Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል
Kanalga Telegram’da o‘tish
💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2
Ko'proq ko'rsatish1 830
Obunachilar
-124 soatlar
-37 kun
-1330 kun
Postlar arxiv
የላቀ የወደፊት ዕድል ለመፍጠር!
እያንዳንዱ ጉዞ የሚጀምረው በአንድ እርምጃ ነው። በጋለ ስሜትና በትጋት ደግሞ ያ እርምጃ ታሪክ የሚሰራ ቅርስ ይሆናል። ይህ ሰርተፍኬት እናንተም ታላቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ማስታወሻ ይሁንልኝ!
📚 ስኬት የዕድል ጉዳይ አይደለም፤ የጥረትን፣ የመማርን እና በየቀኑ ጥረት የማድረግ ውጤት ነው። በጽናት ከሰሩ፣ የማይቻል ነገር የለም!
📚 Artificial Intelligence (AI) / (ሰው ሰራሽ አስተውሎት): የወደፊት ብቻ አይደለም፤ የእናንተ የዛሬው ዕድል ነው። መማር ጀምሩ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አጧጥፉት፣ እና ለነገ ስኬትን የሙከራ እርምጃ ጀምሩ። ይህ ዘርፍ ገደብ የለሽ ዕድሎችን ይዟል፤ እናንተም የዚህ አካል መሆን ትችላላችሁ።
⭕️ ምናልባት አሁን በጥያቄዎችና በጥርጣሬዎች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በትኩረትና በእምነት እነዚያን ጥያቄዎች ወደ ብቃት መቀየር ይቻላል። አሁን የእናንተ ተራ ነው! እያንዳንዱ ጥረታችሁ ፍሬ ያፈራል። ኢንሻአላህ!
ያለፈው ሁኔታችሁ ገደባችሁን አይወስንም፤ የአዕምሮአችሁ ሁኔታ ነው የሚወስነው። ወሰኖችን አፍርሷቸው፣ መሰናክሎችን ጣሷቸው (ሰባብሯቸው)፣ እና ብቃታችሁን ተጠቀሙበት! በውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት።
📚 እያንዳንዱን ትንሽ ድል አክብሩ። ይህ ሰርተፍኬት መጨረሻው አይደለም። በአላህ ፍቃድ ከእናንተ ጋር በፈጠራ እና በለውጥ ወደተሞላ የወደፊት ጊዜ የሚወስድ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ለበለጠ ስኬት መነሻ ይሁን።
📚 ዕድልን አትጠብቁ። ለዕድል ተዘጋጁ ። ተማሩ፣ እደጉ፣ አሁንም አድጉ! እናም በሩ ሲከፈት፣ በልበ-ሙሉነት ለመግባት ዝግጁ ትሆናላችሁ። የእውቀት ፍለጋችሁ መቼም አታቁሙ።
ይህን አስደናቂ ትምህርት ለመማር እና ህይወታችሁን ለመለወጥ ይህ ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ።
ምን ትጠብቃላችሁ ታዲያ⁉️
════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!
ቀን:- ሐምሌ 6/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 18/1447 አ.ሒ]
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
+1
📱Instagram ላይ ሌሎች ሰዎችን invite በማድረግ አካውንታችሁን control እንዲያደርጉላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
ይህን ለማድረግ አካውንታችሁ ላይ Login ማድረግ አይጠበቅባቸውም።
⚫Instagram ከፍታችሁ ፕሮፋይላችሁ ላይ ከገባችሁ በኋላ 3 ሰረዙን ትነካላችሁ።
⚫ታች ላይ shared access የሚል ምርጫ ታገኛላችሁ።
⚫invite new people የሚለውን መርጣችሁ የፈለጋችሁትን ሰው instagram account search አድርጋችሁ invitation ትልኩለታላችሁ።
✔️ይህን invitation ከተቀበላችሁ በእናንተ አካውንት Post ማድረግ፣ Like ማድረግ እንዲሁም comment መፃፍ ይችላል።
✔️አካውንታችሁን disable ማድረግ ወይም account information (username, Display name) መቀየር ግን አይችልም።
✔️የinbox እና የstory access enable/disable ማድረግ ትችላላችሁ።
©️@bighabesha_softwares
Open Ai አዲስ Chatgpt Agent አስተዋወቀ።
እያደር ብዙ ነገሮችን እየጨመረ የመጣው OpenAi አዲስ የchat gpt agent አስተዋወቀ። ይህም የተለያዩ ስራዎችን እኛን ተክቶ መስራት ይችላል።
