cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Sadat kemal(ተውሂድ ቲዩብ)

ወጣት ሆይ ንቃና ፣ ጫት ቁማር ሱስ አቁምና ፣ ስርቆት ወንጀል ሀራም ነውና ፣ ጠቅለል ብለህ ግባ ወደ ሱና ። የተውሂድ ሙሁራኖች ት/ትና የራሴ ግጥምና እይታዎች በፁሁፍና በድምፅ የሚለቀቅበት ((channel))

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganAmxar4 072Din & Maʼnaviyat27 678
Reklama postlari
2 251
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+127 kunlar
+7430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አሰላሙአለይኩም የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ኢንሻ አላህ የነገው የእሁድ ሳምንታዊ ደርስ በሑዘይፋ መስጂድ ይኖራል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ ~ እውነቱን ለመናገር አንዳንድ ችግሮቻችንን እራሳችን ነን የምናውሰበስባቸው። እንዴት 80%፣ 90% ሙስሊም የሆነ ህዝብ "ተጨቆንኩ፣ ተበደልኩ" ብሎ ያለቅሳል?! ወላሂ! 100% ሙስሊም በሆነ ህዝብ ውስጥ በአንድ ተል ካሻ ግለሰብ እምነት ተኮር በደል ሲፈፀም አይቻለሁ። ሰው እንዴት በዚህ መጠን ራሱን ያስደፍራል? "የተናቀ መንደር በአህያ ይወረራል" ይባላል። በዚህ ደረጃ ራሳችንን ካስደፈርን ጩኸት አያምርብንም የሚሆነውን መቀበል ነው። "ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!" ለማንኛውም እስከዛሬ ከደረሱ እልፍ ክስተቶች ትምህርት እንውሰድ። በሰፈር መፈታት የሚችልን ጉዳይ አገር አቀፍ አጀንዳ ካደረግነው መፍትሄ የማግኘት እድሉ በጣም ይመነምናል። ጎንደርም አፋርም ለሚደርስ ትንኮሳ ምላሻችን እኩል ለቅሶ ብቻ ነው መሆን ያለበት? ስለዚህ አካባቢያዊ ችግሮችን ገና ሳይጎመሩ በፊት አስተማሪ በሆነ መልኩ አካባቢያዊ መፍትሄ እናብጅላቸው። "ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ።" Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 14
መውሊድና እልክ
Hammasini ko'rsatish...
መውሊድና እልክ.mp37.88 MB
00:58
Video unavailableShow in Telegram
የውሸት ጥግ "ይበልጣል ከኢዶች ሁላ መውሊዶ ያረሱለላህ"?
Hammasini ko'rsatish...
6.88 MB
👍 5
የአህባሾች ቲቪና መውሊድ
Hammasini ko'rsatish...
የአህባሾች ቲቪና መውሊድ.mp35.16 MB
"ኑሩን ከኑሩ ኸለቀው ጀሊሉ" ~ ይሄ ንግግር ሱፊዮች አካባቢ ተደጋግሞ የሚሰማ ነው። ምን ማለታቸው ነው? * "ኑሩን" ሲሉ ነብዩን ﷺ ማለታቸው ነው። * "ጀሊሉ" ሲሉ አላህ ማለታቸው ነው። * "ከኑሩ" ሲሉ ከአላህ ኑር ማለታቸው ነው። * ኸለቀው = ፈጠረው ጥቅል መልእክቱ:- አላህ ነብዩን ﷺ ከራሱ ኑር (ብርሃን) ነው የፈጠራቸው እያሉ ነው። አንዳንዶቹ ይህንን መነሻ በማድረግ በግልፅ ነብዩ ﷺ የአላህ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው ብለዋል። ይሄ መሰረተ-የለሽ እምነት ነው። ለዚህም በተለያዩ ነጥቦች ምላሽ መስጠት ይቻላል። 1- ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት መሰረተ ቢስ ወሬ እንጂ አንድም የቁርኣንም ይሁን የሐዲሥ መረጃ ማቅረብ አይችሉም። 2- በአፈጣጠር በኩል ነብዩ ﷺ እንደሌላው የአደም ዘር ሰው ናቸው። እዚህ ላይ ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም። አላህ እንዲህ ሲል ሰው አዋጅ እንዲናገሩ አዟቸዋል፦ {قُلۡ إِنَّمَاۤ أَنَا۠ بَشَرࣱ مِّثۡلُكُمۡ} "እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ' በላቸው።" [ከህፍ፡ 110] 3- ወላጆቻቸው እና ዘር ማንዘራቸውም የሚታወቁ ናቸው። እሳቸውን ጨምሮ ሁሉም እንደ ሌላው የሰው ዘር የአደም ዘር ናቸው። አደም ከጭቃ መፈጠራቸው ግልፅ ነው። 4- ነብዩ ﷺ ሞተዋል። ስለዚህ "ከአላህ ኑር ነው የተፈጠሩት፣ የሱ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው'' የሚል ሰው የአላህ ክፍል ሙቷል እያለ ነው። ይሄ ሰቅጣጭ ድምዳሜ ነው። ለነገሩ እነዚህ ሰዎች የነብዩን ﷺ መሞትም ሊከራከሩ ይችላሉ። የሱፊያ እምነት በብዙ ነጥቦች ከ0ቅል ጋር የተኳረፈ እምነት ነው። እንኳን ነብዩን ﷺ ፤ በየመንደሩ ያሉ ሸይኾች ሲሞቱ "አልሞቱም፤ ሌላ አገር ወጥተዋል" እያሉ የሚያምኑ ብዙ ናቸው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ መዲና ሞተው ሶሐቦች አጥበው፣ ከፍነው፣ ሶላተል ጀናዛ ከሰገዱባቸው በኋላ ዓኢሻ ቤት ውስጥ ተቀብረዋቸል። አላህም ሟችነታቸውን እንዲህ ሲል አስረግጦ ተናግሯል:- {إِنَّكَ مَیِّتࣱ وَإِنَّهُم مَّیِّتُونَ} "አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው።" [ዙመር: 30] "ሲሞት እንገላገለዋለን" ሲሉ ለነበሩ ጠላቶችም ''እርማችሁን አውጡ እሱ አይሞትም" አይደለም ያላቸው። ይሄውና ምላሹ፦ {وَمَا جَعَلۡنَا لِبَشَرࣲ مِّن قَبۡلِكَ ٱلۡخُلۡدَۖ أَفَإِی۟ن مِّتَّ فَهُمُ ٱلۡخَـٰلِدُونَ (34) كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤىِٕقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ} "(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም። ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን? ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት።" [አንቢያእ፡ 34-35] ማምታቻ:- - ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት አንድ እንዲህ የሚል የሚያቀርቡት "ሐዲሥ" አላቸው፦ أولُ ما خلق اللهُ نورُ نبيِّكَ يا جابرُ "መጀመሪያ አላህ የፈጠረው የነብይህን ኑር (ብርሃን) ነው፣ ጃቢር ሆይ!" በየትኛውም የሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ የማይገኝ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 4
01:05
Video unavailableShow in Telegram
25.13 MB
👍 7
00:25
Video unavailableShow in Telegram
9.41 MB
የአሽዐሪያ ፅንፈኝነት፣ ፈኽሩ ራዚ እንደ ናሙና ~ ፈኽሩ ራዚ (606 ሂ.)፦ የኢብኑ ኹዘይማን ኪታቡ ተውሒድ “በእውነት እርሱ የሺርክ መፅሀፍ ነው” ይላል። [ተፍሲሩ ራዚ፡ 27/582] የሚገርመው የሰለፎችን ዐቂዳ የሚያፀናውን ኪታብ በዚህ መልኩ በሺርክ የሚወነጅለው ራዚ “السر المكتوم في مخاطبة النجوم” የተሰኘ ወደ ከዋክብት አምልኮና ወደ ድግምት የሚጣራ ኪታብ የፃፈ መሆኑ ነው። በዚህ እጅግ ሰቅጣጭ ኪታብ የተደናገጡ አድራቂዎቹ “ይሄ ኪታብ የሱ ስራ አይደለም” ብለው በከንቱ ሊሟገቱ ሞክረው ነበር። ግና ራሱ ራዚ “መጧሊቡል ዓሊያ” በተሰኘው ኪታቡ ላይ የዚህን የድግምት ኪታብ ስምና የራሱ መሆኑን ጠቅሶት መገኘቱና ወደዚህ ሺርክ መጣራቱ ለመከላከል እንዳይመች አድርጎታል። [ገፅ፡ 199፣ 200፣ 210፣ 216፣ 219-222] ይሄ ግልፅ የሆነ ከኢስላም መውጣት ነው። ያለው ቀዳዳ “ምናልባት ሳይቶብት አይቀርም” የሚለው የአንዳንዶች ግምት ነው። በሚገርም ሁኔታ ራዚ ወደ ቀብር አምልኮ ሲጣራ የአርስቶትል ባልደረቦች የሆነ ጥናት በከበዳቸው ቁጥር ወደ ቀብሩ ሄደው ሲመራመሩ ይገለጥላቸው ነበር ብሎ እንደ ማጠናከሪያ መጥቀሱ ነው። [አልመጧሊብ፡ 243] ሱብሓነላህ! በዚህ ደረጃ ያለ ሰው ነው እንግዲህ የአኢማዎች ኢማም የሆኑትን ኢብኑ ኹዘይማን የሚወርፈው። ይሄ ብቻም አይደለም። የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ከሚያስተባብሉ አሽዐሪዮችና ማቱሪዲያዎች ውስጥ የሱና ሰዎችን ብቻ ሳይሆን አልፈው ቁርኣንና ሐዲሥን ጭምር በተሽቢህ (ፈጣሪን ከፍጡር ጋር በማመሳሰል) በግልፅ እስከ መክሰስ ደርሰዋል። ከነዚህ ደፋሮች ውስጥ አንዱ ይሄው ፈኽሩ ራዚ ነው። በመረጃ ነው የማወራው። ይሄውና ንግግሩ፡- أن الأخبار المذكورة في باب التشبيه بلغت مبلغاً كثيراً في العدد، وبلغت مبلغاً عظيماً في تقوية التشبيه، وإثبات أن إله العالم يجري مجرى إنسان كبير الجثة عظيم الأعضاء! وخرجت عن أن تكون قابلة للتأويل “በማመሳሰል ርእስ ላይ የተጠቀሱት ዘገባዎች በቁጥር ብዙ መጠን ደርሰዋል። ማመሳሰልን በማጠንከርና የአለሙ አምላክ ግዙፍ ክፍሎች ያሉት ትልቅ አካል እንደሆነ በማፅደቅ ላይ ከባድ ደረጃ ደርሰዋል። ተእዊልን (ቁልመማን) የሚያስተናግዱ ከመሆንም አልፈዋል።” [አልመጧሊቡል ዓሊያ፡ 9/213] ንግግሩን በጥሞና አስተውሉት። ሸሪዐዊ ማስረጃዎችን በ“ማመሳሰል” መክሰሱን ተውት። አሽዐሪያ ሰፈር የተለመደ በሽታ ነው። ሰውየውም የአላህን መገለጫዎች (ሲፋት) የሚያፀድቁ ማስረጃዎችን ነው ማመሳሰልን ይሰጣሉ፣ ማመሳሰልን ያጠናክራሉ የሚለው። ነገር ግን የአላህን ሲፋት የሚገልፁ የሸሪዐ ማስረጃዎች ከመብዛታቸው የተነሳ ለቁልመማ እንኳን እንደፈተኗቸው ማመኑን አስምሩበት። (ከመቆልመም ባይመለሱም።) በዚህ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃዎችን ገፍተው ከጣሉ በኋላ ነው እንግዲህ ራሳቸውን የተውሒድ ሰዎች አድርገው የሚያቀርቡት። ደግሞም እወቁ! የዛሬዎቹ አሕባሾች ዑለማዎችን ማkፈር ከቀደሙት የጥፋት አስተማሪዎቻቸው የቀዱት ልክፍት እንጂ አዲስ ነገር አይደለም። የሆነ ሆኖ ራዚ የኋላ ኋላ በከባባድ የዐቂዳ ጉዳዮች ላይ ግራ መጋባቱን ደጋግሞ ይገልፅ ነበር። እድሜውን የፈጀበትን የዒልመል ከላም ፍልስፋና ጥሎ “የአሮጊቶችን መንገድ አጥብቆ የያዘ እርሱ ነው የሚድነው!” ሲል እንደነበር ኢብኑ ከሢር እና ሌሎች አኢማዎች ገልፀዋል። [አልቢዳያ ወኒሃያ፡ 17/12] Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

00:59
Video unavailableShow in Telegram
20.10 MB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.