uz
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Kanalga Telegram’da o‘tish

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

Ko'proq ko'rsatish
1 876
Obunachilar
+124 soatlar
-107 kun
-5130 kun
Postlar arxiv
🔰 ሶብር ያስፈልጋል ከእኛ የሚጠበቀው በመልካም እሳቤ (ንያ) ጥረት ማድረግ ነው። ጥረታችንን እጥፍ ድርብ አድርጎ ወደ ስኬት መቀየሩ የአላህ ነው! ► ለመልካም ጥረታችን ምንዳውን የሚመነዳንም (አጅሩን የሚከፍለንም) አላህ ነው። ⭕️ ስለዚህ ነገሮች ምንም ያህል ቢከብዱን፣ ሰዎች ባይረዱን፣ ሰዎች ስለእኛ የማይሆን ነገር ቢያስቡም...... ሶብር ያስፈልገናል ማለት ነው! ► ጥረታችን፣ ልፋታችንን አላህ በእዝነቱ በብዙ እጥፍ አባዝቶ አጅሩን የሚሰጠን እሱ (አላህ) ነውና ተስፋ አንቆርጥም። ► የምንሰራው ነገር ለአላህ ብለን እስከሆነ ድረስ ተስፋም መቁረጥም አይገባንም። ✅ ተስፋ የሚቆርጡ ደካሞች ብቻ ናቸው❗️ ወንድማችሁ:- ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

