cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

FIDEL POST NEWS

Fast news about Ethiopia

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
15 215
Obunachilar
+5824 soatlar
+3857 kunlar
+1 52330 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
Media files
1 6990Loading...
02
በእግር ኳስ ታሪክ ከፈጣኑ ጎሎች አንዷ የተቆጠረችው ጎል። በሩስያ ሁለተኛ ሊግ የማሹክ-ኪኤምቪ ክለብ ተጫዋች ኒኮላይ ኢቫኖቭ ከመሀል ሜዳ ጨዋታው እንደተጀመረ ኪሺሚክ ዘርሺንክ ላይ ከመሀል ሜዳ የመታት ኳስ ከጎል ውላለች።
2 61613Loading...
03
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈቱ     ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈተዋል።   የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል፡፡   በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል።
2 70436Loading...
04
“ከ274 ሺህ በላይ የትግራይ ሠራዊት አባላት ትጥቅ ይፈታሉ” - ብሔራዊ የተሐድሶ ኮሚሽን የትግራይ ኃይል አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለማሰናበትና ከማህበረሰቡ ጋር ዳግም እንዲቀላቀሉ የሚያስችል የቅድመ ትግበራ ውይይት በመቀለ ተካሂዷል። በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በተካሄደው ምክክር ላይ የፌደራል መንግሥት ተወካዮች፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች እና የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል፣ አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸውን የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚህ ምክክር ላይ የትግራይ ተዋጊዎችን በመበተን እና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሃድ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክቶች መንደፍ እንዲሁም የመጀመሪያው የትግበራ እቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሶ ነበር።
2 7595Loading...
05
በአሜሪካ ላስ ቬጋስ ነዋሪ የሆኑት አንድ ቤተሰብ ሶስት ሜትር ርዝመት ያለው ሰው መሳይ ነገር በጎሮዋቸው እንደመጣና በደህንነት ካሜራ እንደተቀረፀ ተናግረዋል። በአሜሪካ ታዋቂው የፎረንሲክ ሳይንቲስት ስኮት ሮደር በላስ ቬጋስ ውስጥ ያለውን የባዕድ ቪዲዮ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል። ማመን ይቻላል?
2 56424Loading...
06
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለኢትዮጵያ መንግሥት ላይ "ውንጀላ አቅርበዋል"፤ "መንግሥት አገሪቱን እንዴት መምራት እንዳለበትም ያልተጠየቁትን ምክር ለግሰዋል" በማለት ወቅሷል። የአምባሳደሩ ንግግር "ትርጉም የማይሰጡ" እና "በበቂ ኹኔታ ያልተጤኑ" ሃሳቦችን ያካተተ ነው ያለው ሚንስቴሩ፣ አምባሳደሩ "በምርጫ የተመረጠውን መንግሥት በኃይል ለመጣል የሚሠሩ ቡድኖችንም በስም ጠቅሰዋል" በማለት ተችቷል። ኢምባሲው፣ በአምባሳደሩ መግለጫ ላይ የተንጸባረቁትን "የፍሬ ነገር ስህተቶች" ለማስተካከል ከኢምባሲው ጋር እንደሚሠራ ገልጧል። አምባሳደር ማሲንጋ ትናንት የመን የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ውስጥ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በሲቪሎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳይ በመጥቀስ "አገር ዓቀፍ የተኩስ አቁም" እንዲደረግ ጠይቀው ነበር።
3 0818Loading...
07
Media files
3 0970Loading...
08
እነ አቶ ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ! የቀድሞ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት እነ አቶ ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ።የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃን መርምሮ ብይን ሰጥቷል። የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በየደረጃው ተሳትፏቸው ተጠቅሶ የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን የተለያዩ የእርዳታ ዓይነቶችን ከመጋዘን ወጪ በማድረግ ለተረጂዎች ሳይደርስ ተሽጦ ለግል ጥቅም ውሏል በማለት የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እንዲሁም 33 እና የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁ.881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 3 እና በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ምንጩን ደብቆ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ በነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም መመስረቱ ይታወሳል። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:- https://www.fanabc.com/archives/246245
3 4383Loading...
