uz
Feedback
Ebenezer prayer ministry የአቤንኤዘር የፀሎት ሚኒስትሪ

Ebenezer prayer ministry የአቤንኤዘር የፀሎት ሚኒስትሪ

Kanalga Telegram’da o‘tish

+251944081068 "አቤንኤዘር" "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዪ"

Ko'proq ko'rsatish
750
Obunachilar
-224 soatlar
+17 kunlar
-130 kunlar
Postlar arxiv
🙏01320430028002  Awash nank 1000571917033 CBN lulseged kifle &/ Wakoye terfasa🙏 ለፀሎት ኮንፈራንስ የገንዘብ ድጋፍ

🙏 የአቤንኤዘር የፀሎት ሚኒስትሪ 👉 በየዕለቱ የፀሎት ጥያቄዎች እና ወደ ፀሎት ሊመራን የሚችል ለ30 ደቂቃ የሚነበብ የእግዚአብሔር ቃል ወይም ከ“ትንቢት መንፈስ” መጽሐፍ ፕሮግራም ዝርዝር ❤️ ቋሚ የፀሎት ርዕስ 👉 ስለ መንፈስ ቅዱስ መሞላት ━━━━━━━━━━━━━━━ ❤️ እሁድ – የውይይት ቀን (ጠቅላላ ጉባኤ) ❤️ ሰኞ – ቤትና ቤተሰብ 📖 የዳግም ምፃት ተጠባባቂ መጽሐፍ (Adventist Home) ❤️ ማክሰኞ – የወንጌል ሥራ 👉 በኢትዮጵያ ያለው የወንጌል ሥራ 👉 የአጠቃላይ ቤተክርስቲያን የወንጌል ሥርጭትና ግንባታ 👉 የቦርድ አባላትና ምዕመናን በሙሉ 📖 የክርስቶስ ምሳሌያዊ አስተምሮ ❤️ ረቡዕ – መንፈስ ቅዱስ 📖 ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላትና ሥራ 📖 የፈውስ አገልግሎት መጽሐፍ ❤️ ሐሙስ – ስለመንፈሳዊ መሪዎች 👉 የቤተክርስቲያን መሪዎችና ቤተሰቦቻቸው 📖 የበጎ አድራጎት መጽሐፍ ❤️ አርብ – የፀሎት ጥያቄ 👉 በቃልና በፀሎት እንድንታመን 👉 ት/ቤቶች፣ ተማሪዎችና ተቋማት 📖 ታላቁ ተጋድሎ ❤️ ቅዳሜ – የምስጋና ቀን 🙏 ለእግዚአብሔር ምስጋና እና ምስክርነት ━━━━━━━━━━━━━━━ 🔥 በግል፣ በቤታችን፣ በቤተክርስቲያን እና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በፀሎት መንፈስ እንዲበረታ እንጸልይ! 🙏 “መንፈስ ቅዱስ ሙላት የሕይወታችን መሠረት ይሁን!”

🙏የምስጋና ቀን ነው ለእኛ ዛሬ🙏 እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ። መዝሙር 30፥12

🙏 የአቤንኤዘር የፀሎት ሚኒስትሪ 👉 በየዕለቱ የፀሎት ጥያቄዎች እና ወደ ፀሎት ሊመራን የሚችል ለ30 ደቂቃ የሚነበብ የእግዚአብሔር ቃል ወይም ከ“ትንቢት መንፈስ” መጽሐፍ ፕሮግራም ዝርዝር ❤️ ቋሚ የፀሎት ርዕስ 👉 ስለ መንፈስ ቅዱስ መሞላት ━━━━━━━━━━━━━━━ ❤️ እሁድ – የውይይት ቀን (ጠቅላላ ጉባኤ) ❤️ ሰኞ – ቤትና ቤተሰብ 📖 የዳግም ምፃት ተጠባባቂ መጽሐፍ (Adventist Home) ❤️ ማክሰኞ – የወንጌል ሥራ 👉 በኢትዮጵያ ያለው የወንጌል ሥራ 👉 የአጠቃላይ ቤተክርስቲያን የወንጌል ሥርጭትና ግንባታ 👉 የቦርድ አባላትና ምዕመናን በሙሉ 📖 የክርስቶስ ምሳሌያዊ አስተምሮ ❤️ ረቡዕ – መንፈስ ቅዱስ 📖 ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላትና ሥራ 📖 የፈውስ አገልግሎት መጽሐፍ ❤️ ሐሙስ – ስለመንፈሳዊ መሪዎች 👉 የቤተክርስቲያን መሪዎችና ቤተሰቦቻቸው 📖 የበጎ አድራጎት መጽሐፍ ❤️ አርብ – የፀሎት ጥያቄ 👉 በቃልና በፀሎት እንድንታመን 👉 ት/ቤቶች፣ ተማሪዎችና ተቋማት 📖 ታላቁ ተጋድሎ ❤️ ቅዳሜ – የምስጋና ቀን 🙏 ለእግዚአብሔር ምስጋና እና ምስክርነት ━━━━━━━━━━━━━━━ 🔥 በግል፣ በቤታችን፣ በቤተክርስቲያን እና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በፀሎት መንፈስ እንዲበረታ እንጸልይ! 🙏 “መንፈስ ቅዱስ ሙላት የሕይወታችን መሠረት ይሁን!”

፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቲያን አለባበስ በዝርዝር የልብስ ዓይነት አይዘረዝርም፤ ነገር ግን መሠረታዊ መርሆዎችን ይሰጣል። 1. በጨዋነትና በትህትና መልበስ > "እንዲሁም ሴቶች በጨዋነት በልከኝነትም ራሳቸውን ያስውቡ..." 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥9 አለባበሳችን ትኩረትን ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ ራሳችን እንዳይስብ መሆን አለበት። 2. የውስጥ ውበት ከውጭ ውበት ይበልጣል > "የልብ ስውር ሰው... በየዋህነትና በጸጥታ መንፈስ..." 1ኛ ጴጥሮስ 3፥3-4 እግዚአብሔር ከልብ ባሕርይና ቅድስና የሚመጣውን ውበት ይፈልጋል። 3. ክርስቲያኖች በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን ማክበር አለባቸው > "ስለዚህ ብትበሉ ወይም ብትጠጡ ወይም ሌላ ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ።" 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥31 አለባበሳችንም እግዚአብሔርን የሚያከብር መሆን አለበት። 4. ከዓለም ፋሽን ግፊት አለመመሳሰል > "ለዚህ ዓለም አትመሰሉ..." ሮሜ 12፥2 ክርስቲያኖች ፋሽንን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል አለባቸው። 5. ልዩነትን ማክበር > "ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ..." ዘዳግም 22፥5 ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር በፈጠረው የወንድና የሴት ልዩነት ክብር እንዲኖር ያስተምራል። ማጠቃለያ የክርስቲያን አለባበስ መሆን ያለበት፦ በጨዋና የከበረ አለባበስ ትሑትና ያልተጋነነ ንጹህና የተስተካከለ እግዚአብሔርን የሚያከብር የውስጥ ቅድስናን የሚያንጸባርቅ "ሰው ውጫዊውን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል።" (1ኛ ሳሙኤል 16፥7)። ስለዚህ ክርስቲያናዊ አለባበስ የልብ ቅድስናን፣ ትህትናን እና ለእግዚአብሔር ክብር የተሰጠ ሕይወትን የሚያሳይ መሆን አለበት።

🙏 የአቤንኤዘር የፀሎት ሚኒስትሪ 👉 በየዕለቱ የፀሎት ጥያቄዎች እና ወደ ፀሎት ሊመራን የሚችል ለ30 ደቂቃ የሚነበብ የእግዚአብሔር ቃል ወይም ከ“ትንቢት መንፈስ” መጽሐፍ ፕሮግራም ዝርዝር ❤️ ቋሚ የፀሎት ርዕስ 👉 ስለ መንፈስ ቅዱስ መሞላት ━━━━━━━━━━━━━━━ ❤️ እሁድ – የውይይት ቀን (ጠቅላላ ጉባኤ) ❤️ ሰኞ – ቤትና ቤተሰብ 📖 የዳግም ምፃት ተጠባባቂ መጽሐፍ (Adventist Home) ❤️ ማክሰኞ – የወንጌል ሥራ 👉 በኢትዮጵያ ያለው የወንጌል ሥራ 👉 የአጠቃላይ ቤተክርስቲያን የወንጌል ሥርጭትና ግንባታ 👉 የቦርድ አባላትና ምዕመናን በሙሉ 📖 የክርስቶስ ምሳሌያዊ አስተምሮ ❤️ ረቡዕ – መንፈስ ቅዱስ 📖 ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላትና ሥራ 📖 የፈውስ አገልግሎት መጽሐፍ ❤️ ሐሙስ – መንፈሳዊ መሪዎች 👉 የቤተክርስቲያን መሪዎችና ቤተሰቦቻቸው 📖 የበጎ አድራጎት መጽሐፍ ❤️ አርብ – የፀሎት ጥያቄ 👉 በቃልና በፀሎት እንድንታመን 👉 ት/ቤቶች፣ ተማሪዎችና ተቋማት 📖 ታላቁ ተጋድሎ ❤️ ቅዳሜ – የምስጋና ቀን 🙏 ለእግዚአብሔር ምስጋና እና ምስክርነት ━━━━━━━━━━━━━━━ 🔥 በግል፣ በቤታችን፣ በቤተክርስቲያን እና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የፀሎት መንፈስ እንዲበረታ እንጸልይ! 🙏 “መንፈስ ቅዱስ ሙላት የሕይወታችን መሠረት ይሁን!”

