uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን/Federal Tax Appeal Commission

የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን/Federal Tax Appeal Commission

Kanalga Telegram’da o‘tish
1 536
Obunachilar
-124 soatlar
-17 kun
-130 kun
Postlar arxiv
ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም የወጡ ውሳኔዎች ጉምሩክ ኮሚሽን B-3580 ውሳኔ B-3582 ውሳኔ የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛነት ለፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት ! የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook https://www.facebook.com/ftacofficial Telegram https://t.me/ftac_official (x) Twitter https://twitter.com/federal_appeal YouTube channel https://www.youtube.com/channel/UCzpuuuXybdHh7BlgWXMVI

ከጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም  እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም  የወጡ ውሳኔዎች ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም የወጡ ውሳኔዎች ጉምሩክ ኮሚሽን B-2482 ብይን   ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም የወጡ ውሳኔዎች ገቢዎች ሚኒስቴር A-1028 ውሳኔ ጉምሩክ ኮሚሽን B-3077 ብይን     ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም የወጡ ውሳኔዎች ጉምሩክ ኮሚሽን B-4179 ብይን ገቢዎች ሚስቴር A-1071 ውሳኔ   የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛነት ለፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት ! የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook https://www.facebook.com/ftacofficial Telegram https://t.me/ftac_official (x) Twitter https://twitter.com/federal_appeal YouTube channel https://www.youtube.com/channel/UCzpuuuXybdHh7BlgWXMVI

ኮሚሽኑ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ፡፡ ******************** ፌታይኮ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም የኮሚሽኑ ማኔጅመንት የ2019 በጀት ዓመት
ኮሚሽኑ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ፡፡ ******************** ፌታይኮ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም የኮሚሽኑ ማኔጅመንት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ ክንውን ግምገማ መድረክ አካሄደ።   በግምገማ መድረኩ ላይ ሁሉም የስራ ክፍሎች ባለፉት ሶስት ወራት በዕቅድ የያዟቸውን ተግባራትና ያከናወኗቸውን የሥራ አፈፃፀሞች በዝርዝር አቅርበዋል። በቀረቡት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ያጋጠሙ ክፍተቶች በቅርብ ክትትልና ቁጥጥር የሚታረሙበት አሰራር ላይ መክረዋል።   በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ባስተላለፉት መመሪያ በሩብ ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠልና የታዩ ማነቆዎችን በመቅረፍ በቀጣዮቹ ወራት ለተሻለ አፈፃፀምና ላቅ ያለ ውጤት ሁሉም የስራ ክፍሎች በተቀናጀና በላቀ ቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ግልጽ የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።   የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛነት ለፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት ! የማህበራዊ ትስስር ገፃችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook https://www.facebook.com/ftacofficial Telegram https://t.me/ftac_official (x) Twitter https://twitter.com/federal_appeal YouTube channel https://www.youtube.com/channel/UCzpuuuXybdHh7BlgWXMVI

በስራ ላይ ስነ-ምግባር እና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከኮር የስራ ክፍሎች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡ ******************** ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ፌታይኮ የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ማስተባበሪያ ክፍል በተቋሙ በየጊዜው ከሚያካሂደው የዳሰሳ ጥናቶች በተጨማሪ በኮሚሽኑ ኮር የስራ ክፍሎች በሆኑት በዳኝነት እና በሬጅስትራል ክፍሎች ያለውን የስራ ላይ ስነ-ምግባር አስመልክቶ የዳሰሳ ጥናት አከናወነ።   ጥናቱ ከባለጉዳዮች የሚቀርቡ አስተያየቶችን ተጨባጭ በማድረግ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም በስራ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በውይይት ለመፍታት ያለመ ነው።   በቀረበው የዳሰሳ ጥናት ግኝት ላይ የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት፣ ዳኞች እና የሬጂስትራር አካላት በተገኙበት ፍሬያማ እና ገንቢ ውይይት ተካሂዷል።   በውይይቱም ወቅት በቀረቡት ግኝቶች ላይ ሰፊ ምክክር የተደረገ ሲሆን የታዩ ክፍተቶችን በማረም የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ታማኝነት ያለው ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።   የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛነት ለፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት ! የማህበራዊ ትስስር ገፃችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook https://www.facebook.com/ftacofficial Telegram https://t.me/ftac_official (x) Twitter https://twitter.com/federal_appeal YouTube channel https://www.youtube.com/channel/UCzpuuuXybdHh7BlgWXMVI

የኮሚሽኑ ዕለታዊ ውሎ ተቋማዊ ኃላፊነቶችን በብቃት ለመወጣት የተቀናጀና ከፍተኛ ትኩረትን የሚጠይቅ ሂደት ሲሆን ተቋሙ የተጣለበትን ትልቅ አደራ ለማሳካት የሚያደርገውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ እንደሚከተለው ቀርቧል። https://web.facebook.com/share/v/19biuErqJv/

