cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አርቶፊያ (ARTOPHIA) ✍

ጥበብ ባህር ነው ነፍስን ያለመልማል። ገጣሚያን ቃላቶቻቸውን ሰዓሊያን ብሩሽ እና ቀለማቸውን ጸሐፍት ብዕራቸውን ፤ ሁሉም ወደ ባህሩ ይጓዛል ከባህሩም ይረካል ። ባህሩ ግን አይጎድልም ፣ ቃላቶችም ፣ ቀለማትም አይነጥፉም ፣ አይወይቡም!!!

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
396
Obunachilar
+124 soatlar
+17 kunlar
+430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ባልተመቸ ጊዜ ባልተመቸ ቦታ፤ የክረምት ጸሐይ የሌሊት ብልጭታ፤ ከመቅጽበት ታይታ፤ ለዛ ባለው ውበት፤ በሕፃን ፈገግታ፤ እንዲያው በቀስታ፤ እንዲያው በቸልታ፤ በማታውቀው ኃይልዋ፤ ልቤ ውስጥ ገብታ፤ ያረፈች፣ የተኛች፣ ድብቅ ነፍስ ነክታ፤ አንቀሳቀሰችኝ ነቃሁኝ ላንድ አፍታ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Repost from ኑ እናንብብ
Photo unavailableShow in Telegram
" ያ ደግ ሰው በመንገዱ እየኼደ ሳለ ሽፍታ አገኘ፡፡ ያ ደግ ሰው፤ “ሰላም ለአንተ ይኹን! በዚህ ስፍራ ለምን ብቻህን ትዘዋወራለህ?” አለው። ያ ሽፍታም፡ “እኔ ሽፍታ ነኝ! ለዚህም ነው በዚህ ሰዋራ ስፍራ የምዘዋወረው:: ይልቅ ምን ይዘሃል? ወዲህ በል የያዝኸውን ኹላ! አምጣው!” አለው። ያ ደግ ሰው፡ “ለምን ግን ሠርተህ አትበላም? ሰው የደከመበት ገንዘብ ላንተ ምን ያደርግልሃል?" አለው፡፡ ያ ሽፍታ እየሣቀ፡ “ስማ! ማር በልተህ ታውቃለህ?" አለው:: ያ ደግ ሰው፡ “እንዴታ! በደንብ አድርጌ ነዋ የምበላው!" አለው:: ያ ሽፍታ፡ “ሠርተህ ነው ወይስ ከንብ ቀምተህ ነው? በጭስ እያስፈራራህ፣ እንዳትታይ በጭንብል እየተከለልህ ነው ንብ ለፍታ የሠራችውን የምትቀማት” አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፤ ኹሉም ስው “ለፋኹበት” በሚለው ጕዳይ ወስጥ መዝረፍ እንዳለበት ዐወቀ። ከዚያም፣ ለሽፍታው “ብዙ ገንዘብ የለኝም:: ምናልባት ይህቺ ኹለት ፈረንካ ከበቃችህ እንካ” አለው፡፡ ያ ሽፍታ፡ “ለዛሬው ምሬሃለኹ፣ ከዚህ በኋላ ግን በማያገባህ ጕዳይ አትግባ" አለው፡፡ ያ ደግ ሰው፡ “እንኳን ማርኸኝ እንጂ በል ደኅና ሰንብት" ብሎት ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ፡፡ በመንገዱም ላይ ሳለ እንዲህ እያለ እያሰበ ነበር፡፡ “አኹን ግን የእውነት እንቁላልን ዶሮ የምትሸጠው ቢኾን ዋጋው ስንት ይኾን ነበር? ሰው ከዕቅፏ ፈልቅቆ ይወስድባታል እንጂ መቼ ይጠይቃታል። እና፣ ከደምና ከዐጥንቴ ያልሠራኹትን ገንዘብ ሽፍታ ወስዶብኝ እንዲህ ከተንገበገብኹ ልጅ ይኾነኛል ያልኹትን፣ ከብቤ ያኖርኹትን ቢያነሡብኝ ቀድሜ አበድኹኝ” እያለ ኑሮውን እየታዘበ ኼደ፡፡ " " ግርባብ ያ ደግ ሰው " በፍቃዱ አየልኝ መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል :: @jafbok
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ድም ሲል ከበሮ ልቤም እያለ ደጅሽን ስር ለማደር ጥሎኝ ኮበለለ "እናቴም ተጣራች ወዴት አለ ልጄ    በቅዳሴው ጊዜ አጣሁት ከደጄ"       ምትይ ይመስለኛል       በቁም ያቃዠኛል    አለሁኝ እናቴ ከቤትሽ እርቄ እንከራተታለሁ መመለሻ ቀኔን እኔ ምን አውቄ       ይኸውልሽ በአትዬ የከበሮ ድምፁ ዛሬም ይሰማኛል ደውልሽ እየመጣ ይቀሰቅሰኛል ከቅኔ ማህሌት መልክሽን ሲያድሉ    በጣዕመ ዜማ ሀሌ ሉያ ሲሉ ካህናት በአንድ ሆነው ከቤተመቅደሱ ይኸው ይሰማኛል ኪዳኑን ሲያደርሱ ዕጣኑ እንኳን ሽታው እዚህ ድረስ መቶ      ይረባብሸኛል ውስጥ አንጀቴ ቀርቶ                            እባክሽ በአትዬ ይሄንን እያለምኩ እንዲህ ከምባክን    ፍቀጅልኝና ልሳለም ደጅሽን ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️ቤ              3🙏🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
ድንቅ መንፈሳዊ ግጥም ❤️ በዕሌኒ እና በዓደን ..... @smetoch12 @smetoch12
Hammasini ko'rsatish...