🙏 የአቤንኤዘር የፀሎት ሚኒስትሪ 👉 በየዕለቱ የፀሎት ጥያቄዎች እና ወደ ፀሎት ሊመራን የሚችል ለ30 ደቂቃ የሚነበብ የእግዚአብሔር ቃል ወይም ከ“ ትንቢት መንፈስ ” መጽሐፍ ፕሮግራም ዝርዝር ❤️ ቋሚ የፀሎት ርዕስ 👉 ስለ መንፈስ ቅዱስ መሞላት ━━━━━━━━━━━━━━━ ❤️ እሁድ – የውይይት ቀን (ጠቅላላ ጉባኤ) ❤️ ሰኞ – ቤትና ቤተሰብ 📖 የዳግም ምፃት ተጠባባቂ መጽሐፍ (Adventist Home) ❤️ ማክሰኞ – የወንጌል ሥራ 👉 በኢትዮጵያ ያለው የወንጌል ሥራ 👉 የየአጠቃላ ቤተክርስቲያን የወንጌል ሥርጭትና ግንባታ 👉 የቦርድ አባላትና ምዕመናን በሙሉ የክርስቶስ ምሳሌያዊ አስተምሮ ❤️ ረቡዕ – መንፈስ ቅዱስ 📖 ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላትና ስራ 📖 የፈውስ አገልግሎት መጽሐፍ ❤️ ሐሙስ – መንፈሳዊ መሪዎች 👉 የቤተክርስቲያን መሪዎችና ቤተሰቦቻቸው 📖 የበጎ አድራጎት መጽሐፍ ❤️ አርብ – የፀሎት ጥያቄ 👉 በቃልና በፀሎት እንድንታመን 👉 ት/ቤቶች፣ ተማሪዎችና ተቋማት 📖 ታላቁ ተጋድሎ ❤️ ቅዳሜ – የምስጋና ቀን 🙏 ለእግዚአብሔር ምስጋና እና ምስክርነት ━━━━━━━━━━━━━━━ 🔥በግል፣ በቤታችን ፣ በቤተክርስቲያን እና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የፀሎት መንፈስ እንዲበረታ እንጸልይ! 🙏 “መንፈስ ቅዱስ ሙላት የሕይወታችን መሠረት ይሁን!”

Ebenezer Prayer Ministry: የእግዚአብሔር አምላካችን ለስሙ ክብር ምስጋና እናቀርባለን ይሁን ምክንያቱም እንዲህም አለ፤ “ከግብጻውያን እጅና ከፈርዖን ለታደጋችሁ፣ ከግብጻውያን እጅ ሕዝቡን ለታደገ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ በላይ ኀያል እንደ ሆነ አሁን ዐወቅሁ፤ እስራኤልን በትዕቢት ይዘው በነበሩት ሁሉ ላይ ይህን አድርጓልና።”ዘፀአት 18፥10-11 ይህ ቃል የሚያሳየን እግዚአብሔር የሚያድን፣ የሚታደግ፣ ከኀያላን እጅ ሕዝቡን የሚያወጣ ጌታ መሆኑን ነው። ይትሮ የእግዚአብሔርን ሥራ በሰማ ጊዜ ምስጋና አቀረበ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕዝቡን ከባርነት አውጥቶ በክብር አዳናቸው። ዛሬም እኛ የምናመሰግነው፦ ከኃጢአት ባርነት ስለታደገን፣ በመከራ ጊዜ ስላልተወን፣ በትዕቢተኞች ላይ ፍርዱን ስለሚያሳይ፣ ለሕዝቡ ግን ምሕረቱን ስለሚያበዛ ነው። “እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ በላይ ኀያል ነው” የሚለው መግለጫ የድል ምስክርነት ነው። የሰው ኃይል፣ የዓለም ኀይል፣ የጠላት ሴራ ሁሉ በእርሱ ፊት አይቆምም። እንግዲህ ዛሬ እንዲህ እንበል፦ > “አቤቱ ሆይ፣ ከብዙ አደጋና ከጠላት እጅ ስለታደግኸን ለስምህ ምስጋና ይሁን። ከአማልክት ሁሉ በላይ አንተ ታላቅ ነህ፤ ክብርና ምስጋና ለአንተ ብቻ ይሁን። አሜን!” አሜን! ዛሬ በእውነት የምስጋና ሰንበት ነው። ምክንያቱም፦ በሳምንቱ ሁሉ በጥበቃው ስለሸፈነን፣ በጥንቃቄው ስለጠበቀን፣ የማያስፈልገንን ክፉ ነገር ሁሉ ከእኛ ስለከለከለ፣ የሚያስፈልገንን ጸጋና ኃይል ስለሰጠን፣ በማለዳ ቃሉን ስለመገበን፣ ጸሎታችንን ስለሰማ፣ በሰላም ወደ ቅዱስ ሰንበቱ ስላደረሰን፣ ለስሙ ክብርና ምስጋና ይሁን! "ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤ ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣ ሕይወትሽን ከጥፋት ጕድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣ ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።" መዝሙር 103፥1-5 ዛሬ ልባችን በምስጋና ይሞላ፤ አፋችን ምስጋናውን ይናገር፤ ሕይወታችንም ለእርሱ ክብር ይሁን። መልካምና የተባረከ ሰንበት ይሁንልን