09
ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቋል፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናቱ ተጠናቆ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለውሳኔ መላኩን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ፤ ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ስለሌላት በአሁኑ ወቅት ከሉግዘመበርግ ኢ ኤስ ኢ ኩባንያ ኢትዮ ሳትን  በመጠቀም ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡ ኢትዮ ሳት ኢትዮጵያ ለሳተላይት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከመቀነስ፣ የባህል ወረራን ከመከላከል እንዲሁም ሀገራዊ እሴትን ከማስጠበቅ አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተደራጀው የስፔስ ሳይንስና ጂኢስፓሻል ኢንስቲቲዩ፤ በቀጣይ ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቆ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር  መላኩንና ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። Via EBC
3 4665Loading...
10
ቦይንግ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ክስ ሊመሰርትበት እንደሚችል ተገለፀ በኢትዮጵያው አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው የ737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346  ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው አደሳ ምክንያት ቦይንግ ላይ ክስ ለመመስረት እያጤነ እንደሆነ የአሜሪካ የፍትህ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ቦይንግ የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከ3 ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነት መጣሱንም መስሪያ ቤቱ ስለመግለፁ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል። ቦይንግ ስምምነት ጥሷል የተባለውን ክስ አስተባብሏል። ይህ አስከፊ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ በኢትዮጵያው 157 እንዲሁም በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ 189 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ይታወሳል።
3 7324Loading...
11
በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይፈለጉ የነበሩ የመጨረሻው ሁለት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተከሳሾች መሞታቸውን ማረጋገጡን በጉዳዩ ላይ የተቋቋመው ችሎት አስታውቋል። ርያንዱካዮ በሚል ስም ብቻ የሚጠራው እና ቻርለስ ሲኩብዋቦ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ጉዳይ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ችሎት ሲፈለጉ የነበሩ የመጨረሻዎቹ ተከሳሾች ናቸው። በብሔራዊ ደረጃ ግን አሁንም ድረስ ከ1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በመፈለግ ላይ ናቸው። 2ቱ ግለሰቦች ከ30 ዓመት በፊት 800 ሺ ቱትሲዎችን እና ለዘብተኛ ሁትዎችን በጨረሰው የዘር ፍጅት ላይ ተሳትፎ አላቸው በሚል ለሩዋንዳ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በእ.አ.አ 1995 ክስ ቀርቦባቸው ነበር። ሲኩብዋቦ በእ.አ.አ 1998 በቻድ መሞቱን እና በዛው መቀበሩን እንዲሁም ርያንዱካዮ ደግሞ ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከሸሸ በኋላ ከዛም ወደ ዛየር ተሻግሮ ኪንሻሳ ላይ በ1998 ሕይወቱ ማለፉን ፍ/ቤቱ አስታውቋል። በሩዋንዳው የዘር ፍጅት ጉዳይ በዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ሲፈለጉ የነበሩ ተከሳሾች ሁሉ መለየታቸውንም ችሎቱ አስታውቋል። #ቪኦኤ
3 7343Loading...
12
Media files
3 5640Loading...
13
በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ችግር የማዕድን ዘርፉን እየጎዳው ነው ። የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን  የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ሀላፊ  ካሳሁን ለምለሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ሁኔታም ያለንን ሀብት በተገቢው መልኩ እንዳንጠቀም አድርጎናል ብለዋል ፡፡ በሀገራችን በሚገኙ በርካታ ክልሎች ከፍተኛ የሆነ የማዕድን ክምችት እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ ባለ ሀብቶች ወደ ማዕድን ኢንዱስትሪ ከገቡ ሀገሪቱ ከዘርፉ ከፍተኛ ጥቅም ታገኛለች ተብሎ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል፡፡ ማዕድን ለማውጣት የሚያግዙ ከውጪ የሚገቡ ማሽነሪዎች ለማስገባት የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ መሆን እና  የመሰረተ ልማት ችግር  ሌላኛው በዘርፉ የሚነሳ እንቅፋት መሆኑን አቶ ካሳሁን ጠቅሰዋል፡፡ ተቋሙ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለማስተካከልም በማምረት ፣በፍለጋ፣በጥናት እና በማዕድን ሽያጭም ከፍተኛ ስራ ለመስራት የቅድመዝግጅት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ አሁን ካሉት በተጨማሪ በተለያዮ አካባቢዎች ላይ አዳዲስ ሳይቶች እየከፈቱ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። የወርቅ ምርቶችን ፣ኢንዱስትሪ ማዕድናትና የከበሩ ድንጋዮችን ለደንበኞቹ በመላክ ለሀገራችን የውጪ ምንዛሬ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
3 7904Loading...
