Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል
Kanalga Telegram’da o‘tish
💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2
Ko'proq ko'rsatish1 862
Obunachilar
-224 soatlar
-167 kun
-6030 kun
Postlar arxiv
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ብዙ ማስታወሻ የሚወስዱ አፕሊኬሽኖች አሉ ነገርግን ብዙ ሰዎች እንደ Google Keep፣ Evernote ወይም Microsoft OneNote ባሉ ትልልቅ ስሞች ላይ ይሳቡ ይሆናል።
አዲስ ነገር ለመሞከር ከፈለጉ፣ WeNoteን ይመልከቱ።
ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ የእርስዎ ማስታወሻዎች፣ የተግባር ዝርዝሮች፣ አስታዋሾች ወዘተ መተግበሪያ ነው፣ ነገር ግን እንደ አዶ ለማስታወሻዎች ማበጀት፣ የይለፍ ቃሎች ጀርባ ማስታወሻዎችን መቆለፍ፣ ማስታወሻዎችን በሁኔታ አሞሌዎ ላይ መጣበቅ እና ሌሎች ብዙ ባህሪያትን የያዘ መተግበሪያ ነው።
ፕለይስቶር ላይ በመግባት ወደ ስልካችን መጫን እንችላለን።
ይህች አፕልኬሽን ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ እንዲሁም በማንኛውም የሶሻል ሚዲያ ላይ የምናገኛቸውን ማስታወሻዎችን ለመያዝ ያገለግላል።
ማስታወሻ ለመያዝና መጻፍ ብትፈልጉ ይህችንን አፕልኬሽን በመጠቀም ኖት መያዝ እንችላለን።
ይህ አፕልኬሽን ከጎግል ድራይቭ ጋር በማገናኘት አፕልኬሽኑ ላይ የተቀመጡት ማስታዎሻዎች በየግዜው ባክአፕ መያዝ ትችላላችሁ። ይህ ጥቅም(ባክአፕ) ለምሳሌ አፕልኬሽኑ ቢጠፋ፣ ዲሌት ቢሆን፣ ስልኩ ቢጠፋ፣ ስልኩ ቢበላሽ፣ በሌላ ስልክ ከፍተን ማስታወሻውን እንደገና ማግኘት ያስችለናል።
ባክአፕ ለማድረግ ኢሜይል የሚጠይቅ ሲሆን ኢሜይል አድራሻ በማስገባት መረጃውን መያዝ ያስችለናል።
ሌላው ጥቅም
በፈለግነው ካታጎሪ ስያሜ በመስጠት ማዘጋጀት ያስችለናል።
ℹ️ ካላንደር የተዘጋጀለት ነው።
ℹ️ በፈለግነው View style ለእይታ ምቹ በሚሆን መልኩ እንድናዘጋጅ ያደርገናል።
ℹ️ በፍጥነት የገለግነውን መረጃ ጽሁፍ በመጻፍ ከኖታችን ላይ እንድንፈልግ ያስችለናል።
ℹ️ በፈለግነው አይነት Sorting type ሶርት ማድረግ ያስችለናል።
እንዲሁም የተለየ መተግበሪያ ሳያስፈልግዎት አስታዋሾችን ለመከታተል አብሮ የተሰራ የቀን መቁጠሪያ አለው፣ እና እንዲሁም በጭራሽ መረጃዎትን እንዳያጡ ከ Google Drive ጋር ማስተሳሰር ይችላል።
መተግበሪያው እንደ ፕሌይ ስቶር መግለጫው የሚያቀርባቸው ባህሪያት ዝርዝር ይኸውና።
✅ የቀለም ማስታወሻዎችን እና የተግባር ዝርዝሮችን መፍጠር ይችላሉ።
✅ ስዕሎችን፣ ስዕሎችን፣ ወይም የእጅ ጽሑፍን እንደ አባሪ በመጨመር መረጃ እንድንይዝ ያደርገናል።
✅ ማስታወሻዎችን፣ የተግባር ዝርዝሮችን ወይም መተግበሪያውን በራሱ በፒን ፣ በይለፍ ቃል ወይም በጣት አሻራ መቆልፍ እንችላለን።
✅ ከ2 የተለያዩ የቅርጸ አይነቶች፣ 5 የተለያዩ የቅርጸ መጠኖች፣ 4 የተለያዩ ገጽታዎች (ጨለማ ሞድ)፣ 5 የተለያዩ እይታዎች፣ 6 የተለያዩ የመደርደር ሁነታዎች እና 12 ምርጫዎችን ቀለም መቀባት እንድትችሉ ተደርጎ የተሰራ ነው።
✅ አስታዋሾች (ሊበጁ የሚችሉ እና በየቀኑ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ ወይም አመታዊ) እና የቀን መቁጠሪያ (ከጨረቃ ቀን መቁጠሪያ ድጋፍ ጋር፣ ግን ምንም የGoogle Calendar ውህደት የለም)
✅ የምትፈልጉትን ማስታወሻ ፒን ማድረግ ያስችላችኋል።
✅ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከ Google Drive ጋር ማገናኘት ይችላሉ ስለዚህ ማስታወሻዎችን ባክአፕ ያድርጉ
✅ ማስታወሻዎችን እና አባሪዎችን ለኢሜል፣ ኤስኤምኤስ፣ ማህበራዊ አውታረ መረብ እና የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ማጋራት ይችላሉ።
✅ ከሌሎች መተግበሪያዎች የተጋሩ ማስታወሻዎችን እና አባሪዎችን መቀበል ይችላሉ።
✅ ፈጣን የሆነ ፍለጋ
t.me/TechnologyMasterPage
#Source:- Muhammed Computer Technology
👉 ዛሬ Server ማለት ምን ማለት እንደሆነ የምናይ ነው የምሆነው:
➡️ Server(ሰርቨር)
👉 ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server በማለት።
➡️ ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው
ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው።
➡️ Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው።
➡️ በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል።
