cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል። ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ ስልክ- 0935439820 ኢሜይል- [email protected]

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 335
Obunachilar
+124 soatlar
+27 kunlar
+430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358 ላይ ጥሩ የሚባል የህግ ትርጉም! ***** ሰ/መ/ቁ. 144359፡- ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 እና 41 አስቀድሞ መብቱን የሚነካ ክርክር መኖሩን ያወቀ አካል ክርክሩ አብቅቶ ውሳኔውን ከመስማቱ በፊት ወደ ክርክሩ ሊገባ እንደሚገባ የሚያሳዩ ሲሆኑ ፍርድ ሲሰጥ ጠብቀው በመምጣት የተሰጠው ፍርድ ይነሳልኝ በማለት አቤቱታ ማቅረብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ላይ የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ አላማ የሚያሳካ አይደለም። ይሁን እንጂ ይህ ድንጋጌ ለውርስ ሀብት ክርክርን በተመለከተ ተፈፃሚነት ያለው ነው ለማለት የሚቻል አይደለም። እንኳን የውርስ ሀብቱ ሳይከፋፈል ቀርቶ ከተከፋፈለ በኋላም በሌለበት የውርስ ሀብቱ የተከፋፈለበት አካል በሚያቀርበው አቤቱታ ክፍፍሉ ሊፈርስ እና እንደገና ክፍፍል ሊደረግ እንደሚገባ በፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 1080 ላይ ተደንግጎ ይገኛል። ስለሆነም ምንም እንኳን አመልካቾች ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ አስቀድሞ የነበረውን ክርክር በሚያውቁበት ሁኔታ ቢሆንም የፍርድ መቃወሚያ የቀረበበት ክርክር የውርስ ሀብትን መሰረት ያደረገ ከሆነ የውርስ ሀብቱ ክፍፍል ከተደረገ በኋላም ቢሆን የሚቻል ክርክር በመሆኑ የአመልካቾች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ አመልካቾች አስቀድመው ክርክሩን ያውቁት ነበር በሚል ውድቅ ሊሆን አይገባም። የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም 👇👇👇👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
ሰ/መ/ቁ. 184371 /ያልታተመ/ *** የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 106560 መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት እና በሰበር መዝገብ ቁጥር 116583 ታህሳስ 4 ቀን 2008 ዓ/ም በዋለው ችሎት ከመሬት ይዞታ ክርክር ልዩ ባህር እና ጉዳዩን በተለይ የሚገዛው ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 በኋላ የወጣው ልዩ ሕግ አዋጅ ቁጥር 456/1997 መሠረት የተከራካሪ ወገኖች መደበኛ ነዋሪነት የተለያየ ቢሆንም/ባይሆንም የተከራካሪዎቹ ማንነት ከግምት ውስጥ ሳይገባ የገጠር መሬት ይዞታን በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮችን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የገጠር መሬት ይዞታው የሚገኝበት ክልል የገጠር መሬት አዋጅ በሚደነግገው መሰረት መሆኑን አገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም ተከራካሪዎቹ ነዋሪነታቸው በተለያየ ክልል መሆኑ ጉዳዩን የፌዴራል ጉዳይ አያደርገውም ።
Hammasini ko'rsatish...
በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ የገጠር መሬትን የሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል። የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል። ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ እንደሚችል በአዲሱ ድንጋጌ ላይ ሰፍሯል። በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት “መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው”። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው “ለመንግስት እና ለህዝብ” ነው። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተደንግጓል። በእነዚህ ይዞታዎች ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል። እነዚህ ቅጣቶች፤ ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ላይ በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል። ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Hammasini ko'rsatish...
በዋስ ቢወጡ ሌላ ወንጀል የሚፈጽሙበት ሁኔታ ሰፊ ነው በሚል ዋስትናን ሰለመከልከል *** የሰ.መ.ቁ 245661/ያልታተመ/ #Daniel Fikadu Law Office - አመልካቾች የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት በተመሳሳይ ማታለል ወንጀሎች ሌሎች መዛግብቶች ያሉባቸው በወንጀሉም የመጠርጠር ሙያ አድርገው የያዙት መሆኑ ሲታይ በዋስ ቢወጡ ሌላ ወንጀል የሚፈጽሙበት ሁኔታ ሰፊ ነው በሚል ነው፡፡ የዚህ ግምት መሠረቱ አመልካቾች በዋስትና ቢወጡ ሌላ ወንጀል የሚፈጽሙበት እድል ሰፊ ነው የሚል እሳቤ የያዘ ስለመሆኑ ግንዛቤ የሚወሰድበት ነው፡፡ ሕጉ ፍ/ቤቱ ይህን ምክንያት ለግምቱ መነሻ እንዳያደርግ እስካልከለከለ እና ሕጉ ለፍ/ቤቱ ስልጣን የሰጠው ለመሆኑ የሚታመን እስከ ሆነ ድረስ የስር ፍ/ቤት የአመልካችን የዋስትና መብት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67(ሀ)(ለ)(ሐ) መሠረት የከለከለው በሕጋዊ ምክንያት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን የዋስትና መብት በመንፈግ በሰጡት ትዕዛዝ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት አልተገኘበትም፡፡
Hammasini ko'rsatish...
245661 - Stamped.pdf8.20 KB
ከመላኩ ጥላሁን የተወሰደ ****** ሰ/መ/ቁ.220926፡-የወንጀል ድርጊቱ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ከተፈፀመ የወንጀል ድርጊቱ በሌሊት እንደተፈፀመ በማድረግ በወ/ህ/አ.84 (1)(ሐ) መሰረት ቅጣቱን ማክበድ እንዲሁም የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ወንጀል ለመፈፀም ከተቋቋመ ቡድን ጋር መሆኑ ካልተረጋገጠ ተከሳሾች ከአንድ በላይ ቢሆኑም ቅጣቱን በወ/ህ/አ.84(1)(መ) ማክበድ ተገቢ አይደለም። ሚያዝያ 25 ቀን 2014 ዓ/ም
Hammasini ko'rsatish...
185837_የሰበር_አጣሪ_ችሎት_አሰያየምና_ከዳኞች_አሰያየም_አንጻር_የጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_ፕሬዝዳንት_ሥልጣን.pdf3.25 KB
ሰ/መ/ቁ 114927     መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ/ም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143(2) አተረጓጎም በተጠሪ ደንበኛ ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ የተባለው የአመልካቾች ተሸከርካሪ አሽከርካሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 506(1(ሐ)) ተጠቅሶ የወንጀል ክስ ቀርቦበት ድርጊቱ ስለመፈጽሙ የቀረበ ማስረጃ የለም ተብሎ ምንም መከላከል ሳያስፈልገው በነጻ ተሰናብቷል። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143(2) ስር ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ በሚል የተቀመጠው የድንጋጌው አቀራረፅና ይዘቱ ሲታይ ለጉዳቱ የተከሰሰ ሰው በወንጀል ችሎቱ ነፃ መውጣቱ ይርጋውን ወደ ሁለት አመት ዝቅ የሚያደርገው መሆኑን የሚያስገነዝብ ሳይሆን ጉዳቱ በራሱ የወንጀል ድርጊት መሆኑ ብቻ የይርጋውን ጊዜ በወንጀል ሕጉ በተመለከተው የይርጋ አቆጣጠር ለማስላት የሚገባ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ የድንጋጌው የእንግሊዝኛው ቅጂ ሲታይም "where a damage arises form the commission of a criminal offence in respect of which the Penal code prescribes a longer period of limitations, the latter period shall apply to the action for the damage." በሚል የተቀመጠ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ የዚህ ድነጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያሳየው ጉዳቱን ያስከተለው ድርጊት በወንጀል ሕጉ የወንጀል ድርጊት ተብሎ የሚወሰድ ስለመሆኑ እንጂ ድርጊት ፈጸሚው የግድ በወንጀል ጥፋተኛ ሁኖ መገኘትን ለይርጋ አቆጣጠር መለኪያ ሊሆን የሚችል አለመሆኑን ነው፡፡  በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 61326 በቀረበው ጉዳይ ላይ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1) ድንጋጌ አግባብ በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የህግ ትርጉም ሰጥቶአል፡፡ በዚህ ትርጉም ጉዳቱ በወንጀል ድርጊት የተከሰተ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በወንጀል ጥፋተኛ ሁኖ መገኘትን ወይም በወንጀሉ ጉዳይ የማስረጃውን ምዘና ሁሉ የሚመለከት ነው ከተባለ በውጤቱ ለጉዳት ካሳ ተጠያቂ የሚሆኑ ሰዎች(ለምሳሌ ጥፋት ሳይኖር ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች)ሁሉ ተጎጂዎችን እንዳይክሱ የሚያደርግ የሚሆን መሆኑ የሚታመን ስለመሆኑም ተገልጾአል፡፡ ስለሆነም የድንጋጌው አስገዳጅ ትርጉም ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑ የሚለው የድንጋጌው ሐረግ ተከሳሽ በወንጀል ጥፋተኛ ሁኖ መገኘትን የሚያሳይ ሳይሆን ጉዳቱ በወንጀል ሊያስጠይቅ በሚችል ድርጊት መከሰቱ ከተረጋገጠ ብቻ የይርጋ ጊዜ ርዝመት ሊሆን የሚገባው በወንጀል ሕጉ ስር የተመለከተው የይርጋ ጊዜ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡   በአመልካቾች ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በተጠሪ ደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው ጉዳት የወንጀሉ ድርጊት ሊያስጠይቅ የሚችለው የሕግ አግባብ ሲታይ ይርጋው አስር አመት ስለመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀፅ  506(1(ሐ) እና 224(1(ሐ)) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ አኳያ ድርጊቱ ተፈጸመ የተባለው መስከረም 14 ቀን 2005ዓ/ም ሁኖ ክሱ የቀረበው ሁለት አመት ከአለፈ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ግራ ቀኙን ያላከራከረ ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ነው ከተባለ ይርጋው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143 (2) እና ከላይ በተጠቀሱት የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት የአስር አመት የይርጋ ጊዜ አላለፈም፡፡  
Hammasini ko'rsatish...
የቤት ኪራይ .pdf የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016
Hammasini ko'rsatish...
የቤት ኪራይ .pdf3.83 MB
ወራሽ የሆነ ሰው የውርስ ንብረቱን ለመያዝ የወራሽነት ማስረጃ ከፍ/ቤት ማውጣት ግደታ አለበት ወይ ? የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው የውርስ ንብረት የያዘ ሰው የውርስ ክርክር በተነሳ ጊዜ የይርጋ ክርክር ቢያሳ የወራሽነት ማስረጃ ባለማውጣቱ ይርጋን ማንሳት አትችልም ይባላል ወይ ?
Hammasini ko'rsatish...