14
በኢንተርፓል ተይዘዋል የተባሉት ዳዊት ገ/እግዚአብሔር ማናቸው? https://youtube.com/watch?v=8r1EIXDDrRI&si=AaGS_Q5CbZ8weMyw
3 6761Loading...
15
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ከማሸግ የዘለለ እርምጃ መዉሰድ የሚያስችለውን አዋጅ ማዘጋጀቱ ተነገረ! ባለስልጣኑ ባዘጋጀው በዚህ አዋጅ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ሕገ ወጦች ላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ አንቀጾች መካተታቸውን ተጠቁመዋል። አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን በነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያለ እንደሌለ ማስመሰል፣ የነዳጅ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መሸጥ፣ ነዳጅን በተለያዩ ስፍራዎች ደብቆ ማስቀመጥና የመሳሰሉትን ህገወጥ አሰራሮችን ሊያስቀር እንደሚችልከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
3 7371Loading...
16
የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ የማዋሃድ የቅድመ ማስጀመሪያ ምክክር በመቀለ ተጀመረ! የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣መበተን እና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ የማዋሃድ የቅድመ ማስጀመሪያ ምክክር በትግራይ መዲና መቀለ ተጀመረ።ትናንት ግንቦት 5/ 2016 ዓ.ም በተጀመረው በዚህ ምክክር ላይ የፌደራል መንግሥት ተወካዮች፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች እና የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል፣ አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸውን የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚህ ምክክር ላይ ተዋጊዎችን በመበተን እና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ወደ ህብረተሰቡ ለማዋሃድ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክቶች መንደፍ እንዲሁም የመጀመሪያው የትግበራ እቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሷል። ኮሚሽነሩ በተጨማሪም “ተዋጊዎች የሚበተኑበት የተመረጡ ስፍራዎች የመስክ ጉብኝት እንደሚካሄድም” በትናንትናው ዕለት ባሰፈሩት የኤክስ መልዕክታቸው ጠቁመዋል።ለሁለት ዓመት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ የቋጨው የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማስቆም ስምምነት እና የናይሮቢ የትግበራ ሰነድ የትግራይ ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ማውረድ የሚካሄደው የውጭ እና የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት ያልሆኑ የክልል ኃይላት ከትግራይ በተመሳሳይ ወቅት ሲወጡ እንደሆነ ጠቅሷል። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:- https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2001z2zdxo
4 2033Loading...
17
በጂንካ የ8 ዓመት ታዳጊን  አስገድዶ ግብረ ሶዶም  ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ  ጽኑ እስራት ተቀጣ በጂንካ ከተማ በ8 ዓመት ታዳጊ ልጅ ላይ የአስገድዶ ግብረ ሶዶም   መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት እንደተቀጣ የጂንካ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡ የጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔዉን በተከሳሹ ላይ አስላልፎበታል፡፡ተከሳሽ ወጣት ማንያዘዋል አዳሙ  የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አከባቢ ድርጊቱን መፈፀሙን በማመኑ ባመነው መሰረት ማስረጃ መስማት ሳያስፈልግ  ውሳኔ እንደተሰጠ የጂንካ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት  አቶ በቃሃኝ ጥላሁን  በተለይም  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ። ተከሳሽ የግል ተበዳይን እኔ ጋር  አሳድራለው በማለት ከቤተሰቦቹ  በመውሰድ ህፃኑን አስገድዶ  ግብረ ሶዶም ወንጀል  መፈፀሙ አረጋግጧል ። አሰገድዶ የመድፈር ወንጀል የደረሰበትን ህፃን ለጤናም ሆነ ለስነ-ልቦና ጉዳት የሚዳርግ ተግባር ከመሆኑ አንጻር በጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው  ውሳኔ ተከሳሽንና ሌሎችንም  መሠል ወንጀል አድራጊዎችን የሚያስተምር ውሳኔ አስተላልፎበታል፡ በመሆኑም  ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት አስገድዶ ግብረ ሶዶም መፈፀሙን ሙሉ በሙሉ በችሎት ቀርቦ በማመኑ የጂንካ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት  በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ  መወሰኑን አቶ በቃኀኝ ጥላሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ፡፡ በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
4 0895Loading...
