Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
2 343
Obunachilar
+2424 soatlar
+987 kun
+37730 kun
Postlar arxiv
ወጣቶች የፈጠራ ሃሳባቸውን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ እንዲያዳብሩ በማድረግ በክህሎት የዳበረ ዜጋ የማፍራት ተገባርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ::
የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ትምህርቶችና ፈጠራ ላይ ዝንባሌ ያላቸው የ STEM ክበብ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ጉብኝት በኮሌጁ አካሄዱ::
ኮሌጁ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ የፈጠረውን ግንዛቤ በተጠናከረ መልኩ ውጤታማ ለማድረግ በት/ቤቶች ላይ የቴክኒክና ሙያ ክበብ እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በዚህም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ክበቡን እንዲቀላቀሉ ማድረግ መቻሉም ተገልፇል::
ለተማሪዎቹ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በመልእክታቸውም በቅድሚያ በቀጣይ የክህሎት ባለቤት ወደ ምትሆኑበት ኮሌጃችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ኮሌጁ ት/ቤቶች ላይ በስፋት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የሚንቀሳቀሱ ተማሪዎችን በዘላቂነት በክህሎት ለማብቃት ታሳቢ በማድረግ ይህን የቴክኒክና ሙያ ክበብ በየት/ቤቶች እንዲቋቋም አድርገናልያሉ ሲሆን ተማሪዎች በቀጣይም በኮሌጁ የሚኖራችሁን ቆይታ በምትፈልጉት ሙያ መስክ ራሳችሁን ለማብቃት ልትጠቀሙበት ይገባልም ብለዋል::
ተማሪዎች ኮሌጁ ያለውን የማሰልጠን አቅም ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላም በቀጣይ ለክበብ አባላቱ የህይወት ክህሎትና STEMን መሰረት የደረጉ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ የገለፁት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም የSTEM አባላቱ ከመደበኛ ትምህታቸው ጎን ለጎን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ምቹ አጋጣሚ ይፈጠርላቸዋልም ብለዋል::
በተጨማሪም ተማሪዎቹ በኮሌጁ ቆይታቸው የጥናት፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ አስተባባሪ በሆኑት አሰልጣኝ መ/ር ያሬድ ሁሉአለም አማካኝነት ስለ STEM power ፅንሰ ሀሳብ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን በተጨማሪም በክፍሉ አስተባባሪነት በኮሌጁ የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን ለተማሪዎቹ እስጎብኝተዋል::
የSTEM ክበብ አባላት በተቋሙ የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ወርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በየዲፖርትመንቶቹ ስለሚገኙ የሙያ ስልጠናዎች በተመለከተም በአሰልጣኝ መምህራ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ ተደርጎላቸዋል::
በቀጥይ የቴክኒክንይ ሙያ STEM ክበብ አባላት በኮሌጁ በሚዘጋጅላቸ የሙያ ስልጠናዎችን የሚወስዱ ሲሆን ይህም የ2ኛ ደረጃ ትምህታቸውን ከማጠናቀቃቸው አስቀድሞ ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆኑም የሚያስችላቸው እንደሚሆን ተግልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የፈጠራ ሃሳቦችን ወደ ተግባር በመቀየር በስፋት እየተከናወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ላይ ጉልህ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
በኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የሚመራ የኮሌጁ የቦርድ አባላት በተቋሙ የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችና ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል::
በቦርድ አባላቱ የተጎበኙት የፈጠራ ውጤቶችና ፕሮጀክቶች በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ከፍተኛ ጥረትና በኮሌጁ ያልተቋረጠ ድጋፍ የተሰሩ ሲሆን የማህበረሰቡን ችግር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚፈቱ ታምኖባቸው የተሰሩ እንደሆነም ተገልፇል::
በኮሌጁ ችግር ፈቺ ተብለው ከተሰሩ የፈጠራ ስራዎችና ፕሮጀክቶች መካከልም......