➡️ Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን(Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል ለምሳሌ አሁን የምንጠቀምበት ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል ስልክ ስልካችን ክሊያንት ዲቫይስ የሆነበት ምክንያት ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ስለምንጠቀም ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው።
➡️ ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል።
t.me/TechnologyMasterPage
📌Programming language📌
Programming language ማለት ከ ኮምፒዉተር ጋር ሊያግባባን የሚችል program ለመፃፍ የሚጠቅም ቋንቋ ማለት ነው: :
👨💻Computer ላይ የምንጭናቸው ማንኛውም አይነት የ ዳታ አይነቶች ለምሳሌ: photo, video , software....ሌሎችም የሚቀመጡት Mechine language በሚባል 0 እና 1 ቁጥሮች በያዘ የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : ለምሳሌ 10 ቁጥርን ከ keyboard ⌨ ብናስገባ ኮምፒዉተራችን የሚረዳውና የሚያስቀምጠው ወደ እንደዚህ አይነት ቁጥሮች ቀይሮ ነው 👉 010001010...እነዚህ አይነት ቁጥሮች Machine language በመባል ይጠራሉ: :
Machine Language
━━━━━━━━━━━━━
Machine language ማለት computer 💻 ሊረዳው የሚችል የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : የሚጠቀመውም 0 እና 1'ን ብቻ ነው: : ለምሳሌ 33 በ Machine language 00100001 ነው: :
➠ ነገር ግን ለኛ ለሰዎች Machine language'ን ለማንበብና ለመረዳት ከባድም አሰልቺም በመሆኑ ምክንያት በ Machine language program መፃፍ የማይታሰብ ነው: :
➠ በዚም ምክንያት ሰዎች አንብበው ሊረዱት የሚችል program መፃፊያ ቋንቋ(programming language) ለመፍጠር ጥረት መደረግ ተጀመረ: :
ይህ ጥረትም ለ Assembly language መፈጠር ምክንያት ሆነ: :
Assembly Language
━━━━━━━━━━━━━━
✅ Assembly language ሰዎችንና computer'ን በመጠኑም ቢሆን ያቀራረበ ቋንቋ ነው: :
✅ Assembly language ከ Machine language አንፃር ለማነበብና ለመረዳት በመጠኑም ቢሆን ቀለል ያለ programming language ነው: :
✅ Assembly language የእንግሊዝኛ ፊደላትን የያዙ አጫጭር ቃላቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ: ADD, MUL, MOV, INC, POP, PUSH, SUB, DEC,....,e.t.c
✅ እነዚህ Assembly language ላይ ያሉ አጫጭር ቃላት(instructions) mnemonic( ሜሞኒክ) ተብለው ይጠራሉ።
✅ Assembly language እና Machine language ባንድ ላይ low-level programming language በመባል ይጠራሉ: :
✅ Assembly language ከ Machine language አንፃር ለ ሰው ልጅ ቋንቋ ቀረብ ያለ ነው አልን እንጂ እሱም ቢሆን ለ መማንበብ እና ለመረዳት ያን ያህል የቀለለ አልነበረም: :
✅ በዚህም ምክንያት እስካሁን ካየናቸው የተሻለና ለማንበብ ለመፃፍ የበለጠ የቀለለ አዲስ programming language አስፈለገ: :
High-level Programming language
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
➻ በፈረንጆቹ ወደ 1950ዓ.ም ላይ ለ ሰውልጅ ቋንቋ እጅግ የቀረበ, እንግሊዘኛ ቋንቋ መሳይ ለማንበብ , ለመረዳት እና ለመፃፍ ቀላል የሆኑ programming language'ኦች መሰራትና ወደ ገበያ መውጣት ጀመሩ: : እነዚህ programming language'ኦች high-level programming language በመባል ይታወቃሉ: :
➻ አሁን ባለንበት ዘመን ከ 100 በላይ High-level programming language'ኦች ይገኛሉ: : ከነዚህ ውስጥ ታዋቂዎቹ:
C, C++, C#, Java, COBOL, FORTRAN, Python, PHP …ይገኙበታል: :
t.me/TechnologyMasterPage
➡️# ዛሬ የምናየው የ ፍላሽ ዲስክ Eject በማድረግ የምናገኛቸው ብዙ ጥቅሞችን ይሆናል ሙሉውን ያንብቡት:-
👉 ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
👉 ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
➡️ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
➡️ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
➡️ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
➡️ ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
➡️ Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
➡️ Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
Like, Share ያድርጉ እናመሠግናለን!