🚀 የእንግሊዝኛ የንግግር ክህሎትህን አሁንውኑ ክፈት! 🚀 ሰላም ውድ ተማሪዎቻችን! ዛሬ አንድ እጅግ ጠቃሚና ዘመናዊ መሳሪያ ላስተዋውቃችሁ እፈልጋለሁ። ይህ መሳሪያ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በመናገር በልበ ሙሉነት እንድትግባቡና ችሎታችሁን ወደ ላቀ ደረጃ እንድታሳድጉ የሚረዳችሁ ድንቅ ቴክኖሎጂ ነው - ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ያላቸው የቋንቋ ሞዴሎች! ══════════════ 🔑 እነዚህ የ AI ኃይሎች ምንድን ናቸው? እነዚህ ሞዴሎች - ChatGPT፣ Poe፣ Gemini እና Perplexity - ልክ እንደ ብልህና ሁልጊዜ ለመርዳት ዝግጁ የሆኑ የውይይት አጋሮቻችሁ ናቸው። በእንግሊዝኛ ቋንቋ የምትጠይቋቸውን ጥያቄዎች በመረዳት ምላሽ ይሰጡናል፣ ሀሳቦችን እንድታዳብሩ ያግዙናል፣ አልፎ ተርፎም የንግግር ችሎታችሁን እንድታሻሽሉ ድጋፍ ይሰጣሉ። ➊ ChatGPT: በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ እውቀት ያለው በመሆኑ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከእሱ ጋር በመወያየት የቃላት ዝርዝራችሁን ማስፋትና አዳዲስ አገላለጾችን መማር ትችላላችሁ። ❷ Poe: የተለያዩ ምርጥ የ AI ሞዴሎችን በአንድ ላይ ያሰባሰበ መድረክ በመሆኑ ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ልምምድ የተለያየ አማራጭ ይሰጣችኋል። ➌ Perplexity: ከተለያዩ ምንጮች ትክክለኛ መረጃዎችን በማቅረብ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስለተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በጥልቀት ለመወያየት የሚያስፈልጋችሁን እውቀት ይሰጣችኋል። ❹ Gemini: እጅግ የላቀና ሁለገብ በመሆኑ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሃሳባችሁን በግልጽና በፈጠራ እንድትገልጹ ይረዳችኋል። 🚀 እነዚህ መሳሪያዎች የእንግሊዝኛ የንግግር ችሎታችሁን እንዴት ያግዛሉ? 🚀 * በእንግሊዝኛ መናገርን ይለማመዱ! እነዚህን ሞዴሎች በመጠቀም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በእንግሊዝኛ በመወያየት የንግግር ልምምድ ማድረግ ትችላላችሁ። * አዳዲስ ቃላትን ይወቁ! በእንግሊዝኛ የማታውቋቸውን ቃላት በመጠየቅ ትርጉማቸውንና አጠቃቀማቸውን መረዳት ትችላላችሁ። * የአረፍተ ነገር አወቃቀርን ይማሩ! ትክክለኛና የተወሳሰቡ የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮችን እንዴት መገንባት እንደሚችሉ ይጠይቁ። * የአነጋገር ዘይቤን ያሻሽሉ! ትክክለኛ አጠራርንና የተለመዱ የእንግሊዝኛ አባባሎችን ይወቁ። * በራስ መተማመናችሁን ያሳድጉ! በተግባር እየተሻሻላችሁ ስትሄዱ በእንግሊዝኛ የመናገር በራስ መተማመናችሁ ይጨምራል። ⚠️ አንድ ወሳኝ ነገር! ⚠️ እነዚህ መሳሪያዎች እጅግ ጠቃሚ ቢሆኑም፣ የሚሰጡንን መረጃ ሁልጊዜ ማረጋገጥ አለብን። ስህተት ሊኖርባቸው ስለሚችል በራሳችንም ማሰብ አለብን። 🎯 ለሁላችሁም ተማሪዎች የምሰጠው ምክር! 🎯 * ያገኛችሁትን መረጃ በጥንቃቄ መርምሩና አረጋግጡ። * እነዚህ መሳሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትንና ከባለሙያዎች ጋር መወያየትን ሙሉ በሙሉ ሊተኩ አይችሉም። * እነዚህን መሳሪያዎች በመጠቀም የእንግሊዝኛ ቋንቋን መማር አስደሳችና ውጤታማ እንደሆነ ትገነዘባላችሁ! 📚 የቴክኖሎጂው አድናቂዎች ምን ይላሉ? ➊ Elon Musk: "AI የሥልጣኔ አካል እንደመሆናችን የምንጋፈጠው እጅግ አደገኛ ቴክኖሎጂ ነው።" ❷ Bill Gates: "ሙሉ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ማዳበር የሰውን ዘር ፍጻሜ ሊያመጣ ይችላል።" ➌ Yann LeCun: "AI ሰዎችን አይተካም፣ ይልቁንም የበለጠ ሰው ያደርገናል።" ✨ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የብሩህ ተስፋ! ✨ ውድ ተማሪዎቻችን፣ ይህ ዘመን የቴክኖሎጂ ዘመን ነው! እነዚህን የ AI የቋንቋ ሞዴሎች በመጠቀም የእንግሊዝኛ የንግግር ችሎታችሁን በማዳበር ለተሻለ የወደፊት ህይወታችሁ በር መክፈት ትችላላችሁ። ይህንን እድል አሁኑኑ ተጠቀሙበት! ኑ እነዚህን አስደናቂ አፕሊኬሽኖች አሁኑኑ ዳውንሎድ አድርጉ! ➊ #POE 👇👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.poe.android ❷ 📚 #Perplexity 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=ai.perplexity.app.android ➌ 📚 #ChatGPT 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.openai.chatgpt ❹ Gemini 👇👇👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.google.android.apps.bard ══════════════ ✅ እነዚህ የAI የቋንቋ ሞዴሎች የእንግሊዝኛ የንግግር ችሎታችሁን ለማዳበር ወሳኝ መሳሪያዎች ናቸው! ══════════════ ✍️ የናንተው ወንድም ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል 🌐 ዘመኑ የ#ቴክኖሎጂ ነው! 📲 ይህንን እድል በመጠቀም የእንግሊዝኛ ቋንቋን አቀላጥፋችሁ ተናገሩ! 💻

💬 ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት🗨️ ══════════════ ውድ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች! ✅ ሰኔ ወር ከ3 እስከ 11/2017 ዓ.ል የሚሰጠው ወሳኝ ፈተና ከፊታችሁ ይጠብቃል። ይህ ፈተና የትምህርት ጉዟችሁ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን፣ ያላችሁን እውቀትና ክህሎት የምትፈትኑበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። ✅ በተለይም የ6ኛ ክፍል ከተማቀፍ ፈተና ወደ ላቀ የትምህርት ደረጃ ለመሸጋገር የመጀመሪያው እርምጃ ሲሆን፣ የ8ኛ ክፍል አሀረቀፍ ፈተና ደግሞ የወደፊት የትምህርት አቅጣጫችሁን የሚወስን ወሳኝ ምዕራፍ ነው። 📚 በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የምሰጣችሁ ምክሮችና የምታደርጉት ጥረት በእርግጠኝነት መልካም ውጤት እንደሚያስገኝላችሁ እምነቴ ነው። ውድ ተማሪዎች! ➊ በፈጣሪያችሁ ላይ ሙሉ በሙሉ ተመኩ: ማንኛውም ስኬት የሚገኘው በፈጣሪ ፍቃድ ነው። ስለዚህ በምታደርጉት ጥረት ሁሉ ፈጣሪያችሁን አስቀድሙ። ወደርሱ ጸልዩ (ዱዓም አድርጉ)። አላህ ጥረታችሁን እንዲባርክላችሁና እንዲያግዛችሁ በልባችሁ ሙሉ እምነትን አሳድሩ። ❷ ጠንክራችሁ ተዘጋጁ: ፈተናው ከፊታችሁ ሁለት ወራት ብቻ ቀርተውታል። ይህ ጊዜ ለትጋትና ለጠንካራ ዝግጅት ወሳኝ ነው። ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት። ለእያንዳንዱ ትምህርት በቂ ጊዜ መድቡ። የ5ኛ እና 6ኛ ክፍል እንዲሁም የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ትምህርቶችን በደንብ በመከለስና በመድገም እውቀታችሁን አጠናክሩ። ➌ እቅድ አውጡ: በየቀኑ ምን እንደምታጠኑ በግልፅ ያስቀምጡ። ሳምንታዊ እና ዕለታዊ የጥናት እቅድ በማውጣት ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት። ለእያንዳንዱ ትምህርት የተለየ ጊዜ መድቡ እንዲሁም የእረፍት ጊዜያችሁን አትርሱ። ❹ በትኩረት አንብቡ: በምታጠኑበት ጊዜ ሁሉ አእምሮአችሁን ሙሉ በሙሉ በንባቡ ላይ አድርጉ። ትኩረታችሁን የሚረብሹ ነገሮችን ከዙሪያችሁ አስወግዱ። ያልገባችሁን ነጥቦች ለመምህሮቻችሁ ወይም ለሚያውቋችሁ ሰዎች ለመጠየቅ አትፍሩ። ❺ የቀደምት ፈተናዎችን ተመልከቱ: በተቻለ መጠን የቀደምት ዓመታት የፈተና ጥያቄዎችን በመመልከት የፈተናውን ቅርፅና የጥያቄዎቹን አቀራረብ ለመረዳት ሞክሩ። ይህ ለፈተናው የተሻለ ዝግጅት እንድታደርጉ ይረዳችኋል። ❻ ቡድን በመሆን ተማሩ: ከአስተዋይ ጓደኞቻችሁ ጋር በመሆን በቡድን መወያየትና መማር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ያልገባችሁን ነገር በመጠያየቅና በመወያየት የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ትችላላችሁ። ነገር ግን የቡድን ጥናታችሁ ከመወያየትና ከመማር የዘለለ እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ❼ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ተከተሉ: ሰውነታችሁ ጤናማ ካልሆነ በአግባቡ ማጥናት አትችሉም። ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ተኙ፣ የተመጣጠነ ምግብ ተመገቡ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አድርጉ። በተለይም በፈተናው ወቅት ጭንቀትን ለማስወገድ ዘና የሚያደርጉ ነገሮችን አድርጉ። ❽ ጸልዩ(ዱዓ አድርጉ): ከምንም በላይ ጌታችሁን አላህን ተማፀኑ። ፈጣሪ ጥረታችሁን እንዲቀበልላችሁና መልካም ውጤት እንዲሰጣችሁ ሁል ጊዜ ዱዓ አድርጉ። ውድ ተማሪዎች! 🎯 እምነታችሁ ለስኬታችሁ ትልቅ መሠረት ነው። መልካም ስነ ምግባርን ያዙ። ወላጆቻችሁን አክብሩና ምክራቸውን ስሙ። የፈጣሪያችሁን ትዕዛዛት በመጠበቅ ለዚህ ፈተና ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ህይወታችሁም ስኬትን ታገኛላችሁ። 📚 ከፊታችሁ ያለው ጊዜ ፈታኝ ሊሆን ቢችልም በጠንካራ ጥረትና በፈጣሪያችሁ ላይ ባለ ሙሉ እምነት ይህንንም ጊዜ በተሳካ ሁኔታ ማለፍ ትችላላችሁ። አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን! ✅ መልካም የንባብ ጊዜ እመኝላችኋለሁ! ✅ በአላህ ፈቃድ ሁላችሁም ከተመኘችሁትን ውጤት በላይ እንድታገኙ እመኛለሁ። ጌታችን ውጤቱንም ለማህበረሰቡ እድገትና ስኬት ምክንያት  ያድርገው። አላህ ያግዛችሁ! 🤲 ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ (መጋቢት 30/2017 ዓ.ል) ══════════════ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 Join our channel
+2
የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ (መጋቢት 30/2017 ዓ.ል) ══════════════ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 Join our channel ➊ t.me/Grade1_4Infot.me/Grade5and6Infot.me/Grade7Infot.me/Grade8Infot.me/Grade9Infot.me/BasicComputer_Skills