18
Media files
4 5220Loading...
19
ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል። የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል ። [Capital]
4 8902Loading...
20
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደዊ ቀጭኒ ወረዳ አይሱዙ የጭነት መኪና ተገልብጦ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ አስታውቋል ። አደጋው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 13298 አዲስ አበባ የሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ከጊንድሂር ወደ ደዊ ቀጭኒ ወረዳ ልዩ ቦታው ሶፉማር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ተገልብጦ መድረሱ ተገልጿል ። በዚህ ምክንያት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ሃላፊ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ አምባቸው ተናግረዋል ። ሃላፊዋ አያይዘውም ለአደጋው መከሰት መንስኤው የመንገድ ደህንነት ችግር መሆኑን ገልፀዋል ።
4 7452Loading...
21
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዓባይ ወንዝ ድልድይን መረቁ ዛሬ የተመረቀው ዘመናዊ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት እንዳለው ተገልጿል፡፡ በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
5 1314Loading...
22
Media files
4 6984Loading...
23
የመራጮች ምዝገባ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ምርጫ ለማከናወን ዝግጅቶች እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ከሚያዝያ 21 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው ቦርዱ የገለጸው፡፡ ነገር ግን የመራጮች ምዝገባ በወጣበት የጊዜ ሰሌዳ ወቅት ተደራራቢ የሕዝብና የሃይማኖት በዓላት ስለነበሩ፣ የመራጮች ምዝገባ የሚደረግባቸው አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱ ባለመከፈታቸው ብሎም በምርጫ የሚወዳደሩት የፓለቲካ ፓርቲዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ የመራጮች ምዝገባ ቀን እንዲራዘም በመጠየቃቸው የመራጮችን የምዝገባ ቀን እስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ማራዘሙን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ምርጫ በሚካሄድባቸው ምርጫ ክልሎች የሚገኙ መራጮች የተሰጠውን የመራጮች የምዝገባ ወቅት በመጠቀም ለምዝገባ ብቁ የሚያደርጉ ማስረጃዎችን በመያዝ በየአካባቢያቸው በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት በመራጭነት መመዝገብ እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡
4 6983Loading...
