cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

getme(Bicha)💋💋

Yhe yene getem nw achacher endehum leben yememolu yefikir getmochen wode enante akerebalew (bicha )

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
283
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

😊 ሀምሳ አለቃ ገብሩ😄 ( ሁለተኛ ታሪክ) "የዛሬው ለጉድ ነው😑" ብለው ተገረሙ ከነ ከዘራቸው ደጃፍ እንደቆሙ "ጥላኝ ማደሯ ነው!" ሲሉ 😲ደነገጡ "ፈፅሞ አይደረግ" መልሰው ተቆጡ😡 ይህንን በቅናት ሲያስቡ 50ለቃ መጣች አመሻሽ ላይ ነጠላ አዘቅዝቃ ትንሽ ስላስፈራት ያ50ለቃ ነገር ገና ሳትጠየቅ ጀመረች መናገር "ይኸውሎት ዛሬ የደብሬ ባል ሞቶ😔 ጎረቤቱ ሁሉ ከቤቷ ተገኝቶ ሲያፅናናት አምሽቶ ሲያፅናናት እንዲያድር ተመካክሮ ነበር ተሰብስቦ በዕድር እኔ ግን ሳስበው ቁጣዎን ፈርቼ😌 ሰፈር ጉድ እያለኝ ሁሉን ነገር ትቼ መጣሁኝ" እያለች ብዙ ስታወራ ያጣድፏት ጀመር 💪በያዙት ከዘራ ወዲያው ተፈንክታ ብትሆንም ደም በደም ያ50ለቃ ገብሩ ንዴት አልበረደም በሚስታቸው ጩኸት ቤቱ ሲበጠበጥ ምድጃው ተደፍቶ ድስቱ ሲገለበጥ የቤቱን ሁካታ ከሩቅ ስለሰሙ የነፍስ አባታቸው አለቃ ድማሙ ከየት መጡ ሳይባል ገቡ እየተከዙ ነጭ ጭራቸውን እየወዘወዙ ቆም ብለው ሲያዩት ያ50ለቃን ጥፋት የሚስትየዋን ደም የወጡን መደፋት በጣም አዘኑና ተክዘው ሲያበቁ "አዬ ያንተ ነገር! "ብለው አደነቁ🤔 "ያኔ ከሚስቴ ጋር ተው አስታርቁኝ ስትል እንኳን በከዘራ ዝንቧን እሽ ላትል ምለህም አልነበር "ብለው ተገረሙ የገብሩ ነብስ አባት አለቃ ድማሙ "ልክ ኖት አባቴ ሚስቴን አልጠላትም እንኳን በከዘራ በጣቴ አልነካትም ብቻ ግን ለከርሞው. ለከርሞው ምናልባት ያመሸችው ማምሸት ጥፋቷ እንዲገባት ላስፈራራት እንጂ ከዘራ ማንሳቴ በሚስቴ መጨከን አይችልም አንጀቴ ይይህን ጥፋት ብለው ባያውኩኝ ምናል በርግጥ ግንባሯ ላይ ፈንክቻት ይሆናል😣 ቢሆንም..... ቢሆንም ..... የገብሩ ባለቤት ይህን እንደሰማች "አሄሄ "😔በማለት ቁጣዋን አሰማች አላስጨረሷትም 50ለቃ ገብሩ "አይስሟት አባቴ "ብለው ተናገሩ "አይስሟት አባቴ የሚስቴን ምክንያት አብሬው ካላደርኩ ብቻውን መተኛት በጣም ያስፈራዋል ልትል ነው ይሄኔ የሷን ከንቱ ቅጥፈት መች አጣውት እኔ እኮ እኔ ነኝ ፈሪ ለነፍሴ እምሳሳ ሀገር ያደነቀኝ ጀግና ነኝ አንበሳ💪 ኮርያ ዘማች ነኝ ኮንጎም አልቀረውም እርግጥ የውጊያ እለት በስፍራው የለሁም ቢሆንም.. ቢሆንም .."