uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
2 280
Obunachilar
+924 soatlar
+957 kun
+34630 kun
Postlar arxiv
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተሰሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች በአስተዳደሩ ወጣቶች ተጎበኙ:: #EIPC ነሃሴ 07.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ በዛሬው እለት ከተካሄደው የወጣቶች መድረክ ጎን ለጎን በስራና ክህሎት ቢሮ አዘጋጅነት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡበት ኤግዚብሽን በኮሌጃችን ለጉብኝት ክፍት ተደርጓል:: በዚህ ለአስተዳደሩ ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ንቅናቄ ለመፍጠር በቢሮው በተዘጋጀው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ላይ በኮሌጃችን በተለያዩ ጊዜያት የተሰሩና የተሸጋገሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ በቀጣይ 3ቀናት ለጎቡኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ተገልፇል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

ባለፉት አምስት አመታት ከ70 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተገለፀ " የድሬ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት " በሚል መሪ-ሀሳብ በዛሬው እለት የብቃት ፕሮጀክት 4 ተኛ ዙርን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር ተካሂዷል ። መድረኩ ወጣቶች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት የስራ ላይ ልምምድ በማድረግ በቀጣይ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማስቻል ያለመ መድረክ ነው። በመርሀ-ግብሩ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች በሚሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውንም በኢኮኖሚ በማገዝ እንዲሁም ደግሞ ከተማቸውን እና ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ወጣቶች መሆን እንዳለባቸውም ነው ክቡር ከንቲባው በእለቱ ያስታወቁት ። የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ባለፍት ሶስት አመታት ወጣቶችን በስራ ብቁ አድርጎ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ከማድረግ አኳያ በርካታ ስራዎችን መስራቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ አስታውቀው በአራተኛ ዙርም ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በተመሳሳይ ሰልጥነው ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀዋል ። ባለፍት አምስት አመታት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ከ 70 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር ከመቻሉም በላይ በሁለቱም ቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጆች በአጫጭር እና መደበኛ ከ 30 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሰልጠን ለስራ ብቁ ማድረግ መቻሉንም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው በእለቱ ያስታወቁት ። አቶ ሮቤል ጌታቸው አክለውም አሁን ላይ ካለው የስራ አጥነት ቁጥር አንፃር እንዲሁም በየጊዜው እየጨመረ ካለው የወጣቶች ቁጥር አንፃር እየተፈጠረ ያለው የስራ እድል በቂ አለመሆኑን ተናግረው ይህንንም ለመፍታት ተቋሙ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ነው አቶ ሮቤል ጌታቸው ያስታወቁት ። በመድረኩም በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የድሬዳዋ ወጣቶች የስራ ባህል ሽግግር አመለካከትን ከመቀየር አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ እስከመክፈት በሚል ርዕስ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሰነዱንም መነሻ በማድረግም ውይይት ተካሂዷል ። ©️ DGC ነሐሴ 7/2018

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራርና ሰራተኞች የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካላ መርሃ-ግብር አካሄዱ:: #EIPC ነሃሴ 6.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው እለት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ማስጀመርያ መርሃ-ግብር እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም በኮሌጁ ተካሂዷል:: የኮሌጁ አመራና ሰራተኞች በክረምቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ምክንያት በማድረግ በኮሌጁ ባካሄዱት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የተለያዩ ለምግብነት የሚውሉ የችግኝ አይነቶችን በተቋሙ በተመረጡ ቦታዎች ላይ በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል:: ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ በቀጣይ የክረምት በጎ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን በዚህም የደም ልገሳ፣ የማዕድ ማጋራት እንዲሁም አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የመሳሰሉ በጎ ተግባራት በኮሌጁ ማሀበረሰብ እንደሚከናወኑም ተገልፇል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡ #EIPC ሐምሌ 29.2018 ድሬዳዋ የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖችን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ አካሂደዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በተቋም ደረጃ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በዚህም ኮሌጁ ካሳየው ውጤታ ጉዞ ብዙ ልምዶችን መቅሰም መቻላቸውንም ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የ2018 የክረምት የክህሎት ስልጠና በኮሌጁ ተጠናክሮ መካሄዱን ቀጥሏል:: #EIPC ሐምሌ 23. 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 "የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" የክረምት ስልጠና ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለሶስት ቀናት ሲከተታተሉ የቆየውን የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና አጠናቀቁ:: ሰልጣኞቹ የህይወት ክህሎት ስልጠናቸውን እንዳጠናቀቁ በኮሌጁ የሚገኙ ዲፓርትመንቶች እና ስልጠና የሚሰጥባቸውን ወርክሾፖች ተዘዋውረ የተመለከቱ ሲሆን ስለ ሙያ ዘርፎችም ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል:: የክረምት ክህሎት ሰልጣኞቹ በተፈጠረላቸው ግንዛቤ መነሻነት ሚፈልጉትን የሙያ ስልጠና አይነት የመረጡ ሲሆን ቀጣይ በተቀመጠላቸው መርሀ-ግብር መሰረትም ስልጠናቸውን የሚከታተሉ ይሆናል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በአስተዳደሩ ለሚገኙ ወጣቶች የክረምት ወቅት የሙያ ስልጠና በኮሌጁ መስጠት ተጀመረ:: #EIPC ሐምሌ 21. 2018 ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 የክረምት ወቅት የክህሎት ስልጠና "አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" በሚል በአስተዳደሩ ለሚገኙ ተማሪዎችና ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያዘጋጀውን የክህሎት ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሂዷል:: በእለቱ ለወጣቶቹ በተዘጋጀው ኦረንቴሽን ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ የክረምት ወቅት ስልጠና የተዘጋጀበት ዋና አላማ ጊዜው የክህሎት በመሆኑ ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ቁምነገር ላይ በማዋል ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ገልፀው በተለይም የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክረምቱን በኮሌጃችን በሚኖራችሁ ቆይታ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በጥልቀት የምትገነዘቡ በመሆኑ በቀጣይ ምዕራፋችሁ ለሙያ ተኮር ስልጠናዎች ቅድሚያ እንድሰጡ ይረዳችኃልም ብለዋል:: ወጣቶች በትምህርት ያገኙትንም ሆነ ያላቸውን ሀሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር ከየትኛውም ቦታ በተሻለ ቴክኒክና ሙያ ላይ ምቹ ሁኔታ መኖሩን የገለፁት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የትምህርትና ስልጠና ዋና ሀላፊ አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ አክለውም ወጣቶች በተመቻቸላቸው ወርቃማ እድል ስልጠናውን በአግባቡ በመውሰድ በቆይታቸው ተፈላጊውን ክህሎት ይዘው እንዲወጡ አሳስበዋል:: ቴክኒክና ሙያ ከሌሎች የትምህርት ተቋማት ልዩ የሚያደርገው ወጣቶች የተማሩትን በእጃቸው ነካክተው በተግባር የሚሰለጥኑበትና ሰርተው የሚያሳዩበት ተቋም በመሆኑ ነው ያሉት ደግሞ የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን አገልግሎት ዋና ሀላፊ እና ም/ል ዲን የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አያይዘውም የክረምት ሰልጣኞች ከሚወስዷቸው ስልጠናዎች በተጨማሪ ወደ ቢዝነስ ሊቀይሩት የሚችሉት የቢዝነስ ሀሳብ ካላቸው ቢዝነስ ፕላናቸውን በኮሌጁ እንዲሰሩ ከማድረግ በተጨማሪ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትልም የሚደረግ መሆኑን በመድረኩ ገልፀዋል:: የ2018 የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ የክረምት ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ወደ ኮሌጁ የመጡ ወጣቶች በቅድሚያ የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውም የቀጣይ ህይወታቸውን የመምራት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ክህሎት እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን የሚያዳብሩበት ስልጠና ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውን እንዳጠናቀቁ በቀጣይ በመረጡት የሙያ ዘርፍ ላይ ስልጠናቸውን የሚወስዱ ይሆናል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኮንስትራክሽ ዘርፍ ላይ ያተኮረ የሙያ ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል:: #EIPC ሐምሌ 13 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮስትራክሽን ኮንትራክተሮች ማህበር ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት የሚሰጠው ይህ የክህሎት ስልጠና ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ሲሆን በሁለት የሙያ ዘርፎችም በኮሌጁ እየተካሄደ ይገኛል:: በኮሌጁ እየተሰጠ የሚገኘው የክህሎት ስልጠና ለኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን፣ ለኮሌጅ ሰልጣኝ ተማሪዎች እንዲሁም ሳይት ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ባጠቃላይ ለ50 ተሳታፊዎች ሙሉ ማሰልጠኛ ማቴሪያሎች ተሟልተው የተግባር ስልጠናው በሁለት የሙያ ዘርፎች ማለትም በRefrigeration, Heat Pump Technology and Air Conditioning System እንዲሁም በSolar grid system ሙያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝም ተገልፇል:: ይህ ስልጠና በጀርመኑ BAUVERBÄNDE NRW e.V. እና በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ ማህበራት እንዲሁም የሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት መካከል በሚደረግ የሙያ ትምህርትና ስልጠና አጋርነት አማካኝነት የተገኘ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

በክረምት የክህሎት ስልጠና የአንድ ሙያ ባለቤት ይሁኑ!!
በክረምት የክህሎት ስልጠና የአንድ ሙያ ባለቤት ይሁኑ!!

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa) - Telegram kanali @eipc2001 statistikasi va tahlili