cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Shega Media - ሸጋ ሚድያ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚወጡ ማንኛውንም አዝናኝ ዜናዎች በአንድ ቦታ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
45 918
Obunachilar
-4824 soatlar
-4307 kunlar
-96930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

" እናቴ አባቴን ለማስታመም ስትል የጠወለገች ፡ አበባ ነበረች " ከበፊት ጀምሮ ድምጻዊ ቡዜማንን በተመለከተ ብዙ ሞራል የሚነኩ ቀልዶችን እናያለን ፡ ግን እያንዳንዱ መርዛማ ቀልድ ይህንን ወጣት ሊጎዱ እንደሚችሉ አስበን አናውቅም ። ቤተሰቡን ለማኖር ፡ ለአመታት ታመው ያለፉትን አባቱን ለማስታመም ሲሉ የተንገላቱ ፡ የደከሙ ፡ በመጨረሻም አባቱ ካለፉ በኋላ ፡ በህመም ላይ የወደቁትን እናቱን ለመርዳት ፡ እህቱን ለማስተማር ፡ ክለብ ዘፍኖ ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ለሊቱን እያነጋ ህይወትን ለማሸነፍ ፡ በሙያው የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚጥር እናውቅም ። ግን ሳይደርስብን ለርካሽ ላይክ እና ሰውን ለማሳቅ ብለን የሰወችን ልብ እናቆስላለን ። ይህ ጉዳይ በጣም እጅ እጅ ስላለ ነው ዛሬ ሰይፉ ቡዜማንን ተፋቱት ያለው ። ይህ ጉዳይ ዛሬ በቡዜማን ሰማነው እንጂ የብዙ ሰወች ታሪክ ነው ። ከያንዳንዱ ሙድ ከምንይዝበት ሰው ጀርባ ያለውን ታሪክ አናውቅም ። ለርካሽ ላይክና ለአጉል ቀልድ ስንል ሰወች ላይ ባንዘባበት መልካም ነው ። ✍️ዋሲሁን ተስፋዬ 👉የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ: https://t.me/+mGvhgC8uMxRjZGZk
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
መልካም የዕናቶች ቀን ❤ ❤😥 አምስተኛ ክፍል ማጥናት፤ ትምህርት በደንብ መማር፣ መከታተል ጀመርኩ ። ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛ ወጣሁ ደስስ አለኝ። ለእናቴ ስበር ሄጄ ነገርኳት : ሎተሪ እንደደረሰው ሰው ፊቷ ፈካ። ትክ ብላ አይታኝ፤ "ስጋሃ?" አለችኝ (እውነት! እንደማለት ነው ) "ስጋሂ" አልኳት። ግንባሬን፣ አንገቴን ሳመችኝ ። "ጎበዝ ዝወደይ: ከማኻስ ዓሰርተ ዘይምወለድኩ " ( እንዳንተ አስር ልጅ በወለድኩ) ብላ አገላብጣ ደግማ ሳመችኝ። "ወሊድካ ተሓጎስ" (በልጅህ ደስ ይበልህ) "ተመስገን : ተመስገን: ምን ይሳንሃል ጌታዬ " ብቻዋን ከጌታዋ ጋር አጉተምትማ ስታበቃ ፤ "ምን ልግዛህል" አለችኝ ? "ኮካ ኮላ እና ጮርናቄ " አልኩ ከጉያዋ መሃረብ አውጥታ ጭምትር ያለች አምስት ብር ሰጠችኝ :ገዝቼ መጣሁ። "ብላ አባ ዘወደይ" "አንቺ አትበይም?" "ጠግቤያለሁ፤ ደግሞ እኔ ለስላሳ አልወድም አበሩ ጋር ጠላ ጠጥቻለሁ። በሚቀጥለው ደግሞ አንደኛ ትወጣለህ አይደል? " አለችኝ። "እንደዚህ ደስስ የሚልሽ ከሆነ እ'ማ እወጣልሻለሁ ። " "መጣሁ : ቤቱን ጠብቅ" ብላ የሆኑ ከቀበሌ የመጡ የእርዳታ ድርጅቶች የገዙልንን ትልቅ ድስት ይዛ ወጣች: ብዙ ቆይታ መጣች ። ስትመጣ ብረት ድስቱን አልያዘችውም። በብረት ድስቱ ፈንታ ጥቁር ፌስታል ይዛለች። ጥቁሩ ፌስታል የያዘውን ስታወጣው አመድማ ሸራ ጫማ እና ጥልፍልፍ ነጭ ክፍት ዘለበታም የባሊያችንን ቀለም የመሰለ ጫማ ገዛችልኝ ። ደስታ ሊገለኝ ደረሰ። ጋዴ ማድረግ አቆምኩ :ጋዴ ጫማዬ ተጣለ ። ቆይቶ በጣም ቆይቶ ነው በእርዳታ የተሰጠንን ድስቷን ሸጣ ጫማ እንደገዛችልኝ ያወኩት ። የዚህች እናት ልጅ ሆኜ እንዴት መስነፍ ይቻለኛል ?! ✍️በአድሃኖም ምትኩ 👉የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ: https://t.me/+mGvhgC8uMxRjZGZk
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
‹‹ዛሬ በባህርዳር ከተማ የተመረቀው የአባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው። ከግዘፋዊ ቁሳዊ መዋቀሩ ባሻገርም ልዩነቶችን የማጥበብ፤ በተቃራኒ ጎራ ላሉ ሰዎች መገናኛ ድልድዮችን የማነፅ ርዕያችን መዘርጊያ ምልክት ነው። ኅብረታዊ ምሉዕነትን ለማፅናት ከክልላዊ ወሰኖች የሚሻገር ትርክት የመቅረፅ ትልማ ማሳያ ነው። ግባችን በክልከላ እና ቁንፅልነት የሚመሩ የአእምሮ ውቅሮች እና ትርክቶችን በማስወገድ በሁሉም ዘንድ ትብብርን እና አንድነት ማሳደግ ነው።›› -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
ዛሬ ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል 🔥 በሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ደጋፊዎችን ያፈሩት ከቀድሞው የፕሪምየር ሊግ ምስረታ ጀምሮ በከፍተኛ ትንቅንቅ ይፎካከሩ የነበሩት አሁን እንዱ እንደስሙ ማደር የተነሳነው አንዱ ከቀድሞ ስሙን ለመመለስ በመጣር ላይ ሆነው በሊጉ 37ኛ ሳምንት ተገናኝተዋል። የሁለቱ ጨዋታ ሲኖር ዲኤስቲቪ ቤቶች በቶሎ ይሞላሉ ጠጠር መጣያ እስኪታጣ ድረስ ወንበሮች ጢም ብለው ይሞላሉ ብሽሽቁ ይደራል ነቆራው ከየቦታው ይሰማል ለ 90 ደቂቃም ከተማው ፀጥ ረጭ ይላል። 37ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪምየር ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል የጨዋታ ሰዓት - አመሻሽ 12:30 🏟️ ስታድየም - ኦልድትራፎርድ ማን ያሸንፋል…? ዩናይትድ የመድፈኞቹን ጉዞ ያደናቅፋል ወይስ መድፈኞቹ ቀያይ ሴይጣኖችን አጋድሞ ያልፋል? የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1
በዚህ መርሐግብር መሰረት ተዘጋጁ👆 የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡ መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና:— ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል። የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
Hammasini ko'rsatish...
ከፒያሳ በሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ለኮሪደር ልማት ፕሮጀክት 3,250 አባወራዎች ይነሳሉ ተባለ ከፒያሳ በመነሳት በሳር ቤት በኩል እስከ ወሎ ሠፈር ድረስ የሚገነባው አዲሱ የኮሪደር ልማት፣ 3,250 አባወራዎችን ወይም ከ14 ሺሕ በላይ ሰዎችን እንደሚያስነሳ ተመላከተ፡፡ ተነሺዎችን ለማስፈር 21 ሔክታር መሬትና ስድስት ቢሊዮን ብር የካሳ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡ ከአሥር ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ከፒያሳ በመነሳት እስከ ብሔራዊ፣ ከብሔራዊ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሳር ቤትና ከሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ተብሎ በአምስት ንዑስ ፕሮጀክቶች ተከፋፍሎ ዲዛይን እንደወጣለት ሪፖርተር የተመለከታቸው የዲዛይን ዶክመንቶች ያሳያሉ፡፡ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ አምስት ክፍላተ ከተሞችን የሚነካ ሲሆን እነዚህም አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክና ቦሌ ናቸው፡፡ ጠቅላላ ፕሮጀክቱ 460 ሔክታር መሬት ይዞታ የሚነካ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 114 ሔክታር ለመልሶ ማልማት ነፃ እንደሚደረግ ዶክመንቱ ያሳያል፡፡ ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም 40 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለአብነት ያህል ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ለፈጣን የአውቶቡስ መስመር ግንባታ ይውላል፡፡ ስድስት ቢሊዮን ብር ለማኅበራዊ ቤቶች ግንባታ፣ ስድስት ቢሊዮን ለተነሺዎች ካሳ ክፍያ፣ አራት ቢሊዮን ብር ለመንገድ ግንባታ፣ ሦስት ቢሊዮን ለፓርክ (Green Park) ተመድቧል፡፡ በተጨማሪም የፓርኪንግ ቦታዎች፣ ሰባት ያህል ድልድዮች፣ የመሠረተ ልማትና የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች ይገነባሉ፡፡ ወጪ የሚደረገውን 40 ቢሊዮን ብር በአምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ለማስመለስ መታቀዱንም ሰነዱ ያመለክታል፡፡ በኮሪደር መስመሩ ላይ መንግሥት 114 ሔክታር መሬት ነፃ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን፣ ይኼንን መሬት 70 ሺሕ ብር በካሬ ለአልሚዎች በማከራየት በአምስት ዓመት ውስጥ 99 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ዶክመንቱ ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዚህ መስመር ላይ መንግሥት ሊያከራያቸው ካቀዳቸው የመኖሪያ፣ የንግድና የቢሮ ሕንፃና ቤት ከ5.8 ቢሊዮን ብር በላይ በየዓመቱ ገቢ ለማስገኘት መታቀዱ ታውቋል፡፡ ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ አብዛኛው ቦታ ለአረንጓዴ ልማት ማለትም ለሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ታቅዷል፡፡ አምባሳደር አካባቢ ያለው የመከላከያ ሚኒስቴር ግቢ ሙዚየም፣ ካፌና መዝናኛ የሚኖረው የባህል ማዕከል እንደሚቀየር ዲዛይኑ ያሳያል፡፡ የሰይጣን ቤት ተብሎ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ያለው ቦታ ወደ ባህል ማዕከልና መዝናኛ ቦታ በመጠነኛ ለውጥ ያደርጋል፡፡ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት ያለው 1.2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ‹‹የአፍሪካ ማዕከል›› ለመገንባት ይውላል፡፡ ማዕከሉ ሙዚየም፣ ላይብረሪ፣ የባህልና መዝናኛዎች ሲኖሩት አጠቃላይ አካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ ያለው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አገልግሎት ይቀየራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሜክሲኮ ሳር ቤት ባለው ንዑስ ፕሮጀክት ከታሰቡት ብዙ ዕቅዶች ውስጥ ሆስፒታልና አዲሱ ቱሞሮ (Adisu Tomorrow) ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ይገኝበታል፡፡ በዚህ አካባቢ ከአራት ወለል ሕንፃ (G+4) በታች የሆኑ ሕንፃዎች ሁሉም ይፈርሳሉ፡፡ የኮሪደር ልማቱን ለማስፈጸም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች ጽሕፈት ቤት፣ የከተማ አስተዳደሩ፣ የአዲስ አበባ ዕቅድና ልማት ኮሚሽንን ጨምሮ ሃያ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ ሪፖርተር | አሸናፊ እንዳለ
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማራ ክልል ገብተዋል ጎርጎራ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ትናንት ቅዳሜ በአማራ ክልል በገበታ ለሀገር በለማው ጎርጎራ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ ባለበት ነው የፓርቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጎርጎራ የተገኙት። የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
ዛሬ ይቺን ምድር ከፈጣሪ በታች የቀላቀለችን ፤ አለም ፊቷን ብታዞርብን እሷ ግን በደስታ ምትቀበለን ፤ ለኛ ሁሉ ነገራችን የሆነች ፤ ከአይኗ ብሌን በላይ ምትሳሳልን እናታችን ቀኗ ነው በእርግጥም ሁሉም ቀን እናታችንን ማክበር አለብን ነገርግን ዛሬ ልዩ ቀኗ ነው። እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ፤ የእናቶቻችሁን ደስታ ያሳያችሁ ፤ መልካም ቀን! የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
አሁን በኤስ ሚላን እና ካግሊያሪ መካከል እየተደረገ ባለ ጨዋታ ነገ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የእናቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የኤስ ሚላን ሁሉም ተጫዋቾች በማልያቸው ጀርባ ላይ የራሳቸውን ስም በመተው የእናታቸውን ስም አፅፈው ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።😍😍😍 የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
Hammasini ko'rsatish...
የድሬደዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የመንግስት ሰራተኞች 30% ለሚሆኑት የዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች የቤት ኪራይ ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላልፏል። የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በማህበራዊ ዘርፍ እና በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችን ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል፦ 1ኛ :- በአስተዳደሩ ከአጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች 30% ለሚሆኑት የዝቅተኛ ደመወዝ ተከፉዮች የቤት ክራይ ዱጉማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላልፏል። 2ኛ:- የሃዊ ቦሩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍል ጥያቄን ለመመለስ በአቅራቢያው ባሉ ክፍት ቦታዋች ግንባታ ለማከናወን በቀረበው አጀንዳ በመወወያየት የ1.2 ሄክታር መሬት እንዲሰጠው ውሳኔ ተላልፏል። 3:-ለድሬዳዋ ጠቅላይ መምሪያ የፖሊስ ማሰልጠኛ መአከል ግንባታ የሚውል የ150 ሄክታር መሬት ተወያይቶ ወሳኔ አስተላልፏል። 4ኛ፦በተጨማሪ በተለያዩ መሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ ካብኔው በመወያየት ውሳኔዋችን አስተላልፉል የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የስራ ማስታወቅያዎችን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ፡ https://t.me/bankjobsethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 3