብት እና በተዛማጅ ማኅበረሰባዊ እውቀት ላይ ተመስርተው ለሚቀርቡ የፓተንት ማመልከቻዎች አመልካቾቹ የፈጠራዎቻቸውን የዘረመል ሀብቶች እና ተዛማጅ ማኅበረሰባዊ እውቀቶች መገኛ ምንጭ እንዲገልጹ ያስገድዳል ተብሏል። በተጨማሪም የፓተንት ሥርዓቱን ውጤታማነት ፣ ግልጽነት እና ጥራትን ለማሳደግ እንደሚረዳና በዘረመል ሀብቶች እና ተያያዥ ባህላዊ እውቀት ላይ አዲስነት ወይም ፈጠራዊ ብቃት የሌላቸው ፈጠራዎች ያለአግባብ ዕውቅና እንዳያገኙ ለመከላከልም እንሚያስችል ተጠቁሟል። Source: tikvahEthmagazine @Ethiopianbusinessdaily
2430Loading...
24
Mukesh Ambani, Asia's richest man, is making his move on the African telecoms sector, using Ghana as a springboard. Ambani has chosen the appealing Ghana market as his entrance point into Africa's enticing digital revolution. The West African country said this week that it will deliver affordable 5G mobile broadband services by the end of 2024 in partnership with Radisys Corporation, a subsidiary of Reliance Industries Limited, which is owned by Ambani. Ghana, with a population of 33 million and 24 million internet users, or 70% penetration, remains an appealing market for Radisys, a Jio Platforms firm. Jio Platforms manages Reliance Industries' telecom and digital properties. Read More Source: ITWebafrica @Ethiopianbusinessdaily
2251Loading...
25
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካመነጨው ኃይል ሽያጭ 80 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመነጨውን ኃይል ወደ ውጭ በመላክ 80 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። ገቢ የተገኘው በሁለት ተርባይኖች ከመነጨው ኃይልና ቀድሞ በተሠሩት የኃይል ማመንጫዎች መሆኑን፥ ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንጅነር አሸብር ባልቻ ተናግረዋል። ተቋሙ የግድቡን ሥራ ክፍያ በዶላር እንደሚፈፅም ነው ለአራዳ የገለጹት። ከአሁን በኋላ የግድቡን ሥራ ለማጠናቀቅ 850 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፥ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳያጋጥም ዳያስፖራው የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።   ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ሙሉ ሥራውን ሲጀምር በዓመት በአማካይ 15 ሺህ 760 ጊጋ ዋት በሰዓት ኃይል በማምረት ወደ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ያስገኛልም ነው ያሉት።   የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ከገንዘብ ባሻገር ለኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ የሀገር ምርት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አስረድተዋል። በተጨማሪም ንፁህ ኃይል በማቅረብ የካርበን ልቀትን እንደሚቀንስም አስገንዝበዋል። (Arada_Fm)
2450Loading...
26
#Ethiopia ማንኛውንም ሰው #ከሀገር_እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለህ/ ተ/ ም/ ቤት  ቀርቧል። የአዋጅ ማሻሻያው ምን ይዟል ? ማሻሻያው ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ይሰጣል። ነባሩ ህግ ምን ይላል ? " ማንኛውም ሰው #ከኢትዮጵያ_እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት #በፍርድቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው " ይላል። ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ ላይ የተቀመጠውን የፍርድ ቤትን " #ብቸኛ_ስልጣን " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት #ያጋራ ነው። ማሻሻያው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ፦ ⚫️ ከሚመለከታቸው የደህንነት አገልግሎት እና ህግ አስከባሪ አካላት ከሚያገኘው መረጃ ወይም አገልግሎቱ በራሱ ከሚያገኘው መረጃ በመነሳት ፤ ⚫️ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና ድርስ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ሲያምን፤ ማንኛውም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ ማገድ ይችላል ሲል ደንግጓል።  የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፤ " ከሀገር እንዳይወጣ ያገደውን ሰው ይዞ የሚያቆይ ከሆነ ፍ/ቤት መቅረቡን ማረጋገጥ አለበት "ም ይላል የአዋጅ ማሻሻያው።  ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፤ በነባሩ ድንጋጌ ምክንያት እየደረሰ ያለውን " ከፍተኛ ጉዳት " ለመቅረፍ እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል። አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ መሰረት " ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እስኪገኝ ድረስ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉ ሰዎች ከሀገር እየወጡ ከተጠያቂነት እያመለጡ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው " ሲል የረቂቅ አዋጁ ገልጿል። በሌላ በኩል ፦ ማሻሻያ አዋጁ " #አስተዳደራዊ_ቅጣት " አንቀጽ ይዟል። " ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገ ወጥ መንገድ በሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች እየተበራከቱ፤ በህገ ወጥ ድርጊቶች እየተሳተፉ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲል ያስረዳል። በዚህም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን " በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና " እንዳለው ተብራርቷል። #የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት በሚያወጣው ደንብ አማካኝነት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጥል በአዋጅ ማሻሻያው ስልጣን ተሰጥቶታል። " ይህን አዋጅ አሊያ በዚህ አዋጅ መሰረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያን የጣሰ ማንኛውም ሰው ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል " ይላል ማሻሻያው። Credit: #EthiopiaInisider  #JournalistTesfalemWoldeyes @tikvahethiopia
2530Loading...
27
ከወርቅ ወጪ ንግድ 274 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 274 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው የማዕድን ሚኒስቴርን የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል። የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)፥ በበጀት ዓመቱ በኩባንያዎች 2 ነጥብ 414 ቶን እንዲሁም በባህላዊ 0 ነጥብ 609 ቶን በአጠቃላይ 3 ነጥብ 023 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን ተናግረዋል። በዚህም 274 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ እንደተገኘ መናገራቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
3300Loading...
28
መልካምዜና የዘንድሮው የአፍሪካ ምርጡ የባንክ ባለሙያ- አቶ አድማሱ ታደሰ ሞሪሺየስ መቀመጫውን ያደረገው የንግድ እና ልማት ባንክ (Trade and Development Bank- TDA) ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አድማሱ ታደሰ 'Banker of the Year' ወይም 'የአፍሪካ ምርጡ የባንክ ባለሙያ' በመባል በትናንትናው እለት በናይሮቢ፣ ኬንያ በተደረገ ትልቅ ፕሮግራም ላይ ሽልማት ተቀብለዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ በዋና አዘጋጅነት በተሳተፈበት በዚህ ፕሮግራም ላይ አቶ አድማሱ ከሰባት ሌሎች እጩዎች መሀል በአንደኝነት በመመረጥ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። የባንክ ባለሙያው ከዚህ ቀደም በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በአለም አቀፍ ፋይናንስ አማካሪነት፣ በኮርፖሬት እቅድ አስተባባሪነት፣ እንዲሁም ኒውዮርክ በሚገኙ ድርጅቶች ውስጥ በፋይናንስ ተንታኝ ባለሙያነት ሰርተዋል። በአሁን ወቅት የሚመሩት TDA ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የበርካታ ቢልዮን ዶላሮች ፕሮጀክቶችን ያንቀሳቅሳል። Source: EliasMeseret @Ethiopianbusinessdaily
3261Loading...
29
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሌዥ ከተማ ከቀዳሚ የጭነት አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉ ተገለፀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት በቤልጂየም ሌዥ ከተማ ቀዳሚ ከሆኑ የጭነት አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉን ገለፀ። አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2023 ከ160 ሺህ ቶን በላይ ጭነት ከሌዥ ወደ ተለያዩ አህጉራት ማመላለሱን ተጠቁሟል። በዚህም መሠረት ወደ አፍሪካ፣ ኤስያ፣ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሀገራት በትጋት በማመላለስ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ሚና መጫወቱም ነው የተገለፀው። @tikvahEthmagazine
3260Loading...