የራሱን ኮምፒውተር በመጠቀም የተለያዩ ውስብስብ ተግባራትን መከወን ይችላል ሲል ካምፓኒው አትቷል።
ተጠቃሚዎች ይህንን Agent እንደ browsing ማለትም ድረገፆች ላይ የተለያዩ ስራዎችን እንዲሰራ፣ code run እንዲያደርግ፣ እንደ gmail እና calander ያሉ መተግበሪያዎች ላይ login አድርጎ በርካታ ስራዎችን እንዲሰራ እንዲሁም ውስብስብ የሆኑ ስራዎችን እንዲከውን ማዘዝ ይችላሉ።
ይህ Agent ግዢ ከመፈፀምና email ከማድረጉ በፊት የናንተን permission/ፍቃድ ይጠይቃል። እንዲሁም እንደ financial ያሉ ተግባራት ላይ እናንተ የሱን ተግባር የምትቆጣጠሩት ይሆናል። ይሁንና ያዘዛችሁት ተግባር እንዲቋረጥ ከፈለጋችሁ ማቋረጥ ትችላላችሁ ተብሏል።
©bighabesha_softwares
የቀድሞው የTwitter co-founder እና CEO የነበረው Jack Dorsey ያለምንም sim card እና internet network በBluetooth ብቻ text message መላላክ የሚያስችላችሁ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል።
⚫አፕሊኬሽኑ Bitchat ይባላል።
⚫ከPlaystore ላይ አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.hostingduty.bitchat
⚫አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም አካዉንት መክፈት አይጠይቅም።
⚫ምንም አይነት Server ስለሌለው end-to-end encrypted ነው። ያ ማለት 3ኛ ወገን የምንፃፃፈውን ሊያይ አይችልም።
Bluetooth በ10 ሜትር ርቀት ስለሚሰራ text መላላክ የምንችለው በ10 ሜትር ርቀት ብቻ ነዉ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።
ነገር ግን ከዛም በላይ መላላክ እንችላለን። ምክንያቱም በአካባቢያችን ብዙ ተጠቃሚዎች ካሉ የሚፈጠሩት ትንንሽ ኔትዎርኮች ሌላ ትልቅ mesh network እየፈጠሩ ሰፊ ክልል እንዲያካልሉ ያስችላሉ።
ይህ ቴክኖሎጂ በጣም ብዙ አይነት ጠቀሜታዎች አሉት።
⚫የስልክ ኔትዎርክ በሌለባቸውና አደጋ በሚያጋጥማቸው አካባቢዎች communication እንዲኖር ያስችላል።
⚫Security ለሚያሳስባቸው ሰዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ።
©️@bighabesha_softwares
Samsung የትኛዎቹ AI ፊቸሮችን ነፃ እደሚያደርግ ይፋ አደረገ።
Samsung በ2025 መጨረሻ ሁሉንም Galaxy AI ፊቸሮች ማስከፈል እንደሚጀምር ሲነገር ነበር። ነገር ግን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የትኞቹ ፊቸሮች ነፃ እንደሚሆኑ ይፋ አድርጓል።
የSamsung Galaxy AI ፊቸሮች በሁለቱ ይከፈላሉ።
የመጀመሪያው በSamsung በራሱ develop የተደረጉ ሲሆን ሌላው በGoogle develop የተደረጉ Gemini powered የሆኑ ናቸው።
Samsung ባወጣው መግለጫ በራሱ develop የተደረጉት በሙሉ ነፃ የሚሆኑ ሲሆን ከእነዚህ መካከል
⚫Audio Eraser
⚫Object Eraser
⚫Note Assist
⚫Generative Wallpapers
⚫Live Translate
⚫Writing Assist ናቸው።
ሌሎች Gemini powered የሆኑት
⚫Gemini as Google assistant replacement
⚫Circle to search
⚫Gboard AI features
⚫Gemini nano (on-device AI)
⚫Call & sefety features
የመሳሰሉት ደግሞ በSamsung ብቻ የሚወሰኑ ስላልሆኑ ለጊዜው ነፃ ቢሆኑም ወደፊት ነፃ ሆነው ስለመቆየታቸው የታወቀ ነገር የለም።
©️@bighabesha_softwares
የተለያዩ ቪዲዮዎችን በAI generate ማድረግ ከፈለጋቸው በዚህ የCapcut Website ላይ መስራት ትችላላችሁ።
https://pippit.capcut.com/
በጣም ደስ የሚለው feature የፈለጋችሁትን ዌብሳይትም ይሁን የsocial media link አስገብታችሁለት የሚገርም video generate ያደርግላችኋል።
Watermark ይኖረዋል እንጂ በጣም አሪፍ website ነው ሞክሩት።
የተለያዩ ቪዲዮዎችን በAI generate ማድረግ ከፈለጋቸው በዚህ የCapcut Website ላይ መስራት ትችላላችሁ።
https://pippit.capcut.com/
በጣም ደስ የሚለው feature የፈለጋችሁትን ዌብሳይትም ይሁን የsocial media link አስገብታችሁለት የሚገርም video generate ያደርግላችኋል።
Watermark ይኖረዋል እንጂ በጣም አሪፍ website ነው ሞክሩት።
✅ ጉዳዩ፡- የ2018 ትምህርት ዘመን ለኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካንፓስ የ9ኛ ክፍል የተማሪዎች
ውድድርን ስለማሳወቅ፤
📚 ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የኮተቤ ሳይንስ ሼድ ካንፓስ 9ኛ ክፍልን በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡትን ተማሪዎች በማወዳደር በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
📚 በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ 8ኛ ክፍል ተምረው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 9ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ተማሪዎች የኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ አወዳድሮ በ2018 ትምህርት ዘመን ቅበላ ያደርጋል፡፡
⭕️ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተማሪዎች ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 8ኛ ክፍል በመንግስትና የግል ት/ቤቶች በመማር ላይ የነበረ/ች፤
2. በ2017 ትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ /Average/ ውጤት 80% እና በላይ ያስመዘገበ/ች፤
3. በ2017 ትምህርት ዘመን በስነምግባሩ/ሯ በትምህርት ቤቱ የተመሰገነ/ች፤
4. የምዝገባ ቀን ሐምሌ 14 ቀን እስከ 18 ቀን 2017 E.C ይካሄዳል፤
5. መመዝገቢያ ቦታ፡- የኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፤
6. የፈተና ቀን ሐምሌ 23 ቀን 2017 E.C የሚሰጥ መሆኑ ታውቆ ይህ ደብዳቤ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተደራሽ እንዲሆን አሳስባለሁ፡፡
⭕️ 📚 ከዚህ ምዝገባና ፈተና ወቅት ቀድሞም እንዲሁም ዘግይቶ የመጣ አይስተናገድም፡፡
📚 የህልማችሁ ቁልፍ በእጃችሁ ነው! 📚
ውድ ተማሪዎች!
በምስሉ ላይ የምታዩትን ልጅ ተመልከቱት እስኪ። ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብሎ በፈገግታ እየጻፈ ነው፤ በአዕምሮው ግን ወደፊት ምን መሆን እንደሚፈልግ እያሰበ ነው። ዶክተር ሆኖ ሰዎችን ሲያድን፣ ፓይለት ሆኖ አውሮፕላን ሲያበር፣ ወይም መሀንዲስ ሆኖ ትልልቅ ህንጻዎችን ሲገነባ ይታየዋል። እንዴት የሚያስደስት ህልም ነው!
እናንተስ? ወደፊት ምን መሆን ትመኛላችሁ? ምናልባት ዶክተር፣ ፓይለት፣ መሀንዲስ፣ መምህር፣ ፕሮግራመር ወይም ዲዛይነር መሆን ትፈልጉ ይሆናል። እነዚህ ሁሉ በጣም ግሩም ህልሞች ናቸው።
✅ መልካም ነገር ማለም መልካም ነው፤ ነገር ግን የምናልመውን ህልም እውን ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብን።
ታዲያ ይህንን ጣፋጭ ህልም እውን የምናደርገው እንዴት ነው? መልሱ በጣም ቀላል እና አሁን ባላችሁበት ቦታ ላይ የሚገኝ ነው፤ እርሱም ጠንክሮ መማርና ማንበብ ነው!
ህልማችሁን የምትገነቡበት እውን የምታደርጉት በትምህርታችሁ ነው!
✅ ዶክተር መሆን ከፈለጋችሁ፣ ዛሬ በክፍል የምትማሩት የሳይንስ ትምህርት የሰውነትን አሰራር ለመረዳት የመጀመሪያው እርምጃችሁ ነው።
✅ ፓይለት የመሆን ህልም ካላችሁ፣ የሂሳብ ትምህርት አውሮፕላኑን ለማብረር እና አቅጣጫዎችን ለማወቅ ወሳኝ ነው።
✅ መሀንዲስ ሆናችሁ ድልድይና ህንጻ ለመስራት ስታስቡ፣ ዛሬ የምትሰሯቸው የስዕል እና የሂሳብ መልመጃዎች መሰረታችሁ ናቸው።
📚 ስለዚህ ዛሬ በክፍል ውስጥ የምትማሩት እያንዳንዱ ትምህርት፣ የምትጽፉት እያንዳንዱ አረፍተ ነገር እና የምትፈቱት እያንዳንዱ የቤት ስራ ወደ ህልማችሁ የሚወስዳችሁ አንድ መንገድ መሆኑን አስታውሱ።
⭕️ ተስፋ አትቁረጡ፣ ሁሌም ሞክሩ!
አንዳንድ ጊዜ ትምህርት ከባድ ሊሆን ይችላል። አንድ የሂሳብ ቀመር ሊከብዳችሁ ወይም አንድ የእንግሊዝኛ ቃል ሊጠፋባችሁ ይችላል። ይህ ማለት ግን አትችሉም ማለት አይደለም። ተስፋ በፍጹም አትቁረጡ!
➊ ስትሳሳቱ አትፍሩ፦ ስህተት የትምህርት አንዱ አካል ነው። ከስህተታችሁ ትማራላችሁ።
❷ ጥያቄ ጠይቁ፦ ያልገባችሁ ነገር ሲኖር መምህራኖቻችሁን በድፍረት ጠይቁ።
➌ ደጋግማችሁ ሞክሩ፦ አንዴ ካልተሳካላችሁ፣ ደግማችሁ ሞክሩ። ጥረት ማድረግ ውጤት አለው!
📚 መጽሐፍትን ጓደኛችሁ አድርጉ!
ከክፍል ትምህርታችሁ በተጨማሪ መጽሐፍትን ማንበብ አዲስ አለምን ያሳያችኋል። ታሪኮችን፣ ግጥሞችን እና የተለያዩ መረጃዎችን ስታነቡ አዕምሯችሁ ይዳብራል፣ የቃላት እውቀታችሁ ይጨምራል፣ ከሁሉም በላይ ለምህርታችሁ ቅርብ ትሆናላችሁ።
➡ አስታውሱ፣ የወደፊት ህይወታችሁ የሚቀረፀው በዛሬው ጥረታችሁ ነው። ስለዚህ በየቀኑ በደስታና በተነሳሽነት ተማሩ፣ አንብቡ፣ ጥረት አድርጉ። የዛሬው ትንሽ ጥረት የነገውን ትልቅ ህልም እውን ያደርጋል!
በርቱ፣ ጎብዙ! ለሁላችሁም መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ!
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!
ቀን:- ሐምሌ 6/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 18/1447 አ.ሒ]
#tech_tip
የwindows ተጠቃሚ ከሆናችሁ ኪቦርዳችሁ ላይ የሚገኘውን የwindow key ከሌሎች ቁልፎች ጋር አንድ ላይ በመንካት የምታገኟቸው shortcuts (part 2)
⚫Win + tab = task view ወይም እንደስልክ የተከፈቱ መተግበሪያዎችን ለማየት።
⚫Win + Ctrl + D= አዲስ virtual desktop ለመፍጠር።
⚫Win + Ctrl + Left/Right= የፈጠርናቸውን virtual desktops ለመቀያየር።
⚫Win + Ctrl + F4= የፈጠርነውን virtual desktop ለመዝጋት።
⚫Win + Print Screen=ኮምፒውተራችን ላይ screenshot ለማንሳት።
⚫Win + Arrow keys= ሁለትና ከሁለት በላይ ነገሮችን ስክሪናችን ላይ ለመክፈት እንጠቀምባቸዋለን። ሞክሯቸው!
⚫Win + Number (1-9)= taskbar (ከታች) pin የተደረጉ መተግበሪያዎችን ለመክፈት ለምሳሌ መጀመሪያ ላይ Microsoft store ከሆነ ያለው Win+1 ስንነካ Microsoft store ይከፈታል።
©bighabesha_softwares
🐸 Microsoft Office LTSC 2024 for Mac v16.89.2
Microsoft Office LTSC 2024 for Mac v16.89.2 merupakan salah satu software terbaru yang di rancang untuk pekerjaan office yang sangat terkenal dari microsoft untuk pengguna sistem operasi macOS. Terdapat program versi Word, Excel, PowerPoint, Outlook, dan OneNote yang modern, yang menggabungkan antarmuka Office yang familier dengan fitur Mac unik yang Anda sukai.
💠 password: @software_application
💠 download 2 part pada satu folder,
Extract part1 sahaja
💠 saiz selepas extract 2.69 GB
