uz
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Kanalga Telegram’da o‘tish

EEP Communication

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali EEP Communication analitikasi

EEP Communication (@eepcommuication) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 551 obunachidan iborat bo'lib, Texnologiyalar & Aralashmalar toifasida 8 406-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 161-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 551 obunachiga ega bo‘ldi.

19 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -3 ga, so‘nggi 24 soatda esa -5 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 26.69% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 15.00% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 150 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 332 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 10 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
EEP Communication

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 20 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Texnologiyalar & Aralashmalar toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 551
Obunachilar
-524 soatlar
+97 kunlar
-330 kunlar
Postlar arxiv
ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በራስ አቅም የመጠገን ሥራ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የሚያጋጥሙ የቴክኒክ
+7
ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በራስ አቅም የመጠገን ሥራ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የሚያጋጥሙ የቴክኒክ ችግሮችን በጣቢያዎቹ የውስጥ አቅም የመፍታት አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን ሪጅኑ ገለፀ የሪጅኑ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ቢኒያም ታደሰ እንደገለፀት በማከፋፈያ ጣቢያዎች ለሚያጋጥሙ ድንገተኛ ችግሮች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስልታዊ አሠራር ተዘርግቷል። ጣቢያዎቹ የጥገና ሥራዎችን በራሳቸው አቅም ማከናወን እንዲችሉ ለባለሙያዎች ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን አስፈላጊ የመለዋወጫ ዕቃዎችም እንዲሟሉ መደረጉን ገልፀዋል። በዚህም መሰረት ከሪጅኑ ማዕከል ርቀው በሚገኙ እንደ መቱ፣ ጋምቤላ፣ ሚዛን እና በደሌ ባሉ ማከፋፈያ ጣቢያዎች አብዛኞቹ ድንገተኛ የጥገና ሥራዎች በአሁኑ ወቅት በየጣቢያው ባለሙያዎች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል ። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ማከፋፈያ-ጣቢያዎችን-በራስ-አቅም-የመጠገ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

"የአፍሪካ የታዳሽ የኃይል ማዕከል መሆን!" 🇪🇹✨ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይህንን ታላቅ ራዕይ ሰንቆ በዓለም አቀፉ የኮፕ 32 (COP32) አረንጓዴ መድረክ ላይ የሀገራችንን የማይበገር የታዳ
"የአፍሪካ የታዳሽ የኃይል ማዕከል መሆን!" 🇪🇹✨  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይህንን ታላቅ ራዕይ ሰንቆ በዓለም አቀፉ የኮፕ 32 (COP32) አረንጓዴ መድረክ ላይ የሀገራችንን የማይበገር የታዳሽ ኃይል ጉዞ ለዓለም ያበስራል። #COP32 #የአፍሪካየኃይልማዕከል #EEP #ታዳሽኃይል

ሪጅኑ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ........///....... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ለደንበኞች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረ
+9
ሪጅኑ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ........///....... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ለደንበኞች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሆነ የሪጅኑ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ቢኒያም ታደሰ ገልፀዋል ። ተወካዩ እንደተናገሩት በሪጅኑ ከሚገኙ 12 የማከፋፈያ ጣቢያዎች መካከል 10 ተጨማሪ ደንበኞችን የማስተናገድ ሙሉ አቅም ስላላቸው በአሁኑ ወቅት ለሚቀርቡ የኃይል ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ እየተሰጠ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ከሁሉም የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በአጠቃላይ ከ134 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ለደንበኞች እየቀረበ መሆኑንም አብራርተዋል። ሪጅኑ በተለያዩ ምክንያቶች እያደገ ለሚሄደው የኃይል ፍላጎት በአስተማማኝ መልኩ ምላሽ ለመስጠት በጣቢያዎቹ ላይ የአቅም ማሳደግ እና የመቆጣጠሪያ ብሬከሮችን የማዘመን ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ሪጅኑ-አስተማማኝ-ኃይል-ለማቅረብ-የሚያስ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

