uz
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Kanalga Telegram’da o‘tish

EEP Communication

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali EEP Communication analitikasi

EEP Communication (@eepcommuication) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 555 obunachidan iborat bo'lib, Texnologiyalar & Aralashmalar toifasida 8 397-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 165-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 555 obunachiga ega bo‘ldi.

21 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 10 ga, so‘nggi 24 soatda esa 1 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.74% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 14.94% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 003 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 323 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 9 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
EEP Communication

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 22 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Texnologiyalar & Aralashmalar toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 555
Obunachilar
+124 soatlar
+87 kunlar
+1030 kunlar
Postlar arxiv
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከቻይናው የጂሲኤል ኢነርጅ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሊቀመንበር ጋር ተወያየዩ ……..///…….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና የቻይናው ጂሲኤል ኢነርጅ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሊቀመንበር ሚስተር ዡ ጎንግሃን ሁለቱ ተቋማት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ የሲጂኤል ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሊቀመንበር ሚስተር ዡ ጎንግሃን ኩባንያቸው በታዳሽ ኃይል ልማትና ኦፕሬተርነት፣ በሲልከን፣ ሊቲየም እና በሌሎች ማዕድናት ምርትና ማቀነባበር ላይ በስፋት እየተሳተፈ ስለመሆኑ ለኢንጂነር አሸብር አስረድተዋል፡፡ ኩባንያቸው በኢትዮጵያም በቅርቡ በድሬደዋ ከተማ አካባቢ በአሉሚኒየም፣ ኮባልትና ኮፐር ማቀነባበር ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ገልፀው ለዚህም አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ፋብሪካው በአጭር ጊዜ ውስጥ 4 ሺ ሜጋ ዋት እንዲሁም በሚቀጥሉት አምስትና ስድስት ዓመታት 6 ሺ ሜጋ ዋት ኃይል እንደሚያስፈልገው ጠቅሰው ፋብሪካው ውጤታማ እንዲሆን ተቋሙ ይህን ኃይል ዝግጁ እንዲያደርግላቸውም ሊቀመንበሩ ጠይቀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ለፋብሪካው ከሚያስፈልገው የኃይል አቅርቦት ባለፈ በተለያዩ የኃይል ልማት ዘርፎች፣ በዳታ ማይኒንግ፣ በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ ግንባታ እና በአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍና ከተቋሙ ጋር በትብብር ለመስራት  ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው ተቋሙ ከኩባንያው ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃደኛና ደስተኛ እንደሆነ ገልፀው ውይይቱ ፍላጎቶቹን ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡ የዳታ ማይኒንግ ለኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (GDP) እያበረከተ ያለው አስተዋጽዖ አነስተኛ በመሆኑ ተቋሙ አሰራሮቹን እንደገና ለማደራጀት እየሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡ የሁለቱን ተቋማት በጋራ የመስራት ፍላጎት ወደ ተግባር ለመለወጥ ሥራውን የሚያስተባብር የቴክኒክ ቡድን እንዲቋቋም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+6

አብዛኞቹ ግድቦች በቂ ውሃ ይዘዋል ………///……….. አብዛኞቹ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች በክረምቱ የዝናብ ወቅት በቂ ውሃ መያዛቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የግድብ ደህንነት ክትትል እና ቁጥጥር ሥራ አስኪያጅ ገልፀዋል። ሥራ አስኪያጁ አቶ ኤሊያስ ደላሽ እንደተናገሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ የተከዜ፣ጊቤ አንድ፣የፊንጫ እና ቆቃ ግድቦች መያዝ የሚጠበቅባቸውን የውሃ መጠን ሙሉ በሙሉ ይዘዋል። ለበለስ ኃይል ማመንጫ ጥቅም ላይ የሚውለው የውሃ ከፍታ ከሚጠበቀው 1787 ሜትር በላይ በሳንቲም ሜትሮች ከፍ ማለቱን ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተመርቆ ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት መግባቱ ለሌሎች ግድቦች ውሃ የመያዝ ሥራዎችን ያሳለጠ መሆኑን አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል። ግድቦቹ ሳይንሳዊ በሆነ ስሌት ዓመቱን በሙሉ ጥቅም ላይ እንደሚውሉም ነው የገለፁት። ኢትዮጵያ ከምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል 95 ከመቶ በላይ ከውሃ ኃይል ምንጭ መሆኑ ይታወቃል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+4

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! የ2018 የመስቀል በዓል የሰላም እንዲሆንላችሁ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡ በዓሉ የሠላም፣ የጤናና የአብሮነት እንዲሆን
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! የ2018 የመስቀል በዓል የሰላም እንዲሆንላችሁ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡ በዓሉ የሠላም፣ የጤናና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡ አሸብር ባልቻ (ኢንጂነር) ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ግድቡ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ወሳኝ ነው …….///…….. ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ተናገሩ፡፡ ፕሬዝዳንቱ በ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በይፋ መመረቁን አስታውሰዋል፡፡ ግድቡ ከ5 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም እንዳለው የገለፁት አምባሳደር ታዬ በማገዶ እጥረት ለሚሰቃዩ የኢትዮጵያ እናቶች ኃይል በማቅረብ እፎይታ ይሰጣል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ይህ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ እንደሚረዳም ለጉባኤው አስገንዝበዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሌላቸው ከ60 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን የኃይል ተደራሽ ለማድረግ ታልሞ እየተሰራ ሲሆን የህዳሴ ግድብ ግንባታ የዕቅዱ አንዱ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ታዬ እንደገለፁት ግድቡ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባሻገር ለቀጣናዊ የኃይል ትስስርም ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+1

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኑክሌር ልማት ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረሙ …….///…….. በኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ልማት ዙሪያ በሩሲያ አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን(ሮሳቶም) እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የድርጊት መርሃ ግብር ተፈረመ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሲ ሊካቼቭ ፊርማቸውን ባኖሩበት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተገኝተዋል፡፡  በፊርማ ሥነሰሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደተናገሩት በሩሲያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የሚያጠናክር ነው። ኢትዮጵያ ለሁሉን አቀፍ እድገት የሚውል የኑክሌር ልማት ፕሮጀክት ለመጀመር የረጅም ጊዜ ልምድ ካላት ሩሲያ ጋር ተባብራ ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነትም ገልፀዋል። የኒውክሌር ኃይል የረጅም ጊዜ ልማትን ለማስጠበቅ፣ የኃይል ምንጮችን ለማብዛት እና የኢትዮጵያን አቅም ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መሆኑን ጠቁመዋል። ሩሲያ በኒክሌየር ቴክኖሎጂ እና በሌሎች መስኮች ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ በማካፈል ለጋራ እድገት በትብብር እንደምትሰራ ጠይቀዋል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት በተረጋጋ ሁኔታ እያደገ መሆኑን  ተናግረዋል። የሀገራቱ ግንኙነቶች በዘላቂ ሁኔታ እያደጉ እና የንግድ ትስስሩም እየጨመረ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የታላቁ የሕዳሴ ግድብን የሚስተካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ በቅርቡ እንደምትጀምር መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+1

ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ዘርፍ ሪፎርም እውቅና አገኘች .......///...... ከ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደ መርሀግብር ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ዘርፍ ባከናወነችው ስኬታ
+2
ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ዘርፍ ሪፎርም እውቅና አገኘች .......///...... ከ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደ መርሀግብር ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ዘርፍ ባከናወነችው ስኬታማ ሪፎርም ከዓለም ባንክ እውቅና አግኝታለች። ይህን ተከትሎ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ሌሎች የልማት አጋር ድርጅቶች በጋራ ሶስት መቶ ሚሊዮን አፍሪካውያንን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በያዙት ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያ እንድትካተት ተደርጓል። ኢትዮጵያ 30 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ነዋይ በሚጠይቀው በዚህ ኢንሼቲቭ መካተቷ በኢነርጂ ዘርፍ ያላትን እምቅ ሀብት ይበልጥ ለመጠቀም  እንደሚረዳት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በትዊተር ገፁ አስታውቋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም

ሪጅኑ የህፃናት ማቆያ ከፈተ …….///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን የህፃናት ማቆያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ ማቆያ ማዕከሉ ለህፃናት ምቹ የሆነ ክፍል እና የተለያዩ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑን ተናግረዋል። የማቆያ ማዕከሉ የተቋሙ ሴት ሠራተኞችን የስራ ጫና ከመቀነስ ባሻገር የስራ ተነሳሽነታቸውንም እንደሚያሳድግ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ በሪጅኑ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ተወካይ ወ/ሮ መሠረት ካሳ በበኩላቸው የማዕከሉ መከፈት ሴት ሠራተኞች ልጆቻቸውን በቅርበት እየተከታተሉ መደበኛ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ ይረዳል ብለዋል። ለማዕከሉ እውን መሆን የተቋሙ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ፤ የሪጅኑ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን የተናገሩት ደግሞ የሪጅኑ የሰው ሀብት፣የንብረት አስተዳደር  እና ጠቅላላ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ተገኝ ናቸው። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+5

የሥራ ኃላፊዎቹ የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ ........///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጀነሬሽን ቢዝነስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ኤፍሬም ገብረኪዳን የተመራ ሥራ ኃላፊዎች ቡድን በሶማሌ ክልል አይሻ ከተማ አቅራቢያ የተገነባውን የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጎብኝቷል። የሥራ መሪዎቹ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት የጀመሩትን የንፋስ ተርባይን ጀነሬተሮች፣ የመሰረት ቁፋሮና የግንባታ ሥራቸው ተጠናቆ የተርባይ ተከላ የሚቀራቸውን ግንባታዎች፣ የኃይል መቆጣጠሪያ ክፍሎች እና የሠራተኞች የመኖሪያ ቤቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ከሠራተኖች ጋርም በፕሮጀክቱ እና በኦፕሬሽን ሥራዎች እንዲሁም በሥራ ሂደት በሚገጥሟቸው ችግሮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ከውይይቱ በኋላ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር ኤፍሬም ገብረኪዳን እንደተናገሩት የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ፈታኝ የአየር ሁኔታን ተቋቁመው ፕሮጀክቱ 80 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል። የቀሪውን 40 ሜጋ ዋት የግንባታ ሂደት በማጠናቀቅ ወደ ሥራ ለማስገባት እንደተቋም በሚደረገው ርብርብ ሠራተኞቹ በጽናት ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። የተቋሙ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ በበኩላቸው ሠራተኞች በሥራ ሂደት የሚገጥሟቸውን ችግሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ አረጋግጠዋል። የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 120 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ሲኖረው 80 ሜጋ ዋቱ ተጠናቆ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ወይም ከግሪድ ጋር ተገናኝቷል።   💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+4

ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ፣ በጀት እና ጥራት እንዲጠናቀቁ ማድረግ ይገባል ‎........///....... በ2018 በጀት ዓመት በዕቅድ የተያዙ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ እና በጀት በጥራት ማጠናቀቅ እንደሚገባ የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ፡፡ ዘርፉ በ2018 በጀት ዓመት የታቀዱ ሥራዎች በሚከናወኑበት አግባብ በሥሩ ከሚገኙ የመምሪያ ኃላፊዎች እና የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ውድነህ የማነ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት በመዋቅራዊ ለውጡ ዘርፉ እንደ አዲስ ከተደራጀ በኋላ በዲዛይን፣ ፕሮጀክት ትግበራ፣ ኮንትራት አስተዳደር፣ ግዥና ፋይናንስ አፈፃፀም ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እና የኢንጂነሪንግ የሥራ ክፍሎችን በማዋሃድ ቀጣይነት ያለው የሥራ ባህል ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ እንደ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ ዘርፉ በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ የፋይናንስ ወጪን ያገናዘበ የሥራ ጥራት እና ቅልጥፍና መለያዎቹ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል፡፡ ዘርፉ ለተቋሙ የሚያስፈልገው አዋጪ ሥራዎችን ማከናወን እስከቻለ ድረስ ብቻ ነው ያሉት ኢንጂነር ውድነህ ለዚህም በተያዘው በጀት ዓመት የፕሮጀክቶችን የፋይናንስ ቁመና በማስተካከል በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የውስጥ አቅምን በማጠናከር በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሀገር ውጭ በሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳታፊ ለመሆን የያዘውን ግብ ለማሳካት አመራሩና ሠራተኛው በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡ ሙያዊነት ለሥራ ጥራትና ለጋራ መግባባት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ የሥራ ላይ ሥነ-ምግባርን ማሳደግ ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የሠራተኛውን የሥራ ላይ ደህንነት በማስጠበቅና ከተቋሙ የአሰራር ባህል ጋር እንዲዋሃድ በማድረግ ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠር እንደሚያስፈልግም ነው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው የጠቆሙት፡፡ በፕሮጀክቶች ግንባታ ዙሪያ ለሚነሱ የአፈፃፀም ክፍተቶች ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲሁም ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሔ ሰጪ ለመሆን አመራሩ ቁርጠኛ ሊሆን እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡ በውይይቱ ላይ ከዲዛይን፣ ከኮንትራት አስተዳደር፣ ከሥራ ላይ ግንኙነት፣ ከፋይናንስና ግዥ፣ ከዘርፉ አወቃቀር፣ ከአሰራር ሥርዓት እና ከበጀት አቅርቦት እንዲሁም ከፕሮጀክቶች አፈፃፀም ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጦባቸዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+5

#Vacancy የስራ ቅጥር ማስታወቂያ የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ሠራተኞችን በኮንትራት አወዳድሮ ለኮይሻ ፕሮጀክት ለመቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቶቹን የምታሟሉ አመልካቾች የሚከተሉትን
#Vacancy የስራ ቅጥር ማስታወቂያ የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ሠራተኞችን በኮንትራት አወዳድሮ ለኮይሻ ፕሮጀክት ለመቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቶቹን የምታሟሉ አመልካቾች የሚከተሉትን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። Link 1 👉 https://forms.gle/NbERitgfmi49iRf1A Link 2፡ 👇 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdirS8H4d3BJU0WgHBMat5IeRjZ5qr_iyRbYlq3gY7w2DD8wg/viewform?usp=dialog 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም

#update በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች በከፊል የተቋረጠው ኃይል ከጥቂት ቦታዎች ውጪ ከ95 በመቶ በላይ ተመልሷል። ቀሪዎቹንም አካባቢዎች በተወሰኑ ደቂቃዎች ውስጥ ለማገናኘት እየተሰራ ይገኛል። መደበኛ ጥገና  በሚከናወንበት ሰዓት እና በፍተሻ ወቅት የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁን ደንበኞቻችን ምስጋናችንን እናቀርባለን። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች በከፊል የኃይል መቋረጥ ተከስቷል ……..///……. ከሰበታ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ ጥቁር አንበሳ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ፤ ከጥቁር አንበሳ ኃይ
በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች በከፊል የኃይል መቋረጥ ተከስቷል ……..///……. ከሰበታ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ ጥቁር አንበሳ  ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ፤  ከጥቁር አንበሳ  ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ አዲስ ዌስት ወይም ኮልፌ ማከፋፈያ ጣቢያ  በተዘረጋዉ 132 ኪ.ቮ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ መደበኛ የጥገና ሥራ ሲከናወን ውሏል፡፡ ይሁንና ጥገናው ተጠናቆ መስመር በሚሞከርበት ጊዜ በተፈጠረ የመስመሮች መነካካት በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡   የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ በመሆኑ መስመር በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም

‎ተቋሙ ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት በመቄዶኒያ የማዕድ ማጋራት አደረገ ...‎….///…..... ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና መመረቅን ምክንያት በማድረግ ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ በመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማዕከል በመገኘት ማዕድ አጋርቷል፡፡ ‎ ‎በፕሮግራሙ ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻን ጨምሮ የሥራ አመራር አባላት እና የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማዕከል መስራች ቢኒያም በለጠ ተገኝተዋል። ‎ ‎በፕሮግራሙ ላይ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሀገርና ማህበረሰብን የሚያሻግሩ ትልልቅ የኃይል መሰረተ ልማቶችን ከመገንባት ባሻገር በተለያዩ መስኮች የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን በዕቅድ ይዞ በመላ ሀገሪቱ እየሰራ ይገኛል፡፡ ‎ ‎ተቋሙ ቀደም ሲል ለማዕከሉ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡ በዛሬው ዕለት የህዳሴ ግድብ ምረቃ በዓልን በማስመልከት ያከናወነው የማዕድ ማጋራት ተቋሙ የሚያከናውናቸው የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች አካል መሆኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚው በቀጣይም ሠራተኞቹን በማስተባበር ጭምር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ ‎ ‎መቄዶንያ ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን ወገኖች የተስፋ ብርሃንና ሕይወትን የሠጠ ተቋም በመሆኑ ይሄን በጎ ተግባር መደገፍ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ‎የመቂዶኒያ መሥራች ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ድርጅቱ ካለምንም የውጭ ሀገር የገንዘብ ድጋፍ በየቀኑ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ በ52 ቅርንጫፎች የሚገኙ ከ8 ሺህ 500 በላይ ከጎዳና ያነሳቸውን አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን በመደገፍ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ‎ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በራሱ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ፕሮጀክቶችን የሚገነቡ ዊ ቢውልድን የመሰሉ የሥራ ተቋራጮችን በማስተባበር ጭምር ለማዕከሉ ትልቅ እገዛ እያደረገ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ከ15 በላይ ህንጻዎችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ቢኒያም የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 250 በማሳደግ በርካታ አረጋውያንንና የአዕምሮ ህሙማንን ለመደገፍ የያዘውን እቅድ ለማሳካት ተቋሙ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ በማዕከሉ የሚኖሩ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማኑ በበኩላቸው ተቋሙ ላደረገላቸው የማዕድ ማጋራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ለማዕከሉ የሚደርገው ድጋፍ በትክክለኛ ቦታ ላይ ስለሚውል ተቋሙ በቀጣይም ከጎናቸው እንዳይለይ ጠይቀዋል፡፡ የተቋሙ የሥራ አመራር አባላት በማዕከሉ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በየዓመቱ “መስከረም 8 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመቄዶኒያ ለሰብዓዊ ድጋፍ” በሚል መሰየሙም ተገልጿል። ‎“ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው” በሚል መሪ ቃል የአዕምሮ ህሙማንና አረጋውያንን ከጎዳና በማንሳት እየደገፈ የሚገኘው መቂዶኒያ በአዲስ አበባ ማዕከሉ ባለ 15 ወለል ዘመናዊ ሆስፒታል እና መኖሪያ እየገነባ ይገኛል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም