uz
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Ko'proq ko'rsatish
603
Obunachilar
-324 soatlar
-87 kun
-1730 kun
Postlar arxiv
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #የካቲት ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን #ለተጋዳይ_ለታላቁ አባት በቀንና በሌሊት ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ከስግደት ጋር እየጸለ ለአርባ ዓመት በገዳም ለኖረውና በኋላም ወደ በረሃ ከአንዲት ታናሽ ዋሻ ውስጥም ገብቶ እየተጋደለ ብቻውን ለኃምሳ ዓመት ለኖረ፤ ሁለት አንበሶች እንደሰው ለሚላኩለት #ለባለ_አንበሳው_ለአባ_አውሎግ ለዕረፍት በዓል፣ ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ ለአባት #ለአባ_በላትያኖስ በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ለአንድ ዓመት ያህል ተሰቃይቶ ኋላም አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለአባ_ስልዋኖስ ረድእ #ለአባ_በትራ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኤጲስቆጶስ #ከአባ_አብርሃም_ከመነኰስ_ከአባ_መቃቢስና #ከኮንቲ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ  ረድኤትና በረከት ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ባለ_አንበሳው_አባ_አውሎግ፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆች ፍጹም በወርቅና በብርም የበለጸጉ ናቸው። በአንዲትም ዕለት "አውሎግ ያለህን ገንዘብህን ሁሉ ሽጠህ ለድኆች ሰጥተህ መከራ መስቀሉን ተሸክመህ ና ተከተለኝ" የሚለውን የከበረ የወንጌልን ቃል አሰበና ወዲያውኑ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ ወደ አባ አውሎጊን ሔደ እርሱም በደስታ ተቀበለው። ስለ እርሱ እንዲህ የሚለውን ራእይ አይቶ ነበር "እነሆ ወዳንተ ጐልማሳ ይመጣል ተቀበለውና ከሚያገለግሉ መነኰሳት ጋር ቀላቅለው"። እየፈተነውም ሦስት ዓመት ያህል ኖረ ፍጹም የሆነ ቅድስናውንም በአየ ጊዜ የምንኵስናን ልብስ የመላእክትንም አስኬማ አለበሰው። ከሰንበትም እስከ ሰንበት እየጾመ በብዙ ተጋድሎ ኖረ ምግቡም እንጀራና ጨው ነበረ በቀንና በሌሊትም ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ስግደት ጋር ይጸልያል በዚህም ተጋድሎ አርባ ዓመት ኖረ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ለእልፍዮስ ልጅ #ለከበረ_ሐዋርያ_ለቅዱስ_ያዕቆብ በንጉሥ
+3
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ለእልፍዮስ ልጅ #ለከበረ_ሐዋርያ_ለቅዱስ_ያዕቆብ በንጉሥ ቀላውዴዎስ ዘመን በአይሁድ እጅ በድንጋይ ተወግሮ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ #ለኢትዮያዊያኑ_ጻድቅ_ለአቡነ_እንድርያስ ኤርትራ አገር የሚገኘው ታላቁ ገዳም ደብረ ጽጌ ሰፍኣ ለመሰረቱ #ለዘጠኝ_መቶ_ዘጠና_ዘጠኝ_ደቀ_መዛሙርቶች በአረማውያን እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል (ታሪካቸውን የካቲት1 ይመልከቱ)፣ ለንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ለከበረ #ለቅዱስ_ዮስጦስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ፈርማ ከሚባል አገር በገድል ለተጠመደ ምሁር ለሆነ ዐሥራ ስምንት ሺህ መጽሐፍቶችን ተግሣጻትና ድርሳናት ለጻፈ ለዓለሙ ሁሉ #መምህር_ለአባ_ኤስድሮስ ለዕረፍት በዓልና ለፋርስ አገር ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ፌሎ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ #ቅዱሳን_ከኒቅላዎስና_ከስምዖን ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #የካቲት ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን #ለከበረ_በሶርያ_አገር ላሉ መነኰሳት አባት ለሆነ እንደ ኢያሱ ፀሓይን ገዝቶ ላቆመ፣ ዝናብንም በጸሎቱ ላዘነበ፤ ሳይቀመጥ ሃምሣ አራት ዓመት ቁሞ ለኖረ #ለታላቁ_አባት_ለአባ_በርሱማ ለዕረፍት በዓልና ለከበረ ለሶሪያዊ ከሃድያን ይዘው ምላሱን በመቁረጥ፣ በእሳት በማቃጠል፣ የብረት ችንካሮችን በእሳት አግለው በአፉና በጆሮዎቹ ለቸነከሩበትና በመጨረሻውም አንገቱን ለሰየፉት #ለቅዱስ_ጳውሎስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከከበረ_ሰማዕት_ከቅዱስ_ጴጥሮስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_በርሱማ_ዘሶርያ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ሳሚሳጥ ከሚባል አገር ሰዎች ውስጥ ናቸው አንድ በዋሻ ውስጥ የሚኖር ሰው በእርሱ ላይ ትንቢትን ተናገረ ከመወለዱ አስቀድሞ ለአባቱ እንዲህ አለው "የትሩፋቱ ዜና በሶርያ አገር ሁሉ የሚሰማ ጣዕም ያለው ፍሬ ከአንተ ይወጣል ከእርሱ የሚሆነውንም አሰረዳው"። ተወልዶም አድጎ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ በደረሰ ጊዜ ወላጆቹን ሸሽቶ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ደርሶ በዚያ ስሙ አብርሃም ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጠ እርሱም ወላጆቹን ስለፈራ ኪዚያ ገዳም ሰደደውና ሒዶ በአለት ውስጥ ኖረ በዚያም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ወሬውም በሶርያ አገሮች ሁሉ በተሰማ ጊዜ ብዙዎች ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ የዚያ ቦታ ውኃ ግን እጅግ መራራ ነበር በላዩ በጸለየ ጊዜ ተለውጦ ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቅች ተአምራቶችን አደረገ ከእርሳቸውም በአንዲት ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከበአቱ ርቆ ሳለ የፀሓይ መግቢያ ሰዓት ተቃረበ የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ወደ በአቱም እስቲደርስ ያን ጊዜ ፀሓይን አቆመለት። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካች_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከዘጠኙ ንዑስ በዓል ለአንዱ ከከበረ
+1
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን"። ❤              ❤ #የካቲት ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካች_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከዘጠኙ ንዑስ በዓል ለአንዱ ከከበረ ልደቱ ከአርባ ቀኖች በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ለገባበት በዓል፣ በድሜው ላይ ጌታችን ተወልዶ እስኪያይ ድረስ ሦስት መቶ ዓመት ለተጨመረለት ለካህኑ #አረጋዊ_ቅዱስ_ስምዖን ለልደቱ (ለዕረፍቱ) በዓል፣ ከአሴር ወገን ለሆነች ለፋሩኤል ልጅ #ለነቢዪት_ቅድስት_ሐና ለዕረፍቷ በዓል፣ በትሩፉቱ ፍጹም ለሆነ ለታላቅ አረጋዊ ለገዳመ ሲሐቱ #ለአባ_ኤልያስ ለዕረፍት በዓልና ከቊስጥንጥንያ አገር ከነገሥታት ወገን ለነበረች ዓለምን ንቃ ዋሻ ውስጥ ገብታ 11ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ምግቧንም የሰማይ ወፎች ያመጡላት ለነበረችው ለከበረች #ለእመቤት_ቅድስት_አመተ_ክርስቶስ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአመተ_ክርስቶስ_ከሁለቱም_አገልጋዮቿ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

[ ሥ ላ ሴ ያ ስ ጨ ክ ና ሉ ] " አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ " አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም √ የዩቲዩብ ገጻችንን
[  ሥ ላ ሴ   ያ ስ ጨ ክ ና ሉ   ] " አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ  " አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_አገር አርባ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ በአገሩ የነገሡ የተለያዩ አሕዛብ ነገሥታት በጽኑ ሥቃ
+1
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ❤                ❤ #የካቲት ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_አገር አርባ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ በአገሩ የነገሡ የተለያዩ አሕዛብ ነገሥታት በጽኑ ሥቃይ ላሠቃዩት ለከበረ አባት #ለአባ_እለስክድሮስና ለአርባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳስ ለከበረ አባት #ለአባ_ቴዎድሮስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ የሰውን ፊት ሳያይ በበረሀ ለሰባ ዓመት ለኖረ አባ ዕብሎይን ላረጋጋ ለገዳማዊው አባት #ለአባ_አብዱልማስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ #ከአብራቅያ_ከአባዲር፣ #ከአባርያኖስና ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የእስክንድርያ_ሀገር_ሊቀ_ጳጳሳት #አባ_እለእስክንድሮስ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ሦስተኛ ነው። ይህም አባት "ታሮን" በሚባል ገዳም መነኰሰ ትርጓሜውም "የአባቶች ገዳም" ማለት ነው በጌታችንም ፈቃድ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ እርሱ የተማረ አዋቂ ጻድቅ ሰው ነበረና። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ቅድስት አርሴማ ሰማዕት " ጻድቃን ስለአንተ ታመሙ [ መከራን ተቀበሉ ] መከራቸውም ደስታ ሆነላቸው ክብር ይገባቸዋል በተጋድሎአቸው ሰማዕታት በትዕግስታቸውም መንግሥተ ሰማያትን ወረሱ" ቅዱስ ያሬድ √
ቅድስት አርሴማ  ሰማዕት  " ጻድቃን ስለአንተ ታመሙ [ መከራን ተቀበሉ ] መከራቸውም ደስታ ሆነላቸው  ክብር ይገባቸዋል  በተጋድሎአቸው ሰማዕታት  በትዕግስታቸውም መንግሥተ ሰማያትን ወረሱ"       ቅዱስ ያሬድ  √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የካቲት ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን #ጌታችንን_ሽቱ_ለቀባችው_ለማርያም_እንተ ዕፍረት ለዕለፍቷ መታሰቢያ በዓል፣ ለዓለሙ ሁሉ መም
+3
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #የካቲት ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን #ጌታችንን_ሽቱ_ለቀባችው_ለማርያም_እንተ ዕፍረት ለዕለፍቷ መታሰቢያ በዓል፣ ለዓለሙ ሁሉ መምህር ለሆነ ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ አባት #ለአባ_አቡሊዲስ ሥጋው ከባሕር ለወጣበት በዓልና #ለከበሩ_ቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ ለሦስቱ ደናግላን #ለቅድሳት_ቴዎድራ_ቴዎፍና_ቴዎዶክስያና ለእናታቸው #ለቅድስት_አትናስያ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ  ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                  ✝ ✝ ✝ ❤ #ማርያም እንተ ዕፍረት፦ ይችም ቅድስት አስቀድማ ኑሮዋን በዝሙት ያሳለፈች ኃጢኣተኛ ነበረች። እርሷም ጐልማሶችን ወደርሷ ትማርካቸው ዘንድ በየራሱ በሆነ ሽልማትና ጌጥ ትሸለም ነበር። በአንዲትም ዕለት እንደ ልማድዋ ተሸልማ አጊጣ ሽቱም ተቀብታ ፊቷን በመስታዋት ተመለከተች የጉንጯ ቅላትና ደም ግባቷ፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ++++++++++++++++++++++++++++++ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃ
+2
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ++++++++++++++++++++++++++++++ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ የካቲት 5/2016 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁኔታና ቀጣይ የቤት ሥራዎች ላይ ተወያይተዋል። በውይይቱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይን ጨምሮ የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት ተገኝተዋል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #የካቲት ፭ (5) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊያኑ_ጻድቃን_ለአቡነ_አሞኒ ለልደታቸው በዓልና ለልጃቸው #ለአቡነ_ዮሐኒም ለመታሰ
+1
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝             ✝ #የካቲት ፭ (5) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊያኑ_ጻድቃን_ለአቡነ_አሞኒ ለልደታቸው በዓልና ለልጃቸው #ለአቡነ_ዮሐኒም ለመታሰቢያቸው በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #አቡነ_አሞኒ፦ አባታችን የካቲት 5 ቀን አክሱም ውስጥ ሲወለዱ ሰይጣናት የወላጆታቸውን ቤት ከበው በማየታቸው እንደተወለዱ በእጃቸው ቢያመለክቱ በአንድ ጊዜ 60ሰይጣናት ተሸንፈው እንጢስ በነው ጠፍተዋል። አሞኒ ማለት አሸናፊ ማለት ነው። አባ አሞኒ የራስ ፀጉራቸው ልብስ መጎናጸፊያ ሆኖቸው የኖሩ ታላቅና ቀደምት አባት ናቸው። በደመና ተጭነው ኢየሩሳሌም ደብረ ዘይት ድረስ በመሄድ ከአባ ዕብሎይ ጋር ተገናኝተው ብዙ ምሥጢርን፡ አውርተዋል። አባ ዮሐኒንያ ሳደጉት አስተምረው ያሳደጓቸው አባ አሞኒ ናቸው፡፡ የእናቱን ጡት ፈጽሞ ጠብቶ የማያውቀውን የመንፈስ ቅዱስ ልጃቸውን አባ ዮሐኒን እሳቸው እያጫወቱት የታዘዘ አሞራ በክንፎቹ እያለበሰው ቶራ (ሰሳ) እያጠባችው ነው ያደገው፡፡                              √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝ ✝ #የካቲት ፫ (3) ቀን። ✝ እንኳን ለባሕታውያን አለቃ #ኑሯቸውም_የመላእክት_ኑሮ_ለሚመስል ከትሩፋቱም የሃይማኖት ፍሬ ለተገኘ ቅዱሳን መ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ✝                ✝ #የካቲት ፫ (3) ቀን። ✝ እንኳን  ለባሕታውያን አለቃ #ኑሯቸውም_የመላእክት_ኑሮ_ለሚመስል ከትሩፋቱም የሃይማኖት ፍሬ ለተገኘ ቅዱሳን መላእክትም ክብራቸውን ለመሰከሩላቸው፤ በሌላ ቦታ ያሉ ሰዎችን በቃላቸው ብቻ ይፈውሱ ለነበሩ ለከበሩ አባት #ለአባ_ዕብሎይ ለዕረፍት በዓል፣ ተጋዳይ ለሆነ ለመነኰስ ሰይጣን በፈተና ጥሏቸው ለነበሩና በኋላም ምግብ ሳይበሉ ሳር ብቻ እየተመገቡ 30ዓመት ለኖሩት እግዚአብሔርም ይቅር ብሏቸው ስለእርሳቸው ብሎ በድርቅ ወቅት ዝናብ ላዘነበላቸው #ለአባ_ያዕቆብ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት #ለሶርያዊ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ለሥጋው_ፍልሰት በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                              ✝ ✝ ✝ ✝ በዚችም ቀን #የሶርያዊ_ቅዱስ_ኤፍሬም_የሥጋው_ፍልሰት_ሆነ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #የካቲት ፩ (1) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮያዊያኑ_ጻድቅ ኤርትራ አገር የሚገኘው #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_ጽጌ_ሰፍኣ ለመሰረቱት ዘጠ
+2
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝               ✝ #የካቲት ፩ (1) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮያዊያኑ_ጻድቅ ኤርትራ አገር የሚገኘው #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_ጽጌ_ሰፍኣ ለመሰረቱት ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ደቀ መዝሙርቶቻቸው (ልጆቻቸውን) ከሰማይ ስንዴና ወርቅ በማዝነብ ውሃውን በመባረክ ወይን አድርገው ይመግባቸው ለነበሩ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_እንድርያስ_ዘደብረ_ጽጌ_ሰፍኣ ለዕረፍት በዓል፣ ለመካኖች ልዩ ቃል ኪዳን ለተሰጣቸው ለታላቁ አባት ለሰማዕቱ #ለአቡነ_ሲኖዳ ለፍልሠተ ዐፅማቸው በዓል በሰላም አደረሰን።                                ✝ ✝ ✝ ✝ #አቡነ_እንድርያስ፦ የእናታቸው ስም ቅድስት ዓመተ መንፈስ ቅዱስ የአባታቸው ስም ቅዱስ ዘአማኑኤል ይባላል። የተወለዱትም ትግራ እንደርታ አካባቢ ነው። እናትና አባታቸው ልጅ ስሌላቸው ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እየጸልዩ እናታቸውም "አንተ ደስ የሚያሰኝ ልጅ ካልሰጠኸኝ ማኅፀኔን ዝጋ" ይሉ ነበር። የእመቤታችንንም ዝክር በየወሩ ይዘክሩ ነበር። እመቤታችንም አንድ ቀን ተገልጻ "ደስ የሚያሰኝ ልጅ ትወልዳላችሁ የሚወለደውም እኔ በተወለድኩበት ቀን ነው" አለቻቸው √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ዛሬ አሜሪካ ገብተዋል። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አሜሪካ ሲደርሱ አቀባበ
+2
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ዛሬ አሜሪካ ገብተዋል። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አሜሪካ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸው። ማክሰኞ ጥር 28 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ የነበራቸውን አገልግሎት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱም በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከደረሱ በኃላ ወደ #ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ዛሬ ወደ አሜሪካ ለመመለስ ተገደዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለከተው የመንግስት አካል የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ  የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ  መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ  እንዲፈቀድላቸው እንዲያደርግ ብትጠይቅም የመፍትሄ ምላሽ ባለመገኘቱ ወደ መጡበት አሜሪካ ተመልሰዋል። መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ የሰጠው ማብራሪያ የሌለ ሲሆን በቀጣይ የሚሰጠው ማብራሪያ ካለ ተከታትለን እናቀርባለን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ጥር ፴ (30) ቀን። ✝ እንኳን #ለማኅበረ_ዴጔ_ለሦስት_ሺህ_ጻድቃን እንደ ቅዱሳን ኄኖክና ዕዝራ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝             ✝ #ጥር ፴ (30) ቀን። ✝ እንኳን #ለማኅበረ_ዴጔ_ለሦስት_ሺህ_ጻድቃን እንደ ቅዱሳን ኄኖክና ዕዝራ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው፣ ለከበሩ ደናግል #ለቅድስት_ሶፍያ_ልጆች ለቅድሳት #ለጲስጢስ_ለአላጲስና_ለአጋጲስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ስሙ መርቅያኖስ ለሚባል ለጣዖት ለሚሰግድ ለሮሜ ንጉሥ ልጅ ለከበረች #ለቅድስት_ኦርኒ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል፣ ለከበረች #ቅድስት_ጤቅላ ከእርሷ ጋር ከሚኖሩ አራት ደናግል ጋር ፎላ በሚባል ኃጥእ ቄስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋዳይ ለሆነ ለመነኰስ ለከበረ #አባ_አክርስጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለመለኮትን ነገር ለሚናገር ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመታሰቢያ በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ አገር አርባ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ሚናስ ዕረፍትና #ከቅድስት_ኦርኒ_ማኅበር ከሆኑ #ከዐሥራ_ሦስት_ሺህ_ሰዎች በሰማዕትነት  ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።         √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝ ✝ #ጥር ፳፱ 29 ቀን ✝ እንኳን #ጌታችን_አምላካች_መድኀኒታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል ተገልጦ በደሃ ሰው ተመስሎ ከማኅበረ ዴጔ ጋር በ
+1
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ✝             ✝ #ጥር ፳፱ 29 ቀን ✝ እንኳን #ጌታችን_አምላካች_መድኀኒታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል ተገልጦ በደሃ ሰው ተመስሎ ከማኅበረ ዴጔ ጋር በመካከላቸውም ተገኝቶ የጽዋ ማኅበር እየጠጣ ተራው ደርሶ ተዓምር አድርጎ አምላክነቱ ለገለጠበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣  የስሟ ትርጓሜ መጻተኛ ለሆነ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ በራእይ ለተገለጠላትና ከከበሩ ነገሥታት ወገን ለሆነችው ዓለምን ንቃ በመመንኰስ በምትተኛ ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ እየተኛችና ጥሬ ባቄላን ብቻ እየተመገበች በታላቅ ተጋድሎ ለኖረችው ለከበረች #ቅድስት_አክሳኒ ለዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ፣ ተጋዳይ ለሆነ በበረሃ ውስጥ የሞተ ሰው ራስ ቅል አግኝተው የራስ ቅሉን ላነጋገሩና ሥራውን መርምረው ለተረዱ በኋላም አማልደውት ምሕረትን ላሰጡት #አባ_እስጢፍኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከድንግል እመቤታችን ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከተወለደበት #ከልደቱ_በዓለ_ወልድ_ወራዊ መታሰቢያ፣ ከመስተጋድል ከከበረ #ሰማዕት_ከሰርያኮስ ከመታሰቢያው፣                 √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል ! ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል። ብፁዕነታቸው ከደቂቃዎች በፊት ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል " አሁን አሳፍረውኝ ተመለስኩ ወደ አሜሪካ ወደመጣሁበት መለሱኝ  ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ " ብለዋል። ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃላቸውን በሰጡበት ወቅት አውሮፕላኑ ሊነሳ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ የሚደረግበት ምክንያት ምንድነው ? ተብለው ተጠይቀው  ብፅዕነታቸው  " በቃ ግሪን ካርዱን ብቻ ነው የምንፈልገው እኛ ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም ግሪንካርድ ብቻ ነው የምንፈልገው ብለው ወሰዱ በሩን ዘጉ !! " ሲሉ ተናግረዋል። ይህን ያደረጉት የደህንነት ሰዎች ናቸው ብለዋል። ብፅዕነታቸው ወደ አውሮፕላን እንዲገቡ ከመደረጋቸው በፊት ውጭ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር ተናግረው አንድ የኢሚግሬሽን ሰው " የማውቀው ነገር የለም ግሪንካርዱ ትክክል አይደለም " እንዳላቸውና እሳቸውን ግሪንካርዱ ገና 3 ዓመት እንደሚቀረው እንደነገሩት አስረድተዋል። ይህን ሲያስረዱ ከግለሰቡ መልስ እንዳልተሰጣቸውና " ሌሎች ሰዎችንም #ዲፖርት እያደረግን ነው " በማለት እንደነገራቸው ገልጸዋል። ብፅዕነታቸው የአሜሪካ ፓስፖርት እንዳላቸው ገልጸው  " እሱን ምንም ለማድረግ ስላልቻሉ ግሪንካርድ እንወስዳለን በማለት ወስደዋል " ሲሉ ተናግረዋል። ከሳምንታት በፊት ለአገልግሎት ከሀገር ሲወጡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎችም " ሊያስቀሩህ ይችላሉ " የሚል ነገር ሰምተው እንደነገሯቸው ነገር ግን በአሜሪካ የያዙትን አገልግሎት መተው ስላልፈለጉ ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ገልጸዋል። ብፅዕነታቸው ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት " ኮበለሉ " የሚሉ መረጃዎች ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል በኃላም ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ በህጋዊ መንገድ በቤተክርስቲያን እውቅና ከሀገር እንደወጡ የሚደበቁም ሆነ የሚኮበልሉ የወንጀል ሰው እንዳልሆኑ አሳውቃ ነበር። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨር
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል። ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል። ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝ ✝ #ጥር ፳፰ (28) ቀን። ✝ እንኳን #ለአምላካች_ለቅዱስ_አማኑኤል ተአምራት አድርጎ አምስት እንጀራንና ሁለት ዓሣን አበርክቶ ሕፃናትና ሴ
+1
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝               ✝ #ጥር ፳፰ (28) ቀን። ✝ እንኳን #ለአምላካች_ለቅዱስ_አማኑኤል ተአምራት አድርጎ አምስት እንጀራንና ሁለት ዓሣን አበርክቶ ሕፃናትና ሴቶች ሳይቆጠሩ አምስት ሺህ (አምስት የገብያ ሕዝብ ለመገበበት (ላጠገበበት) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ኪራኮስ ከሚባል አገር ስሟ አክሮስያ የምትባል ለመበለት ልጅ ሰባት ጊዜ ታላላቅ አሠቃቂ መከራዎችን በመቀበል ሰማዕትነቱን ለፈጸመው ለከበረ #ለቅዱስ_ቀሌምንጦስ ለዕረፍቱ በዓል፣ ፍዩም ከሚባል ሀገር ለሆነ ሰይጣን ይዞ በራሱ ጠጉር አሥሮ ለቀጣው ለከበረ መነኰስ #ለአባ_አካውህ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና፣ ለከበረ ለአይሁዳዊ ለማኅው ልጅ እመቤታችን ከእሳት ውስጥ አውጥታ ላዳነችው በዕረፍቱም ጊዜ "በሦስተኛው ቀን በሦስት ሰዓት ወደኔ ትመጣለህና ደስ ይበልህ" ላለችው #ለቅዱስ_ዮሴፍ ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_አባ_አካውህ_ማኅበር ከስምንት መቶ ሰማዕታት፣ ከአባቶቻችን #ከቅዱሳን_አብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ፣ #ከሠልስቱ_ደቂቅና_ከታቤላ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝               ✝ #ጥር ፳፯ (27) ቀን። ✝ እንኳን #ሳፍራ_ለሚባል_ለመልአክ_ለቅዱስ_ሱርያል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ በሞት ፋንታ ለተሰውረው #ለነቢዩ_ቅዱስ_ኄኖክ ለዕርገቱ መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ሐዋርያ #ለቅዱስ_ጢሞቴዎስ ከኤፌሶን አገር ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ለሥጋው ፍልሰት በዓል፣ ከግብጽ ደቡብ ከታችኛዪቱ ምስር አውራጃ በብኑዲ ከምትባል መንደር ለሆነ ለከበረ #ቅዱስ_ሰራብዮን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ከታናሽነቱ ድንግል ለሆነ እግዚአብሔርን ለሚወድ ለድኆችና ለችግረኞች ለሚመጸውት ይህንንም ዓለም ንቆ ለተወ በእሳት ተቃጥሎ ሰማዕትነት ለተቀበለ ለከበረ #ቅዱስ_ቢፋሞን ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቸሩ_መድኃኔዓለም_ከስቅለቱ ከወራዊ መታሰቢያ፣ #ከሰማዕታት_ትውፍሎን_ከዮስና_ከሰርኒስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ✝ በዚች ቀን #ሳፍራ_የሚባል_የመልአክ_ሱርያል በዓል ነው እርሱም #ከነቢይ_እዝራ ጋር የኖረ የተሠወረ ምሥጢርንም የገለጠለት ነው እርሱም ስለ ሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር የሚለምን ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሱርያል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️ በጉጉት የምንጠብቀው ታላቁ የምስጋና መርሀግብራችን የፊታችን እሑድ እናከብራለን ሁላችሁም የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ : አለን!!! በእ
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️ በጉጉት የምንጠብቀው ታላቁ የምስጋና መርሀግብራችን የፊታችን እሑድ እናከብራለን ሁላችሁም የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ : አለን!!! በእለቱ ሁላችንም ጥምቀትን በክብር አሳልፎ ለዚህች ቀን ያደረሰንን አምላካችን እግዚአብሔርን ለማመስገን ዝግጁ ሆነን እንገኝ። ፈጣሪያችን ለዚህች ቀን ያድርሰን አሜን!!! ➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