24
የ10 ዓመት ታዳጊን ዋና ካልዋኘህ በማለት ውሃ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል የተባለ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን  ጃርቱ ወረዳ ሙለታ  ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የ10 ዓመት ታዳጊ ውሃ ውስጥ ዘሎ ለመዋኘት ሲገባ ህይወቱ ማለፉን  የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ገልጿል፡፡ ተከሳሽ አንሴ አህመድ የተባለው የ20 ዓመት ወጣት  10 ዓመት ከሆነው  ሙዓዝ  ጋር እየተጫወቱ  በነበረበት  ሰዓት ለምን አትዋኝም የሚል ጥያቄ ሲያቀርብለት መዋኘት አልችልም  የሚል ምላሽ ሲሰጠው  እንዴት ትፈራለህ ወንድ አደለህ ወይ  ግባ  በማለት ወደ ውሃ ዘሎ  እንዲገባ ገፋፍቶት ለሞት ምክንያት እንደሆነ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ካሚል ቱጅሃን በተለይም  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በሰዓቱም የ10 ዓመት ታዳጊው ለመዋኘት  ተንደርድሮ ሲገባ  ውሃው ውስጥ ያለው ድንጋይ ላያጭንቅለቱ ላይ ያርፋል በዚህም አደጋ ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።  በሁኔታው የተደናገጠው  አንሴ  ልጁን ለማውጣት ይሞክራል። በአካባቢው የነበሩ ነዋሪዎች ደርሰው ተጋግዘው ያወጡታል ይሁን እና ልጁ ጭንቅላቱ ላይ ከባድ ግጭት አጋጥሞት ከውሃ ውስጥ ሳይወጣ  ህይወቱ ማለፉን ይረዳሉ ስለሆነም አደጋውን ለፖሊስ ያሳውቃሉ :: ፖሊስም  አስከሬኑን  ወደ ሆስፒታል ወድያውኑ በመላክ   ምርመራውን ማጣራት ይጀምራል  ተከሳሽም ልጁ ውሃ ውስጥ ሲገባ ልረዳው ነው የገባሁት እንጂ ምንም የማውቀው  ነገር የለም የሚል ምላሽ ቢሰጥም  በአካባቢው የነበሩ የሁለቱን ንግግር ያዳመጡ ምስክሮች ቃላቸውን ይሰጣሉ ፖሊስም በህክምና እና በሰው ማስረጃ መዝገቡን በማደራጀት  ለዓቃቢህግ ይልካል፡፡ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ  ቤት  ዓቃቢ ህግ ባቀረበው መሰረት ተከሳሸ ሆን  ብሎ ለአደጋ በሚጥል መንገድ ሰውን  በመገፋፋት የግድያ ወንጀል በመፈጸም የተመሰረተበት ክስ  በመመልከት  በተከሳሽ አንሴ አህመድ  ላይ  በ7 ዓመት ከ8 ወር እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ  የተላለፈበት መሆኑን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ካሚል ቱጅሃን ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
5 2003Loading...
25
አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት "የቅስቀሳ ወንጀል" ጥፋተኛ ተባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምስራቅ አዉስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት የገዳማት መምሪያ የበላይ ሃላፊ ሊቀጳጳስ አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት "የቅስቀሳ ወንጀል" የጥፋተኝነት ፍርድ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ችሎት ተላለፈባቸው። ከ3 ወራት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ስር እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች አቅርቦባቸዋል። በቀረበባቸው ክስ ላይ፤ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በጵጵስና በማገልገል ላይ እያሉ ስለ ሰላም እና አንድነት የመስበክ ሃይማኖታዊ ግዴታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ በታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገረ አሜሪካ ቴክሳስ እና አካባቢዉ በሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተክርስቲያን ታቦት ወጥቶ በቆመበት አዉደምህረት ላይ በመገኘት "የአመፅ ቅስቀሳ" ማድረጋቸውን ዐቃቤ ሕግ በዝርዝር ጠቅሷል። በዚህ በቀረበባቸው ክስ ላይ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሌሉበት የተከሰሱባቸው ክሶች በአንቀጽ 247 (ሐ) ስር ተጠቃሎ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶባቸዋል። ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ፋና ዘግቧል።
4 2464Loading...
26
መገኛውን በወሰን ካራ ያደረገው ዋርካ አካዳሚ የምርቃት መርሐግብር ተካሄደ የዋርካ አካዳሚ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርቃት ስነስርዓት  መክፈቻ ግንባት 3/2016 ዓ.ም በትምህርት ቤቱ ጊቢ ውስጥ ተካሂዷል ። የምርቃት በዓሉ አከባበር በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ግንቦት 10 እና 11 ለሁለት ቀናት  የካርኒቫል ፌስቲቫል  እንደሚከናወንና ለሁሉም ክፍት በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በተለያዩ ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጦች  መዝናናትና  ትምህርት ቤቱን መጎብኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል። ዋርካ አካዳሚ ከትምህርት አመራርና  ፔዳጎጂ፣ከሳይኮሎጂ፣ በአለምአቀፍ ኪነጥበብ፣ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ከባንኪንግና ከአለም አቀፍ ፋይናንስ አመራር ሙያዎች በተውጣጡ ባለሙያዎች እንደተቋቋመና የተማሪዎችን የፈጠራ መንፈስ የማያነቃቃና በትምህርት ብቃትና በቴክኖሎጂ እውቀት የሚጎለብቱበት አቅም ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልጸዋል ። ትምህርት ቤቱ በአንድ  ክፍል ውስጥ  የሚገኙ የተማሪዎች ብዛት እስከ 25 ብቻ በመጠን ለእያንዳንዱ ተማሪ ተገቢውን ትኩረት በመስጠትና የአገር አቀፍ ካሪኩለም ህግ  በመከተል የመማር ማሰተማር ስርዓቱን እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል። በመጪው አመትም 2017 ዓ.ም ተማሪ ዎችን ተቀብለው ማስተማር አንደሚጀምሩ  አሳውቀዋል ። በአገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ  በትምህርት ተቋማት ጋር ትብብር በመፍጠር ተጨማሪ እሴቶችን መሰብሰብም የእቅዱ አካል እንደሆነና እስካሁንም ዋርካ ደቬንቸር ከተሰኘው በስዊዘርላንድ የሚገኝ ተቋም ጋር ያደረገ ሲሆን፣ ደቬንቸር ለዋርካ መምህራን የኦንላይን  ስልጠናዎችን በመስጠት በተፈለገው መስክ ኤክስፐርት የሆኑ አማካሪ ባለሙያዎችን በማቅረብና ወደፊትም ፈቃደኛ መምህራንን በዋርካ አካዳሚ በማምጣት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መስማማታቸውን ገልጸዋል።
3 9052Loading...
27
Media files
4 6112Loading...
28
የ52 አመቱ አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይ ሻኪል ኦኔል ከ21 አመት ፍቅረኛው ጋር በስፔን ሲዝናና።
4 08120Loading...
29
በዓለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ባለው የኦንላየን የቻይና የችርዘቻሮ ንግድ ላይ የሚሰሩ ሰዎች አንዲህ ፋታ ቤለለው ስራ ይጠመዳሉ። በቀን 12 ሰዓት ሲሰሩ 240 ዩዋን ወይም ወደ 30 የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ያገኛሉ።
3 8805Loading...
30
በደቡብ ኢትዮጵያ 148 ቀበሌዎች ከ75 ሺህ በላይ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተነገረ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ ተከትሎ 148 ቀበሌዎች ከ75 ሺህ በላይ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ለጎርፍና ለአፈር ናዳ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸው የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋንታ ጋምአ ለኢዜአ እንደገለጹት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ የበልግ ዝናብ ስርጭት በክልሉ የጎርፍና የአፈር ናዳ አደጋዎችን ሊያስከትል ይችላል። በተለይ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ አሌ እና አሪ ዞኖች ለጎርፍና ለናዳ እንዲሁም ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶና ጌዴኦ ዞኖች ለጎርፍ አደጋ የመጋላጥ ስጋት ያለባቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በክልሉ የአደጋ ተጋላጭ አካባቢዎችን በመለየት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የቅድመ መከላከል ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
3 9462Loading...
31
8.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት የእህተ ማርያም አገልግል ባህላዊ እና ዘመናዊ ምግብ ቤት ተመርቆ ተከፈተ። አገልግል ባህላዊ እና ዘመናዊ ምግብ ቤት ተመርቆ ተከፈተ። ጀሞ ሚካኤል አከባቢ ዛሬ ግንቦት 2/2016 ዓም ተመርቆ የተከፈተው ምግብ ቤቱ አልኮል እና ቡና እንደማይሸጥበት ተነግሯል። ሙሉ በሙሉ ኦርጋኒክ የሆኑ ምግቦች የሚሸጡበት ቤት እንደሆነ ማርኬቲግ ማናጀር አቶ ዮናስ መልካሙ ተናግሯል። ለምግብ አንደኛ ደረጃ የምግብ ዘይት እንደሚጠቀሙ የተናገሩት አቶ ዮናስ ከአልኮል በተጨማሪ የለስላሳ መጠጥ በአገልግል አይሸጥም ብሏል። ብርዝ እና የሎሚ ውኃ ብቻ እንደሚሸጥም ተነግሯል። ምግቦቹ ሙሉ በሙሉ ከማዳበሪያ ነፃ ሆኖ የበቀሉ እህሎች እንደሚዘጋጅ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም ከራሳቸው የእርሻ መሬት እንደሚያመርቱ ተናግሯል። አገልግል ምግብ ቤት ለ60 ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረ የቤቱ ባለቤት እህተ ማርያም ተናግሯል። 8.5 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሆነበት ተነግሯል። የቤቱ ባለቤት እህተ ማርያም ቤቱ የተከፈተበት አንድ ሰው እርዱልኝ ከምል የስራ እድል ከፍቼ ሰርተው ቢበሉ የሚል እምነት ስላለኝ ነው ብለዋል።
3 49510Loading...
32
Media files
3 1924Loading...
33
በድጋሜ እና ቀሪ ምርጫ አንሳተፍም ሲሉ እናት ፓርቲ እና መኢአድ አስታወቁ፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አንደኛዉ መገለጫ ሕዝብ በነፃ ምርጫ በመረጠዉ አካል እንዲተዳደር መቻሉ መሆኑ ነው የሚለው መግለጫው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ በ6ተኛዉ ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ምርጫ ባልተከናወነባቸዉና ድጋሜ ምርጫ በሚደረግባቸዉ አካባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንቅስቃሴ  እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የተጠቀሰዉን ምርጫ አስመልክቶ አገር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ከመሆኗ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ካለዉ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ኹኔታዎች እንደሌሉ በመጥቀስ አስቻይ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ ምርጫዉ እንዲዘገይ ቦርዱን በደብዳቤ መጠየቃችን ይታወሳል የሚለው የፓርቲዎቹ መግለጫ፡፡ ይሁን እንጂ ቦርዱ ያቀረብነዉን ጥያቄ ከግንዛቤ በማስገባት የተጠየቀዉን ማስተካከያ ማድረግ ባለመቻሉ በተጠቀሰዉ ቀሪና ድጋሜ ምርጫ የማንሳተፍ መሆናችንን ለሕዝባችን በይፋ እናደርጋለን ሲሉ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
3 2393Loading...
34
Media files
3 0240Loading...
35
230 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡ ከሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከኦማን ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 460 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡ በኦማን የሚገኙ 1 ሺህ 590 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ለመመለስ መታቀዱ የሚታወስ ነው። #ዳጉ_ጆርናል
3 4061Loading...
36
አንዳንዴ እንዲህ ያሰኛል
3 43510Loading...
37
በሀላባ ዞን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ! በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡በዞኑ ዌራ ዲጆ ወረዳ ትናንትና የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል፡፡ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ካለፉት ውስጥ የሶስቱ አስክሬን ሲገኝ፤ የሁለቱ አስክሬስ እስካሁን እንዳልተገኘ ተጠቁሟል፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን÷ በቀጣይም ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በተለይም ሕብረተሰቡ የጎርፍ ማፋሰሻ ቦታዎችን ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርግ አስገንዝበዋል፡፡በጎርፍ አደጋው ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም የተሰማቸውን ሀዘን እንደገለጹም የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃን ያመላክታል፡፡ Via FBC
3 5871Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
1🔥 1
00:14
Video unavailableShow in Telegram
በእግር ኳስ ታሪክ ከፈጣኑ ጎሎች አንዷ የተቆጠረችው ጎል። በሩስያ ሁለተኛ ሊግ የማሹክ-ኪኤምቪ ክለብ ተጫዋች ኒኮላይ ኢቫኖቭ ከመሀል ሜዳ ጨዋታው እንደተጀመረ ኪሺሚክ ዘርሺንክ ላይ ከመሀል ሜዳ የመታት ኳስ ከጎል ውላለች።
Hammasini ko'rsatish...
👍 13😱 1
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈቱ     ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈተዋል።   የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል፡፡   በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 13
Photo unavailableShow in Telegram
“ከ274 ሺህ በላይ የትግራይ ሠራዊት አባላት ትጥቅ ይፈታሉ” - ብሔራዊ የተሐድሶ ኮሚሽን የትግራይ ኃይል አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለማሰናበትና ከማህበረሰቡ ጋር ዳግም እንዲቀላቀሉ የሚያስችል የቅድመ ትግበራ ውይይት በመቀለ ተካሂዷል። በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በተካሄደው ምክክር ላይ የፌደራል መንግሥት ተወካዮች፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች እና የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል፣ አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸውን የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚህ ምክክር ላይ የትግራይ ተዋጊዎችን በመበተን እና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሃድ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክቶች መንደፍ እንዲሁም የመጀመሪያው የትግበራ እቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሶ ነበር።
Hammasini ko'rsatish...
👍 7😁 7
00:37
Video unavailableShow in Telegram
በአሜሪካ ላስ ቬጋስ ነዋሪ የሆኑት አንድ ቤተሰብ ሶስት ሜትር ርዝመት ያለው ሰው መሳይ ነገር በጎሮዋቸው እንደመጣና በደህንነት ካሜራ እንደተቀረፀ ተናግረዋል። በአሜሪካ ታዋቂው የፎረንሲክ ሳይንቲስት ስኮት ሮደር በላስ ቬጋስ ውስጥ ያለውን የባዕድ ቪዲዮ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል። ማመን ይቻላል?
Hammasini ko'rsatish...
🤔 10🤯 4😱 2🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለኢትዮጵያ መንግሥት ላይ "ውንጀላ አቅርበዋል"፤ "መንግሥት አገሪቱን እንዴት መምራት እንዳለበትም ያልተጠየቁትን ምክር ለግሰዋል" በማለት ወቅሷል። የአምባሳደሩ ንግግር "ትርጉም የማይሰጡ" እና "በበቂ ኹኔታ ያልተጤኑ" ሃሳቦችን ያካተተ ነው ያለው ሚንስቴሩ፣ አምባሳደሩ "በምርጫ የተመረጠውን መንግሥት በኃይል ለመጣል የሚሠሩ ቡድኖችንም በስም ጠቅሰዋል" በማለት ተችቷል። ኢምባሲው፣ በአምባሳደሩ መግለጫ ላይ የተንጸባረቁትን "የፍሬ ነገር ስህተቶች" ለማስተካከል ከኢምባሲው ጋር እንደሚሠራ ገልጧል። አምባሳደር ማሲንጋ ትናንት የመን የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ውስጥ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በሲቪሎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳይ በመጥቀስ "አገር ዓቀፍ የተኩስ አቁም" እንዲደረግ ጠይቀው ነበር።
Hammasini ko'rsatish...
👎 7👍 4😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
እነ አቶ ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ! የቀድሞ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት እነ አቶ ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ።የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃን መርምሮ ብይን ሰጥቷል። የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በየደረጃው ተሳትፏቸው ተጠቅሶ የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን የተለያዩ የእርዳታ ዓይነቶችን ከመጋዘን ወጪ በማድረግ ለተረጂዎች ሳይደርስ ተሽጦ ለግል ጥቅም ውሏል በማለት የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እንዲሁም 33 እና የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁ.881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 3 እና በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ምንጩን ደብቆ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ በነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም መመስረቱ ይታወሳል። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:- https://www.fanabc.com/archives/246245
Hammasini ko'rsatish...
👍 5 2
ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቋል፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናቱ ተጠናቆ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለውሳኔ መላኩን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ፤ ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ስለሌላት በአሁኑ ወቅት ከሉግዘመበርግ ኢ ኤስ ኢ ኩባንያ ኢትዮ ሳትን  በመጠቀም ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡ ኢትዮ ሳት ኢትዮጵያ ለሳተላይት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከመቀነስ፣ የባህል ወረራን ከመከላከል እንዲሁም ሀገራዊ እሴትን ከማስጠበቅ አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተደራጀው የስፔስ ሳይንስና ጂኢስፓሻል ኢንስቲቲዩ፤ በቀጣይ ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቆ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር  መላኩንና ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። Via EBC
Hammasini ko'rsatish...
😁 11👍 7

👍 8😱 2 1