ዓለምን ከብክለት የመታደግ ብሔራዊ ኃላፊነት! ብዙ ሀገራት ከከሰልና ከነዳጅ ኃይል ለመላቀቅ በሚታገሉበት በዚህ ዘመን፣ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት ከካርቦን ነፃ (Zero-Carb
ዓለምን ከብክለት የመታደግ ብሔራዊ ኃላፊነት! ብዙ ሀገራት ከከሰልና ከነዳጅ ኃይል ለመላቀቅ በሚታገሉበት በዚህ ዘመን፣ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት ከካርቦን ነፃ (Zero-Carbon) የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ረገድ ቀዳሚ ናት። ኮፕ 32ን ስናስተናግድ፣ ተቋማችን የዓለምን የአየር ንብረት ሙቀት ለመቀነስ እያበረከተ ያለውን ተጨባጭ አስተዋጽኦ በኩራት እናሳያለን። እኛ የምናመነጨው ኃይል ሀገርን ያበራል፣ አየር ንብረትን ግን አይበክልም! ⚡️ ንፁህ አየር፣ አስተማማኝ ኃይል! #ZeroCarbon #Decarbonization #ClimateAction #COP32Host #EEPGreen 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ እያከናወናቸው ያሉ የኃይል ተደራሽነት ሥራዎች የማህበረሰቡን ቅሬታ እየፈቱ ነው .......///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደቡብ ምዕራብ ክልል እያከናወናቸው ያሉ የኃይል ማከፋፈ
+7
ተቋሙ እያከናወናቸው ያሉ የኃይል ተደራሽነት ሥራዎች የማህበረሰቡን ቅሬታ እየፈቱ ነው .......///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደቡብ ምዕራብ ክልል እያከናወናቸው ያሉ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተደራሽነት ሥራዎች ማህበረሰቡ ከኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ለሚያነሳቸው ቅሬታዎች ተጨባጭ መፍትሔ እየሰጡ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ ምዕራብ ሪጅን አስታወቀ የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ገብሬ እንደገለፁት ሪጅኑ ከማሻ፣ ቦንጋ፣ አባ እና ሚዛን ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል በመቀበል በደቡብ ምዕራብ ክልል ለሚገኙ ስድስት ዞኖች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ከሚዛን ማከፋፈያ ጣቢያ በስተቀር ከሌሎች ጣቢያዎች በቂ የኃይል አቅርቦት እያገኘ በመሆኑ ደንበኞችን በአግባቡ ማገልገል መቻሉን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-አቅርቦቱ-የፋብሪካው-ማሽኖች-ደህ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል አቅርቦቱ የፋብሪካው ማሽኖች ደህንነታቸው ተጠብቆ ምርታማ እንዲሆኑ እያስቻለ ነው …….//…… በሃይንከን ኢትዮጵያ ስር ለሚገኘው ለበደሌ ቢራ ፋብሪካ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የፋብሪ
+9
የኃይል አቅርቦቱ የፋብሪካው ማሽኖች ደህንነታቸው ተጠብቆ ምርታማ እንዲሆኑ እያስቻለ ነው …….//…… በሃይንከን ኢትዮጵያ ስር ለሚገኘው ለበደሌ ቢራ ፋብሪካ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የፋብሪካው ማሽኖች ደህንነታቸው ተጠብቆ ምርታማ እንዲሆኑ እያስቻለ መሆኑን የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ ተገኑ ዲባባ ገለፁ። ሥራ አስኪያጁ እንደገለፁት ፋብሪካው ቀጥታ ከበደሌ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ለብቻው በተዘረጋ በባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመር ኃይል እያገኘ ነው። ይህም ለምርት እንቅስቃሴው የሚያስፈልገውን በቂ ኃይል ሳይቆራረጥ በአግባቡ እንዲያገኝ አስችሎታል። አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት መኖሩ ማሽነሪዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጡ በማስቻል የፋብሪካው ምርታማነት ከጊዜ ወደጊዜ እንዲጨምር አድርጎታልም ብለዋል ። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-አቅርቦቱ-የፋብሪካው-ማሽኖች-ደህ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ የምስራቅ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ማጠናከሪያ ፕሮጀክትን ለማስጀመር ከአካባቢው መስተዳድሮች ጋር ተወያየ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመላው አገሪቱ የሚያከናውናቸው የኤሌክት
+9
ተቋሙ የምስራቅ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ማጠናከሪያ ፕሮጀክትን ለማስጀመር ከአካባቢው መስተዳድሮች ጋር ተወያየ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመላው አገሪቱ የሚያከናውናቸው የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግንባታዎች ማህበረሰቡን ባቀፈ መልኩ የሚሰሩ መሆናቸውን አስታወቀ ተቋሙ ይህንን የገለፀው የምስራቅ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ማጠናከሪያ ፕሮጀክትን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችል የጋራ ውይይት ከአካባቢው የመስተዳድር አካላት ጋር ባካሄደበት ወቅት ነው። ውይይቱ በዋናነት ከይዞታ አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የነበሩ የቆዩ ተግዳሮቶችን በመፍታት ግንባታውን በፍጥነት ለማስጀመር በሚያስችሉ የጋራ መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ ነው። ተቋሙ ከሐረር ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ለሚገነባው ማከፋፈያ ጣቢያ የሚሆን ቦታ ከአሁን በፊት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ወደ ኋላ የተመለሰበትን ምክንያት የአካባቢው የመስተዳድር አካላት ማብራሪያ እንዲሰጡበት በውይይቱ ላይ ጠይቋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-የምስራቅ-ኢትዮጵያ-ኤሌክትሪሲቲ-ማ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም

"ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ሃገራዊ ዕድገትን ማረጋገጥ አይታሰብም" አቶ ከሊል ሽፋ .....///..... ያለ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚከናወን የልማት እንቅስቃሴም ሆነ ሃገራዊ ዕድገት
+7
"ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ሃገራዊ ዕድገትን ማረጋገጥ አይታሰብም"  አቶ ከሊል ሽፋ .....///..... ያለ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚከናወን የልማት እንቅስቃሴም ሆነ ሃገራዊ ዕድገት እንደሌለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋማዊ ደህንነትና አስተዳደራዊ ጉዳዮች መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ ገለፁ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምሥራቅ አንድ ሪጅን የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ደህንነትን ለማስጠበቅ ከአካባቢው የመስተዳድር፣  የፍትህና ፀጥታ አካላት እና ከማህበረሰቡ ተወካዮች ጋር በድሬዳዋ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ በከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶችን እና መሰረተ ልማቶቹ በተገነቡበት ቦታዎች የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ግንባታዎችን እንዴት ማስቆም እንደሚቻል ግንዛቤ ለመፍጠርና የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ያለ-ኤሌክትሪክ-ኃይል-ሃገራዊ-ዕድገትን-ማ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም

በሪጅኑ ከሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በቂ ኃይል እያገኘን ነው ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሥር ከሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለኅብረተሰቡና ለኢንዱስትሪዎች አገልግሎት የሚውል በቂ ኃይል እየቀረበ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን አስታወቀ:: በአገልግሎቱ የጅማ ሪጅን የማሰራጫ መስመሮች ኦፕሬሽንና ጥገና ክፍል ኃላፊ አቶ ሻምበል አድማሱ እንደገለፁት ሪጅኑ ከወልቂጤ ማከፋፈያ ጣቢያ በአንድ ወጪ መስመር የሚያገኘውን ጨምሮ በአጠቃላይ ከስድስት ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል እየተቀበለ ይገኛል። የጅማ ሪጅን ከእነዚህ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሚነሱ 22 የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመሮችን በመጠቀም በሪጅኑ ለሚገኙ ደንበኞች በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በማቅረብ ላይ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማከፋፈያ ጣቢያዎችን የቁጥጥር ሥርዓት የማዘመን ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል። ይህ የማዘመን ሥራ በመስመሮቹ ላይ የሚከሰቱ ብልሽቶችንና መቆራረጦችን በፍጥነት በመለየትና ለመፍታት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አቶ ሻምበል አስረድተዋል። ይህ የቴክኖሎጂ ማሻሻያ በተለይም እንደ ሊሙ ለመሳሰሉ ከማከፋፈያ ጣቢያ በረጅም ርቀት ለሚጓዙ የኃይል ማሰራጫ መስመሮች ላይ ብልሽቶች ሲፈጠሩ ችግሩን በቀላሉ ተቆጣጥሮ ለመጠገን ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ እያከናወናቸው ያሉ የአቅም ማሳደግና የማዘመን ሥራዎች በአገልግሎቱ ደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን እየቀረፉ እንደሚገኝ የጠቀሱት ኃላፊው ተቋሙ በቀጣይም ይህን በጎ ጅምር አጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸውን አቶ ሻምበል ገልፀዋል። ለኅብረተሰቡ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ሲባል ሁለቱ ተቋማት በኃይል አቅርቦት ላይ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው የሰው ኃይላቸውንና ማሽነሪዎቻቸውን በማስተባበር በጋራና በትጋት እየሠሩ እንደሚገኙ ኃላፊው ተናግረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+6

ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለጅማ ከተማዋና አካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ነው በጅማ ከተማ የሚገኙት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለከተማዋና ለአካባቢው ሁለንተናዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ የጣቢያዎቹ የሥራ ኃላፊዎች ገለፁ። የጅማ ቁጥር አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ናትናኤል ወርቅነህ እንደተናገሩት ጣቢያው ከመስከረም 1980 ዓ.ም ጀምሮ የጅማ ቁጥር ሁለት ማከፉፈያ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት እስከጀመረበት እስከ ነሐሴ 2007 ዓ.ም ድረስ ለከተማዋና ለአካባቢው ብቸኛ የኃይል አቅራቢ በመሆን አገልግሏል። ይሁንና የቁጥር ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ የተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች ከቁጥር ሁለት እንዲያገኙ በመደረጉ አሁን ላይ ጣቢያው 90 በመቶ የሚሆነውን የከተማዋን የኃይል አቅርቦት እየሸፈነ ይገኛል ብለዋል። ጣቢያው ባለ 20 እና ባለ 16 ሜጋ ቮልት አምፔር አቅም ያላቸው ሁለት ትራንስፎርመሮች፣ አንድ ባለ 132፣ ዘጠኝ ባለ 15 እና ስድስት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች አሉት። አሁን ላይ በአራት ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች አማካኝነት ለጅማ ከተማ እስከ 18 ሜጋ ዋት ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ናትናኤል በሦስት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ደግሞ ለሊሙ ገነትና ለሾቤ ወረዳዎች እንዲሁም ለጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ እስከ 8 ሜጋ ዋት ኃይል በማቅረብ ላይ ይገኛል። ይህም ለአካባቢው ኢኮኖሚ መነቃቃት ትልቅ መሠረት ጥሏል። ቀሪዎቹ አምስት ባለ 15 እና ሦስት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ለታለመው የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትና ለሌሎች አዳዲስ አገልግሎቶች በመጠባበቂያነት መዘጋጀታቸውንም ኃላፊው አክለዋል። በአሁኑ ወቅት የባለ 20 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሩ የመጫን አቅሙ በመሙላቱ ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ እንደማይችል ጠቁመው የባለ 16 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሩ ደግሞ ከአቅሙ 55 በመቶ በላይ  የሚሆነው ጥቅም ላይ ውሏል ብለዋል። ከቴክኖሎጂ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ከዘጠኝ ወር በፊት የጣቢያውን የ33 ኪሎ ቮልት የመቆጣጠሪያ ብሬከሮች ወደ ዘመናዊው የጂአይኤስ (GIS) ሥርዓት በመቀየር ከመረጃ አያያዝ እና ከኦፕሬሽን አሰራር ጋር ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን መቅረፍ ተችሏል። በቀጣይም ለረጅም ዓመታት ያገለገሉትን የሲዊች ያርድ፣ የባዝ ባርና ሌሎች የጣቢያው አካላትን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ኃላፊው አስገንዝበዋል። የጅማ ቁጥር ሁለት ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ይልማ አበበ በበኩላቸው ጣቢያው እያንዳንዳቸው 63 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸው ሁለት አዉቶ ትራንስፎርመሮች እና የ25 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለው አንድ ፖወር ትራንስፎርመር እንዳለው ገልፀዋል። በተጨማሪም አንድ ባለ 230 ጥምር ገቢ፣ አንድ ባለ 230 ጥምር፣ ሁለት ባለ 132 እና አምስት ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች አሉት። ጣቢያው በአሁኑ ወቅት በባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮቹ ለጅማ ከተማ ማህበረሰብ፣ ለጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ለውሃ አገልግሎት ተቋማት፣ ለአባ ጅፋር ቤተ መንግስት እና ለሰርቦ ከተማ እስከ 18 ሜጋ ዋት ኃይል በማሰራጨት ላይ ይገኛል። እንደ አቶ ይልማ ማብራሪያ የጣቢያው አውቶ ትራንስፎርመሮች እስከ 100 ሜጋ ዋት የመጫን አቅም ቢኖራቸውም የፖወር ትራንስፎርመሩ አቅም አነስተኛ በመሆኑ ያለውን አጠቃላይ አቅም በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል አልተቻለም። ስለሆነም በአካባቢው በፍጥነት እያደገ ለመጣው የኃይል ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እና የቁጥር ሁለት አውቶ ትራንስፎርመሮችን ሙሉ አቅም ለመጠቀም የቁጥር አንድ ባለ 20 እና የቁጥር ሁለት ባለ 25 ሜጋ ቮልት አምፔር ትራንስፎርመሮችን አቅም የማሳደግ ሥራ በዕቅድ መያዙን የሥራ ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል። ከዚህ ጎን ለጎን የቁጥር ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያ የመቆጣጠሪያ ሥርዓትን በጂአይኤስ (GIS) ብሬከር ለማዘመን ዕቅድ ተይዟል። የማከፋፈያ ጣቢያዎቹ በአካባቢው መኖራቸው ስማርት ከተሞች እንዲመሠረቱ፣ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ እና ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የገለፁት የሥራ ኃላፊዎቹ በቀጣይም ይበልጥ አስተማማኝና ያልተቋረጠ የኤሌክትሪክ ኃይል ለደንበኞች ለማቅረብ ከአገልግሎቱ ተቋሙ ጋር በቅንጅትና በትብብር እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+8