30
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከኃላፊነት በተነሱ አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመት ሰጥቷል። በቅርቡ የባንኩ ምክትል ቺፎች፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የመምሪያ ዳይሬክተሮች ከኃላፊነት መነሳታቸው ተሰምቷል። ባንኩ በምትካቸውም አዳዲስ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሹሟል፡፡ በዚህም መሠረት፦ ✔አቶ ግርማ ፈቀደ - ቺፍ ደንበኞችና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ኦፊሰር፣ ✔አቶ ሳምሶን አምዲሳ - ቺፍ ፋይናንስና ፋሲሊቲ ኦፊሰር፣ ✔ አቶ በላይ ጎርፉ - ምክትል ቺፍ ስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ኦፊሰር፣ ✔ወይዘሮ ሐረገወይን አምሳለ - ምክትል ቺፍ ዓለም አቀፍ ባንኪንግ ኦፊሰር፣ ✔አቶ ዘውዱ ሐኪሙ - ምክትል ቺፍ ሒዩማን ካፒታል ኦፊሰር እና ✔ አቶ ነጻነት ይርጋ ምክትል ቺፍ ክሬዲት ኦፊሰር በመሆን ተሹመዋል፡፡ ''በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም አዳዲስ የሥራ ኃላፊዎች ከቀሪዎቹ ነባር የማኔጅመንት አባላት ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት የትውውቅ መድረክ አካሂደዋል፡፡ ባንኩን የተቀላቀሉት አዲሶቹ የማኔጅመንት አባላት፤ ቀድሞ ይሠሩበት ከነበረው ተቋም በተሻለ ደረጃ ለማገልገልና ባንኩ አሁን ካለበት ችግር እንዲላቀቅ በላቀ ትጋት ለማገልገል እንደተዘጋጁ አረጋግጠዋል፡፡ “ምቹና ከስጋት ነጻ ከሆነ ሥራ ላይ ወጥቶ ተግዳሮት ወዳለበት የሥራ ከባቢን መቀላቀል እጅግ ተፈላጊና መልካም አጋጣሚ እንደሆነም በትውውቅ መድረኩ ተገልጧል። ========================= Join👉https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 Subscribe👉https://bit.ly/3wNvP8H የውስጥ መስመር @wasumohammed
3513Loading...
31
ከ150 በላይ የህክምና ግብአት አምራቾች የሚሳተፉበት ሃገራዊ አውደርዕይ ሊካሄድ ነው የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የህክምና ግብዓት፣ ምርትና ኢኖቬሽን አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከ150 በላይ ከአነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የህክምና ግብዓት አምራቾች ምርቶቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። የመድሃኒት አምራቾችና አከፋፋዮች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ የከፍተኛ ትምህርትና የምርምር ተቋማትና ዘርፉን የሚደግፋ የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ። የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻ ከፍ እንዲል እና የሀገሪቱ ፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል። የፈጠራ ባለሙያዎች የተለያዩ የኢኖቬሽን ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፥ በዘርፉ እየተመረቱ ያሉ ምርቶች የድጋፍ፣ የምርምርና በዘርፉ የፓናል ውይይትም ይካሄዳል ነው የተባለው። የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና አውደርዕዩ ‘ጤናችን በምርታችን’ በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 20 ቀን ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል። አራዳ ኤፍ ኤም
2740Loading...
32
በአፍሪካ ከፍተኛ የወርቅ ተቀማጭ ያላቸው 10 ሀገራት የዋጋ ግሽበትን ተከትሎ ሀገራት በግምዣ ቤቶቻቸው ከፍተኛ የመግዛት አቅም ያለቸውን የውጭ ገንዘቦችና ወርቅ ያስቀምጣሉ። ከፍተኛ የማዕድን ክምችት እንዳላት በሚነገርላት አፍሪካ በሜትሪክ ቶን የሚመዝን ወርቅ በግምዣ ቤቶች ውስጥ ይገኛል። በግምጃ ቤት ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ያላቸውን የአፍሪካ ሀገራት ይመልከቱ፦ https://shorturl.at/0ZjMj
2440Loading...
33
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የተጋረጠባቸውን ተግዳሮቶች መፍትሔ ለመስጠት ግዙፉ የቢግ 5 ኮንስትራክሽን እድል እንዳለዉ ተመላከተ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ላይ ትኩረቱን ያደረገውን እና ቢግ 5 የተሰኘዉ ኤግዚቢሽን ከ 160 በላይ በግንባታው ላይ ያሉ አዳዲስ ምርቶችን ለገበያዉ ይዞ እንደሚወጣ ይጠበቃል ተብሏል። በኢትዮጵያ ትልቁና አለምአቀፋዊ የኮንስትራክሽን ክስተት ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ይህም ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመጨመር በሀገሪቱ ውስጥ ከሚደረጉ የልማት ፕሮጀክቶች ጎን ለጎን የሚሄድ ነዉ ተብሏል። እንደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ ከሆነ የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከ2024 እስከ 2027 በ8.9 በመቶ እንደሚያድግ ትንበያውን አስቀምጧል ። አሁን ላይ በዘርፉ ከሚስተዋሉ ተግዳሮቶች መካከል የዕዳ አሰባሰብ መዘግየት፣ የድንበር መዘጋት፣ ከፍተኛ ወለድ ያለው የባንክ ብድር ላይ ጥገኛ መሆን፣ የካፒታል እጥረት፣ የግንባታ እቃዎች ወጪን በተመለከተ የኢንዱስትሪ ደንቦች አለመኖራቸው እና የኮንትራት አስተዳደር ልምድ ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ይነገራል። ይሁን እንጂ ትኩረቱን በኮንስትራክሽን ላይ ያደረገዉ ቢግ 5 የአገር ውስጥ ግንባታና መሠረተ ልማትን መሠረት ያደረጉ ፍላጎቶችን በአዳዲስ መፍትሄዎች ለመፍታት፣ አጠቃላይ የግንባታ ኢንዱስትሪውን ከግንባታ አገልግሎት እስከ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች የሚሸፍን መሆኑ ተነግሮለታል ።(capital)
2490Loading...
34
How Ethiopia is Positioning Itself as a Competitive BPO Destination While McDonald’s doesn’t have a physical presence in Ethiopia, you might be surprised to learn some of their customer service calls are handled by an Ethiopian startup. An in-depth look into the emerging Business Process Outsourcing (BPO) sector in Ethiopia and how the country is trying to attract foreign companies seeking to outsource their operations. Read More Source: shegamedia @Ethiopianbusinessdaily
2480Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ሹመኞችን ለሚጠቁም ጉርሻ የሚያሰጥ መመሪያ ሊወጣ ነው የአዲስ አበባ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሃብታቸውን በትክክል ያላስመዘገቡ የመንግሥት ሹመኞችን ለሚጠቁም ጉርሻ መስጠት የሚያስችል መመሪያ እያወጣሁ ነው ብሏል። ኮሚሽኑ እንደገለፀው ከሆነ መመሪያው ለጠቋሚዎች ከሚገኘው ሀብት 25 በመቶ ድርሻ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው። ይህም በሃብት ምዝገባ ሂደት ላይ የሚፈጸም ሙስናን ለመከላከል አጋዥ እንደሚሆን ታምኖበታል።(Arada_Fm)
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
Addis Ababa’s Vital Registration Embraces Telebirr The Addis Ababa Civil Registration & Residency Service Agency (CRRSA) is transitioning to a cashless system accepting payments only through telebirr starting next year. Read More Source: shegahq @Ethiopianbusinessdaily
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ለግሉ ዘርፍ የሀገር ቤት የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ በሩን ከፍቷል። የግል አየር ትራንስፖርት እንዲሰጡ የተጋበዙት ድርጅቶች እየሰጡት ካሉት የቻርተር በረራ በተጨማሪ መደበኛ የመንገደኞች እና የጭነት በረራ አገልግሎት እንዲሰጡ ነው የተፈቀደላቸው። ይህ ፍቃድ መሰጠቱ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ያሳድጋል፣ ምርትና አገልግሎትን ከ አንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ለማሸጋገር ይረዳል፣ ቱሪዝምን ያሳድጋል ያለው ባለስልጣኑ ነው። የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ከዚህ በተጨማሪም ይህ ፍቃድ መሰጠቱ የአውሮፕላን የበረራ አገልግሎት ዋጋንም ይቀንሳል ገና ብዙ ያልተነካ ዘርፍ ነው ብሏል። ሸገር በዚህ ጉዳይ የጠየቃቸው የአቢሲንያ በረራ ድርጅት ሀላፊና መስራች ካፒቴን ሰለሞን ግዛው መፈቀዱ በጎ ቢሆንም ቀድሞ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ብለዋል፡፡ ካፒቴን ሰለሞን በ ሐገር ውስጥ የአውሮፕላን ጥገና ለማድረግ አይቻልም ይህን ለማድረግ ወደ ውጭ እንበራለን ይህ ደግሞ ከፍተኛ ወጪና የሀገርም ሀብት ያባክናል ብለዋል፡፡ ባንኮች ይህ ቢዝነስ ወደ ፊት እንዲራመድ ማገዝ አይችሉም አቅምና ብቃትም የላቸውም ብለው ነግረውናል፡፡ አውሮፕላን ለመግዛትና መለዋወጫውን ለማምጣትም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ ካፒቴን ሰለሞን ይህን አገልግሎት በሀገር ውስጥ እየሰጡ የውጭ ምንዛሪውን ማካካስ የሚቻልበት መንገድ የለም ማለታቸውን አስረድተዋል፡፡ የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ይህን ፍቃድ መጀመሩ በጎ ሆኖ ሳል ጎን ለጎን መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ተብሏል፡፡ በኢትዮዽያ የግል የቻርተርና አቬዬሽን ሞያ የሚሰጡ ድርጅቶች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡(ተህቦ ንጉሴ)
Hammasini ko'rsatish...
