cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Kokebe Tsibah General Secondary School

Since 1924

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 345
Obunachilar
+724 soatlar
+377 kunlar
+19730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በየካ ክ/ከተማ ትም/ት ጽ/ቤት ስር የሚገኘዉ የኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከግንቦት 21-27/2016 ዓ.ም በተዘጋጀዉ የኢ.ብ.ሲ የንባብ ሳምንት በክ/ከተማ እና በትምህርት ቢሮ በወጣለት የጉብኝት መርሃ -ግብር መሠረት ግንቦት 26/2016 ዓ.ም በኢ.ብ.ሲ በመገኘት የመፅሐፍ አዉደ ርዕዩን እና የጊቢዉን ገፅታ ጉብኝት አድርጓል:: 👉 በጉብኝቱም ተሳታፊ አካላት የተሻለ ልምድ መቅሰማቸዉን ገልፀዋል:: 👉 ጉብኝቱን ላስተባበራችሁ እና ለተሳተፋችሁ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን:: ት/ቤቱ
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወረቀት አልባ በማድረግ የዲጂታል ጉዞውን አንድ ምዕራፍ ጀምሯል። ይሄንንም ጉዞ የተሳካ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ለተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ (URL) ከፈተናው በፊት ገብተው የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው እለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናል። ስለሆነም ከዚህ በታች በምትፈተኑበት የፈተና ክላስተር ፊትለፊት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መለማምድ ትችላላችሁ፡፡ እስካሁን username እና password ያለገኘ ተፈታኝ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች ስለተላከ፣ ከየትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ክላስተር አንድ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር፡ https://c2.exam.et ሲዳማ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et ትግራይ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et ክላስተር ሁለት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et ጋምቤላ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et አማራ ብሄራዊ ክልል፡ https://c3.exam.et ክላስተር ሶስት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et ሀረሪ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et አፋር ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 1 • አዳማ ከተማ: https://c4.exam.et • አጋሮ ከተማ: https://c4.exam.et • አምቦ ከተማ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ አርሲ: https://c4.exam.et • ምዕራብ አርሲ: https://c4.exam.et • አሰላ ከተማ: https://c4.exam.et • ባሌ: https://c4.exam.et • ባቱ ከተማ: https://c4.exam.et • ቤሾፍቱ ከተማ: https://c4.exam.et • ቦረና: https://c4.exam.et • ቡሌ ሆራ ከተማ: https://c4.exam.et • ቡኖ በደሌ: https://c4.exam.et • ዶዶላ ከተማ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ባሌ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ቦረና: https://c4.exam.et • ጉጂ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ሐረርጌ: https://c4.exam.et • ምዕራብ ሐረርጌ: https://c4.exam.et • ሆለታ ከተማ: https://c4.exam.et • ሆሮ ጉዱሩ: https://c4.exam.et • ኢሉባቦር: https://c4.exam.et ክላስተር አራት ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2 • ጅማ: https://c5.exam.et • ጅማ ከተማ: https://c5.exam.et • ቄለም ወለጋ: https://c5.exam.et • ማያ ከተማ: https://c5.exam.et • መቱ ከተማ: https://c5.exam.et • ሞጆ ከተማ: https://c5.exam.et • ሞያሌ ከተማ: https://c5.exam.et • ነጆ ከተማ: https://c5.exam.et • ነቀምት ከተማ: https://c5.exam.et • ሮቤ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et • ሰንዳፋ በኬ: https://c5.exam.et • ሻኪሶ ከተማ: https://c5.exam.et • ሻሸመኔ ከተማ: https://c5.exam.et • ሸገር ከተማ: https://c5.exam.et • ሸኖ ከተማ: https://c5.exam.et • ምስራቅ ሸዋ: https://c5.exam.et • ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ): https://c5.exam.et • ደቡብ ምዕራብ ሸዋ: https://c5.exam.et • መዕራብ ሸዋ፡ https://c5.exam.et • ምስራቅ ወለጋ፡ https://c5.exam.et • መዕራብ ወለጋ፡ https://c5.exam.et • መዕራብ ጉጂ፡ https://c5.exam.et • ወሊሶ ከተማ፡ https://c5.exam.et በተጨማሪም ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ለመፈተን ዋናው ዌብሳይት ላይ ሲገቡ ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን አጭር ትምህርታዊ ምስል በዚህ መመልከት ይችላሉ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M
Hammasini ko'rsatish...
