uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀

Kanalga Telegram’da o‘tish

« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 analitikasi

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 13 836 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 6 309-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 572-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 13 836 obunachiga ega bo‘ldi.

27 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -200 ga, so‘nggi 24 soatda esa -7 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 26.90% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 6.08% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 723 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 842 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 0 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 28 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

13 836
Obunachilar
-724 soatlar
-447 kun
-20030 kun
Postlar arxiv
ብዙ ጊዜ ሰዎች ዘንድ ሲቀርቡ ፈገግ የሚሉና ደስተኛ የሚመስሉ ሰዎች ብቻቸውን ሲሆኑ ሌላ አለም ውስጥ ናቸው።

"እንክብካቤ" ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅርን ሲወልድ ችላ ማለት ደግሞ ፍቅር ላይ ሌላ ተፈቃሪን ይወልዳል! ||

~የገንዘብ ይሁን የጓደኛ ሪዝቅ ከአላህ ነው። በሆነ ጊዜ አላህ ከሰማይ በእዝነት መልክ ያወርድልሃል። በሕይወትህ ጣልቃ እየገቡ መንገድ የሚያቃኑልህን ሰዎች ድንገት ይልክልሃል። ቀልብህን ይዳብሳሉ፣ ቁስልህን ያክማሉ፣ ቅርበታቸው ሰላም ይሰጥሃል፣ መኖራቸው ፀጋ ነው፣ ድምፃቸው ደስታ ነው፣ ፈገግታቸው ጀነት ነው፣ ምክራቸው ጤና ነው። አላህ ይጠብቅልን። =t.me/AbuSufiyan_Albenan

ከመጥፎ ጓደኚነት ጥሩ ብቸኚነት ይሻላል። ──────⊹⊱✫⊰⊹──────

خلاصة تعظيم العلم. (1).mp39.75 MB

አንተን ከማግኘቴ በፊት ምድር ላይ ይህ ሁሉ ደስታ አለ ብዬ አላስብም ነበር‥.! ለሀላልሽ ላኪለት 🖐 #ፍቅር =

🏷 በልብ ያለን ነገር ሁሉ መናገር ይከብዳል...ለዛም ነው አላህ ጩኸትን፣ እንባን እንቅልፍንና ቀዝቃዛ ፈገግታን የፈጠረልን! =

ውበቷ ሲረግፍ አረጀሽ ብሎ አልተዋትም ጤንነቱን ሲያጣም በሽተኛ ብላ አለተወችውም። هكذا كان الحب في زمن أجدادنا ፍቅር በአያቶቻችን ጊዜ እንዲህ ነበር =
ውበቷ ሲረግፍ አረጀሽ ብሎ አልተዋትም ጤንነቱን ሲያጣም በሽተኛ ብላ አለተወችውም። هكذا كان الحب في زمن أجدادنا ፍቅር በአያቶቻችን ጊዜ እንዲህ ነበር =

አንድ ሚስት ባሏን ከጓደኞቹ ጋር እንዳይዝናና ቤት ተቀመጥ ብላ ትከለክለዋለች ...ባል ይሄኔ " አንዲት ሴት አስራ ባስቀመጠቻት ድመት ጀሃነም ገብታለች ...አንቺ አንበሳ አስረሽ አስቀምጠሽ ምን ሊደርስብሽ  እንደሚችል አስቢ እስኪ..."  ብሎ ተናገራት ...ህእ! ፈገግ በሉ ፋሚሊዎች 🖐 =

እንደተጋባቹ ሰሞን ለትዳር አጋራቹ ታደርጉት የነበረ አሁን የተዋቹት ምንድነው?? እንደተጋባን ካልሲህን ካልተኮስኩልህ እለው ነበር አሁን ግን ግራና ቀኝ አርጎ ነው ሚሄደው አለች። ፈገግ ብላችሁ ዋሉልኝ ¡ |||

የፍቅር ህግ ... ~ "መዋሸት የለም ፣ ማጭበርበር የለም፣ መለያየት የለም፣ እንጣላለን፣ እንታረቃለን ፣ እስከመጨረሻ ድረስ አብረን እንቆያለን። " ||