t.me/TechnologyMasterPage
➡️ ዛሬ የማሳያችሁ የ Laptop CPU /central processing unit / ሲያሜን በተመለከተ የግድ ማወቅ ያለብን ወሳኝ ነገሮችን ይሆናል:-
➡️ ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ ማወዳደር እንደሌለብን እንረዳለን፡፡
✅ በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡
👉 ልብ ይበሉ የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡
K– Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር የሚደረግ CPU ናቸው፡፡
ለምሳሌ Core i7-6700k እና Core i7-5820k ባሉ የሞዴል ቁጥር መጨረሻ ላይ unlocked(ያልተቆለፈ) ስለሆሀን Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) የተሠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ማለት Unloc Processors ከፋብሪካ ዋና ፍጥነቶች በበለጠ ፍጥነት ከመጠን በላይ ሊጫኑ ይችላሉ ፡፡ የተቆለፉ ማቀነባበሪያዎች (Processors) ከመጠን በላይ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) አይችሉም።
ስለዚህ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ እምብዛም ነው፡፡
➡️ ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-8600K
H– High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።
Q – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡
👉 በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡
➡️ ምሳሌ፡ Intel® Core™ i7-7700HQ
M– Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) የደረጋል፡፡
Y- Extremely low Power
U – Ultra low Power
👉 ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡
➡️ ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-7200U
👉 Like, Follow, Share & Invite ያድርጉ👈👈
✅ ደንበኞቹ ከአጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳሰበ።
📍ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያዘጋጃቸውን የሽልማት ፕሮግራሞች በመንተራስ የሌብነት ተግባር ከሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አሳሰቡ፡፡
📍ወደ ደንበኞች ስልክ ደውለው ሽልማት እንደደረሳቸው በመንገርና ገንዘብ እንዲያስገቡ በመጠየቅ ሌብነት የሚፈጽሙ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡
📍ባንኩ ወደ ደንበኞች ስልክ የሚደውልበት አጋጣሚ መኖሩን የተናገሩት አቶ አቤ፣ ነገር ግን ደንበኞቹ ወደ ባንኩ በአካል እንዲቀርቡ ወይም ሰነድ እንዲያቀርቡ እንጂ በስልክ ይህን አስገቡ ያን አስወጡ የሚለው ነገር እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
📍ደንበኞች ከባንክ ነው በሚል ስልክ ሲደወልላቸው ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባቸው እና በስልክ መረጃ እንዳይሰጡ ያሳሰቡት አቶ አቤ፣ ይልቁንስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም 951 ላይ በመደወል የመረጃውን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
📍የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚሰጠው አገልግሎት ስልክ ደውሎ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠይቅም ነው አቶ አቤ ያስገነዘቡት፡፡
📍በተጨማሪም ደንበኞች ሞባይላቸው ሲጠፋባቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታቸው እንዲቋረጥ ማስደረግ እንዳለባቸው አቶ አቤ አሳስበዋል፡፡
@TechnologyMasterPage
“አግራሞቴን በብዕር” ከተሰኘው የፅሑፍ ማህደሬ የተወሰዱ የድንቅ መስመሮች ሀሳብ ▼▼
➝የእይታን አድማስ የሚያሰፉበት፣
➝የጥሩነት ጥሩነት የሚያውቁበት፣
➝የመጥፎነትን መጥፎነት የሚያውቁበት፣
➝ለነገሮች ያሎትን ምልከታ የሚያሳድግ።
➝ጊዜ ሮጦ እንዲያመልጦት ሳይሆን ጊዜን ሮጠው እንዲያመልጡ የሚያግዝ።
➝ደግነትን የሚዘክሩ፤ ክፋትን የሚያወግዙ ብሎም የሚጠሉ።
➝አንዳንዴ ደስታ፤ አንዳንዴ ደግሞ ሀዘን የሚቦርቅበት።
➝ሰውና ሰብዓዊነት የሚፋረዱበት፤ ሰብዓዊነት የሚረታበት።
➝የአቅሙን ያህል ለሞከረ የሚያጨበጭብ፤
➝የአቅሙን ያህል ያልሞከረን፤ የአቅሙን እንዲሞክር የሚያነሳሱ።
➝ለውጥን የሚፈሩ ሰዎች ለውጥን የሚያለማምድ፤ ለውጥን የለመዱ ሰዎች ደግሞ ትክክለኛ መለወጥን እንዲለወጡ የሚያደርግ።
➝ዘረኝነት የሚባለውን የካንሰር በሽታ መድሃኒት የሚያቅጣጭ።
➝ፍርሃት የሚባለውን ተራራ የሚደረምስ፤
➝ድፍረት የሚባለውን ግንብ በአግባቡ የሚገነባ።
➝ፍትህን ለማስፈን አስተዋጽኦ የሚዶግም፤
➝ኢፍትሃዊነትን ለማስቀረት የራሱን ጥረት የሚያደርግ።
➝መፃፍ ስለቻልን ብቻ መፃፍ እንደሌለብን የሚያቅጣጭ፤ መናገር ስለቻልን ብቻ መናገር እንደሌለብን ጠቆም የሚያደርግ።
➝የሰው ቁስል ስናክም የኛው ማመርቀዙን፤
የማይድን ስናክም የማይሞት መግደላችንን የሚነግረን።
➝መንገዱ ረጅም ነውና መፍጠን እንዳለብን የሚነግረን፤ ስንፈጥንም ተጠንቅቀን ምናረገውን ክንዋኔ ማከናወን እንዳለብን የሚጦቅምም።
➝የትግል ውጤትና ደረጃን የሚያቅጣጭ።
➝የውሸትን ውሸትነት፤ የእውነትን እውነትነት የሚጦቅም።
➝ህልማችንን ለማሯሯጥ የሚያነሳሳ ልብ ሲያዝን ብዕር ሲያነባ የሚገልፅ፤
● ልብ ሲደሰት፤ ብዕር እየሳቀ የሚያሳይ።
➝ብዕር የተባለን የሳለ ሰይፍ የሚያሞግስና የሚያበረታታ....
▮እነዚህንና ሌሎችንም ድንቅ የሚያነቃቁ አስተማሪ የሆኑ ሐሳቦችን የያዘ....
▮“አግራሞቴን በብዕር” የተሰኘ
● ▮በትንሽ በስመሮች ብዙ ሐሳብን የሚዳስስ
▮የሚያነቃቁና በድንቅ የስነ-ፅሑፍ ዘይቤ የቀረቡ መልዕክቶችን የያዘ ፅሑፍ የሚቀርብበት የናተው መድረክ።
↪️ “አግራሞቴን በብዕር” (“My Marveled with pen”)
↪️ #ስለታማ ሰይፎች (The sharp swords) ብየ የሰየምኳቸውን ፅሑፎች ይዤ መጥቻለሁ!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📚 የቻናሉ ማስፈንጠሪያ (Link) ከታች አለላችቹ!!
● ከኛ ጋር በመሆን፣ አብረን የእይታችንን አድማስ እናስፋው፣
●የመነፅራችን መስታወት እንቀይረው፤
● የእይታችን መነፅሩ ቁጥሩ አንሶ ከሆነም ከፍ እናድርገው!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#በረሻድ_ዒብኑ_ሙዘሚል
t.me/SharpSwords
የሞባይል ባትሪን እድሜ ለማስረዘም እነዚህን 5 ነጥቦች ይተግብሩ
1 👉 Original ( ትክክለኛ ) ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ኦርጅናል ያልሆኑ ቻርጀሮች ዋጋቸው ሪካሽ ብሆንም ጥራታቸው ዝቅተኛ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይል ባትሪው ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ይጎደዋል ወይም የሞባይሉን ባትሪ እድሜ ያሳጥራል፡፡
2 👉 ሞባይላችንን ቻርጅ እያደረግን አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠሩ ባለፈ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በተጨማሪም ሞባይላችንን ራሱ ሊፈነዳብን ይችላል።
3 👉 ሞባይሎቻችንን ቻርጅ ሰክቶ አለማሳደር ( ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ ) ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ችግሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጅ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡
የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞልቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4 👉 ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣
ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች ማለትም ብሉቱዝ፣ጂፒኤስ፣ ዳታ ወዘተ ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5 👉 ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ 0% እስክሆን ጠብቀን ቻርጅ ማድረግ ይህም የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥሩት አንዱ ነው ባትሪው ግማሽ ወይም ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርግ የተሻለ የባሪውን እድሜ ይጨምርልናል።
Like Share Follow Invite በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ !!
t.me/TechnologyMasterPage