የፍትሕ ዘርፍ የሥነ-ምግባር ፎረም ጠንካራ የፍትሕ ሥርዓትን ለመገንባት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመለከተ ******************** የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የፍትሕ ዘ
የፍትሕ ዘርፍ የሥነ-ምግባር ፎረም ጠንካራ የፍትሕ ሥርዓትን ለመገንባት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመለከተ ******************** የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የፍትሕ ዘርፍ የሥነ-ምግባር ፎረም የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡ በመድረኩ መክፈቻ እንደተገለጸው፤ ፎረሙ የሥነ-ምግባር መርሆዎችን፣ ግልጸኝነትንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከፍተኛ ሚና አለው። በመሆኑም አካላት ኃላፊነታቸውን ተረድተው መስራት እንደሚገባቸው እና በአሁኑ ወቅት የሚስተዋሉ የሥነ-ምግባርና የመልካም አስተዳደር ክፍተቶች እንዲወገዱ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ በቀጣይም ግልጸኝነትንና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ ብልሹ አሰራሮችን የሚያስወግዱ ሥርዓቶችን ለመዘርጋት፣ የተሞክሮ ልውውጥን ለማዳበር፣ አመራርና ባለሙያዎችን በማሳተፍ ዘላቂ የአሰራር ለውጥ ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ ፍትሕ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ሠነዶች ማረጋገጫ፣ የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እና የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ በሚገኙበት በዚህ ፎረም፤ በሩብ ዓመቱ በእቅድ ዝግጅት፣ በቅንጅት፣ በሥነ-ምግባር አቅም ግንባታና ክትትል እንዲሁም በሀብት ማስመዝገብ ግቦች ላይ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡   Via:-MOJ የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛነት ለፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት !

በችሎት መክፈቻ ዕለት ለ60 ባለጉዳዮች ቀልጣፋ የፍትሕ አገልግሎት ተሰጠ! ****************** ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ.ም ፌታይኮ የችሎት ሥራ በይፋ በተጀመረበት ዕለት የተቀላጠፈና ፍትሐዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በማስፈን ለአጠቃላይ 60 ባለጉዳዮች ፈጣን ምላሽ መስጠት ተችሏል።   በዕለቱ የጠዋት ችሎት ውሎ 43 የአፈፃፀም መዝገቦች የተስተናገዱ ሲሆን ይህም ባለጉዳዮች በሕግ ሂደት ያገኟቸው ውሳኔዎች ሳይዘገዩ ወደ ተግባር እንዲቀየሩና ፈጣን የፍትሕ ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።   ከችሎት ውሎው ጎን ለጎን በሬጂስትራር ክፍል ከተለያዩ አካላት የቀረቡና ለተለያዩ መሥሪያ ቤቶች/ባለድርሻ አካላት የሚላኩ 16 አስተዳደራዊና የሕግ ደብዳቤዎች ተስተናግደው ተገቢው ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል።   ከይግባኝ አቀራረብ ጋር ተያይዞ አስፈላጊ ማስረጃዎችና መረጃዎች ሙሉ በሙሉ ተሟልተው የቀረቡበት 1 የይግባኝ መዝገብ ተስተናግዶ ወደ ሕጋዊ ሂደቱ እንዲገባ ተደርጓል።   በዕለቱ የተከናወኑት ተግባራት የባለጉዳዮችን ጊዜና እንግልት በመቀነስ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ቅልጥፍና በማሳየትና የፍትሕ ሥርዓቱን ተገዳዳሪነት በማጠናከር ረገድ ትልቅ አዎንታዊ ተፅዕኖ ፈጥረዋል።   የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛነት ለፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት ! የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook https://www.facebook.com/ftacofficial Telegram https://t.me/ftac_official (x) Twitter https://twitter.com/federal_appeal YouTube channel https://www.youtube.com/channel/UCzpuuuXybdHh7BlgWXMVI

የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ችሎት በይፋ ስራውን ጀመረ፡፡ ****************** ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ፌታይኮ የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ችሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ስራውን
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ችሎት በይፋ ስራውን ጀመረ፡፡ ****************** ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ፌታይኮ የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ችሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ስራውን ጀመረ፡፡   የችሎቱን መጀመር ምክንያት በማድረግ የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት፣ ዳኞች፣ አመራሮች፣ መላ ሠራተኞች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እና የኮሚሽኑ ተገልጋዮች ተገኝተዋል።   በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙለጌታ አያሌው፤ ኮሚሽኑ ዕለት ከዕለት አፈፃፀሙን እያሻሻለ ለተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ላደረጉት ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡   በተጨማሪም፤ ተቋሙ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዲያከናውን እና ተቋማዊ ትስስሩን እንዲያጠናክር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ላደረገው ድጋፍና ቅን ትብብር አመስግነዋል፡፡   በችሎት መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው፤ ሀገርና መንግስት ጸንተው የሚቀጥሉት እንዲሁም ህዝባዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ የሚቻለው ከግብር ከፋዩ ህብረተሰብ በሚሰበሰብ ግብር በመሆኑ የግብር ከፋዩ ቅሬታዎች አፋጣኝ፣ ፍትሃዊና ህጉን የተከተለ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡   ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም፣ ለኮሚሽኑ የሚደረግ ማንኛውም አይነት ድጋፍና እገዛ ቀጥታ ሀገርን እንደመደገፍና ህዝብን እንደማገልገል የሚቆጠር በመሆኑ ይህ በቅንጅትና በትስስር የመስራት መልካም ጅማሮ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡   የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛነት ለፍትሐዊ የታክስ ሥርዓት !