የሀገራችን በርበሬ የማጠን ባህላችን መመለስ አለበት ጋይስ ! አይመስላችሁም ¡ =

ከትዳር በፊት ፍቅር የለም ብዬ የኸዲጃን ፍቅር ገደል አልከተውም… ምክንያቱ ምንም ይሁን አፍቅራ እንዳገባቻቸው አልጠራጠርም… በሪራ በሚሏት ሰሓቢት ፍቅር ተለክፎ በመዲና መንገዶች ላይ ከኋላዋ እየተከተለ…  የእንባ ቋንጣውን በመዲና አድማስ  ሲወረውር የነበረውን ሰሓባው ሙጊስ … አፍቃሪ አልነበርክም ልለው አልችልም… ቀድመው ቢለያዩና ከዚያ በኋላ ባያገባትም “ሙጊስ ለበሪራ ባለው ፍቅር፣ በሪራ ደግሞ ለሙግስ ባላት ጥላቻ አልተገረምክም ወይ” የተባለለት አፍቃሪ ነው… ያውም በረሱል አንደበት። አንድ ነገር ግን አምናለሁ… ፍቅር በስሙ የሚደረጉ ኃጥያቶችን እንደማያውቃቸውና  የአፍቃሪ መድሀኒቱም ትዳር እንደሆነ…  ማንነትህን ፣ እምነትህንና ጉዞህን የሚያመክንብህ ከሆነ በሽታ እንደሆነ… አምናለሁ። ነብይህ “ለተዋደዱ ሰዎች ከኒካህ ውጪ (አማራጭ) አላየሁም” ሲሉም… ከትዳር በፊት መዋደድ እንዳለና ኒካህ ካልታከለበት ግን የኪሳራ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ነው… አፍቅርሃል? በበር በኩል ና በቃ … በፍቅር ስም ሙድ አትያዝ!! t.me/abdu_rheman_aman

ውለታን አትርሳ ! በህይወትህ ትልቅ ዋጋ የከፈሉልህ ሰዎች እነማን ናቸው? ላንተ አሁን ላለህበት ቦታ ለመሆንህ እዚህ ለመድረስህ ከአላህ ቀጥሎ ትልቁን ሚና የተጫወተልህ ማነው? ያንን ሰው ከልብህ ዋጋ ስጠው ውለታውን መክፈል ባይቻልም እንኳን በምትችለው መጠን ያለህን ፍቅር እና ክብር ለግሰው ! ክብር የሚገባቸውን አንርሳ ! || t.me/abuUseyminabdurehman

