uz
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Kanalga Telegram’da o‘tish

EEP Communication

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali EEP Communication analitikasi

EEP Communication (@eepcommuication) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 553 obunachidan iborat bo'lib, Texnologiyalar & Aralashmalar toifasida 8 406-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 161-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 553 obunachiga ega bo‘ldi.

19 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -3 ga, so‘nggi 24 soatda esa -5 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 26.69% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 15.00% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 150 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 332 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 10 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
EEP Communication

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 20 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Texnologiyalar & Aralashmalar toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 553
Obunachilar
-524 soatlar
+97 kunlar
-330 kunlar
Postlar arxiv
የህብረት ሥራ ማህበሩ በሥራ ምክንያት ለተጎዱ ሠራተኞች የበዓል ስጦታ አበረከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ሥራ ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በሥራ ላይ ጉዳት ደርሶባቸው በደጃዝማች ባልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሠራተኞችን በመጠየቅ የበዓል ስጦታ አበርክተዋል። ይህ የማህበሩ የሰብአዊነት ተግባር ከገላን፣ ከጭሮና ከአዲስ አበባ አካባቢዎች በተለያየ የሥራ አጋጣሚ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሉ ተኝተው ለሚታከሙ ስምንት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች የተደረገ ሲሆን ለእያንዳንዳቸውም የ10 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። በሥራ አመራር ቦርዱ የማህበራዊ ዘርፍ ሰብሳቢ አቶ ደመላሽ ንጉስ በወቅቱ እንደተናገሩት በህክምና ላይ የሚገኙት ሠራተኞች ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ በመሆናቸው ይህ የጥየቃ መርሃ ግብር ቤተሰባዊ ቅርርብን ለመፍጠርና ለታካሚዎቹ በጎ የሞራል ተነሳሽነትን ለመስጠት ያለመ ነው። የሥራ አመራር ቦርዱ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን የሁለቱ ተቋማት ሠራተኞች የማህበሩ አባል ቢሆኑም ባይሆኑም ያለምንም ልዩነት በመጠየቅና ስጦታ በማበርከት አጋርነቱን እያሳየ እንደሚገኝም አቶ ደመላሽ አብራርተዋል። የህብረት ሥራ ማህበሩ ሂሳብ ሹም ወ/ሮ ዝናሽ ደረሰ በበኩላቸው ማህበሩ የተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን ለመወጣት በጀት መድቦ ድጋፎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው የሠራተኞች ጥየቃና የበዓል ስጦታውም የዚሁ ሰፊ ተግባር አካል ነው። በመሆኑም የማህበሩ አባል ያልሆኑ የሁለቱ ተቋማት ሠራተኞች ወደ ማህበሩ በመቀላቀል የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ የማህበራዊ ዘርፍ ጸሐፊ አቶ እስከንድር ጌታቸውም ይህ ተግባር ማህበሩ ለቁጠባና ለብድር ብቻ የተቋቋመ አለመሆኑንና በማቋቋሚያ ደንቡ የተሰጠውን ማህበራዊ ኃላፊነት ጭምር በብቃት እየተወጣ መሆኑን ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+6

🇪🇹 ⚡️ ኢትዮጵያ የኃይል ማማ (Power Hub) የመሆን ጉዞዋን አፋጥናለች! ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኃይል ማመንጨት ዘርፍ አስደናቂ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች። አጠቃላይ ሀገራዊ የማመንጨት አቅማችን አሁን ላይ 9,760 ሜጋ ዋት (MW) ደርሷል፤ ይህም ለኢንዱስትሪዎቻችን ዕድገትና ለቀጣናዊ ትስስር ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ 🇪🇹የውሃ ኃይል ማመንጫዎቻችን ድርሻ በኃይል ማመንጨት ሂደት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት የውሃ ኃይል ማመንጫዎቻችን ሲሆን ከሚመነጨው 96% አስተዋጽዖ አላቸው፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD)፦ በ 5,150 MW ግዙፍ አቅሙ የኃይል ማመንጫችን በመሆን በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ከመነጨው የ51% ድርሻ ነበረው፡፡ ጊቤ III (1,870 MW)፣ በለስ (460 MW) እና ሌሎችም የኃይል ማመንጫዎች እንደ ማመንጨት አቅማቸው ለኃይል አቅርቦቱ የራሳቸውን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛሉ። እያደገ የመጣው የንፋስ እና የሌሎች ታዳሽ ኃይሎች ድርሻ የንፋስ ኃይል (~504 MW)፦ በአዳማ፣ በአሸጎዳ፣ በአይሻ እና በአሰላ የሚገኙ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ኢትዮጵያን በአፍሪካ የንፋስ ኃይል ቀዳሚ እያደረጓት ይገኛሉ። ♻️ ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ፡- በረጲ የተገነባው ከደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በአፍሪካ የመጀመሪያው ጣቢያ ሲሆን ከኃይል ማመንጨት በተጓዳኝ የከተማዋን ቆሻሻ በማስወገድ ረገድ አርአያ የሆነ ተግባር እያከናወነ ነው፡፡ ♨️🌋 ጂኦተርማል፦ በአሉቶ ላንጋኖ፣ በቱሉ ሞዬና በኮርቤቲ የሚከናወኑ የከርሰ-ምድር እንፋሎት ፍለጋዎች አዲስ የኃይል አማራጭ ይዘውልን እየመጡ ነው። ቀጣይ ግባችን - የማመንጨት አቅምን 17,000 ሜጋ ዋት ማድረስ! የሀገራችንን የኃይል አቅርቦት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በግንባታና በሂደት ላይ ይገኛሉ፦ ኮይሻ (1,800 MW) የውሃ ኃይል ማመንጫ፤ አይሻ I እና III የንፋስ ኃይል ፕሮጀክቶች ቱሉ ሞዬ እና ኮርቤቲ የግል ባለሀብቶች (IPPs) የሚሳተፉባቸው ግዙፍ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ 🇪🇹 ኢትዮጵያ የራሷን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ የቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ማዕከል እየሆነች ነው። ይህ የሁላችንም ኩራትና የብልጽግናችን መሠረት ነው!

photo content
+2

የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ የኢንዱስትሪ ፓርኩን የኃይል ፍላጎት ያሟላል ….….///…….. የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክን የኃይል አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለ
+4
የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ የኢንዱስትሪ ፓርኩን የኃይል ፍላጎት ያሟላል ….….///…….. የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክን የኃይል አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተጀመረው የወይናንታ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ የጀመሩ ፋብሪካዎችን የኃይል ጥያቄ እንደሚመልስ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ባዴጎ በቀለ እንደገለፁት የወይናናታ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ለኢንዱስትሪ ፓርኩ ከ50 ሜጋ ዋት በላይ ኤሌክትሪክ ያቀርባል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኩ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየሰሩ ለሚገኙ ዘጠኝ ፋብሪካዎች እያቀረበ ያለው የኃይል መጠን 12 ሜጋ ዋት ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የማከፋፈያ-ጣቢያው-መጠናቀቅ-የኢንዱስት&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

⚡️🇪🇹 የኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍና የግል ባለሀብቶች ተሳትፎ፦ ከውጥን ወደ ተግባር! ኢትዮጵያ የኃይል ማመንጨት ዘርፉን ለግል ባለሀብቶች (Independent Power Producers - IPPs)
⚡️🇪🇹 የኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍና የግል ባለሀብቶች ተሳትፎ፦ ከውጥን ወደ ተግባር! ኢትዮጵያ የኃይል ማመንጨት ዘርፉን ለግል ባለሀብቶች (Independent Power Producers - IPPs) ክፍት በማድረግ አዲስ ምዕራፍ ጀምራለች። ይህ ታሪካዊ ውሳኔ የሀገሪቱን ታዳሽ የኃይል ፀጋ በግል ባለሀብቶች የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅም በማልማት የኢኮኖሚ ዕድገታችንን ለማፋጠን ትልቅ ዕድል ይፈጥራል። 🏗⚡️ በዘርፉ ለመሰማራት ተግዳሮቶች አይኖሩም ወይ? በእርግጥ እንደማንኛውም ግዙፍ ኢንቨስትመንት፣ በኃይል ግዥ ስምምነት (PPA)፣ በመሬት አቅርቦትና በጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ ፈታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ሆኖም መንግሥት እነዚህን መሠረታዊ እንቅፋቶች ለመቅረፍ ቁርጠኝነቱን በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡ ⚡️🇪🇹 የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ፡ 💡 የምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ባለሀብቶች ትርፋቸውን በቀላሉ ወደ ውጭ መላክ (Repatriation) እንዲችሉ መንገድ ይከፍታል። ⚡️🇪🇹 የታሪፍ ማሻሻያ፡ 💡 የኤሌክትሪክ ሽያጭ ዋጋ ከማምረቻ ወጪው ጋር እንዲመጣጠን መደረጉ ፕሮጀክቶች አትራፊና በራሳቸው የሚቆሙ (Bankable) እንዲሆኑ ያስችላል። ⚡️🇪 የPPP ሕግና መዋቅር፡ 💡 በመንግሥትና በግል አጋርነት አዋጅ አማካኝነት የባለሀብቱ መብትና ግዴታ በግልጽ ተቀምጧል። ⚡️🇪🇹 የአንድ ማዕከል አገልግሎት፡ 💡 ቢሮክራሲን በማሳጠር ባለሀብቶች ፈቃድና መሬት በቀላሉ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። 🏗⚡️ የግል ዘርፉ ተሳትፎ ሲጎለብት የኃይል አቅርቦታችን አስተማማኝነት ያድጋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን በሙሉ አቅማቸው የሚያመርቱበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ሀገራችን የቀጣናው የኃይል ማዕከል የመሆን ራዕይዋ እውን ይሆናል!

የማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ ከ65 መቶ በላይ ተጠናቋል ……...///…..…. የሺግዳን ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ አፈፃፀም ከ65 በመቶ በላይ መድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
+6
የማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ ከ65 መቶ በላይ ተጠናቋል ……...///…..…. የሺግዳን ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ አፈፃፀም ከ65 በመቶ በላይ መድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የሳይት 2 ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ አርጋው ታዲ እንዳስታወቁት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የሲቪል ሥራ 70 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮሜካኒካል ሥራ 35 በመቶ ተጠናቋል። በአሁኑ ወቅት የአምስት ትራንስፎርመሮች እና የሁለት ሻንት ሪአክተሮችን ተከላ በማጠናቀቅ ዘይት የመሙላት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የማከፋፈያ-ጣቢያው-ግንባታ-ከ65-መቶ-በላይ-ተ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ለፓርኩ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው ……..///……... የወይናንታ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የሲቪል ሥራ ከ71 በመቶ በላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ
+5
ለፓርኩ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው ……..///……... የወይናንታ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የሲቪል ሥራ ከ71 በመቶ በላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ የሲቪል ሥራዎች አስተባባሪ አስታወቁ፡፡ አስተባባሪው አቶ ኤሊያስ መሀመድ እንደገለፁት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ ለይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ለማቅረብ ያስችላል። ለኢንዱስትሪ ፓርኩ ኃይል ለማቅረብ ከአራት ዓመት በፊት ሥምምነት ቢፈረምም በወቅቱ ከውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር በተያያዘ ግንባታው መዘግየቱን ገልፀዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ለፓርኩ-የኃይል-አቅርቦት-ጥያቄ-ምላሽ-ለመ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም

🇪🇹⚡️ 🇪🇹 የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ጸጋ፦ ያልተነካው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ዕድል! ኢትዮጵያ በታዳሽ የኃይል ምንጮች የታደለች ሀገር ብትሆንም፣ እስካሁን ጥቅም ላይ የዋለው እምቅ አቅም ከመቶ ሰባት (7%) እንኳን አይበልጥም። ይህ ክፍተት ዘርፉ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስትመንት ምን ያህል ክፍት እንደሆነ ማሳያ ነው። ዋነኞቹን የኃይል አማራጮች፣ ያላቸውን እምቅ አቅም እና በሀገሪቱ ያላቸውን ስርጭት እንደሚከተለው በዝርዝር ማየት ይቻላል፦ 🇪🇹⚡️ የንፋስ ኃይል (Wind Energy) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የንፋስ ኃይል እምቅ አቅም ካላቸው ቀዳሚ ሀገራት አንዷ ናት። 💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ 1,350 ጊጋ ዋት (GW) በላይ፤ 🌱 ተስማሚ አካባቢዎች፦ የንፋስ ፍጥነታቸው በሰከንድ ከ6.5 ሜትር በላይ የሆኑ አካባቢዎች ለኃይል ማመንጫነት ይመረጣሉ። 💨 ⚡️ ክልላዊ ስርጭት፦ 📍 o ትግራይ ክልል፦ መቐለና አካባቢው፤ o ሶማሌ ክልል፦ አይሻ (Aysha) — ይህ አካባቢ በሀገሪቱ ከፍተኛው የንፋስ ፍጥነት ያለበት ነው፤ 🌪 o ኦሮሚያ ክልል፦ አዳማ፣ ኢተያ (Iteya) እና የምሥራቅ ሸዋ አካባቢዎች፤ o አማራ ክልል፦ ደብረ ብርሃንና የሰሜን ወሎ አካባቢዎች። የፀሐይ ኃይል (Solar Energy) ☀️🔅 ኢትዮጵያ በምድር ወገብ አቅራቢያ የምትገኝ በመሆኗ ዓመቱን ሙሉ ከፍተኛ የፀሐይ ብርሃን ታገኛለች። 💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ በዓመት 2.1 ሚሊዮን ቴራዋት ሰዓት (TWh)፤ በአማካይ በቀን በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 5.5 ኪሎዋት ሰዓት (kWh) ኃይል ማግኘት ይቻላል። ክልላዊ ስርጭት፦ o ከፍተኛ አቅም ያላቸው፦ አፋር፣ ሶማሌ፣ ትግራይ፣ አማራ እና ምሥራቅ ኢትዮጵያ፤ o መካከለኛ አቅም ያላቸው፦ ኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ። ☀️ ልዩ ባህሪ፦ የፀሐይ ኃይል በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ከግሪድ ጋር ላልተገናኙ (Off-grid) የገጠር ማህበረሰቦች ተደራሽ ለማድረግ እጅግ አመቺ ነው። 🇪🇹⚡️ የጂኦተርማል ኃይል (Geothermal Energy) 🌋♨️ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ (Rift Valley) መካከል ላይ በመገኘቷ ከፍተኛ የከርሰ-ምድር እንፋሎት አቅም አላት። 💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ ከ 10,000 ሜጋ ዋት (MW) በላይ። ⚡️ ክልላዊ ስርጭት፦ 📍 በዋነኝነት በስምጥ ሸለቆው መስመር ላይ በሚገኙት አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ይገኛል። 🌱 ተስማሚ አካባቢዎች፦ አሉቶ ላንጋኖ (Aluto Langano)፣ ኮርቤቲ (Corbetti)፣ ቱሉ ሞዬ (Tulu Moye) እና ፈንታሌ፤ ጥቅሙ፦ እንደ ንፋስና ፀሐይ ሳይሆን፣ ጂኦተርማል በቀን 24 ሰዓትና ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ ኃይል የመስጠት (Base-load) ብቃት አለው።

photo content

🇪🇹⚡️ 🇪🇹 የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ጸጋ፦ ያልተነካው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ዕድል! ኢትዮጵያ በታዳሽ የኃይል ምንጮች የታደለች ሀገር ብትሆንም፣ እስካሁን ጥቅም ላይ የዋለው እምቅ አቅም ከመቶ ሰባት (7%) እንኳን አይበልጥም። ይህ ክፍተት ዘርፉ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስትመንት ምን ያህል ክፍት እንደሆነ ማሳያ ነው። ዋነኞቹን የኃይል አማራጮች፣ ያላቸውን እምቅ አቅም እና በሀገሪቱ ያላቸውን ስርጭት እንደሚከተለው በዝርዝር ማየት ይቻላል፦ 🇪🇹⚡️ የንፋስ ኃይል (Wind Energy) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የንፋስ ኃይል እምቅ አቅም ካላቸው ቀዳሚ ሀገራት አንዷ ናት። 💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ 1,350 ጊጋ ዋት (GW) በላይ፤ 🌱 ተስማሚ አካባቢዎች፦ የንፋስ ፍጥነታቸው በሰከንድ ከ6.5 ሜትር በላይ የሆኑ አካባቢዎች ለኃይል ማመንጫነት ይመረጣሉ። 💨 ⚡️ ክልላዊ ስርጭት፦ 📍 o ትግራይ ክልል፦ መቐለና አካባቢው፤ o ሶማሌ ክልል፦ አይሻ (Aysha) — ይህ አካባቢ በሀገሪቱ ከፍተኛው የንፋስ ፍጥነት ያለበት ነው፤ 🌪 o ኦሮሚያ ክልል፦ አዳማ፣ ኢተያ (Iteya) እና የምሥራቅ ሸዋ አካባቢዎች፤ o አማራ ክልል፦ ደብረ ብርሃንና የሰሜን ወሎ አካባቢዎች። የፀሐይ ኃይል (Solar Energy) ☀️🔅 ኢትዮጵያ በምድር ወገብ አቅራቢያ የምትገኝ በመሆኗ ዓመቱን ሙሉ ከፍተኛ የፀሐይ ብርሃን ታገኛለች። 💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ በዓመት 2.1 ሚሊዮን ቴራዋት ሰዓት (TWh)፤ በአማካይ በቀን በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 5.5 ኪሎዋት ሰዓት (kWh) ኃይል ማግኘት ይቻላል። ክልላዊ ስርጭት፦ o ከፍተኛ አቅም ያላቸው፦ አፋር፣ ሶማሌ፣ ትግራይ፣ አማራ እና ምሥራቅ ኢትዮጵያ፤ o መካከለኛ አቅም ያላቸው፦ ኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ። ☀️ ልዩ ባህሪ፦ የፀሐይ ኃይል በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ከግሪድ ጋር ላልተገናኙ (Off-grid) የገጠር ማህበረሰቦች ተደራሽ ለማድረግ እጅግ አመቺ ነው። 🇪🇹⚡️ የጂኦተርማል ኃይል (Geothermal Energy) 🌋♨️ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ (Rift Valley) መካከል ላይ በመገኘቷ ከፍተኛ የከርሰ-ምድር እንፋሎት አቅም አላት። 💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ ከ 10,000 ሜጋ ዋት (MW) በላይ። ⚡️ ክልላዊ ስርጭት፦ 📍 በዋነኝነት በስምጥ ሸለቆው መስመር ላይ በሚገኙት አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ይገኛል። 🌱 ተስማሚ አካባቢዎች፦ አሉቶ ላንጋኖ (Aluto Langano)፣ ኮርቤቲ (Corbetti)፣ ቱሉ ሞዬ (Tulu Moye) እና ፈንታሌ፤ ጥቅሙ፦ እንደ ንፋስና ፀሐይ ሳይሆን፣ ጂኦተርማል በቀን 24 ሰዓትና ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ ኃይል የመስጠት (Base-load) ብቃት አለው።

photo content

ማከፋፈያ ጣቢያው ተጨማሪ የኃይል ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነው ‎…....///…….. ‎የጅግጅጋ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጨማሪ የኃይል ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑ
+6
ማከፋፈያ ጣቢያው ተጨማሪ የኃይል ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነው ‎…....///…….. ‎የጅግጅጋ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጨማሪ የኃይል ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ‎ ‎ሥራ አስኪያጁ አቶ ደምለው እሸቱ እንደገለጹት ‎በማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በተከናወኑ የአቅም ማሳደግና የማዘመን ሥራዎች አሁን ላይ የጅጅጋ ከተማና አካባቢው አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እያገኙ ነው። ጣቢያው እስከ 60 ሜጋ ዋት ኃይል የማቅረብ አቅም ቢኖረውም በአሁኑ ወቅት ለደንበኞች እየቀረበ ያለው የኃይል መጠን 30 ሜጋ ዋት ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ማከፋፈያ-ጣቢያው-ተጨማሪ-የኃይል-ጥያቄ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

ማስታወቂያ ......///....... የጄንደርና ሶሻል አፌርስ ኤክስፐርት V (Gender and Social Affairs Expert V) የጄንደርና ሶሻል አፌርስ ኤክስፐርት V (Gender and So
ማስታወቂያ ......///....... የጄንደርና ሶሻል አፌርስ ኤክስፐርት V (Gender and Social Affairs Expert V) የጄንደርና ሶሻል አፌርስ ኤክስፐርት V (Gender and Social Affairs Expert V) የሥራ መደብ የተመዘገባችሁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን እና የሥራ ልምዳችሁን በኢሜይል አድራሻ tsbprojectresourceproject@gmail.com እንድትልኩ እናሳስባለን። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል ምንጭ ጥገኝነትን መቀነስ! ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት በውሃ ኃይል (Hydro-power) ላይ ጥገኛ ሆና ቆይታለች። ይሁንና የኃይል ስብጥሩን ለማስፋት የተለያዩ ሥራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡
የኃይል ምንጭ ጥገኝነትን መቀነስ! ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት በውሃ ኃይል (Hydro-power) ላይ ጥገኛ ሆና ቆይታለች። ይሁንና የኃይል ስብጥሩን ለማስፋት የተለያዩ ሥራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ በቀጣይ ዓመታ ይተገበራሉ ተብለው በዕቅድ ከተያዙት መካከል የንፋስና የፀሐይ ኃይልን በስፋት ማካተቷ የአቅርቦት አስተማማኝነትን (Power Supply Reliability) ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ በመሆኑም የኃይል ምንጭ ጥገኝነት (Over-reliance on Hydropower) መቀነስ የሚኖሩትን አራት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዎች ቀጥለን እንመለከታለን። የአየር ንብረት ለውጥንና ድርቅን መቋቋም (Climate Resilience) የውሃ ኃይል ማመንጫዎች የዝናብ መጠን ሲቀንስ እና የግድቦች ውሃ የመያዝ አቅም ሲቀንስ የማመንጨት አቅማቸው በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ስለሆነም እንደ ንፋስና ፀሐይ ባሉ ሌሎች ታዳሽ የኃይል ምንጮች ላይ ኢንቨስት ማድረጓ የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-ምንጭ-ጥገኝነትን-መቀነስ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

የተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ ተጠናቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ ….....///…….. በባህር ዳር ከተማ የተገነባው የባለ 230 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ አገልግሎ
+2
የተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ ተጠናቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ ….....///…….. በባህር ዳር ከተማ የተገነባው የባለ 230 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተሻገር እንደገለፁት በከተማዋ አንድ ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኝ ቢሆንም እያደገ የመጣውን የነዋሪውን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ጥያቄ የሚመልስ አልነበረም፡፡ ነባሩ የባህር ዳር የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለከተማዋና አካባቢው ኢንዱስትሪዎች 125 ሜጋ ዋት ኃይል እያቀረበ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ሆኖም ጣቢያው ኃይል የመጫን አቅሙ በመሙላቱ ምክንያት ተጨማሪ ጥያቄዎችን ማስተናገድ የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውሰዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የተንቀሳቃሽ-ማከፋፈያ-ጣቢያው-ግንባታ-ተ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኢነርጂ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ - ዘመናዊ፣ ፍትሐዊና ዘላቂ የፖሊሲ ማዕቀፍ! ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት አስርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየውን የኢነርጂ ፖሊሲ በመከለስ፣ ሀገራዊና ዓ
🇪🇹 የኢትዮጵያ ኢነርጂ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ - ዘመናዊ፣ ፍትሐዊና ዘላቂ የፖሊሲ ማዕቀፍ! ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት አስርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየውን የኢነርጂ ፖሊሲ በመከለስ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ አዲስ ረቂቅ ፖሊሲ ለውይይት ቀርቧል። ይህ ፖሊሲ ኢትዮጵያን የአህጉሪቱ የኃይል ማማ ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል ዋነኛ ምሰሶ ነው። 🇪🇹⚡️ በፖሊሲው ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮች፡- የኢነርጂ ስብጥርን ማመጣጠን (Energy Mix) 💡 ከውኃ ኃይል (Hydro) ባለፈ የንፋስ፣ የፀሐይ፣ የጂኦተርማልና የባዮ-ጋዝ አማራጮችን በስፋት በማካተት በተወሰኑ የኃይል ምንጮች ላይ ያለንን ጥገኝነት በመቀነስ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ፤ 🌅 ኃይል ላይ የተመሠረተ ልማት ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም 100% አረንጓዴና ታዳሽ የሆነ የኃይል ልማትን ማረጋገጥ የፖሊሲው ዋነኛ ግብ ነው። በመሆኑም የፖሊሲው ትኩረት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምናደርገውን ጥረት መደገፍ ነው፡፡ 🌅 የኢነርጂ ተደራሽነትና ፍትሐዊነት ኃይል ለሁሉም ለማዳረስና በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ አማራጮችን ያመቻቻል። ይህም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ለኢንዱስትሪ ልማት መፋጠን ቁልፍ ሚና ይጫወታል። 🌅 የግል ዘርፉን ተሳትፎ ማሳደግ በዘርፉ የሚታዩ የአቅርቦት ውስንነቶችን ለመቅረፍና ግዙፍ የኢነርጂ ፕሮጀክቶችን በገንዘብና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የግል ባለሀብቶች (IPPs) በስፋት የሚሳተፉበት ግልጽ አሠራር እንዲዘረጋ ማድረግ፤ ይህ አዲስ የፖሊሲ ማሻሻያ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን "የኢነርጂ ነዳጅ" እንደሚሆን ይታመናል።

በጣቢያው የኃይል አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያስችል ሁለተኛ ዙር የአቅም ማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው ……..///…..… በምዕራብ አርሲ ዞን እና በአካባቢው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍ
+5
በጣቢያው የኃይል አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያስችል ሁለተኛ ዙር የአቅም ማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው ……..///…..… በምዕራብ አርሲ ዞን እና በአካባቢው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማርካት በሻሸመኔ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሁለተኛ ዙር የአቅም ማሳደግ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ምህረቱ ግዛው እንደገለፁት ጣቢያው ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ መቆጣጠሪያዎችን በዘመናዊ የጂ.አይ.ኤስ ብሬከሮች በመቀየር አስተማማኝና ያልተቆራረጠ ኃይል ለማቅረብ እየተሰራ ነው። ቀደም ሲል በማከፋፈያ ጣቢያው የነበሩት የ33 እና 15 ኪሎ ቮልት መቆጣጠሪያ ብሬከሮች በዘመናዊ የጂ.አይ.ኤስ ብሬከሮች ተቀይረው አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ሥራ አስኪያጁ አስታውሰዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በጣቢያው-የኃይል-አቅርቦትን-ለማሻሻል-የ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

🇪🇹💡 የሰባት ዓመታት የኃይል ዘርፍ ጉዞ፦ ከእጥፍ በላይ ዕድገትና የ100% ታዳሽ ኃይል ድል! ከ2011 ጀምሮ በነበሩት ባለፉት ሰባት ዓመታት በሀገራችን የኃይል ማመንጨትና መሠረተ-ልማት ግንባታ ላይ የተመዘገበው ውጤት እጅግ አስደናቂ ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ነው። አሐዞች እንደሚነግሩን ዘርፉ በየዓመቱ በአማካይ የ10% እድገት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል። ⚡️ ዋና ዋና የስኬት አመልካቾች (2011 እስከ 2017) 💡 የኃይል ምርት መጠን፦ ከ15.3 ቴራዋት ሰዓት (TWh) ወደ 29.5 ቴራዋት ሰዓት በእጥፍ አድጓል። 💡 የማመንጨት አቅም፦ ከ4,500 ሜጋ ዋት (MW) ተነስቶ አሁን 9,760 ሜጋ ዋት ደርሷል። 💡 አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ፦ ከነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ወደ 75.4 ቢሊዮን ብር አድጓል። 💡 የውጭ ምንዛሬ ገቢ፦ ከቀጣናዊ የኃይል ሽያጭና ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚገኘው ገቢ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በታች የነበረ ሲሆን አሁን 338.7 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። 🇪🇹💡 ኢትዮጵያን በዓለም ልዩ የሚያደርጋት ምንድነው? ሀገራችን አጠቃላይ የኃይል ምንጯን 100 በመቶ ወደ ታዳሽ ኃይል (Renewable Energy) ያሸጋገረች ጥቂት ከሚባሉ የዓለም ሀገራት ተርታ መሰለፏ ትልቅ ኩራት ነው። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፦ 💡 17 የውኃ ኃይል ማመንጫዎችን፤ 💡 5 የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን፤ 💡 1 የጂኦተርማል (የከርሰ ምድር እንፋሎት) እና 💡 1 ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል የሚያመነጭ ጣቢያን ያስተዳድራል። 🏗⚡️ የመሠረተ-ልማት አውታራችን ስፋት፦ ከተለያዩ የኃይል ማመንጫዎች የተመረተው የኃይል ምርት 15,857 ኪሎ ሜትር የሰርኪዩት ርዝመት ባላቸው የማስተላለፊያ መስመሮችና የተለያየ የቮልቴጅ መጠን ባላቸው 148 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች (Substations) ባሉት ዘመናዊ የግሪድ ኔትወርክ ለተጠቃሚዎች እየደረሰ ይገኛል። 💡🇪🇹 የኢትዮጵያ ብርሃን ለቀጣናውም ትርፍ የሚሆን ብርታት እየሆነ ነው! 💡🇪🇹