cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

✞︎ቤተ ቅዱስ ሚካኤል ✞︎የትምህርት ክፍል ✞︎⛪️

✞︎✞︎✞︎በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✞︎የተለያዩ_ተከታታይ ትምህርት ✞︎ስንክሳር _የቅዱሳን _ገድል _ በየዕየለቱ አለ ✞︎ስበከት ✞︎መንፈሳዊ ጥያቄዎች በዕየለቱ አለ ✞︎የተለያዩ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎ ✞︎በዚህ ቻናል ✞︎ ይቀርብበታል።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 052
Obunachilar
+7124 soatlar
+1927 kunlar
+55430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ቅዱስ ገብርኤል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በመጽሐፈ ዳንኤል ነው። የስሙም ትርጉም "ከእግዚአብሔር የሆነ አለቃ" ማለት ነው። በእግዚአብሔር ፊት መቆም ከሚችሉ ሰባት ሊቃነ መላዕክት ውስጥም አንዱ ነው። የአምላካችን፣ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ለቅድስት ድንግል ማርያም አብሥሯል። ከሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብረኤል በገነት አበቦች መካከል የተሾመው የአምላክ ባለሙዋል ነበር [መ.ሔኖክ 10፡14]፡፡ ከእሳቱ ውስጥ የነበርው፡፡ ለአምላካቸው የሚታመኑትን የሚረዱና የሚያገለግሉ የአምላካችን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ቅዱሳን መላእክት ሁሌም ቢሆን እኛን ለመርዳት ይፈጥናሉ፡፡ በመሆኑም መላእክት ፈጣንና ሰውን ለመታደግ የሚተጉ ናቸው፡፡ "ቅዱሳን መላእክት አፈጣጠራቸው እም ኀበ አልቦ ኀበ ቦ (ካለመኖር ወደ መኖር) አምጥቶ ነው፡ ነገር ግን በግበራቸው በእሳትና በነፋስ ተመስለዋል፡፡ ይህውም እሳት ረቂቅ ነው መላእክትም እንደዚሁ ረቂቃን ናቸው፡ ነፋስ ፈጣን ነው እንደዚሁ መላእክት ፈጣን ናቸው ለተልእኮና እኛን ለመርዳት ፈጣን ናቸው" (አክሲማሮስ) መዝ. "መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዮቹን እሳት ነበልባል" ይላል በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ተፈጥሮ ሲነግረን እንዲሁም በዐዲስ ኪዳን ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ እንዲህ ይለናል፡-"ሁሉ መዳንን ይወረሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን" [ዕብራውያን 1፡14]፡፡ አምላካችን ሁላችንንም ከዚህ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ኁላችንንም ይጠብቀን፡፡ ሰውን ይረዳሉ ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/ ስግደት ይገባቸዋል ዘፍ.19፡1-2/ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12-14/ መሳ.13፡2-22/ 1ኛ ዜና 21፡1-16/ ዳን.8፡15-17 https://t.me/egzihabern_amesgnu_cher_newna
Hammasini ko'rsatish...
✞︎ቤተ ቅዱስ ሚካኤል ✞︎የትምህርት ክፍል ✞︎⛪️

✞︎✞︎✞︎በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✞︎የተለያዩ_ተከታታይ ትምህርት ✞︎ስንክሳር _የቅዱሳን _ገድል _ በየዕየለቱ አለ ✞︎ስበከት ✞︎መንፈሳዊ ጥያቄዎች በዕየለቱ አለ ✞︎የተለያዩ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎ ✞︎በዚህ ቻናል ✞︎ ይቀርብበታል።

Photo unavailableShow in Telegram
•➢ ጾመ ሐዋርያት መች ይገባል እና ዓርብ ረቡዕን የምንጾምበት ምክንያትና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል 👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
አሁኑኑ ይቀላቀሉ 📍
🎚JOIN 🔐
" ጥያቄ " ------------- ➪ ዔሳው ለወንድሙ ያዕቆብ ብኩርናውን በምን ሸጠ ?
Hammasini ko'rsatish...
ሀ. በ30 ዲናር
ለ. በ2 መክሊት
ሐ. ሀ/ እና ለ/
መ. በምስር ወጥ
Photo unavailableShow in Telegram
🕊  💖  ▬▬    †    ▬▬  💖  🕊 [ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  ❝  ባሕርዩን ሳይለቅ ሰው ሆነ !  ❞  ] 🕊 ❝ መድኃኒታችን በሥጋ ያደረገውን ተዋሕዶ አምናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ቃል በአካሉ በባሕርዩ ጸንቶ ኖሯልና ፤ ሰውን ያድሰው ዘንድ ሳይለወጥ ፤ ባሕርዩን ሳይለቅ ሰው ሆነ፡፡ ከእግዚአብሔር አብ በተወለደው በቀዳማዊ ልደቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው፡፡ ከድንግል በተወለደው በደኃራዊ ልደቱ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ [ገላ.፬፥፬] እርሱ አንዱ በመለኮት ከአብ ጋር  አንድ የሚሆን የሚተካከል ፍጹም አምላክ ነው ፤  እርሱ ብቻ ከድንግል በተወለደው ልደት በሥጋ ከሰው ጋር አንድ የሚሆን ፍጹም ሰው ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ሥጋን ይዞ እንደመጣ የሚናገር ወይም ጌታችን የተዋሐደው ሥጋ በቅድምና በመኖር ከአብ ጋር ትክክል ነው የሚል ቢኖር የተወገዘ የተለየ ይሁን፡፡ ጌታችን የተዋሐደው ሥጋ ከድንግል እንደተገኘ ከእኛም ጋር አንድ እንደሆነ የማያምን ቢኖር የተወገዘ የተለየ ይሁን፡፡ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነሥቶ ሰው ስለሆነ ስለ ጌታችን ስለ መድኃኒታችን ሥጋው ነፍስ የሌለው ነው ፣ ምትሐት ነው ወይም የማይናገር ነው የሚል ሰው ቢኖር የተወገዘ የተለየ ይሁን። ክርስቶስ በሥጋ ስለ እኛ የታመመ የሚለውን የመጽሐፍን ቃል ትቶ ደፍሮ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ያይደለ በመለኮት ታመመ የሚል ቢኖር የተወገዘ የተለየ ይሁን። ❞ [      ቅዱስ ናጣሊስ      ] ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን። †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Hammasini ko'rsatish...
ድርሳን ዘቅዱስ ገብርኤል ዘወርሃ ሰኔ https://t.me/egzihabern_amesgnu_cher_newna
Hammasini ko'rsatish...
ድርሳን_ዘቅዱስ_ገብርኤል_ዘወርሃ_ሰኔ_.mp39.12 MB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.