ኢብራሂም– አንድ ሰው፣ ሁለት ስም! ~ አንተ ከሰዎች ዘንድ ማነህ? ደግ ወይስ ክፉ? ትሁት ወይስ በጥራራ? ፊተ በሻሻ ወይስ ጨፍጋጋ? ምራቅ የዋጠ በሳል ወይስ በቀዳዳ ሱሪ የሚጀነን ከንቱ ፍንዳታ? አንተ ማነህ? ሰዎች ስላንተ ምን ይላሉ? ምን እንደሚሉ ታውቃለህ? በክፉ መነሳት ያሳስብሀል? ወይስ የሰው ጉዳይ የማይጨንቅህ በራስህ ዛቢያ ላይ የምትሽከረከር ፍጡር ነህ? አንቺስ ከሰው ዘንድ ማነሽ? ማን መባል ያምርሻል? ምን ስም እንዳይወጣልሽ ይጨንቅሻል? ባገር በመንደሩ ምን ስም አለሽ? ጨዋ? ዘል.ዛላ? ምላሳም? ቁጥብ? አጉል ነቃሁ ባይ? ግብረ ገብ? ቀብራራ? ኮስታራ? ይህ ከሰው ዘንድ ነው። ከአላህ ዘንድስ እኛ ማነን? ምንስ ቦታ አለን? እስኪ ራሳችንን እንመልከት? አላህ ካዘዘብን ቦታ አለን? አላህ ከከለከለን ቦታ ርቀናል? ከሆነ ምንኛ መታደል ነው?! ከሆነ ከሰው ዘንድ ያለን ስም አያስጨንቀንም። ከሰዎች ዘንድ እፍኝ የማይሞሉ፣ አይን የማይገቡ፣ ቢናገሩ ቃላቸው የማይሰማ፣ ቢጠይቁ ፊት የማይስሰጣቸው፣ በሰዎች መለኪያ እዚህ ግባ የማይባሉ ከአላህ ዘንድ ግን የላቀ የራቀ ደረጃ ያላቸው ስንትና ስንት የአላህ ሰዎች አሉ?! አላህ ዘንድ "ሰው" ከሆኑ በኋላ ሰዎች እንደ ሰው ባይቆጥሯቸው ምን ያጣሉ?! ኢብራሂምን አታይም? ከነዚያ ከበርቴዎች ዘንድ ማን ነበሩ? አንድ ተራ ወጣት! (قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ) "ኢብራሂም የሚባል #ወጣት (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል ተባባሉ።" [አልአንቢያእ: 60] ከአላህ ዘንድስ ማን ነበሩ? (إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ) "ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ የሆነ #ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡፡" [አንነሕል: 120] ከሰዎች ዘንድ እንደ ዋዛ "አንድ ወጣት" ተብለው የተቃለሉት ኢብራሂም ከአላህ ዘንድ "ህዝብ" ተብለው ነበር የተሞካሹት!! አንዱ ኢብራሂም ሁለት ስም ሲኖራቸው ተመልከት። አንዱ እንደ ምድር፣ አንዱ እንደ ሰማይ። አንዱ ከምድር፣ ሌላው ከሰማይ። ልዩነቱን አየኸው?! አላህ እንዲህ ከሰቀላቸው በኋላ ፍጡር ሊያወርዷቸው ቢጣጣር ምን ያመጣል?! በተውሒድ የነገሰን ማን ያወርደዋል?! · ድሮ ነው። ወሎ፣ ወረባቦ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ዑካሻ የተሰኙ በተውሒድ ጠንካራ የሆኑ፣ ህዝቡን የወረረውን ሺርካ ሺርክ የሚነቅፉና የሚፀየፉ ሸይኽ ነበሩ። "ከዘልማዳችን ወጥጣ" ብለው በጊዜው የነበሩ መሻይኾች ተሰብስበው "ፌንጥ" አሏቸው።  ("ፌንጥ" አሁንም ድረስ ያለ አደገኛ ማህበራዊ ማእቀብ ነው። "ፌንጥ" የተባለ ሰው ከየትኛውም ማህበራዊ ህይወት ይገለላል። ሰላምታ እንኳን ይነፈጋል። ከሕዝብ መሐል እየኖረ በጫካ ውስጥ ከመኖር በላይ እየተሳቀቀ ባይተዋርነትን ይገፋል።) ዑካሻ በጠንካራው የተውሒድ አቋማቸው የተነሳ አድማ ተመታባቸው። ከአቋማቸው ሊያሽመደምዷቸው በማለም ሸይኾቹ ተሰብስበው "ፌንጥ ብለንሀል" አሏቸው። የዑካሻ መልስ ግን ያልተጠበቀ ነበር። "እኔም ፌንጥ ብያችሁዋለሁ! ምን ታመጣላችሁ?!" · አዎ ሁለ ነገሩን ለአላህ የሰጠ ሰው፣ የሰው ሴራ ለአላህ ብሎ ከያዘው አቋሙ አያጥፈውም። የሰው ጭብጨባ በሙቀት አያቀልጠውም። አላህን የያዘ ምን አጥቷል! ከአላህ ጋር የሆነ ምን ያስፈራዋል! · ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! ከምንም በፊት ከአላህ ዘንድ ሰው እንሁን። በምኞት ሳይሆን በተግባር ሰው ለመሆንም እንጣር። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 13/2011) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor