cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Tikvah-University

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
3 075
Obunachilar
-124 soatlar
+57 kunlar
+2730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለጤና ሚኒስቴር አዲስ የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ (NMEI) 2016 ዕጩ ተወዳዳሪዎች በቅርቡ ሰጥቶት የነበረውን የፅሁፍ ፈተና ውጤት በሙሉ ሰርዟል፡፡ ስለተፈጠው ነገር ኮሌጁ ምን አለ? በፈተናው ውጤት ላይ ቅሬታ ካቀረቡ አስር ተፈታኞች ውስጥ ስምንቱ የቃል ፈተና ላይ ሊካተቱ ችለዋል፡፡ በአንፃሩ አንድ ተፈታኝ ለቃል ፈተናዉ ያላለፈ፣ ነገር ግን ቅሬታ አቅርቦ በእጅ በሚታረምበት ወቅት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ቃል ፈተናዉ ተካቶ ነበር፡፡ ተፈታኞች የተሳሳተ የኮድ አጠቋቆር በመጠቀማቸው ፈተናው የራሱ ባልሆነ ኮድ መታረሙ ኮሌጁ ገልጿል፡፡ አንዳንድ ተፈታኞች ከተሰጠው ቦታ ውጪ በማጥቆራቸውና ሌሎች ደግሞ በደንብ ባለማጥቆራቸው በዕርማት ወቅት የኮምፒውተር ስህተት ማስከተሉ ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ በእጅ ሲታረም ግን ትክክል ሆኖ መገኘቱን ኮሌጁ ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም "የሁሉንም ተፈታኞች መብት ለማስጠበቅና የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረም" የሁሉም የመልስ መስጫ ወረቀቶች በእጅ እንዲታረሙ መደረጉን ኮሌጁ ገልጿል፡፡ በዚህም ሁሉም የተለጠፉ የፈተና ውጤቶች መሰረዛቸውን ኮሌጁ አረጋግጧል፡፡ ለግንቦት 11/2016 ዓ.ም ተይዞ የነበረው የቃል ፈተናም መሰረዙን ገልጿል፡፡ ሁሉም የፈተና ውጤት በእጅ ከታረመ በኃላ ለቃል ፈተናው ብቁ የሆኑትን የስም ዝርዝር በድጋሚ በድረ-ገጽ እንደሚለጠፍ ኮሌጁ አሳውቋል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ሚኒስቴር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አምባሳደሮች 10ኛ ዙር ስልጠና መርሐግብር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስጀምሯል፡፡ ሚኒስቴሩ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሚሰጠው ስልጠና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 2,000 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አምባሳደሮች ለ33 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በዘጠኝ ዙሮች ከ47 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ አምባሳደሮችን አሰልጥኖ ማስመረቁ ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
በሳምንቱ መጨረሻ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር ተቋሙ አሳውቋል። በዩኒቨርሲቲው ብሎክ አራት 4ኛ ፎቅ አንድ ዶርም ላይ "ተከስቶ የነበረው መጠነኛ የእሳት አደጋ የከፋ አደጋ ሳያደርስ ወዲያው በቁጥጥር ስር መዋሉን ተቋሙ ገልጿል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚወስዱ የተዘጋጀ መለማመጃ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት የኦንላይን ፈተናውን ይለማመዱ። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
በአዲስ አበባ የተገነባ የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተመርቋል። የትምህርት ቤቱ ግንባታ በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባ ሲሆን፤ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ግንባታው መከናወኑ ተገልጿል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ከ300 በላይ አይነ ስውራን ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተማር አቅም አለው ተብሏል። ለአይነ ስውራን ምቹ የሆኑ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፃሕፍት እና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን መያዙ ተመላክቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳሪ ትምህርት ቤቱን መረከቡ ታውቋል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#Tecno #Camon30Pro5G የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነውና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ፥ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል አስተዋውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሔደው የማስተዋወቂያ መርሐግብር፥ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ (SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው። "ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እንደሚሠሩ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ሰኢድ አራጋው በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡ #Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
Hammasini ko'rsatish...
#Update የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆኗል፡፡ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ብቻ ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡ ስለሆነም ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድርግ አስፈላጊ በመሆኑም ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የበይነ መረብ ተፈታኞች ባሉበት ሆነው ልምምድ ማድረግ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል/ከተማ አስተዳደር የተላከውን የይለፍ ቃል እና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡ በዚሁ መሠረት መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡ ተፈታኞች ከተደለደሉበት ክለስተር ውጪ ሲሰትሙን መጠቀም #እንደማይችሉ አገልግሎቱ አሳስቧል። (ፈተናው የሚሰጥበት አድራሻ እና ተፈታኞቹ የሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ከላይ ተያይዟል።) @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE የዩኒቨርሲቲዎችን አፈጻጸም ለመለካት የሚረዱ ቁልፍ የውጤት መለኪያ አመላካቾች (KPIs) መዘጋጀታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ቁልፍ የለውጥ አጀንዳዎች አንፃር በውጤት እየተለኩ የሚሔዱበት የአሰራር ስርዓት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ እንደሚዘረጋ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ ገልፀዋል፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ሥራ ፈጣሪ እና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ የሰው ኃይል ማፍራት እንዲችሉ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተልኳቸውን በሚገባ እንዲወጡ ቁልፍ የለውጥ አጀንዳዎች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲዎች እድገት እና ውጤት ለመለካት የሚረዱ ቁልፍ የውጤት መለኪያ አመላካች መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን አቶ ኮራ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ባለው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፎረም ላይ አንስተዋል። በተዘጋጁት ቁልፍ የውጤት መለኪያ አመላካች መስፈርቶች (KPIs) ላይ ውይይት በማድረግ ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ፕሬዝዳንቶቹ ውል እንሚገቡ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
#Update የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ገለፀ። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው "ሰላም ሰፈር" ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ረቡዕ ከጠዋቱ 2:45 አካባቢ እንደሆነ ፖሊስ አመልክቷል። "በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት፣ ተጠርጣሪው ሟችን ጀርባዋ ላይ በጩቤ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል" ሲል ፖሊስ ገልጿል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጭ እንደሆነም ተግልጿል፡፡ ተጠርጣሪው የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆነና ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለሥራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመ ፖሊስ ገልጿል። በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች "ድርጊቱ የተፈጸመው በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ነው" በሚል የተሰራጨው እና ከብሔር ጋር የተያያዘ ግድያ ለማስመሰል የሚደረገው ሙከራ ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው የነበሩ መሆኑን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል። @tikvahethiopia @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
#ጥቆማ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡ የብሪቲሽ ካውንስል IELTS የፈተና ማዕከል የIELTS ፈተና ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡ ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል። የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇 https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589 @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...