uz
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Kanalga Telegram’da o‘tish

EEP Communication

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali EEP Communication analitikasi

EEP Communication (@eepcommuication) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 546 obunachidan iborat bo'lib, Texnologiyalar & Aralashmalar toifasida 8 351-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 178-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 546 obunachiga ega bo‘ldi.

02 Iyul, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 27 ga, so‘nggi 24 soatda esa 8 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.76% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 15.84% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 005 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 463 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 9 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
EEP Communication

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 03 Iyul, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Texnologiyalar & Aralashmalar toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 546
Obunachilar
+824 soatlar
-227 kunlar
+2730 kunlar
Postlar arxiv
photo content
+2

የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን የሰረቁና የተሰረቀውን የገዙ ግለሰቦች ተያዙ ……..///……. ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን ፈተው የሸጡ ግለሰቦች በቁጥ
+4
የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን የሰረቁና የተሰረቀውን የገዙ ግለሰቦች ተያዙ ……..///……. ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን ፈተው የሸጡ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ በደቡብ ጎንደር ዞን የሐሙሲት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ፈንታሁን ግርማ እንደገለፁት ግለሰቦቹ የምሰሶ ብረቶቹን የፈቱት ከባህር ዳር - ወልዲያ - ኮምቦልቻ ከተዘረጋው የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ ነው፡፡ የስርቆት ወንጀሉን እንደፈፀሙ የተጠረጠሩት ስድስቱ ግለሰቦች እንዲሁም ብረቱን የገዙ አራት ግለሰቦች በዳማስ መኪና ጭነው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን መሰል ወንጀሎችን ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ሊከላከል እንደሚገባ ረዳት ኢንስፔክተር ፈንታሁን ግርማ ማሳሰባቸው የሐሙሲት ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያወጣው ዘገባ አመልክቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content

የቃል ፈተና ጥሪ በሎየር 1ኛ የሥራ መደብ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግንቦት 08 ቀን 2014 ዓ.ም ማስታወቂያ ወጥቶ ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም የጽሑፍ ፈተና መሰጠቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የጽሑፍ ፈተና ከወሰዳችሁት ውስጥ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተወዳዳሪዎች የስም ዝርዝራችሁ ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም የቃል ፈተና የሚሰጥ ስለሆነ ሜክሲኮ ኬ ኬር ህንፃ በሚገኘው የተቋሙ ዋናው መስሪያ ቤት ሁለተኛ ፎቅ ሰራተኛ ምደባ ቢሮ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

photo content
+5

የወልዲያ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ……….////………. የወልዲያ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የሲቪል ስራ 94 በመቶ መድረሱን የፕሮጀክቱ የሲቪል ሥራዎች ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ቴዎድሮስ ከፈለኝ እንደገለፁት የኃይል መቆጣጠሪያ ክፍል መሰታወትና ኮርኒስ መግጠም እንዲሁም ግቢውን ማስተካከልና ጠጠር ከማልበስ በስተቀር አብዛኛው የሲቪል ስራ ተጠናቋል። የስዊችያርድ እና የትራንስፎርመር ማስቀመጫ ቦታዎች ግንባታ ስራ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪዎቹን የሲቪል ሥራዎች በአስር ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ራስ ኃይል ኮንስትራክሽን መምሪያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ኃ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ተከላ 27 በመቶ መድረሱን አስታውቀዋል፡፡ የትራንስፎርመር ማስቀመጫ ቦታ መሰረት በመጠናቀቁ ትራንስፎርመር አጓጉዞ ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑ ገልፀዋል። ለትራንስፎርመር ማጓጓዝ የሚያስፈልገው ጊዜ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ቀሪ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እስከ ሁለት ወር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። አጠቃላይ ሥራውን ለማጠናቀቅ ከሦስት ወር ያልበለጠ ጊዜ አንደሚፈልግ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ማከፋፈያ ጣቢያው ከተጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ከነባሩ ባለ 66 ኪሎ ቮልት መስመር ጋር የማገናኘት ሥራዎች እንደሚፈልጉና በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው ዳይሬክተሩ አሳስበዋል። የወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታው ተጠናቆ አግልግሎት መስጠት ሲጀምር ቀደም ሲል ከነበረው አገልግሎት በተጨማሪ ከአላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል መስጠት ያስችላል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content
+5

የኤሌክትሪክ ችግር እንዲፈታላቸው የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ ......////....... የኤሌክትሪክ ችግር እንዲፈታላቸውና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተሟልተው እንዲሰጡ የላሊበላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጠየቁ። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በመሩትና የአሸንድዬ በዓልን ምክንያት በማድረግ በላሊበላ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ላይ ነዋሪዎቹ ከኤሌክትሪክ፣ ከማህበራዊ አገልግሎትና ከቱሪዝም ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች አቅርበዋል። ኤሌክትሪክን በተመለከተ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን፣ የዋግ ኽምራ ዞንና የላስታ ላሊበላ ከተማና አካባቢው ችግር የመነጨው አካባቢው በህወኃት ቁጥጥር ስር ካለው የአላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ ኤሌክትሪክ ያገኝ የነበረ በመሆኑና ኃይል ወደተጠቀሱት አካባቢዎች ኃይል መልሶ ማገናኘት ባለመቻሉ ነው ብለዋል። ይሁንና ከአላማጣ ኃይል ማገናኘት እስከሚቻል ድረስ አዲስ እየተገነባ ካለው የወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ ወይም ከጋሸና ማከፋፈያ ጣቢያ ለላሊበላና አካባቢው ኃይል ማገናኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። እየተሰሩ ያሉት ሥራዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በቅርበትና በቅንጅት መሰራት ያለበት በመሆኑ ተገቢው ዝግጅት እንዲደረግበት አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content
+9

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እግር ኳስ ክለብ ለመጪው የውድድር ዘመን ራሱን በማጠናከር ላይ ነው ..........////.......... ኢትዮ ኤሌክትሪክ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ ለመጪው የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚዬር ሊግ ተፎካካሪ ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ የክለቡ ጽ/ቤት አስታውቋል። የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ እጅጉ እንደገለፁት በ2015 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚዬር ሊግ ጠንክሮ ለመቅረብ ክለቡ 11 አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን የ10 ነባር ተጫዋቾችን ውልም አራዝሟል። የፈረሙት ተጫዋቾች ከግብ ጠባቂ ጀምሮ የተከላካይ፥አማካይና አጥቂ ተጫዋቾችን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን የጽ/ቤት ኃላፊው ተናግረዋል። በግብ ጠባቂነት ፍቅሩ ወዴሳን ያስፈረመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተከላካይ ቦታ የሚጫወቱ እንደ ተስፋዬ በቀለ፥ ኃይሌ ገ/ተንሳይ፥ ጌቱ ኃይለማርያም እና ወንድማገኝ ማዕረግ የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። በፊት መስመርም ሔኖክ አየለን ያስፈረመ ሲሆን የአማካኝ ቦታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ማምጣቱን አቶ አሸናፊ ተናግረዋል። ከአዲስ ተጫዋቾች ባሻገር የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አንጋፋ ተጫዋች ምንያህል ተሾመን ጨምሮ የ10 ነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙን ክለቡ አስታውቋል። የክለቡ የቦርድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ መንግስቱ የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብን ለማዘመንና ይበልጥ ተፎካካሪ ለማድረግ በርካታ የለውጥ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል። የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 20 እንደሚጀመር የሚጠበቅ ሲሆን ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከባህር ዳር ከነማ አቻው ጋር የሚያደርግ ይሆናል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

photo content
+5

AnimatedSticker.tgs0.08 KB

AnimatedSticker.tgs0.14 KB

የማሰልጠኛ ማዕከል እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለማስጀመር ያለመ ምክክር ተካሔደ ...........////......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ ድጋፍ በቢሾፍቱ ከተማ ሊያስገነባው ያቀደው የማሰልጠኛ ማዕከል ወደ ትግበራ ምዕራፍ እንዲገባ ከኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሒዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የተቋሙ የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ዳይሬክተር ዶክተር ወንድወሰን ካሳ እንደተናገሩት በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ የፋይናንስ ድጋፍ የሚከናወነው የሰው ሀይል አቅም ግንባታ ስልጠና በ2015 ዓ.ም የሚጀመር ሲሆን የማሰልጠኛ ማዕከሉም ዲዛይን በመጠናቀቅ ላይ ነው። በተቋሙ ለሚገኙ ባለሙያዎችና የሥራ መሪዎች የአቅም ግንባታና የቴክኒክ ሥልጠና የሚሰጡ አማካሪ ድርጅቶችን ለመቅጠር የማወዳደሪያ መስፈርቶች እየተከናወኑ ስለመሆኑ ዶክተር ወንድወሰን ተናግረዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው የማሰልጠኛ ማዕከል ከሀገር ውስጥ ስልጠናዎች ባሻገር በኤሌክትሪክ ኃይል ልማት ዘርፍ ለጎረቤት ሀገራት ባለሙዎች ሥልጠና በመስጠት የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ያለመ ነው፡፡ በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ የታስክ ቡድን መሪ (Task team leader) የሆኑት ሚስተር አንሮይን ቤሎሰልስኪ ለማሰልጠኛ ማዕከሉ ግንባታ እና ለአቅም ግንባታ የሚውል 10 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ በፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ በኩል መፈቀዱን ገልፀዋል፡፡ ሚስተር አንሮይን እንደገለፁት የአማካሪ ቅጥርና የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች በ2015 ዓ.ም የሚጀመሩ ሲሆን የማሰልጠኛ ማዕከሉ ግንባታ በ2016 በጀት ዓመት እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡ ይህ የገንዘብ ድጋፍ እስከ አምስት ዓመት እንደሚዘልቅና ከግዥ ስርዓት ጀምሮ አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈፃፀም ሂደቱን ኤጀንሲው እንደሚከታተል ሚስተር አንሮይን ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር ቀጣይ ውይይቶች እንደሚካሔዱ በምክክር መድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

በኃይል ማመንጫ ጣቢያው የአፈር መናድ መከላከያ ሥራና የመንገድ ጥገና ሥራ እየተከናወነ ነው --------////--- የአዋሽ 2 እና 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተንሸራታች መሬት መከላከያ ግንብና የመንገድ ጥገና ስራዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን የትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን የራስ ኃይል ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የሲቪል ሥራዎች ጥገና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ግርማ መንገሻ እንደገለፁት በጣቢያው እየተገነባ ያለው የተንሸታራች መሬት መከላከያ ግንብ ሥራ 90 ሜትር ርዝመትና 10 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ እስካሁን በተሰራው ሥራ ሙሉ በሙሉ ቁፋሮው መጠናቀቁና 15 ነጥብ 8 ሜትር ርዝመት ያለውና 7 ነጥብ 9 ሜትር ከፍታ ያለው የግንባታ ሥራ ተከናውኗል። ይህም የፕሮጀክቱን አፈፃፀም 41.5 ከመቶ ያህሉን መጠናቀቁን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል። የግንባታ ሥራውን በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከበ ከኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ጽ/ቤት ኮንትራት የተወሰደ መሆኑን ያወሱት ሥራ አስኪያጁ በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች በታሰበው ፍጥነት ልክ ግንባታውን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቁመዋል። ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ ዐለታማ መሆኑና የተለያዩ ከባድ ማሽነሪዎችን መጠቀም የግድ ሆኖ መገኘቱ ፕሮጀክቱን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር ገልፀዋል። ሥራ አስኪያጁ እንደተናገሩት ለግንባታው አጠቃላይ ከ18 ሚለየን ብር በላይ በጀት የተያዘ ቢሆንም በወቅቱ ካለው የግብዓት ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ የኮንትራት ማሻሻያ እንደተጠየቀበትና ግንባታውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በተለይም የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽ ጽ/ቤት እያደረገ ለሚገኘው ቀና ትብብብር ምስጋና ያቀረቡት ኢንጂነር ግርማ ይህ ፕሮጀክት የራስ ኃይል ኮንስትራክሽን ቢሮ በኃይል ማመንጫዎች እያከናወነ ከሚገኘው የጥገና ስራዎች ወስጥ ትልቁ መሆኑን ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ በደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ለይ የሚገኘኙት የአዋሽ ሁለት እና ሦስት ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እያንዳንዳቸው 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም አላቸው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content
+6

የፕሮጀክቱ ግንባታ 85 በመቶ ተጠናቋል ........////...... የአዘዞ ጭልጋ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ 85 በመቶ መድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዘዞ ጭልጋ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ገለፀ። የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዳንግብጹ መንገሻ እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ወሳኝ ሥራዎች የሚባሉት የኤሌክትሪክ ተሸካሚ ምሰሶ ተከላ፣ የማስተላለፊያ ገመድ ዝርጋታ፣ የማከፋፈያ ጣቢያው የውስጥ አጥር እና የአፈር ምለሳ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ። ለመስመር ዝርጋታው ከሚያስፈልጉት 105 የኤሌክትሪክ ተሸካሚ ምሰሶዎች ውስጥ 89 ያህሉ መጠናቀቃቸውን የገለፁት አስተባባሪው በካሳ ክፍያና ተያያዥ ጉዳዮች የዘገዩ የማስተላለፊያ መስመር የመሰረት ግንባታ፣ የምሰሶ ተከላና የዝርጋታ ሥራዎች በቀጣይ የሚሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ፕሮጀክቱ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና አንድ ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት አዲስ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታን የሚያጠቃልል ነው፡፡ የአዲስ የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ግንባታ በጭልጋ፣ በነባሩ የአዘዞ ማከፋፈያ ጣቢያ ውስጥ ደግሞ ማስፋፊያ እየተከናወነ ሲሆን የጭልጋ ማከፋፈያ ጣቢያ የመጀመሪያ ሙከራ እየተደረገለት መሆኑንም አስተባባሪው ጠቁመዋል። የአዘዞ ጭልጋ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት በአካባቢው የነበረውን ከፍተኛ የኃይል መዋዠቅና መቆራረጥ ከማስቀረት አልፎ ለአካባቢው የኢንቨስትመንት መስፋፋት በር እንደሚከፍት እና በተደጋጋሚ የሚነሳውን የኃይል አቅርቦት ጥያቄ እንደሚፈታ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ የፕሮጀክቱን ግንባታ ሲኖ ኃይድሮ ኮርፖሬሽን የተባለው የቻይና ኩባኒያ ሲያከናውን በአማካሪነት ደግሞ ኢ.ኤል.ሲ. (ELC) የተባለ የጣሊያን ኩባኒያ እየተሳተፈበት ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በ780 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ በአንጓባ ቡላድጌ ቀበሌ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

photo content
+6

photo content
+7