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአስተናጋጅ (Waiter) የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር በቁጥር አ.ኤ.ኃ/8.4/245/18 ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የውጭ ማስ
+3
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ   የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአስተናጋጅ (Waiter) የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር በቁጥር አ.ኤ.ኃ/8.4/245/18 ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የውጭ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ስም ዝርዝራችሁ ከዚህ በታች የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ሰኔ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 የፅሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ  ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

በማከፋፈያ ጣቢያው የኃይል ፍላጎት በማደጉ የአቅም ማሳደግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ ....///…. በአካባቢው ካለው የከተሞችና የኢንዱስትሪ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በሚዛን ባለ 132 ኪሎ ቮልት
+6
በማከፋፈያ ጣቢያው የኃይል ፍላጎት በማደጉ የአቅም ማሳደግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ ....///…. በአካባቢው ካለው የከተሞችና የኢንዱስትሪ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በሚዛን ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ያለው የኃይል ጭነት በፍጥነት እያደገ መምጣቱን የጣቢያው ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋነሽ ሞላ ተናግረዋል ማከፋፈያ ጣቢያው በአሁኑ ወቅት 6 ነጥብ 3 እና 25 ሜጋ ቮልት አምፒር ኃይል መሸከም የሚችሉ ሁለት ትራንስፎርመሮች ያሉት ሲሆን በ132 ኪሎ ቮልት የተቀበለውን ኃይል በስድስት ባለ 15 እና ባለ 33 እንዲሁም በአንድ ባለ 66 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች አማካኝነት እያቀረበ ይገኛል። የጣቢያው ኃላፊ እንዳብራሩት በሦስት ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ለሚዛን፣ ሸኮ፣ አማን ከተሞችና አካባቢዎቻቸው ኃይል የሚሰራጭ ሲሆን በ33 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ደግሞ ለዲማ፣ ጨና 1 እና 2፣ ባቹማ፣ ሸዋ ቤንች ከተሞችና አካባቢዎች እስከ ጋምቤላ ክልል ድረስ ኃይል ያቀርባል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በማከፋፈያ-ጣቢያው-የኃይል-ፍላጎት-በማደ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ የካይዘን ሥርዓትን ተግባራዊ አደረገ ....///…. የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ብክነትን በመቀነስ የሥራ ቅልጥፍናን የሚያሳድገውን የካይዘን የአሠራ
+5
የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ የካይዘን ሥርዓትን ተግባራዊ አደረገ ....///…. የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ብክነትን በመቀነስ የሥራ ቅልጥፍናን የሚያሳድገውን የካይዘን የአሠራር ሥርዓት በተግባር ማዋል ጀመረ የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ግርማ እንደገለፁት በጣቢያው የሚገኙ ልዩ ልዩ የመለዋወጫ ዕቃዎች በካይዘን ፍልስፍና መርሆዎች መሠረት በግምጃ ቤት ውስጥ በሥርዓት እንዲቀመጡና እንዲደራጁ ተደርጓል። ይህም ዕቃዎቹ ለአገልግሎት በሚፈለጉበት ወቅት ያለ ምንም እንግልትና ጊዜ ሳይባክን በቀላሉ ለማግኘት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። ስለ አሠራሩ አስፈላጊነት አቶ ሀብታሙ ሲያብራሩ የካይዘን ሥርዓት መተግበሩ በጣቢያው የሚታዩ አላስፈላጊ የሀብትና የጊዜ ብክነቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይረዳል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የወላይታ-ሶዶ-ኮንቨርተር-ጣቢያ-የካይዘን 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙን ከተለያዩ የሕግና የፋይናንስ ስጋቶች ለመከላከል በትኩረት መስራት ይገባል ....///…. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ገቨርናንስ እና ኮምፕሊያንስ ሥራ አስፈፃሚ ተቋሙን ከተለያዩ የ
+7
ተቋሙን ከተለያዩ የሕግና የፋይናንስ ስጋቶች ለመከላከል በትኩረት መስራት ይገባል ....///…. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ገቨርናንስ እና ኮምፕሊያንስ ሥራ አስፈፃሚ ተቋሙን ከተለያዩ የሕግና የፋይናንስ ስጋቶች ለመከላከል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳሰቡ። ይህ መልዕክት የተላለፈው ተቋሙ ለሕግ ባለሙያዎቹ በሕግና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ  ሥልጠና እንዲሰጥለት ለፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተዘጋጀው የሥልጠና ማጠናቀቂያ መርሃ-ግብር ላይ ነው። የኮርፖሬት ገቨርናንስ እና ኮምፕሊያንስ ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዱጉማ ነዳ ባስተላለፉት መልዕክት ሥልጠናው የሕግ ባለሙያዎቹ ከተቋሙ ነባራዊ ሁኔታና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ጋር የተጣጣመ የላቀ የሕግ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በእጅጉ ያግዛል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙን-ከተለያዩ-የሕግና-የፋይናንስ-ስጋ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የጣቢያው ሁለተኛ የግንባታ ምዕራፍ እየተከናወነ ነው ....///…. የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሁለተኛው የግንባታ ምዕራፍ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የፕሮጀክቱ አማካሪ ተወካይ ሪዚ
+9
የጣቢያው ሁለተኛ የግንባታ ምዕራፍ እየተከናወነ ነው ....///…. የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሁለተኛው  የግንባታ ምዕራፍ  በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የፕሮጀክቱ አማካሪ ተወካይ ሪዚደንት መሀንዲስ አስታወቁ:: ተወካዩ አቶ ሰለሞን ክንፈ እንደገለፁት የጣቢያው ግንባታ በሁለት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን በመጀመሪያው ምዕራፍ 32 የንፋስ ተርባይኖችን በመትከል 80 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ተችሏል። በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ ባለው በሁለተኛው የግንባታ ምዕራፍ ደግሞ የ16 ተርባይኖች ተከላ ሥራ እየተሠራ ይገኛል። ይህም ጣቢያው ተጨማሪ 40 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ የሚያስችለው ሲሆን አጠቃላይ የማመንጨት አቅሙን 120 ሜጋ ዋት በማድረስ ሀገሪቱ በኃይል አቅርቦት ዘርፍ ለምታደርገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የጣቢያው-ሁለተኛ-የግንባታ-ምዕራፍ-እየተ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ - የምሥራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ኃይል አቅራቢ! የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ድንበር የለውም። ተቋማችን ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ኃይል ከማመንጨት ባለፈ፣ ንፁህና ታዳሽ የሆነውን የኤ
ኢትዮጵያ - የምሥራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ኃይል አቅራቢ! የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ድንበር የለውም። ተቋማችን ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ኃይል ከማመንጨት ባለፈ፣ ንፁህና ታዳሽ የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል። ሀገራችን የምታስተናግደው ኮፕ 32 (COP 32) ጉባኤ፣ ተቋማችን የአፍሪካን አህጉር ካርቦን የመቀነስ (Decarbonization) ጉዞ በግንባር ቀደምትነት እየመራ መሆኑን ያበስራል። ንፁህ ኃይልን በመሸጥ የውጭ ምንዛሬን እናሰባስባለን፤ የአየር ንብረት ብክለትንም በጋራ እንከላከላለን! ቀጣናዊ ትስስር በታዳሽ ኃይል ልማት! #RegionalIntegration #PowerExport #GreenAfrica #COP32 #EthiopianElectricPower 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ - የምሥራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ኃይል አቅራቢ! የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ድንበር የለውም። ተቋማችን ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ኃይል ከማመንጨት ባለፈ፣ ንፁህና ታዳሽ የሆነውን የኤ
ኢትዮጵያ - የምሥራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ኃይል አቅራቢ! የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ድንበር የለውም። ተቋማችን ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ኃይል ከማመንጨት ባለፈ፣ ንፁህና ታዳሽ የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል። ሀገራችን የምታስተናግደው ኮፕ 32 (COP 32) ጉባኤ፣ ተቋማችን የአፍሪካን አህጉር ካርቦን የመቀነስ (Decarbonization) ጉዞ በግንባር ቀደምትነት እየመራ መሆኑን ያበስራል። ንፁህ ኃይልን በመሸጥ የውጭ ምንዛሬን እናሰባስባለን፤ የአየር ንብረት ብክለትንም በጋራ እንከላከላለን! ቀጣናዊ ትስስር በታዳሽ ኃይል ልማት! #RegionalIntegration #PowerExport #GreenAfrica #COP32 #EthiopianElectricPower 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ማመንጫ ጣቢያው የ9 ወራት ዕቅዱን 99 ነጥብ 1 በመቶ አሳካ ...///… የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 256 ነጥብ 11 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማምረት የዕቅዱን 9
+6
ማመንጫ ጣቢያው የ9 ወራት ዕቅዱን 99 ነጥብ 1 በመቶ አሳካ ...///… የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 256 ነጥብ 11 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማምረት የዕቅዱን 99 ነጥብ 1 በመቶ ማሳካቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ:: ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙሉቀን ተሰማ እንዳስታወቁት ጣቢያው ባለፉት ዘጠኝ ወራት በ32 ተርባይኖች 258 ነጥብ 28 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማመንጨት አቅዶ 256 ነጥብ 11 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ማምረት ችሏል። አፈፃፀሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ8 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም የ3 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም ገልፀዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት የጣቢያው ዝግጁነት ወይም የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ (Plant Availability) እና ኃይል ከሚያመነጨው አቅም አንፃር ጥቅም ላይ የዋለው (Utilization Index – UI) አፈፃፀም ከዕቅዱ በላይ መሆኑን አብራርተዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ማመንጫ-ጣቢያው-የ9-ወራት-ዕቅዱን-99-ነጥብ-1-በ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም