uz
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Ko'proq ko'rsatish
603
Obunachilar
-324 soatlar
-87 kun
-1730 kun
Postlar arxiv
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤             ❤ #የካቲት ፳፪ (22) ቀን። ❤ እንኳን የፋርስ ንጉሥ ልጅ በጸሎቱ ከነበረባት ጋኔን ለፈወሳት #ለኤጲስቆጶስ_ለአባ_ማሩና ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያና በከሀዲ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን #በፋርስ_አገር_ለተገደሉ_ሰማዕታት ለሥጋቸው ለፈለሰበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰቡ፦ ከከበረ #ከአባ_ቡላና_ከሦስት_መቶ_ሰማንያ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ማሩና፦ ኤጲስቆጶስ ማሩናንም ስለ ድንቆች ተአምራቶቹ ስለ ትሩፋቱና ስለ ጽድቁ የአኖርዮስና የአርቃድዎስ አባት ታላቁ ቴዎዶስዮስ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋር እጅ መንሻ በመካከላቸው ስለ አለው ፍቅር ተላከ። ወደ ሳቦር ወደ ፋርስ ንጉሥም በደረሰ ጊዜ ታላቅ ክብርንም አከበረው በቤተ መንግሥቱም እልፍኝ ውስጥ አኖረው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን አምላክን ለወለደች #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ለወራዊ በዓልዋ መታሰቢያ፣ ለከበ
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #የካቲት ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን  አምላክን ለወለደች #ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ለወራዊ በዓልዋ መታሰቢያ፣ ለከበረ ለሐዋርያው #ለቅዱስ_ጳውሎስ ደቀ መዝሙር ለሆነ #ለቅዱስ_አናሲሞስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክድርያ ኃምሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ገብርኤል ለዕረፍት በዓልና ለአገረ ስሐ ኤጲስቆጶስ ለከበረ አባት #ለአባ_ዘካርያስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ #ከአባ_አካክዮስና ከኢትዮጵያ አገር ጳጳስ #ከአባ_ገብርኤል ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን አምላክን ለወለደች #ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በአማላጅነቷና በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ዝክረ አድዋ መርሃግብር የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 23 ከ 8:30 ጀምሮ በግራር ደብር አባይ ቅድስት አርሴማ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ዝክረ አድዋ በሚል ስያሜ ኪነጥበብ ክፍሉ ልዩ ልዩ መርሃግብሮችን አ
ዝክረ አድዋ መርሃግብር የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 23 ከ 8:30 ጀምሮ በግራር ደብር አባይ ቅድስት አርሴማ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት  ዝክረ አድዋ በሚል ስያሜ ኪነጥበብ ክፍሉ ልዩ ልዩ መርሃግብሮችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል::በዕለቱ ይገኙ ዘንድ  ግብዣችን ነው :: በ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ኪነ ጥበብ ክፍል የተዘጋጀ

ዝክረ አድዋ መርሃግብር የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 23 ከ 8:30 ጀምሮ በግራር ደብር አባይ ቅድስት አርሴማ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ዝክረ አድዋ በሚል ስያሜ ኪነጥበብ ክፍሉ ልዩ ልዩ መርሃግብሮችን አ
ዝክረ አድዋ መርሃግብር የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 23 ከ 8:30 ጀምሮ በግራር ደብር አባይ ቅድስት አርሴማ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት  ዝክረ አድዋ በሚል ስያሜ ኪነጥበብ ክፍሉ ልዩ ልዩ መርሃግብሮችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል::በዕለቱ ይገኙ ዘንድ  ግብዣችን ነው :: በ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ኪነ ጥበብ ክፍል የተዘጋጀ

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያውያን_ጻድቅ ውኃ ከዓለት ድንጋይ ላይ እያፈለቁ አሕዛብን ሁሉ እያስተማሩ ያጠምቁ
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #የካቲት ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያውያን_ጻድቅ ውኃ ከዓለት ድንጋይ ላይ እያፈለቁ አሕዛብን ሁሉ እያስተማሩ ያጠምቁ ለነበረ፤ ኅብስትም ከሰማይ እየወረደላቸው ሕዝቡን ያቆርቡ ለነበረ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ክፍለ_ማርያም_ዘድባጋ ከዚህ ዓለም እንደነ #ቅዱሳን_ሄኖክና_ኤልያስ ከሞት ለተሰወሩበት በዓልና #ለአባ_ገብረ_መርዓዊ_ዘአግዶ_ገዳም ለመታሰቢያ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ለአቡነ_ክፍለ_ማርያም_ዘድባጋ፦ ትውልዳቸው እንደርታ ሲሆን በ14 ዓመታቸው መንኵሰው፡ መንነው በቅተው ሲኖሩ በአንድ ወቅት ወደ አክሱም ሄዱና ወላጆቻቸው ካሉበት ደረሱ። ከቅዳሴ በኋላ መክፈልት ቆርሰው ሲያድሉ ወላጅ እናታቸው ከስተውና ጠቁረው ስላዩአቸው ለእናታቸው አዳልተው በብዙ ሰጧቸው። እናትየው ግን ጻድቁ የሰሩትን አያወቁም ነበር። ጻድቁ ከብቃታቸው የተነሳ መና ከሰማይ አየወረደላቸው ከዓለትም ላይ ውኃ እያፈለቁ ይጠጡ ነበር።                 √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨            

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢 በደብራችን ለተጀመረው ህንፃ ቤተክርስትያን ሁላችንም የምንችለውን አስተዋፅኦ በመደበኛ መርሀ ግብር እያመጣን  እናድርግ ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ ምንኵስና ለተቀበሉ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አ
+1
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ ምንኵስና ለተቀበሉ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አባለ_ክርስቶስ ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_አባለ_ክርስቶስ፦ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ አባለ ክርስቶስ ዘደብረ መድኃኒት ጻድቁ አቡነ አባለ ክርስቶስ ከአባታቸው ቅዱስ አቃርዮስ እና ከእናታቸው ቅድስት ታውክልያ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በየካቲት 19 910 ዓ.ም በአክሱም ከተማ የተወለዱ ጻድቅ ሲሆኑ ከሰውነታቸው ማሀል ዲካባ፣ ማርትያስ፣ ክስብኤል የሚሉ ኅቡአን የሥላሴ አስማት ተጽፎውላቸው የተወለዱ ጻድቅ ናቸው። ❤ በዚሁ መሰረት ከጻድቁ አቡነ ጰንጠሌዎን በሠላሳ ሁለት ዓመታቸው ምንኲስናን ከተቀብሉ በኋላ ጽላትን ለ24 ዓመታት ያህል እያጠኑ ከቆዩ እንደ ሌሎቹ ቅዱሳን ዛሬ ገደማቸው በሚገኝበት እና አፅማቸው ካረፈበት ገዳማቸው ተጋድሎን በመፈጸም ከፈጣሪያቸው በታሕሳስ 19 ቀን ቃልኪዳን ተቀብለው በ 332 ዕድሜያቸው ያረፉ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ናቸው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

Repost from N/a
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!! ✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የካቲት 23 የሚከበረውን የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን በግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተዘጋጀውን የኪነጥበብ መርሐግብር ቅዳሜ ከ08:00 ሰዓት ጀምሮ ተገኝታችሁ እንድታተርፉበት በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል። ✍️✍️✍️ኪነጥበብ ክፍል✍️✍️✍️

የካቲት ፲፰ [ 18] ጾመ ነነዌ ! " የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ  ለጾም አዋጅ ነገሩ  ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውና አወለቀ ማቅም ለበሰ በአመድም ላይ ተቀመጠ  አዋጅም አስነገረ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ  እንዲህም አለ ፦ ሰዎችን እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ  ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል ? እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ በሥራቸውን አየ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም" [ ት.ዮናስ ፫፥፭ -፲ ]        √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨                        

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ ለጌታችን ወንድም ለተባለ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ያዕቆብ ለዓ
+1
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #የካቲት ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ ለጌታችን ወንድም ለተባለ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ያዕቆብ ለዓመታዊ ለመታሰቢያ በዓሉና ለታማኝ ለከበረ አባት ለአንጾክያ አገር ሊቀ ጳጳስ ከአርዮሳውያን ብዙ ስደትና እንግልት ለደረሰበት #ለአባ_መላልዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን፡፡                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ፦ ይኸውም ቅዱስ የጌታችን ወንድም የተባለውና የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የነበረው ነው፡፡ እርሱም የጠራቢው የዮሴፍ፡ልጅ ሲሆን ከአራቱ ልጆቹ ትንሹ መጨሻው ነው፡፡የቅዱስ ያዕቆብ ወላጅ እናቱ በልጅነቱ ስለሞተችበትና የብርሃን እናቱ የሆነች ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን ዮሴፍ አረጋዊ በ83 ዓመቱ ጠባቂ ይሆናት ዘንድ ወደቤቱ ሲወስዳት ድንግል ማርያም ቅዱስ ያዕቆብን የሙት ልጅ ሆኖ አግኝታው ከተወደደ ልጇ ከጌታች ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብራ ተንከባክባ አሳድጋዋለች፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ያዕቆብ ድንግልና ንጹሕ ሆኖ ከጌታችን ጋር እየተጫወተ አብሮ አድጓል፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን #የእግዚአብሔር_ሰው ለሆነ #ለየዋህ_ለትሑቱ_ለነቢያት_አለቃ_ለቅዱስ_ሙሴ ለዕረፍቱ መታሰቢ
+1
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #የካቲት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን #የእግዚአብሔር_ሰው ለሆነ #ለየዋህ_ለትሑቱ_ለነቢያት_አለቃ_ለቅዱስ_ሙሴ ለዕረፍቱ መታሰቢያ ለበዓል፣ ከላይኛው ግብጽ ከአክሚም መንደር ለሆነ ስለ #እግዚአብሔር_አብ_አባትነት_ስለ_ወልድ_ልጅነት መስክሮ በእስላሞች መኰንን እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለታላቁ_ጻድቅ_ወሰማዕት_ለመነኰስ_አባ_ሚናስ ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #ሊቀ_ነቢያት_ቅዱስ_ሙሴ፦ ይህ ነቢይ ነፍሱን ስለእርሳቸው አሳልፎ እስከ መስጠት ደርሶ ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር የደከመ ነው እርሱም በግብጽ አገር በኤርትራ ባሕርም ድንቆች ተአምራትን ያደረገ ነው። ይህም ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ወላጆቹ በግብጽ ወንዝ ውስጥ በጣሉት ጊዜ አውጥታ ላሳደገችው ለፈርዖን ልጅ ለተርሙት ልጅዋ መባልን አልወደደም። እርሱ ፈርዖን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ይገድሏቸው ዘንድ አዝዞ ነበርና። በአገኘችውም ጊዜ ለርሷ ልጅ ሊሆናት ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት የሚጀመረውን ጾመ ነነዌ በማስመልከ
+3
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት የሚጀመረውን ጾመ ነነዌ በማስመልከት አባታዊ ቃለ በረከት አስተላለፉ፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን #አምላክን_ለወለደች_ለእናታችን_ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ከተወደደ ልጅዋ #ከጌ
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #የካቲት ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን #አምላክን_ለወለደች_ለእናታችን_ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ከተወደደ ልጅዋ #ከጌታችና_ከመድኃኒታች_ከኢየሱስ_ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን ለተቀበለችበት (#ለኪዳነ_ምሕረት) ዓመታዊ በዓልና ለመጥምቀ መለኮት #ለቅዱስ_ዮሐንስ_እናት ለከበረች #ለቅድስት_ኤልሣቤጥ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል  በሰላም አደረሰን።                                                   ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ዕለት የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በዓልን ያደርጋሉ። በዚች ዕለት መታቢያውን ለሚያደርግ ስሟን ለሚጣራ ለድኆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጥ የክብር ባለቤት ከሆነ ከተወደደ ልጅዋ ከጌታችና ከመድኃኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተቀብላለችና። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ምንኩስና የተጀመረው እንዴት ነበር? ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻዎቹ ባሻገር የምንኩስናን ታሪክ ስናጠና በ4ኛው ክፍለ ዘመን እንደተጀመረ ይታወቃል ለሦስት መቶ ዓመታት በአሰቃቂው ዘመነ ሰማዕታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መከራ ስትቀበል ክርስቲያኖችም በየቀኑ ሲገደሉ የነበረበት ዘመን ድንገት አበቃ በደማቸው ለመጠመቅና በሞታቸው ክብር ለመቀዳጀት የተዘጋጁ ምእመናንን ድንገት "በቃ ከእንግዲህ አትሞቱም" የሚል አዋጅ ታወጀባቸው:: ዕረፍት አገኘን ብለው የተደሰቱ እንደነበሩ ሁሉ ለሰማዕትነት ቆርጠው ለክብር አክሊል ተዘጋጅተው የነበሩ ብዙዎች ግን ድንገት ሰማዕትነት ሲቆም አዘኑ ከሰማዕትነት ክብር ወርደው እንደማንኛውም ሰው መኖር ከበዳቸው ስለዚህም በሰይፍ ባይሞቱም በፈቃዳቸው ሞተው ለክርስቶስ ሕያው ሆነው ሊኖሩ ወደ ገዳማዊ ሕይወት ወደ ምንኩስና ጎረፉ ይህም ክስተት ለምንኩስናና ለገዳማዊ ሕይወት ምክንያት ሆነ:: ዝቋላን በመሳሰሉ ገዳማት የሚገኙ መነኮሳት በሥጋ የሚሞቱበት ቀን ሳይደርስ በክርስቶስ ፍቅር በፈቃዳቸው የሞቱ ሐዋርያው እንዳለው "ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር የሰቀሉት" ናቸው ሰማዕትነትም ቀድመው የተመኙት ክብር ነበር በእነርሱ መገደል የሞትነው በእነርሱ ጸሎት ብርሃንነት የምንኖር  ስንጨነቅ ከእግራቸው ሥር የምናለቅስ  በዓለም ማዕበል ስንላተም በመስቀላቸው መልሕቅ ወደ ጸጥታ ወደብ የምንደርስ እኛው ነን:: ባለቆቡ ሰማዕት አባቴ ሆይ እርስዎን የገደሉ የገደሉት የእኔን ተስፋ ነው ሰማዕቱ መነኩሴ ሆይ በእርስዎ ሞት የተቀደደው የዕንባዬ መሐረብ ነው አንጀታችን በኀዘን እርር የሚለው ለእናንተ ሳይሆን ለራሳችን ነውጰከእናንተ ጸሎት በቀር ምርኩዝ የሌለን እኛ ይለቀስልን እንጂ ለእናንተ አናለቅስም ቀድማችሁ የጠላችኋት ዓለም ብትጠላችሁ አይገርምም በፍቅርዋ ለተሸነፍን ለእኛ ግን ዕንባ ያስፈልገናል እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የትኛዋ እንደሆነች ዘመነ ሰማዕታትን የምትደግመዋ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ማን እንደሆነች በደማችሁ ያሳያችሁ ምስክሮች ሆይ ለእኛ እንጂ ለእናንተ አናለቅስም የእኛን እግር ከማጠብ  የእኛን ብሶት ከመስማት  የእኛን የክርስትና ስም ዘወትር በጸሎት ከመጥራት እኛን ተቀብሎ ከማስተናገድ አረፍ ብላችሁ ከመነኮሳችሁለት አምላክ ዕቅፍ ስለገባችሁ አናዝንም የምናዝነው በተራራ ላይ ያለ መብራታችን ለጠፋብን ለእኛ ነው የእኛ ደብረ ታቦር ዝቋላ ሥሉስ ቅዱስ በደመና ይጋርድሽ እንጂ ምን እንላለን? ገዳምንና ገዳማውያንን መንካት የንቡን ቀፎ ማፍረስ ነው ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ዐቃቢት ያሉት ሁሉ በገዳም ቀፎነት የተሠሩ የማር እንጀራዎች ናቸው ማሩን የሚጋግሩት ንቦች ያሉት ከቀፎው ገዳም ውስጥ ነው: የአቡየ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቆብ ልጆች በአስኬማ ላይ የሰማዕትነት አክሊል የደረባችሁ ቅዱሳን መነኮሳት ጸልዩልን በዙፋኑ ፊት ቆማችሁ  "ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?" ብላችሁ ስለ እኛ አማልዱ:: (ራእ. 6:10) (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፲፭ (15) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት ለአንዱ ለታላቁ ለእውነተኛው ነቢይ #ለቅዱስ_ዘካርያስ ለዕረ
+1
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #የካቲት ፲፭ (15) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት ለአንዱ ለታላቁ ለእውነተኛው ነቢይ #ለቅዱስ_ዘካርያስ ለዕረፍት በዓል፣ በገድል ተጠምዶ ለኖረ የገዳማውያን አባቶችን ገድል ለመጻፍ ብዙ ለደከመ (በበረሀ ውስጥ በመግባቱ ከርኃብ የተነሣ ሥቃይ ደርሶበታል ያለምግብ ሦስት ቀን ከቆየ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት ሰውነቱን ሁሉ አፉንም ለሠሠው ያለ ምግብም ዐሥራ ሰባት ቀን ለኖረ) ስለእነርሱም ብዙ ምሥጢራትን ላወቀ #ለአባ_በፍኑትዮስ ለዕረፍት በዓልና ስብስጥያ በምትባል አገር የሰማዕታት #አርባ_ሐራ_ሰማይ_ቤተ_ክርስቲያናቸው_ለከበረችበት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ነቢዩ_ቅዱስ_ዘካርያስ፦ እርሱም ከሌዊ ነገድ ነው የአባቱም ስም በራክዩ ነው በገለዓድም ወለደው በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ተማረከ ከዚያ ሳለም በላዩ የወረደለትን መለኮታዊ ትንቢትን ተናገረ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ አንደበት ጠቃሚዎች የሆኑ ብዙ ቃሎችን ተናገረ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨                              

√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanz
+1
√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ❤              ❤ #የካቲት ፲፫ (13) ቀን። ❤ እንኳን #መልካም_ስም_አጠራርና ጣፋጭ ዜና ላለው ለሶርያ መስፍን ልጁ ለሆነ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤልና_ቅዱስ_ገብርኤል ከሞት አስነሥተውት፤ #ቅዱስ_ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14 ዓመት ለኖረ፤ ተመልሶ ወደ ምድር መጥቶ 40 ዓመት ለኖረ በተአምራቱና በትምህርቱ 85ሺህ አረማውያንን አሳምኖ ላጠመቀ #ለተመሰገነ_ለሁለተኛው_ለቅዱስ_አውሳብዮስ ለምስክርነቱና ለዕረፍቱ በዓል፣ ለከበረ #ለቅዱስ_ሰርግዮስ ከአባቱና እናቱ ከወድሞቹም ከሌሎችም ብዙ ሰዎች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለኅርማኖስ ልጅ ለታላቁ ሰማዕት #ለቅዱስ_ፊቅጦር ለልደቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ አባት ከእስክድርያ አገር ሠላሳ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ጢሞቴዎስ ዕረፍት፣ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ ልጅ #ከቅዱስ_ቴዎድሮስ ከምስክርነቱ መታሰቢያ፣ #ከአባ_ክፍላና_ከአባ_ኅብስት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                      ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ፊቅጦር፦ ለዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ኅርማኖስ ነው እርሱም ለዲዮቅልጥያኖስ የአማካሪዎቹና የሠራዊቱ አለቃ ነው ስለ አምልኮ ጣዖት ሥራ ምክሩና ንግግሩ ሁሉ ከእርሱ ጋራ ነበር የእናቱም ስም ማርታ ይባላል በክርስትናዋ የጸናች ብፅዕት ናት። ❤ ቅዱስ ፊቅጦርም በአደገ ጊዜ አባቱ ወደ ንጉሥ አቀረበው ንጉሡም በመንግሥቱ ውስጥ ሦስተኛ ማዕርግ አድርጎ ሾመው በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበረ። እርሱም የዚህን ዓለም ክብር ናቀ ሥጋ አይባላም ወይን አይጠጣም ዘወትርም ይጾማል ጸሎትንም ባለማቋረጥ በቀንና በሌሊት ይጸልያል። በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም የታሠሩትን ይጐበኛቸዋል ለድኆችና ለምስኪኖችም ይመጸውታል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን #ለመላእክት_አለቃ ለከበረ #ለቅዱስ_ሚካኤል ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ተልኮ ኃይልን ሰጥ
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን #ለመላእክት_አለቃ ለከበረ #ለቅዱስ_ሚካኤል ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ተልኮ ኃይልን ሰጥቶት ጠላቶቹን ድል እንዲያደርግ ለረዳበት ወራዊ መታሰቢያ በዓል፣ ተጋዳይ ፍጹም የዋሕና ትሑት ለሆነው ለከበረ አባት #ለአባ_ገላስዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከዶርቃስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የከበረ_ቅዱስ_ሚካኤልን በዚች ዕለት እግዚአብሔር ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ላከው የፍልስዔም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስከ አደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ ረዳው ኃይልንም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ ከእርሳቸው አንድ ሺህ ሰዎችን ገደለ። ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠለትና አጸናው እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