uz
Feedback
ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

ሀገረ ማርያም መሰረተ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ተዋሕዶ ሰንበት ት/ት ቤት አባላት መማሪያና መልእክት መጋሪያ ብቻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ አውታር ነው።

Ko'proq ko'rsatish
957
Obunachilar
+224 soatlar
+117 kunlar
+1330 kunlar
Postlar arxiv
ዛሬ የነበረን የሰርክ መርሃግብር በምስል የተማማርንበት ትምህርት ርዕሰ ወኋ አጠጭኝ ዮሐንስ 4:7 ነገም ይቀጥላል ልደታ ለማርያም
+5
ዛሬ የነበረን የሰርክ መርሃግብር በምስል የተማማርንበት ትምህርት ርዕሰ ወኋ አጠጭኝ ዮሐንስ 4:7 ነገም ይቀጥላል ልደታ ለማርያም

ቡሌ ሆራ ሾንኮራን መስላ ዋለች 13. መልአኩም እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። 14. ደስታና ተ
+7
ቡሌ ሆራ ሾንኮራን መስላ ዋለች 13. መልአኩም እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። 14. ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። 15. በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤ 16. ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።

ታምራላችሁ እግዜር ያብዛችሁ ቤተሰቦቼ

የፈለገ ዮርዳኖስ ገጽታ
+3
የፈለገ ዮርዳኖስ ገጽታ

እየተሠራ የሚገኘው የደብራችን የግብ በር በሥዕል እና በቀለም የማስዋብ ሥራ አሁናዊ ገጽታ ለሰኔ 30 በዓለ ንግስ ሙሉ በሙሉ የሚጠናቀቅ ይሆናል ። "Hojiin fakkii fi qalamaan miidhagsuu balbala seensaa debrii (mana amantaa) keenyaa kan amma hojjetamaa jiru, ayyaana Waxabajjii 30tiif guutummaatti kan xumuramu ta'a. https://t.me/felege_yohanis

የብጹዕ አቡነ ገሪማ አስተዳደግ፣ ያሳለፋትን የሰንበት ት/ቤት ህይወት፣ የአለማዊ የትምህርት ደረጃ፣ የመንፈሳዊ ትምህርት ዝግጅት፣ ወደ ምንኩስና እንዴት እንደገቡ፣ የገዳም ህይወት ምን እንደሚመስል፣
የብጹዕ አቡነ ገሪማ አስተዳደግ፣ ያሳለፋትን የሰንበት ት/ቤት ህይወት፣ የአለማዊ የትምህርት ደረጃ፣ የመንፈሳዊ ትምህርት ዝግጅት፣ ወደ ምንኩስና እንዴት እንደገቡ፣ የገዳም ህይወት ምን እንደሚመስል፣ ለሊቀ ጵጵስና እንዴት እንደደረሱ፣ አመራረጣቸው ምን እንደሚመስል፣ በስተመጨረሻም የጵጵስና ማዕረግ የደረሱበትን ሂደት ከራሳቸው አንደበት ታደምጡት ዘንድ በሁለት ክፍል አዘጋጅተንላችኋል። ከስር የሚገኙትን ሊንኮች(ማስፈንጠሪያ) በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ። ክፍል ፩፡-https://youtu.be/AWlAAKPM0G8?si=8E_W61PL6pUTmMX6 ክፍል ፪:- https://youtu.be/530W3eU5fOI?si=o-MHbzt0cOR6GMC0

"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11 እህታችን ማኅሌት መንግስቱ የ11ኛ ክፍል ትምህርት ከክፍል
+2
"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11 እህታችን ማኅሌት መንግስቱ የ11ኛ ክፍል ትምህርት ከክፍል እንዲሁም ከsocial ተማሪዎች ሁሉም ከፍተኛ ወጤት በማምጣት ተሸላሚ ሆናለች ። እግዚአብሔር ድካምሽን ባርኮልሽ እንኳን ላማረ ውጤት አበቃሽ ። ሰንበት ትምህርት ቤት በሚገባ ለተጠቀመባት እንዲህ በመንፈሳዊ እና በሚያስፈልገን ነገር ውጤታማ እንሆንበታለን ። የእህታችን ስኬት ሌላው እና ዋና ወላጆች ናቸው አባቷ ካህን ልጅ አስተዳደግ የተረዱና የሚያስምሩ በመሆናቸው ለዚህ እንድትበቃ ምክንያት ሆኗታል ። ይህን ጽሑፍ የምናነብ ተማሪዎች ከእታችን ትጋትንና ብርታትን እንዲሁ መንፈሳዊነት ልንማር ይገባል። ወላጆች ደግሞ ከእህታችን ወላጆች ልጅ አስተዳደግ አስፈለጊ ነገር አሟልቷ ትምህርት ቤት መላክ ብቻ አለመሆኑን አውቀን ልጆቻችንን በሚገባ ክትትል እና ጥበቃ ማድረግ እና ለመልካም ውጤት ማብቃት ይጠበቅብናል ። https://t.me/felege_yohanis

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ። በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም መንገድህን ያቀናል።" ‎ኢያሱ 1፥9 ‎እህታችን ቤተልሔም ትባላለች በሰንበት ትምሀርት ቤት የ
+1
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ። በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም መንገድህን ያቀናል።" ‎ኢያሱ 1፥9 ‎እህታችን ቤተልሔም ትባላለች በሰንበት ትምሀርት ቤት የምናውቃት ለትንሽ ግዜ ነው ።ብሆንም ግን ቆም ብለን ሕይወቷን እና ጥንካሬዋን ስናይ በጣም አስተማሪ ነው። እኔ ለመጀመሪያ የማውቃት በግቢ ጉባኤ ኮርስ ለመስጠት በሄርኩ ሰዓት ነው። እናም በቃለ እግዘብሔርን በጣም ጎበዝ እንድሁም ክርስቲያናዊ ሕይወቷም መልካም ነው ። ነጋ ለኪዳን ከሰዓት ለቅዳሴ ስመሽ በሰር ክ በአገልግሎት ላይ በዝማሬ በገና በመማር ኮርስ በመማር ትታወቃለች እናም በሁለቱም መንገድ የተሳለች ለምስጥራት ቅርብ የሆነች እህታችን ለተከታታይ ለሰምንት አመታት ስትደክም ቆይታ የመውጫ ፈተና እንድሁም የሙያና ማረጋገጫ (licens ) ፈተናዎችን በምገባ በማለፍ ከቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ በመጀመሪያ ዲግር በጤና ከፍተኛ ወጤት በማምጣት የወርቅ መዳልያ ተሸላሚ ሆናለች ። እናም ለሁላችን ይጠቅመናል ብዬ የስከትሽ ምስጥሩ ምንድነው ብዬ ስጠይቃት መልሷ ይህ ነበር/ "እግዚአብሔር እና ጥረት"/ ልክ ናት እግዚአብሔር የሚባርከው ጥረታችንን ነው ።ሁላችንም እንደ እህታችን እግዚአብሔን አስቀድመን ከምስጥራት ሳንርቅ ባለንበት ስከታማ ለመሆን መጣር አለብን።እርሷን የረዳች ለሁላችን ቅርብ የሆነች እናታችን የቡሌ ሆራዋ ድንግል ማርያም ሁላችንንም ትርዳን አሜን።እናም እህቴ ዶክተር ቤተልሔም ሞላ እንኳን የተማመንሽው ፈጣርሽ ረዳሽ እንኳን ደስ አለሽ!!!!መልካም የስራ ዘመን

የተከበራችሁ የመሰረተ ተዋህዶ እንቁዎች እንዴት ቆያችሁ የእህታችን የፍጹም ሲሳይ ወንድም የሆነው አቶ ወንድማገኝ (አቢ) ሲሳይ አርፏል ስለ ሆነም የቀብር ስነ ስርዓት በቀን 20/10/2018 ከቀኑ 9 ሰዓት ስለሆነ ሁላችንም በመገናኘት እንድናስቀብር ይሁን ።ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን።