Joseph Math Tutor
Kanalga Telegram’da o‘tish
Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/oavDFT_BLNM?si=-8fh6SmrX2jSsmC- Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580
Ko'proq ko'rsatish2 189
Obunachilar
+424 soatlar
+997 kun
+32130 kun
Postlar arxiv
2 191
+1
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና የማታ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት አሳውቋል፡፡
በዚህም፦
➫ በ2017 ዓ.ም Freshman እና በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ተማሪዎች የነበራቸሁ ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት መስከረም 05 እና 06/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ (ሪፖርት ምታደርጉበትን ካምፓስ ለማወቅ ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ፡፡)
➫ ሌሎች ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 08 እና 09/2018 ዓ.ም፤ ፕሮግራሞቹ በሚገኙበት ካምፓሶች ይካሔዳል፡፡
➫ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ የማታ (Extension) ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 15 እና 16/2018 ዓ.ም፤ ፕሮግራሞቹ በሚገኙበት ካምፓሶች ይከናወናል፡፡
➫ በሁሉም ፕሮግራሞች የግብርና ኮሌጅ፣ የእንስሳት ሀክምና፣ የስነ-ምድር እና የአደጋ መከላከል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት በዘንዘልማ ካምፓስ መሆኑ ተገልጿል፡፡
🔔 በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል፡፡
@Joseph_maths_tutorial
2 191
+1
#JigjigaUniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ነባር ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 08 እና 09/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የነበራችሁና ያለፋችሁ እንዲሁም 1ኛ ዓመት 2ኛ አጋማሽ ነባር ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 05 እና 06/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የትምህርት ሰነዶች (ከ8ኛ-12ኛ ክፍል) ዋናውና ኮፒው፣
➫ የቅርብ ጊዜ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ (8)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።
@Joseph_maths_tutorial
2 191
#UniversityOfGondar
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ ገቢ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።
በዚህም የሁሉም ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 05 እና 06/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
በትምህርት ሚኒስቴር የሚመደቡ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በጎንደር የኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት መስከረም 07 እና 08/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)
@Joseph_maths_tutorial
2 191
ዉጤት ሲገለፅ በቀላሉ የምታዩባቸው መንገዶች !!!
1. eaes.et
2. eaes.gov.et
3. eaes.edu.et
4. result.neaea.gov.et
5. SMS 6284
6.https://t.me/EAESbot
Share our channel 👇🏿👇🏿👇🏿
@Joseph_maths_tutorial
2 191
የ12ኛ ክፍል ውጤት ሊለቀቅ 4 ቀናት ብቻ ቀርቶታል‼️
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል ።
ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ተማሪዎችን መቀበል ይጀመራሉ
ውጤት ይፋ ሊደረግ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቶታል።
2 191
#ArbaminchUniversity
የጥሪ ማስታወቂያ!!
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ እና ኢ-መደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች የ2018 ትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ እሁድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሰኞ እና ማክሰኞ መስከረም 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም፣ እና ትምህርት መጀመሪያ ረቡዕ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
የ2018 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ አመት (አዲስ) ተማሪዎች፣ እንዲሁም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያጠናቀቁና የትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች መግቢያ ከትምህርት ሚኒስቴር የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መረጃ እንደደረሰን ወድያውኑ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
በ2017 ትምህርት ዘመን 1ኛ ዓመት ትምህርት አጠናቀው ትምህርት ክፍል ምደባ ያላገኙ ተማሪዎች ትምህርት ክፍል ምርጫ ሰኞ መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ ምደባ የሚፈጸመው ማክሰኞ መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ ውጤት የሚገለጸው ረቡዕ መስከረም 07 ቀን 2017 ዓ.ም. ይሆናል፡፡
ሁሉም የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ከምዝገባ በፊት በኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ክፍል አስተባባሪነት የሚሰጠውን የ e-SHE SSS ሥልጠና በማጠናቀቅ ቢያንስ አንድ (1) ሰርተፊኬት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
JOIN: @Joseph_math_tutorial
--------------------------------------------
2 191
#JinkaUniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም አዲስ እና ነባር የመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።
የመደበኛ ፕሮግራም ነባር ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በሪሚዲያል እና በፍሬሽማን ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች፤ የ2018 ዓ.ም ምዝገባ መስከረም 05 እና 06/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የ2018 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመረው መስከረም 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል፡፡
በሪሚዲያል እና ፍሬሽማን ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ እና ብርድ ልብስ እንዲሁም ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉትን የትምህርት ማስረጃ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
#share
#share
JOIN: @Joseph_maths_tutorial
-------------------------------------------
2 191
#DireDawaUniversity
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።
➫ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን መስከረም 10/2018 ዓ.ም፣
➫ የምዝገባ ቀን መስከረም 12 እና 13/2018 ዓ.ም፣
➫ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ይህ ጥሪ አይመለከታችሁም። በተመሳሳይ Withdraw ያደረጋችሁ ወይም Readmission ተማሪዎችን አይመለከትም ተብሏል።
#share
#share
JOIN: @Joseph_maths_tutorial
-------------------------------------------
2 191
+1
#HawassaUniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ፣ የማታ እና የእረፍት ቀናት ፕሮግራም ነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።
በዚህም የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገባ፦
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ፕሮግራም እና የሁሉም የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች መስከረም ዐ8-09/2018 ዓ.ም
➫ የማታ እና የእረፍት ቀናት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች፦ ከመስከረም ዐ8-10/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
የ2ኛ ዓመት መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ በየተመደባችሁበት ካምፓስ ይከናወናል ተብሏል።
@joseph_math_tutor
2 191
የጥሪ ማስታወቂያ
#Assosa_university
#share
#share
JOIN: የጥሪ ማስታወቂያ
#Assosa_university
#share
#share
JOIN: የጥሪ ማስታወቂያ
#Assosa_university
#share
#share
JOIN: @joseph_math_tutor
2 191
+1
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲሄዱ ገቢዎች ሚኒስቴር አሳሰበ።
የገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ክፍያ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ የወጪ መጋራት ተጠቃሚ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማውጣት እንዳለበት አስታውሷል።
ሚኒስቴሩ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ በአካባቢያቸው በሚገኝ ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት (ገቢዎች) ወይም ቢሮ በመቅረብ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እንዲያወጡ ማሳሰቡን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚገቡበት ወቅት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲቀርቡ አስገንዝቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