Repost from ሰሌዳ | Seleda
Photo unavailableShow in Telegram
አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞችን የሚቆጣጠሩ ካሜራዎች በየወረዳዎች ሊገጠሙ ነው👏 አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞችን የሚቆጣጠሩ ካሜራዎች ዛሬ በየክፍለ ከተሞች እንደሚሰራጩ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ። ይህም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ደንበኞች ላይ እንግልት የሚፈፅሙ ሰራተኞችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል። ኤጀንሲው በ11 ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር ሲያደርግ እንደቆየና አሁን ደግሞ በ119 ወረዳዎች የካሜራ ቁጥጥር ስራ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል። ኤጀንሲው ለአራዳ ኤፍ ኤም እንደገለፀው የካሜራዎቹ ግዢ ተጠናቆ ዛሬ በየክፍለ ከተሞች ይሰራጫሉ። ይህም ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ለመፍጠር እንዲሁም ክፍለ ከተሞች የየራሳቸውን ወረዳዎች መመልከት የሚችሉበት ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚረዳ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የደንበኞችን እንግልት ይቀንሳሉ የተባሉና ምስልን እንዲሁም ንግግርን የሚቆጣጠሩት ካሜራዎች ገጠማ በሁለት ሳምንት ይጠናቀቃል ተብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ ደረጃ ያለውን የደንበኛ መጉላላት ለመቀነስ ተቋሙ መታወቂያ ሲታተምና በክፍለ ከተማ ያለውን የፅህፈት ቤት አገልግሎቶች ሂደት በካሜራ ሲቆጣጠር መቆየቱ ይታወቃል። (አራዳ ኤፍ ኤም)
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ደረጃ መዘጋጀቱ ተነገረ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስትም አስገዳጅነት ወደ ሀገር ቤት በብዛት እየገቡ ለሚገኙት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የደረጃ መለኪያ መስፈር መዘጋጀቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። በርካታ ባለሙያዎች ወደሀገር ዉስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወኪል አልባ ናቸዉ ከሚለዉ ጀምሮ ካለ መለኪያ መስፈርት የሚገቡ መሆናቸውን ሲናገሩ ይደመጣል። የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በምን ደረጃ ላይ መገኘት አለባቸዉ የሚለዉን የሚመዝን ደረጃ ማዘጋጀቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ሰምቷል። በተጨማሪም የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑም ተገልጿል። በሌላ በኩል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሀይል መሙያ ማዕከላት የአተገባበር መመሪያ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሀይል መሙያ ማዕከላትን መላዉ ኢትዮጵያን የሚሸፍን ለማድረግ የቅድመ አዋጭነት ጥናት መደረጉንም ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሀይል መሙያ ለመገንባት ለሚያቅዱ ባለሃብቶችም ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የፕሮጀክት እቅድ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ ይፋ አድረወገዋል። በአሁኑ ወቅትም ለ 162 የኤሌክትሪክ መኪና አስመጪዎች ፈቃድ መሰጠቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ማስታወሻ " የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ? ➡️ የመኖሪያ ቤት አከራዮች #በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ መጨመር #አይችሉም። ➡️ አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪ አካል #በዓመት_አንድ_ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው። ➡️ ማንኛውም የቤት ኪራይ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ 1 ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል። ➡️ የቤት ኪራይ ውል ዘመን #ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው። ➡️ አከራዮች #ከ2_ወር_የቤቱ_ኪራይ_በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም። ➡️ የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው #የመያዝ_ግዴታ አለባቸው። ➡️ ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት። ➡️ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል #ከሁለት_ዓመት ሊያንስ አይችልም። NB. በአዋጁ መሠረት " ተቆጣጣሪው አካል ፣ ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡ More : https://t.me/tikvahethiopia/86580?single #Ethiopia #የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥርና_አስተዳደር_አዋጅ @onestopetnews
Hammasini ko'rsatish...
👍 1