3
እንኳን መጣህልኝመጣህልኝ.... ፧ ፧ ለምን ሄድክ አልልም፤ እንዲህ አደረገኝ ብየም አልወቅስህም፤ እንኳን መጣህልኝ፤ እንካንም አወከኝ፤ እንኳንም አቀፍከኝ፤ አንኳንም ዳበስከኝ። በቅንጭብጭቡ ትርክት፤ በደራሲያ መፀሀፍት፤ ፍቅርን ላወቀችው ፍቅርን ላጠናችው፤ ለእደእኔ አይነቷ ሴት፤ መምጣት ሀሴት ናት። ተለያዩ እያለ ሀገሬው ተረተ፤ ፊደል ያወኩ ባንተ፤ ፍቅርን ያየሁ ባንተ፤ ጣት አየጨበጠ ቃል ያስደረደረ፤ አድስ ማንነትን ሰብኮ የፈጠረ፤ መጥፌየን ከጥሩ ለይቶ የሳየኝ፤ የህይወቴን ቅመም ትዝታ የሰጠኝ፤ የልብህ ብራና ቢሰርዘኝ እንኳን። የመውደድ ልኩ፤ የመኖሬ መልኩ፤ ፍቅርህ ዘላለሜ፤ መኖርህ አለሜ። የትም ሁን ግደለም፤ ብትሄድም ብትቀርም፤ ቃሌን እኔ አላጥፍም፤ ያዳም ዘር ቢሞላም፤ እመነኝ መውደድ፤ ካንተ ሌላ አላቅፍም። ✍️ዕሌኒ @eluuu2112 @arthopia @smetoch12
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
“ይኸውልህ... ማንበብ እኮ ለአንዳንዱ እጣው ነው። ለኔ በጣም ደስ ብሎኛል። እንኳን ማንበብ ተማርኩ። እንኳን እግዜር ፊደል ሰጠን እላለሁ። ግን ሳያነቡ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ፥ ከኔ የበለጠ ሀብታም ኑሮ ነው የሚኖሩት። ፀጋ ውስጥ ነው ያሉት። እኛኮ ወሬዎች... ምናምኖች... ግጥሞች... ስላቆች... እንዲ እናውቃለን እንጂ፥ ህይወትን የሚያውቃት እኮ ታጥቆ የሚገባባት ነው። እኛኮ ትንሽ እንደመሸሽ ብለን፥ በቃላት ተሸሽገን ምናምን ነው ምንታየው።” ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
Hammasini ko'rsatish...
👍 4😁 4
“A happy ending cannot come in the middle of the story”
Hammasini ko'rsatish...
2👍 1
ገጣሚ አታፍቅሪ         ገጣሚ ከሴት መተኛት ምንም ስሜት አይሰጠው ለእርሱ ከቃል ነው እንጂ ከሴት ፍቅር አይዘው እርሱ                 ስለዚህ አፈቀርኩሽ ወደድኩሽ ብሎ ቢያወራልሽ ከሺህ ቃላት ወስዶ እንድ ቃል ቢነግርሽ እንዳትሰሚው እርሱን እንዳታደንቂ ቃላት አጠቃቀሙን        ምክንያቱም ላንቺ ቃል እምነት ነው ላንቺ ቃል ፍቅር ነው ላንቺ ቃል ተስፋ ነው                ግን ቃል ለእርሱ ቀላል ነው በቃ ዝም ብሎ ፊደል መመስረት ነው       ገጣሚ ስንታየው ታገሰ
Hammasini ko'rsatish...
👍 5👏 2
“What a terrible era in which idiots govern the blind.” - Julius Caesar
Hammasini ko'rsatish...
2