ሲሉ ለመሟገት የገብሩ ነፍስ አባት ተቆጡ😡 በድንገት "ፉከራውን ተወዉ ገብቶኛል ፀባችሁ አዳምጬዋለሁ ቆሜ በደጃችሁ ደብሬን ያህል ወዳጅ ባሏ ሲሞትባት ሲሆን ውላ አድራ ማፅናናት ሲገባት ወዳንተ ስትመጣ ሀገር ጉድ እያላት እንደባብ ቀጥቅጠህ ሚስትህን ትገላት የዛሬን እንተወዉ አንተም አርፈህ ተኛ ውግዝ ከማሪዮስ አትንካት ዳግመኛ" ብለው ገሰፁና እንደ ልማዳቸው አለቃም ወደ ቤት ገብሩም ወዳልጋቸው ምሽቱ ወደሌት ሲቀየር ሲለወጥ በድንገት ሸቷቸው ያ የተደፋ ወጥ ነገሩን ሲያስቡት ብስጭትጭት 😤አሉና "ኧረ ለመሆኑ ጉድሽ መች ያልቅና ምንስ ጥንቁቅ ብሆን ለሚስቴ እምቀና ደብሬን ያህል ወዳጅ ባለቤቷ ሞቶ ጎረቤቱ ሁሉ በስፍራው ተገኝቶ እያስተዛዘነ እያፅናናት ሲያድር በተከበርኩበት በኖርኩበት ዕድር ማን ክፋ እንዲባል ነው ማንን ለማሳጣት ይህንን ያሰብሽው ከሰው ተነጥለሽ ቤትሽ የገባሽው? አሉና ተነሱ ከነከዘራቸው በስስ ካኔቴራ በረጅም ቁምጣቸው😳😢
Hammasini ko'rsatish...
( 😊ሃምሳ አለቃ ገብሩ 😄) "አያድርስ እኮ ነው" አሉና ተከዙ😔 ሹል ከይዘራቸውን እየወዘወዙ " አያድርስኮ ነው ብቻ ግን ደረሰ ሚስቴም ኮበለለች🏃 ቤቴም ፈራረሰ" ይህንን የሚሉት ሀምሳ አለቃ ገብሩ ጥንት ያላየናቸው ዛሬም ያልነበሩ ምናልባት ወደፊት ገና እሚፈጠሩ የስምንተኛው ሺህ ደግሰው ነበሩ ዛሬ ግን ተክዘው😩 የቅሬታን አሰሙ ለነፍስ አባታቸው ለ አለቃ ድማሙ " እስቲ እኔ ምን አልኳት ምንድነው በደሌ ቤቴን አክባሪ ነኝ ለትዳሬ ሎሌ ባያድላት እንጂ ደግ እንድታወራ ባሳፋሪ ነገር ስሙ ያልተጠራ ኧረ እንደኔም የለ ጭምት አባወራ ለሚስቴ ታዛዥ ነኝ ትዳሬን አክባሪ ቤተሰቤን ወዳድ ጋብቻዬን ፈሪ ይሄ ሀሰት ቢሆን ይመስክር አገሌ ትመስክር እገሊት እርግጥ አመሻለሁ እስከ አኩለ ለሊት " ቢሆንም ቢሆንም ብለው ተማረሩ የስምንተኛው ሺህ ሀምሳለቃ ገብሩ የገብሩ ነፍስ አባት አለቃ ድማሙ "እሷኮ እምትለው "ብለው ሲቃወሙ " የሷ ቅጥፈትማ ምናል ባይነሳ እንደኔ ማን ነበር ሚስቱን የሚናፍቅ ለሚስቱ እሚሳሳ ይፈልጉ እንደሆን እውነቱን መረዳት ማንም የለ እንደኔ ሚስቱን የሚወዳት እርግጥ ነው! እርግጥ ነው! 😰 (ከአንድ ሁለት ሴቶች ጋር አድሬ ይሆናል) ቢሆንም... ቢሆንም... አሉ በቅሬታ አልጥማቸው ብሎ ያለቃ ጨዋታ አስታራቂው አባት አለቃ ድማሙ ያምሳለቃ ገብሩን ብሶት እንደሰሙ ነጭ ጭራቸውን እየወዘወዙ "መቼ ይሄ ብቻ" አሉና ተከዙ😳 "መቼ ይሄ ብቻ እውነት ከሆነማ ከሆነ ምናልባት" ብለው ሲቀጥሉ አስታራቂው አባት " ገብቶኛል ገብቶኛል መች አጣውት እኔ ለቤቱ አይጨነቅ ሊሉኝ ነው ይሔኔ እስቲ ያሰላስሉት ይታዮት አባቴ እንዴት አልጨነቅ እንዴትስ አላስብ ለትዳር ለቤቴ ሁሌ ደስ እንዲላት ውዷ ባለቤቴ ኧረ እጨነቃለሁ ኑሮዬ እንዲሰምር ትዳሬ እንዲሻሻል ጋብቻዬ እንዲያምር (እርግጥ የቤት ወጪ ሰጥቻት አላውቅም😧) ቢሆንም! ቢሆንም! እያሉ ሲያቅማሙ የገብሩ ነፍስ አባት በጣም ተገረሙ " እንደው ይህች አለም መች ነው የሚያልፍላት አጠፋሁኝ የሚል ሰው የሚበቅልባት መቼ ይሆን ወቅቱ?" ብለው ሲናገሩ ዕንባ ቀደማቸው😢 ሀምሳለቃ ገብሩ "ልክ ኖት አባቴ ጊዜው ተበላሽቷል ያለንበት ዘመን ይቅርታ ጠይቃኝ ጥፋቷን በማመን ብንኖር ይሻል ነበር ጭቅጭቅ አቁመን እና ዕውነት ብለዋል ምናል ብትፈራ ጡር በእኔ ይጨከናል በየዋሁ ፍጡር ሁሌ መፈንጠዝ ነው መጫወት ነው መሳቅ ለራሴ የግዜር በግ🐑 ክፋትን የማላቅ እርግጥ አንዳንድ ቀን! (በጩቤ አስደንግጫት አስጩኪያት ይሆናል) ቢሆንም... ቢሆንም ... ይሄን ጥቃቅኑን ካይምሮዋ አውጥታ ምናል ብታመጣው መልካሙን ትዝታ አዎ.... ያ የጥንቱ ደግ ደጉን ዘመን መኝታ ቤት ሆነን በፍቅር ሰመመን ካልጋ እየገፈተርኩ የምወረዉራት ግድግዳ እያጋጨሁ የማሽቀነጥራት ምናል ትዝ ቢላት.... ምናል ብታስታውስ የጥንቱን መዋደድ እሷም ከሚከፋት እኔም ከምናደድ በሉ እንግዲህ ሂዱ ይህንን ንገሯት የዋሁ አባወራ ብቻውን ነው በሏት ብቻውን ነው በሏት ይህንን ንገሯት ዛሬም ብቻዬን ነኝ አላውቅም የሷን ግን ጭር ባለ አልጋ ላይ አድራለሁ ስበግን እርግጥ አንዳንድ ቀን ሲረዝምብኝ ሌቱ አብራኝ ትተኛለች ሰራተኛይቱ 😰😣 ቢሆንም😶...ቢሆንም ... ✏በ አሜን ከታገል ሰይፋ ቀፎውን አትንኩት የግጥም መድብል
Hammasini ko'rsatish...
"ልፅፍልህ ነበር...."✍ ያቀናሁት እጄን የገዛ እንባዬ ዘንቦ እየገረፈው እንደምን በርትቼ ከወረቀቱ ላይ ስምህን ልፃፈው የለኮስኩት ኩራዝ ጨልሞ እስኪፈዝ አቅም እስኪነሳው በምን ልቋጨው ነው አንተን በመናፈቅ ብእር የማነሳው ልፅፍልህ ነበር.... አልተሳካም እንጂ ቢሳካልኝና ፊደል ቢታዘዘኝ እንዴት ያለ ናፍቆት እንዴት ያለ ፍቅር ካንተ እንደያዘኝ ልነግርህ አስቤ ሰርዤ ደልዤ ይህንን ስላልኩኝ የፃፍኩትን ሳይሆን አንብበው ብዬ ነው ልፅፍ እንዳሰብኩኝ
Hammasini ko'rsatish...
​​​​​​​​❦ ​​​​​​══•⊰❂ ጣፋጭ ግጥሞች  ❂⊱•══ ❦ #የታባቱ_ናፍቆት !! ናፍቆትሽ እንደ ጧፍ ፥ ትዝታሽ እንደ ሰም ፣ ያ'ቻምና ተስፋዬ ፥ ዘንድሮም ሳይከስም፤ ቀናቶች አርጠዉ ፣ ወራቶች ተሟጠዉ፤ ገባ እንቁ ጣጣሽ ፣ እኔ  እንዳመንኩሽ ፣ አንቺም ቶሎ መጣሽ ፡፡ አንቺን ስጠባበቅ ያሸሞረዉ አገር ፥ እጁን ባ'ፉ ያዘ ፣ አሽሟጣጩ መንደር ፥ በአግራሞት ፈዘዘ፡፡ የታ'ባቱ ሽሙጥ ! የታ'ባቱ አሽሙር ! በተራዉ ይተክዝ ፥ እሱም አንገት ይድፋ ፣ ባንቺ የመጣብኝ ፥ ከምድረገፅ ይጥፋ፡፡ ፍቅርሽ ባለ ዝና ፣ አስማኝ ብስራት ፥ አስደመጠኝ ዜና ፣ ማ'ናት ሌላ ሰዉ ? ብርሃን የሆነቺዉ ፤ እሷ ሻማ ሆና ፡፡ ማንም ! ስላንቺ እያሰብኩ ፣ ስላንቸቺ እያወራሁ ፥ ስላንቺ እየፃፍኩ ፤ ግብርሽን ስለካ ፥ ፍቅርሽን ስገምት ፣ ካሳለፍነዉ ጥምቀት ካከበርነዉ ሞ'ሊድ ፥ ካየሁት አዉዳ'መት፣ ምህረት ስላገኘሁ ዘንድሮ ነዉ ዉዴ ፥ የኔ ዐዲስ ዓመት ፡፡ አምና'ና፣ ካቻ'ምና ፣ ስጋዬ በድሎ ፥ ነፍሴ ሀጢ' ሆና ፤ በተመሳሳይ ቀን . . መልካም ዐዲስ ዓመት ፥ አሉኝ ወዳጆቼ ፣ አንቺ የሌለሽበት ፥ ኦና ቤት ተኝቼ ፡፡ እኔ ያንቺ አፍቃሪ  ጥለሺኝ እንደሄድሽ ፥ እንዳለሁኝ አለሁ አዲስ ነገር የለም - አንቺን ካላገኘሁ ፡፡ የሚል ወግ ነበረኝ፣ የታባቱ ናፍቆት !  ፍቅርሽ አስከበረኝ፡፡ #ምንተስኖት_ዋቆ_ብዙነህ 😉 𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር 🙏 ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
Hammasini ko'rsatish...
የማይሰራ ሰዓት ግን የሚሽከረከር ( የታመመ ዛሬ ) ✍ ካሊድ አቅሉ የማይሰራ ሰዓት ግን የሚሽከረከር ዋናው ቦታን ጥሎ እንድያው ዙሩን                  ሚያከር ሚሰራ መስሏቸው ወደላይ ቢያንጋጡ መቅደም ወይንም ማርፈድ ተላብሷቸው                        ወጡ      በየለም እንዳያዝ ድምፁም አልተነካ ቀስቱም እንደቀድሞ በመዞር አልረካ ፀሀይ መጥለቅያ ላይ መንጋቱን ያበስራል በጠዋትዋ ጀንበር ቀትር ነው እያለ                           ስድስት ሰዓት ያሳያል ። እኔም ስትሄጂ      ሌላውን ስትለምጂ ሆንኩኝ ያንን ሰዓት አካሌ ሚሰራ          አእምሮዬ ቆሞ ጤንነት ሰብካለው በትናንቴ መጉደል          የኔ  ዛሬ ታሞ !! by @kalidakelu @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
ፍቅር ደግና ታጋሽ ነው ፍቅር አይቀናም አይኮራም ፍቅር ራስ ወዳድ አይደለም ፍቅር ትዕግስት የሌለው አይደለም
Hammasini ko'rsatish...