እንዴት አርገን ፋይል አታች እናረጋለን Gmail ላይ? ምክር 6 | How to attach a file in Gmail Tip 6 ══════════════ ✍️ Basic Computer Skills 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 Telegram: t.me/BasicComputer_Skills tiktok.com/@basiccomputerskillst.me/Grade1_4Infot.me/Grade5and6Infot.me/Grade7Infot.me/Grade8Infot.me/Grade9Info

How To Make Markdown Text On Telegram

አስተያየት ጥያቄ መቀበያ ቴሌግራም ቡት እንዴት መስራት እንችላለን How To Create Your Own Bot AMHARICK

ከቴክኖሎጂ ጋር የምትቀራረቡ ከሆናችሁ እነዚህን website ሞክሯቸው። https://nanoreview.net/ ስለተለያዩ ላፕቶፕ እና ስልኮች መረጃዎችን የምታገኙበት webiste ነው። በተጨማሪም ከላይ የሚገኘውን phones የሚለውን ፅሁፍ በመንካት ሁለት ስልኮችን ማወዳደር ትችላላችሁ። Dev.to በሚልዮን የሚቆጠሩ ዴቨሎፐሮች የሚገኙበት ፕላትፎርም ሲሆን ከሌሎች ፕላትፎርሞች አንፃር እዚህ ላይ ብዙ የቴክ ዕውቀት መቅሰም ትችላላችሁ። w3schools.com የተለያዩ programming languages በቀላሉ እዚህ website ላይ መማር ትችላላችሁ። Hackthebox.com ራሳችሁን challenge በማድረግ cyber security የምትማሩበት ፕላትፎርም ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ይህንን website ethical hacker , penetration tester የሆኑ ግለሰቦች ልምዳቸውን ለማጎልበት ይጠቀሙታል። Eevblog.com ስለ electronics, hardware ጠቃሚ መረጃዎችን የምታገኙበትን website ነው። electrical engineering ተማሪ ከሆናችሁ ይጠቅማችኋል። ©bighabesha_softwares

❝It is necessary to help others, not only in our prayers, but in our daily lives. If we find we cannot help others, the least we can do is to desist from harming them.❞

+7
📚 Grade 8 General Science: ✅ Unit 7: Physical Phenomena in the Surrounding ✅ ከReview Questions ጋር 8 ቪድዮዎች ከላይ ተለቋል። ✅ ተጠቀሙበት። ለሌሎች እህት ወንድሞቻችሁ አጋሯቸው። ✅ አላህ ይርዳችሁ!! ══════════════ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 Join our channel ➊ t.me/Grade1_4Infot.me/Grade5and6Infot.me/Grade7Infot.me/Grade8Infot.me/Grade9Infot.me/BasicComputer_Skills

ስልክ ላይ nanometer (nm) ሲባል ምን ማለት ነው? የስልክ ማስታወቂያ ላይ ባለ 4,6,8 nanometers processor ሲባል እንሰማለን ታዲያ ይህም የስልኩ performance ላይ ትልቅ
ስልክ ላይ nanometer (nm) ሲባል ምን ማለት ነው? የስልክ ማስታወቂያ ላይ ባለ 4,6,8 nanometers processor ሲባል እንሰማለን ታዲያ ይህም የስልኩ performance ላይ ትልቅ ሚና አለው። ነገሩ እንዲህ ነው nanometer ማለት 1 × 10⁻⁹ ሜትር ወይም ከፊቱ 9 ዜሮዎችን ከፊቱ የደረደረ  ሜትር/የልኬት አሀድ ነው። nanometer ብዙ ጊዜ ጥቃቅን  ነገሮች ለመለካት ጥቅም ላይ ይውላል። እንደ transistor ያሉ በስልካችን chip ውስጥ የሚገኙ components መጠን በnanometer የሚለኩ ሲሆን ይህም  nanometer የነዚህን component size ይገልፃል። chip ውስጥ የሚገኙት ኮምፖነንቶች መጠን ባነሰ ቁጥር በርካታ component መያዝ ስለሚችል አንድ ስልክ የnanometer መጠኑ ባነሰ ቁጥር ይበልጥ ጥራት ይኖረዋል። ስልኮች ላይ የሚገኘው የnanometer መጠን ትንሽ እየሆነ በመጣ ቁጥር፦ ⚫ጥሩ performance ይኖረዋል። ⚫ይበልጥ battery ቆጣቢ ይሆናል። ⚫ብዙ ሙቀት አይፈጥርም ማለትም የመጋል እድሉ እየቀነሰ ይመጣል። አዳዲስ የሚወጡ ስልኮች ከ8 nanometer በታች processor ቢኖራቸው ተመራጭ ነው። የእናንተ ስልክ nanometer ስንት ነው? ©bighabesha

🇵🇸 ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ በፍቅር፣ በሳቅ እና በበረከት የተሞላ የደስታ ኢድ እንዲሆን እመኛለሁ። ... ይህ ኢድ ለቤታችሁ ሰላም ፣ ደስታ እና ብልጽግና ያድርግላችሁ። ... በዚህ መልካም አ
🇵🇸 ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ በፍቅር፣ በሳቅ እና በበረከት የተሞላ የደስታ ኢድ እንዲሆን እመኛለሁ። ... ይህ ኢድ ለቤታችሁ ሰላም ፣ ደስታ እና ብልጽግና ያድርግላችሁ። ... በዚህ መልካም አጋጣሚ አላህ በእናንተና በቤተሰቦቻችሁ ላይ መለኮታዊ ፀጋውን እንዲያወርድ እማፀነዋለሁ። ... 🇵🇸 ኢድ ሙባረክ! 🇵🇸 ይድረስ ለወንድም እህቶቼ (ለተማሪዎቼ) እና ለቤተሰቦቻቸው! በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

📚 መፅሀፍትን ስናነብ 📚 መፅሀፍት ዝም ብለው አይፃፉም። ታሪክን ከመሀረክ ከማስተላለፍ በዘለለ በአንባቢው ህይወት ውስጥ የሚፈጥሩት አንዳች ነገር ወይም አላማ አለ ተብሎ ይታመናል። 🕞 ስለዚህ ጊ
📚 መፅሀፍትን ስናነብ 📚 መፅሀፍት ዝም ብለው አይፃፉም። ታሪክን ከመሀረክ ከማስተላለፍ በዘለለ በአንባቢው ህይወት ውስጥ የሚፈጥሩት አንዳች ነገር ወይም አላማ አለ ተብሎ ይታመናል። 🕞 ስለዚህ ጊዜን ለማሳለፍና ለመዝናኛ ከማዋል በዘለለ በህይወቴ ላይ ምን ፋይዳ አመጣ ማለት መልካም ይመስለኛል።ለዚህ ደግሞ አጭር ማስታወሻን እየያዙ ማንበብ በጣም ጠቃሚ ነው። 📚 በመፅሀፉ ውስጥ ያነበብነውን ሀሳብ ወይም አንድ አረፍተ ነገር በተለያዩ ቦታዎችና በውይይቶች ላይ ማሰላሰል የመፅሀፉን አላማ ከመረዳትም በዘለለ በህይወቴ ምን ነገረኝ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ይረዳል። በእኔ አስተሳሰብ ጎበዝ እንባቢ መፅሀፍን በትንሽ ጊዜ አንብቦ የጨረሰ ሳይሆን፤ መፅሀፉን ለሚገባው ጥቅም ያዋለ ወይም በትክክል ከመፅሀፉ የተጠቀመ ሰው ነው። ስለዚህ በምናነብበት ጊዜ አጭር አጭር ነገሮችንና ዋና ሀሳቡን በመያዝ እነሱንም በማሰላሰልና ጠቃሚ ነገሮችን ከህይወታችን ጋር ለማዋሀድ ጊዜ ይኑረን!! ✅ ማንበብ መሰልጠን ነው❕ ✅ ማንበብ በእውቀት መብሰል ነው❕ ✅ ማንበብ ዕርድና ነው ❕ ✅ ማንበብ በጥሩ ቅመሞች ተቀምሞ እንደተሰራ ወጥ የራስን ስብዕና ማጣፈጥ ነው❕ ✅ የሚያነብ ሰው ዛሬንና የቀደመ በታሪክ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ይሆናል ❕ ✅ የሚያነብ ሰው ሁሌም የመፍትሄ ሰው ነው❕ ✅ የሚያነብ ሰው በወንዝ ዳር እንደተተከለ ፍሬዋንም በየግዜው እንደምትሰጥ ለምለም ዛፍ ነው❕ ◉ ማንበብ ማንበብ እና ማንበብ!! እናንብብ፤ እንወቅ፤ እንብሰል፤ እንመርምር፤ እንጠይቅ፤ እንሰልጥን‼️          ➴ማንበብ ባህል ነው ❕       ➴ማንበብ መሉ መሆን ነው❕        ➴ማንበብ መሰልጠን ነው❕ 📚 እናምብብ❕ እናምብብ❕ በማምበብ እውቀትን ትጋትን ባህልን እናሳድግ! የመፍትሄ ሰው እንሁን! ©️ 📚 ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት

💬 የዕለቱ መልዕክት... 💬 💡💡💡💡💡 🔰 በህይወት እያለህ አንተን ይበልጥ የሚገድልህ በሰዎች አልያም በፈተናዎች መጎዳትህ፣ መጎሳቆልህ፣ ወድቀሀል መባልህ ሳይሆን ዳግም የመመለስ፣ ራስህን
💬 የዕለቱ መልዕክት... 💬 💡💡💡💡💡 🔰 በህይወት እያለህ አንተን ይበልጥ የሚገድልህ በሰዎች አልያም በፈተናዎች መጎዳትህ፣ መጎሳቆልህ፣ ወድቀሀል መባልህ ሳይሆን ዳግም የመመለስ፣ ራስህን የማደስ፣ አዲስ ራዕይ እንዲኖርህ የሚያደርግ «ተስፋ» ከሌለህ ነው❗️ ወንድምና እህቶቼ ተስፋ አትቁረጡ። ➤ ጊዜው ረፍዶብኛል.....፣ ➤ ካሁን በኋላ ሁለንም የትምህርት አይነት ጨርሼ ማንበብ አልችልም ወይም ይህ ትምህርት አይገባኝም አትበሉ። አዎ ወንድምና እህቶቼ..... እስካሁን ማንበብ ካልጀመራችሁ እራሱ አሁኑኑ ጀምሩ! ✅ የምትችሉትን ሁሉ ጥረት አድርጉ፤ ጥረት ካደረጋችሁ በኋላ በአላህ ሙሉ ተስፋ ይኑራችሁ። ✅ አላህ ለቤተሰብ ደስታ፣ ለማህበረሰቡ ተድላ፣ ስኬትና ግርማሞገስ ሰበብ የሚሆንን ውጤት ይሰጣችኋል። ኢንሻአላህ!! ✍️ በወንድማችሁ:- ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ══════════════ 📚 ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት ══════════════ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇 Join our channel ➊ t.me/Grade1_4Infot.me/Grade5and6Infot.me/Grade7Infot.me/Grade8Infot.me/Grade9Infot.me/BasicComputer_Skills

Bugatti Tourbillon ይህ መኪና ዘመናዊና ቅንጡ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው የፈረንሳዩ ድርጅት Bugatti ያመረተው እጅግ ፈጣንና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የተላበሰ Bugatti Tou
+2
Bugatti Tourbillon ይህ መኪና ዘመናዊና ቅንጡ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው የፈረንሳዩ ድርጅት Bugatti ያመረተው እጅግ ፈጣንና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የተላበሰ Bugatti Tourbillon ይባላል። ይህ የዘመናችን ምርጥ መኪና ለጊዜው የተመረተው በቁጥር 25 ፍሬ ብቻ ሲሆን የአንዱ ዋጋ 3.8 ሚሊዮን ዩሮ ያወጣል። ይህን መኪና የሚገዙ ሰዎች መኪናውን በራሳቸው ምርጫ customize ይደረግላቸዋል። Logo, Personal mark, ቀለሙ፣ ውስጣዊ ዲዛይኑ እንደተመቻቸው ይስተካከልላቸዋል ተብሏል። 1000 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ የV16 engine እንዲሁም እያንዳንዳቸው 800 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጩ 3 የኤሌክትሪክ ሞተሮች ተገጥመውለታል። በአጠቃላይ ቢያንስ እስከ 1800 የፈረስ ጉልበት ማመንጨት የሚችል hybrid engine ተገጥሞለታል። መኪናው እስከ 277MPH(mile per hour) የሚደርስ ፍጥነት ሲኖረው ከቆመበት ተነስቶ 62MPH ፍጥነት ላይ ለመድረስ 2 ሰከንድ ብቻ ይፈጅበታል። Bugatti ረጅም አመት የሰበሰበውን የኢንጂነሪንግ ልህቀት በመጠቀም ይህን masterpiece የሆነ sport car እውን ማድረግ ችሏል። ➡️ወደፊት ይህን መኪና መግዛቱ አይቀርም ብላችሁ ለምታስቡት ጓደኛችሁ Share አድርጉለት።💪 ©️bighabesha

ከላይ የለቀቅኩትን ስልጠና የትኛውም ትምህርት ቤት ለተማሪዎቻችሁ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። ⭕️ PowerPoint'ን ከፈለጋችሁ በውስጥ አውሩኝ። PowerPoint'ን ግን ለመምህራን/ለርዕሰ-መምህራን/ለት/ቤት ባለቤቶች ነው የምሰጠው። ✅ ተማሪዎቻችንን በምንችለው አቅም እንደግፋቸው። ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል t.me/ReshadMuzemil

#Payroll #የሚገርም ቪድዮ ✴️ Income tax ✴️ Pension ✴️ Allowance ✴️ Net payment #እነዚህን በExcel ላይ እንዴት እንደ ሚሰራ የምታሳይ አጠር ያለች ቪድዮ ✅ MB size = 13.65MB ✅ Time = 10:02 Minutes ✅ Sound: Reshad Muzemil ✅ Prepared by: Reshad Muzemil ══════════════ ✍️ Basic Computer Skills 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 Telegram: t.me/BasicComputer_Skills tiktok.com/@basiccomputerskillst.me/Grade1_4Infot.me/Grade5and6Infot.me/Grade7Infot.me/Grade8Infot.me/Grade9Info