1.በአንድ በሬ ማረስ የሚያስችል የእርሻ ማረሻ ፈጠራ፣
2. የዘር ብክነትን የሚያስቀር ዘር መዝርያ ማሽን፣
3. በአንድ ጊዜ 500 እቁላሎችን ማስፈልፈል የሚችል ማሽን፣
4. እፅዋትን ጨምሮ ከተለያዩ ግብአቶች የተመረተ የነዳጅ ዘይት፣
5. ዘመናዊ የመንገድ ዳር ቁሻሻ ማጠራቀሚያ፣
6. ለኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ውበት የሚያጎናፅፍ ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ሼድ፣
7. የመንገደኞች ማረፊያ አግዳሚ ወንበር... የሚገኙበት ሲሆን በቀጣይ በስፋት ተመርተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ እንደሚደረግም ተገልፇል::
ኮሌጁ የፈጠራ ሃሳብ ማበልጸጊያ ማዕከል እንዲሁም የኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ ተቋም መሆኑን በተግባር እያሳየ እንደሆነ ተመልክተናል ያሉት የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አክለውም በቀጣይ የተጀመሩ ስራዎችን በፍጥነትና በጥራት በማከናወን የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ከመፍታት በተጨማሪ ተቋሙም የራሱን ገቢ ማሳደግ ያስችለዋልም ብለዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት ለኮሌጁ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው የ3ኛዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ከድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት በገባው ውል መሰረት ለ3ኛ ዙር ለኮሌጁ የፅዳትና ጥበቃ ሰራተኞች ለተከታታይ 3 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል::
ለ3 ተከታታይ ቀናት የተሰጠውን ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ምስጋና ያቀረቡት የድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ አክለውም ኮሌጁ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ የሚሰጡት አገልግሎት እንዲሻሻል በማቀድ ይህንና መሰል ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ማመቻቸቱ የሚበረታታ ነውም ብለዋል::
በዚህ 3ኛ ዙር ስልጠና ላይ የተካፈሉ ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና በተግባር ላይ ማዋል የሚጠበቅባቸው መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም በቀጣይ በሚፈጠርላቸው መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ አቅማቸውን እንዲገነቡና በተመደቡበት የስራ ዘርፍ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ለተቋሙ ራዕይና ስኬት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል::
ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኃላ በስራ ገበታችሁ ላይ ያመጣውን ለውጥ በተግባር እንድታሳዩ ያስፈልጋል ያሉት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም በመሰል ስልጠናዎች የሚመዘገቡ ውጤቶችን በድጋፍና ክትትል እናረጋግጣለንም ብለዋል::
የ3ኛው ዙር ስልጠና ቀደም ብለው ከተሰጡት የ1ኛና 2ኛ ዙር ስልጠናዎች በተለያየ ምክንያት ዘግይቶ እንደተሰጠ ያስታወሱት የEASE ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ አክለውም ይህ ስልጠና ማስጀመርያ መሆኑንና ኮሌጁ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅንጅት ለመስራት ባደረገው ስምምነት መሰረት አስፈላጊ የሆኑ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቀጣይ እንደሚዘጋጁም ገልፀዋል::
የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞችም ከእለቱ ክብር እንግዶች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት17/2017 ዓ.ም
"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ 4ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የክህሎት ውድድር መነሻ በማድረግ በክላስተር ደረጃ በኮሌጁ መካሄድ ጀመረ::
የክህሎት ውድድሩ ከዚህ ቀደም በተቋም ደረጃ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በክላስተር ደረጃ የሚካሄደው ውድድርም በስራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተካሂዷል::
በዛሬው እለት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተካሄደው ውድድር በ7 ዲፓርትመንቶች በሚገኙ 7 የሙያ ዘርፎች ላይ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ያሳተፈ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን......
በAuto mechanics
በBuilding Electrical Installation
በIndustrial Electrical/Electronic control technology
በStructural construction work
በWood work technology....
በMechanics
በHardware & Network Servicing
በUllinary Art
የሙያ ዘርፎች ላይ ውድድሮች ተደርገዋል::
ኮሌጁ ከተቋም ጀምሮ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ በየጊዜው በሚካሄደው የክህሎት ውድድር መድመቅ የቻሉ እንዲሁም ሀገርን ወክለው በአለም አቀፍ ደረጃ የተወዳደሩ ውጤታማ ተወዳዳሪዎችን ያፈራ በመሆኑ ከስር ለሚመጡ ሰልጣኞች የበለጠ መነሳሳትን እንደሚፈጥር የገለፁት ደግሞ የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ናቸው::
ም/ዲኑ አክለውም ይህ ውድድር ወቅቱን ጠብቆ በየጊዜው መደረጉ ዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ በክህሎት የበቁ ዜጎችን በማፍራት ኢንዱስትሪውን ለመመገብ በሚያደርገው ርብርብ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ገልፀዋል::
በተቋሙ በክላስተር ደረጃ የተካሄደውን ውድድር የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በእለቱ ተወዳዳሪ የነበሩ ሰልጣኝ ተማሪዎችንም አበረታተዋል::
ይህን ውድድር በበላይነት የሚያጠናቅቁ ተወዳዳሪዎች በቀጣይ በአስተዳደር/በክልል ደረጃ በሚደረገው ውድድር ላይ ኮሌጁን ወክለው የሚሳተፉም ይሆናል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 16/2017 ዓ.ም
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የሚካሄደው የ2017 ዓ.ም የክህሎት ውድድር በክላስተር ደረጃ መካሄድ ጀመረ።
በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በጋርመንት፣ ዉድ ወርክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ሆቴል እና ቱሪዝም፣ ኮንስትራክሽን፣ አውቶሞቲቭ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና በአይሲቲ ላይ ሰልጣኝ ተማሪዎች በአስተዳደር ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ኮሌጃቸውን ወክለው ለመሳተፍ ከየዘርፉ በተመረጡ ዳኞች ፊት ክህሎታቸውን በመጠቀም ስራዎቻቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በዚህም በክላስተርና በአስተዳደር ያለውን ውድድር በበላይነት የሚያጠናቅቁ ተወዳዳሪዎች ኮሌጆቹን እንዲሁም አስተዳደሩን በመወከል በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የክህሎት ውድድር የሚሳተፉ እንደሚሆን በዳይሬክቶሬቱ የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ ቡድን መሪ ወ/ሮ አለምጸሃይ ጌታቸው ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 16/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