ሀባ- - - መውደድ ስትመጪ - - -ይገባል ብቸኝነት ሞቶ - - -አንድ መሆን ያድጋል ። ዳሩስ - - - መቼ ጠፋኝ፣ በዝናቡ መሀል የምትወጣ ፀሀይ ፥እየተከተለች ፥እንምትወልድ ጅብ ውሃ ማያጠፋኝ፥እሳት እንደሆንኩኝ ፥በኩራት ባነጅብ እውነት እልሻለው ተሳክቶልኝ በእድሜ በስኬት ባረጅም በፍቅር ረገድ እኔ ካንቺ ውጪ ለማንም አልበጅም @yengetm @yengetm @yengetm 📩yinoral
Hammasini ko'rsatish...
የተለየለችኝ ቀን ሌላ ወደሀል ብላ ልቤ ሲሸራረፍ በቁጭት ሲበላ እንደማትመለስ ዳግም ወደ ኋላ አረጋግጣ ኖሮ.... ውድጄብህ ነበር አብረን ስንኖር ድሮ ብላ ጣፈችልኝ በእልህ ወረቀት እውነት - - - ይሁን -- -- ውሽት ያን ጊዜ ከሰመ የጥፋቴ ፀፀት ደግ አረኳት እውነት! @yengetm @yengetm @yengetm 📩@yinoral (ሚካኤል ,አ)
Hammasini ko'rsatish...
❤️ፍቅሬ❤️ 😍😍😍 ጅረት ይመስል ልቤ ሲንጠለጠል ትላንት መሽ ዛሬን ነጋ ቢባል ፍቅሬን ለማሳየት ቃላቶችም ጠፍቷል። ቃላትን ፍለጋ ከመፅሀፍ ስሰጣ ቃላት ፈልጌ አንቺን ሚገልጥ ሳጣ። ቋንቋ ሁሉ ተጣምሮ ቢመጣ እንኳ ትላንት ዛሬ ተቀይሮ ቃላትን ሰብስቤ ገና ስጀምር ሁሉም ያንስብሻል እንዲው ላንቺ ፍቅር። አይኖችሽ ካአይኖቼ ቢወሩ ልብሽ ከልቤ እንዲው ቢጣመሩ ማሰቤን አላቆም ስላንቺ ዘወትር ማታም በሕልሜ እያልሽብኝ ድንቅር እንጃ አላውቅም ይሕን መሰል ፍቅር። በቀንም መተሽ ከጎኔ ለይ ሆነሽ ጎኔን በእጆችሽ ዳብሰሽ አይኔን በአይኖችሽ አይተሽ ቃላት ሳደረድሪ ዝም ብለሽ ፍቅርን አሳየሽኝ በድርጊትሽ። እኔስ እድለኛ..... እንደሆንኩ ባቅም አንቺን ካጣውሽ ምሆነውን አላቅም። እና የኔ ፍቅር እኔ አንቺኑ ስወድሽ በተብታባው አፌ ፍቅሬን ስነግርሽ ከአፌ በላይ የአይኔን አንብበሽ ዘላለም አኑሪኝ ከጎንሽ ወሽቀሽ። ✍ምንተስኖት ሱሌይማን ቀን፦08/02/2014 ✋አንዴ🤚 የቻናል ጥቆማ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Getami_mintesnot @Getami_mintesnot @Getami_mintesnot @Getami_mintesnot
Hammasini ko'rsatish...
መውደዴን ስነግራት ፣ ሳቅ ሲተናነቃት፡፡ ‹‹አብረን እንሁን›› ስላት ፣ ሳቅ ሲተናነቃት ፡፡ ‹‹አፈቀርኩሽ›› ስላት ፣ ሳቅ ሲተናነቃት ፡፡ መልሱን ስጠይቃት ፣ ሳቅ ሲተናነቃት ፡፡ ‹‹ ላግባሽ ባልኳት›› ጊዜ ፣ ትንታ ገደላት ፡፡ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @efrem_seyum ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ❥❥________⚘_______❥❥
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.