Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
Kanalga Telegram’da o‘tish
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite
Ko'proq ko'rsatish3 585
Obunachilar
-324 soatlar
-227 kun
-1130 kun
Postlar arxiv
Share CLAIMS IN ETHIOPIAN CONSTRUCTION INDUSTRY.pdf
+5
የብዙዎች ጥያቄ የሆነው ተሰርቶ ያለቀ ጣራ የጣራ ክዳን EGA quantity በAutocad ቀለል ባለ መልኩ እንዴት ሰርተን ማዘዝ እንዳለብን የሚያሳይ screenshot ነው።
በተለይ ለጀማሪ የሳይት መሀንዲሶች ጠቃሚ ነው።
እንበልና ተሰርቶ ሞራሌ ተመቶ ያለቀ የአንድ ቪላ የጣራ ልባስ ቆርቆሮ roof tiles ለማልበስ ፈልገን ከሆነ እንደምትመለከቱት ሁሉንም የጣራው section sketch አድርገን actual measurement ከወሰድን በኋላ የያዝነውን መረጃ በአውቶካድ በመሳል እንደምናዘው የቆርቆሮ ስፋት መከፋፈል ነው
አብዛኞቹ ፋብሪካዎች የሚያመርቱት ስፋት ሁለት አይነት ሲሆን እነዚህም ባለ90ሳ.ሜና ባለ 110ሳ.ሜ ሲሆን በፎቶ የምታዩት የተሰራው ክፍልፋይ ለባለ 90ሳ.ሜ ነው
ርዝመት እስከ ስድስት ሜትር ድረስ ወጥ ማዘዝ ይቻላል።
ምንም እንኳን ባለ 90cm ስፋት ብንጠቀምም ክፍልፋይ በ80cm የሚታየው 10cm overlap ስለሚደረግ ስናከፋፍል 10cm ተቀናሽ ተደርጎ ነው።
ባለ110cm ስፋት ማዘዝ ከፈለግን ደግሞ በ1m እናከፋፍላለን ማለት ነው።
በአሁን ሰዐት በአብዛኛው በየ40cm ርቀት ክርክር የተረገላቸው የዚህ አይነት ወጥ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች እየተመረቱ እየቀረቡ ነው።
የዚህ አይነቱ የቤት ክዳን ትልቁ ደካማ ጎኑ ብዙ ብክነት (waste) መኖሩ ነው እንደምትመለከቱት ከጣራው section ውጪ የሚታዩት በሙሉ waste ነው በአንፃሩ ለስራ ደግሞ በጣም ምቹና ቀላል ነው ለምን ቢባል በቦታ ልክ የሚታዘዝ ስለሆነ አስቀምጦ መትቶ በግራይንደር መቁረጥ ብቻ ነው።
ሌላኛው (48cm×110cm) ይመረት የነበረ ሲሆን ብዙ waste ባይኖረውም ለስራ እየቀጣጠሉ መምታት አመቺ ካለመሆኑም በላይ too many overlap ስላለው ተጨማሪ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ያስጨምራል።
@etconp
የቤቶችን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ የቤቶች ፋይናንስ ሥርዓት እንደ ሀገር ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተሰማ
የቤት ችግርን ለመቅረፍ ይቋቋማል ለተባለዉ ስርዓት ጥናት መደረጉ እና የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።
35 በመቶ በሀገሪቱ የሚገነባው የመኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበራት መገንባት አለበት ተብሏል። ይህን ለመገንባት ሁለት መሰረታዊ ችግሮች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን እነርሱም የመሬት አቅርቦት እና የፋይናንስ ችግሮች መሆናቸው ለመረዳት ተችሏል።
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ አቶ ፀጋዬ ሞሼ እንደተናገሩት አዲስ በሚወጣው የመሬት ሊዝ አዋጅ 30 በመቶ የሚሆነው መሬት ከተሞች በምደባ ከሚያቀርቡት አስገዳጅ ሆኖ ለመኖሪያ ቤት መዋል እንዳለበት እና ይህም የቤት ችግርን እንደሚቀርፍ ታስቧል።
ይህን ተከትሎ የፋይናንስ ችግርይ ለመቅረፍ " Housing Finance System" እንደሀገር ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱንና ስርዓቱን ለማቋቋም ጥናት መጠቱና የህግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸው አስረድቷል።
ከ 1999 ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ የተገነባው ቤት 62 ሺህ አይበልጥም አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ግን ባለፉት ስድስት ወራት 20 ሺህ 754 ቤቶች መገንባት መቻሉን ካፒታል ለመረዳት ችላለች።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Share Quantity Estimation practical book.pdf
🧱 New Point Bricks factory 新点砖厂 🧱 🧱Our Bricks:- Tough,Don't decay, warp or twist, resistance to water & harsh soils, don't fade....🧱The brick plant currently Produces 60,000 Bricks daily with high quality bricks with affordable price 🧱 we produce standard size brick 25*12*6 Engineering bricks and solid bricks 🧱 For more information join our telegram channel https://t.me/+d8A-rQlF5p5lZThk if you have demand contact us thank you谢谢 0912854327&0902378888
የ "Site Diary" ጥቅምና ይዘት
{The importance and Format of Site Diary}
በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል። በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል።
ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን።
ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።
ክፍል አንድ ዋና ዋና ጥቅሙ፦1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ፡ ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል። 2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦ በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው። ለምሳሌ ያህል፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል። በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው። 3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦ site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል። ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።
Share To_prepare_a_consultancy_service_plan_for_the_Entoto_to_Peacock.docx
+3
ኦቪድ ሪል ስቴት በአዲስ አበባ አቧሬ አካባቢ (ጥይት ቤት) 1 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ግንባታና ሽያጭ መጀመሩን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ ኪንግስ ታዎር ፕሮጀክት በሚል አቧሬ አካባቢ ከሚገነባቸው ቤቶች ውስጥ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 249 ዘመናዊ ቤቶችንም ለገዢዎች አስረክቧል። በዛሬው እለት ተመርቀው ለደንበኞች የተላለፉት 249 ቤቶች በ3 ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ባለ 1፣ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ክፍል ቤቶች ናቸው። የኦቪድ የጥይት ቤት ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ኖላዊ ተፈራ በዚሁ ወቅት፤ ኦቪድ ሪል ስቴት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥራት ያላቸው ቤቶችን በመገንባት በተመጣጣኝ ዋጋ ለደንበኞች ማቅረቡን ይቀጥላል ብለዋል። የህንፃዎቹ ግንባታ የተፈጥሮ አደጋን መቋቋም እንዲችል ተደርገው እንደሚሰሩም ተናግረዋል። የፕሮጀክቱ 2ኛው ዙር ግንባታ በዛሬው እለት በይፋ የተጀመረ ሲሆን በ2 ዓመታት ውስጥ ከስቱዲዮ እስከ ባለ 3 መኝታ ክፍል ቤቶችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍም ተቋሙ እንደሚሰራ ገልፀዋል። የቤቶቹ ግንባታ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በአጋርነት የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑም አክለዋል። ጊዜን መቀነስ የሚችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን በሚቀጥሉት 2 ዓመት አጠናቅቆ ለገዢዎች እንደሚያስረክብም ነው ስራ አስኪያጁ የገለፁት። በኪንግስ ታዎር የሚገነቡ መኖሪያና የንግድ ቤቶች የሽያጭ ዋጋ መረጃ ከዛሬ ጀምሮ በማንኛውም የኢቪድ የሽያጭ ቢሮ እንደሚገኝም ተገልጿል። የጥይት ቤት ኪንግስ ታዎር ፕሮጀክት ቤቶች ግንባታ በአጠቀላይ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።ከ40 በላይ እህት ኩባንያዎች ያሉት ድርጅቱ ለሁሉም ሰው በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው የቤት አቅርቦት ለማዳረስ እንደሚሰራ አስታውቋል።
ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ተገቢ ክትትል መደረግ እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ተገቢ ክትትል ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል።
ቋሚ ኮሚቴው የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በዘርፋ ጥራትን ለማስጠበቅ ቁጥጥር ማድረግና የህንጻ ደረጃዎችና ኮዶችን የሚመለከቱ መረጃዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።
የአረንጓዴ ልማት ስራዎችም ከሌሎች አገሮች ጋር ለመወዳደር በሚያስችል መልኩ ደረጃ ሊኖራቸው እና ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል ።
በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ስራው ጥሩ መሆኑን ጠቁመው የመኪና ማቆሚያ፣ የመጫኛና ማውረጃ ቦታዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።
በዘርፉ ዲጂታላይዜሽን ማጠናከር፣ጥሩ ተሞክሮዎችን ማስፋት እና የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ፣ በጀትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ለከተሞችና ለነዋሪዎች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳላቸው ገልፀዋል ።
ክብርት ሚንስትሯ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ አጠቃላይ ሽፋን 175ሺ 879 ኪ.ሜ መሆኑን ገልጸዋል ።
የፕላን ዝግጅት ስራ በሚመለከት ከዚህ በፊት ፕላን ያልነበራቸው 16 አነስተኛ ከተሞችን ፕላን እንዲኖራቸው መደረጉን ገልጸዋል ።
የከተማ መሬትና ካዳስተር ስራዎች ጋር በተያያዘ በክልልና ከተማ አስተዳደሮች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል 7ሺ ሄክታር መሬት ለማቅረብ ታቅዶ በምደባና በጫረታ ከ11ሺ ሄክታር በላይ መሬት ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።
ያለፈቃድ የተያዙ ቦታዎችን በሚመለከት ወደ 85ሺ 256 ይዞታዎች ስርአት
እንዲይዙ መደረጉን ገልጸዋል ።
የቤቶች ልማትን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ 8ሺ ቤቶች ለመገንባት ታቅዶ ወደ 20ሺ 754 ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል።
በዘርፉ ከ110ሺ በላይ ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል መፈጠሩን እና ሌሎች በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር አቅርበዋል። (ፖርላማ)