Step by step Guide for Grade 12 Online National Exam የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና

How to take the Grade 12 Online National Exam #ethiopia #ministryofeducation #matric #enteranceexam #grade12exam

👍 6
የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎቹን በት/ቤታቸው ለማስፈተን ምን ማሟላት አለባቸው? ግንቦት 24/2016 ዓ.ም ( የትምህርት ሚኒስቴር) በዚህ አመት በኦንላይን የተዘጋጅውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ለማስፈተን ፍላጎት ያለው ማንኛዉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የተደራጀ የኮምፒዉተር ላብራቶሪ ሊኖረው ግድ ይለዋል። ይሄውም: 1. ዴስክቶፕ ወይም ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች 2. የዉስጥ ኔትዎርክ ያለዉ (የገመድ) ኔትዎርክ/Local Area Network / 3. የኢንተርኔት መስመር ከበቂ ባንድዊድዝ ጋር እንደ የመፈተኛ ኮምፒዉተር ብዛት 4. የባክ አፕ ፓዎር (ጄኔሬተር) ጋር አሟልተው መገኘትና ለትምህርት ቢሮዎች በማሳወቅ በቢሮዎች በኩል መሟላቱ ሲረጋግጥ የፈተና ማእከል በመሆን ተማሪዎቹን ማስፈተን እንደሚችሉ እያሳውቅን ለፈተና የሚዘጋጁት ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች ማሟላት ያለበቸዉ ትንሹ ስፔስፊኬሽን እንደሚከተለው ቀርቧል። 1. RAM --------------- 4GB or higher 2. Storage --------------250GB or higher 3. Processor Speed -------- 2.5GHZ or higher 4. Processors ---------- Intel Core i3 or higher 5. OS --------------- Windows 10 6. Browsers ---------------Safe Exam Browser and other 7. Accessories ---------- Keyboards and Mouse for desktop computers. ትምህርት ሚኒስቴር
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
የኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በት/ቤቶች ኦሎፒክ የመዝጊያ ፕሮግራም እንደሌሎቹ የንቅናቄ ቀናት ሁሉ በሰዓቱ ተገኝቶቷል:: 👉 ላስተባበራችሁ መምህራን እና ጥሪ ተደርጎላችሁ በሰዓቱ ተገኝታችሁ በፕሮግራሙ ለታደማችሁ መምህራን እና ተማሪዎች ምስጋና እናቀርባለን:: ት/ቤቱ
Hammasini ko'rsatish...
ቅዳሜ ግንቦት 24/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታድየም የት/ቤቶች ኦሎምፒክ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ለሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች በቀን 23/2016 ዓ.ም የክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የተሰጠዉን ኦረንኔሽን መሠረት በማድረግ ገለፃ ተደርጓል:: 👉 ተማሪዎች በተግባባነዉ መሠረት ሁሉም 12:30 ሰዓት መገኘት ይኖርባችሗል:: 👉 በሰዓት መገኘት የስልጣኔ መገለጫ ነዉ:: ት/ቤቱ
Hammasini ko'rsatish...
ለተሻለ ነገ እናንብብ በሚል መሪ ሐሳብ በ ETV አስተባባሪነት በተዘጋጀዉ የንባብ ሳምንት በየካ ክ/ከተማ ትም/ት ፅ/ቤት ስር የሚገኘዉ የኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እየተሳተፈ ይገኛል::
Hammasini ko'rsatish...
ስፓርታዊ መረጃ የየካ ክ/ከተማ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ኦሎምፒክ ተወካይ የሆነዉ የኮከበ ፅባህ አጠ/2ኛ ደ/ት/ቤት የወንዶች እግር ኳስ  ቡድን በቀን 20/9/2016 ዓ.ም በሳር ቤት ሜዳ  ከቦሌ አቻዉ ጋር ተስተካካይ ጫዎታ ለማድረግ ቀድሞ በቦታዉ ተገኝቶ ነበር::   ይሁን እንጅ   የቦሌ አቻዉ በወጣለት መርሃ - ግብር ሳይገኝ በመቅረቱ ፎርፌ አግኝቷል:: 👉ቡድኑ ከምድቡ አንደኛ ሆኖ ወደ ጥሎ ማለፋ በቀጥታ ለመግባት የሌሎች ምድብ ጫዎታዎችን ዉጤት መጠበቅ የግድ ሆኖበታል:: 👉 ቡድኑን በመምራት:በማሰልጠን እና ሌሎች ድጋፎችን እያደረጋችሁ ላላችሁ የት/ቤታችን እንቁ የጤናና ሰዉነት ማጎልመሻ/HPE/መምህራን የከበረ ምስጋናችን እናቀርባለን:: 👉 ከፍተኛ የማሸነፍ ወኔ ሰንቃችሁ እየተጫዎታችሁ ለምትገኙ ዉድ ተማሪዎቻችን ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን:: 👉 በቀጣይም መልካም ዕድል እንዲገጥማችሁ እንመኛለን::            /ቤቱ
Hammasini ko'rsatish...
👍 11 5
Photo unavailableShow in Telegram
ቀን 20/09/2016 ዓ. ም ማስታወቂያ 💥ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ 🎓 የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ከነገ እሮብ እስከ አርብ ከቀን 21-23/09/2016 ዓ. ም የሚሰጥ መሆን ይታወቃል:: ስለሆነም 👉ሁሉም ተማሪ በሰዓቱ መገናኘት 👉የፈተና ስርዓትን በአግባቡ ማክበር 👉ፈተናን ተረጋግቶ መስራት 👉አለመኮረጅ/የራስን ፈተና ብቻ መስራት/ 👉በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደፈተና መግባት 👉መምህራን የሚያቀምጡትን መመሪያ ማክበር 👉ሁሉም ተማሪ በምንም አይነት በፈተና ላይ ያልተገኘ incomplete ይደረጋል:: 👉የፈተናን ሕግ ማክበር የሁሉም ተማሪ ግዴታ ነው ✨✨መልካም ፈተና ይሁንላችሁ🎓🎓    ት/ቤቱ Follow for more ⚡️⚡️t.me/kokebetsibahexam🔑
Hammasini ko'rsatish...
👍 10
Photo unavailableShow in Telegram
ቀን 20/09/2016 ዓ. ም ማስታወቂያ ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መምህራን የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ከቀን 21-23/09/2016 ዓ. ም የሚሰጥ መሆን ይታወቃል:: ስለሆነም በወጣላችሁ የፈተና ፕሮገራም መሰረት በሰዓቱ ተገኝታችሁ እንድትፈጠኑ እናሳስባለን::     ት/ቤቱ
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 2
የየካ ክ/ከተማ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተወካይ የሆነዉ የኮከበ ፅባህ አጠ/2ኛ ደ/ት/ቤት የወንዶች እግር ኳስ ቡድን በቀን 18/9/2016 ዓ.ም በተደረገ የሁለተኛ ዙር ጫዎታ የቂርቆስ አቻዉን 4ለ2 በሆነ ዉጤት አሸነፈ:: 👉 በቀጣይ ማክሰኞ በሚደረገዉ ተስተካካይ ጫዎታም መልካም ዕድል እንዲገጥማችሁ ከወዲሁ እንመኛለን:: /ቤት
Hammasini ko'rsatish...
👍 19