Ethio Construction Engineering
🔨 World Construction Engineering Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World. Learn, build, and grow with us! 📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Ko'proq ko'rsatish📈 Telegram kanali Ethio Construction Engineering analitikasi
Ethio Construction Engineering (@etconp) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 31 964 obunachidan iborat bo'lib, Taʼlim toifasida 5 959-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 1 057-o'rinni egallagan.
📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika
невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 31 964 obunachiga ega bo‘ldi.
26 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 233 ga, so‘nggi 24 soatda esa 59 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.
- Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
- Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 12.02% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 6.99% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
- Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 842 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 234 ta ko‘rish yig‘iladi.
- Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 10 ta reaksiya keladi.
📝 Tavsif va kontent siyosati
Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!
📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT
For Ad:- https://telega.io/c/etconp”
Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 27 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Taʼlim toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.
አዲስ አበባ — የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 57ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የሀገሪቱን የግንባታ እና የከተማ ዕድገት መዋቅር በከፍተኛ ደረጃ ይቀይራሉ የተባሉ ሁለት ወሳኝ ረቂቅ ፖሊሲዎችን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።ምክር ቤቱ በሰፊው ተወያይቶ ያፀደቃቸው እነዚህ ሰነዶች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ እና የከተማ ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ናቸው። ሁለቱም ፖሊሲዎች ከዛሬው ዕለት ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውሉ ተወስኗል። 1. የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፦ ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ከፍተኛ ምርታማነት ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ፣ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዓመታት ሲተገበር የነበረው ነባሩ የኮንስትራክሽን ፖሊሲ በዘርፉ የተወሰኑ ለውጦችን ቢያስመዘግብም፣ አሁን ካለው የዓለም የቴክኖሎጂ ዕድገትና የፈጣን መሰረተ ልማት ፍላጎት አንጻር ሰፊ ክፍተቶች የነበሩበት መሆኑን አውስቷል።
አዲሱ ፖሊሲ እነዚህን ክፍተቶች በመሙላት ረገድ የሚከተሉትን ዋና ዋና ግቦች ያሳካል ተብሏል፤◂▸ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፦ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ዓለም አቀፋዊ ደረጃና ብቃት ማረጋገጥ። ◂▸ የሕግ ማዕቀፎችን ማጣጣም፦ በሥራ ላይ ያሉ አሰራሮችንና ሕጎችን በማዋሃድ ለግልና ለሕዝብ ኢንቨስትመንት ምቹ ማድረግ። ◂▸ አቅምን አሟጦ መጠቀም፦ የኢንዱስትሪውን የመልማት አቅም በመጠቀም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን የማድረግ ጉዞን ማፋጠን።
2. የከተማ ልማት ፖሊሲ፦ የከተማና ገጠር ትስስርን ማጠናከርየሚኒስትሮች ምክር ቤት ሁለተኛ አድርጎ ያፀደቀው፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት (ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ) በሥራ ላይ የቆየውን የከተማ ልማት ፖሊሲ በአዲስ መልክ የሚተካውን ሰነድ ነው። ነባሩ ፖሊሲ በከተሞች የመሰረተ ልማት መስፋፋትና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ውጤቶች ቢያስመዘግብም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተሞች አካባቢ እየታዩ ያሉ አበረታች ለውጦችን ለማፅናትና ይበልጥ ለማጎልበት አዲስ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
የአዲሱ የከተማ ልማት ፖሊሲ ትኩረቶች፦▸◂ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እና አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ማድረግ። ▸◂ ከተሞችን በኢኮኖሚ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችን መዘርጋት። ▸◂ የከተማ-ገጠር እና የከተማ-ከተማ ትስስርን በበለጠ ማጠናከር። ◂▸ የማምረቻና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን በስፋት ማዳረስ።
ሁለቱም ፖሊሲዎች በምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ አስፈላጊ ግብዓቶች ከተካተቱባቸው በኋላ ከዛሬው ዕለት ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ በሥራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የምክር ቤቱ መግለጫ ያሳያል።@etconp
ይህ መመሪያ በሰራተኛች ብቃት ማነስ ምክንያት በንብረት እና በግንባት ጥራት ላይ የሚደርስን ችግር ለመቀነስ ነው ተብሏል።💫የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ዘርፍ እየታየ ያለውን የጥራትና የደህንነት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አዲስ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን አስታውቋል። ❇️ይህ አዲስ መመሪያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ዕለት ተዕለት የሚሰሩ የቀን ሠራተኞችንም የብቃት ደረጃ ማረጋገጥን ግዴታ የሚያደርግ ነው። ሚኒስቴሩ በዘርፉ የተሻለ ጥራትና ደህንነትን ለማስፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል። 🏷እንደ አዲሱ መመሪያ ዝርዝር ሁኔታ፡- 📌በየትኛውም የግንባታ ቦታ ላይ ለመስራት የሚፈልጉ ባለሙያዎች እና የቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ ግዴታ ይሆናል። 📌ሕጋዊ የሰርተፊኬሽን ሥርዓት ያላሟላ እና ብቃቱ ያልተረጋገጠ ማንኛውም ባለሙያ ወይም ሠራተኛ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንዳይሳተፍ ሙሉ በሙሉ ይከለከላል። 📌መመሪያው ሙሉ በሙሉ ሕግ ሆኖ ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የተወሰኑ ዓመታት ሊወስድ ይችላል። 📌 በአሁኑ ወቅት ግን የዚህ አሠራር የቅድመ ዝግጅት እና የሙከራ እንቅስቃሴዎች በይፋ መጀመራቸው ተገልጿል። 🪧የዚህ አሠራር ዋና ዓላማ የግንባታ ሥራዎችን ጥራትና የሥራ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ማሻሻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። @etconp
Endi mavjud! Telegram Tadqiqoti 2025 — yilning asosiy insaytlari 
