cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ጊዮናዊነት

💥 አማራ የለመለመች አረንጓዴ መሬት ነች፡፡ ♠♥ "ለማበድ እንኳን ሀገር ያስፈልጋል፡፡" መጋቢ ሐዲስ እሸቱ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
583
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በወለጋ  ‼ …ህፃን… አራስ… ነፍሰጡር ሴት… አረጋዊ ሽማግሌ… ካህን… ሼክ አይመረጥም። ወንድም ሴትም ዐማራ ከሆነ ይረፈረፋል። ይረሸናል። ይታረዳል… ይገደላል። በምዕራብ ወለጋ የተገኘውን ዐማራ ሁሉ እረድ ነው የተባሉት አሉ ገዳዮቹ። ጨፍጭፈው ነው የተባሉት። ዐማሮቹ ከወለጋ በህይወት እንዳይወጡ የተፈረደባቸውም ይመስላል። … ጎበዝ ጉዳዩ ከምታስቡት እና ከምትገምቱት በላይ ነው። በወለጋ የሚኖር የዐማራ ዘርና አማርኛ ተናጋሪ የሆነ በሙሉ ዐቢይ አሕመድ በሚመራት ሀገርና በእነ ሽመልስ አብዲሳ ክልል ከሩዋንዳ በበለጠ እንዲያውም ከዚያ በከፋም ሁናቴ ዐማራው እየተጨፈጨፈ ነው። በዚህ አያያዝ በወለጋ ለዘር እንኳ የሚተርፍ ዐማራ የሚገኝም አይመስልም ነው እየተባለ ያለው። … በወለጋ የቆሰለ ዐማራና የሞተ የዐማራ ሬሳ ማንሣትም ያስገድላል። አስከሬን መቅበርም ክልክል ነው። አጋጣሚውንና ዕድሉን አግኝቶ ቆስሎ ህክምና ጣቢያ የደረሰ ዐማራ ካለ ዐማራ የሚያክም ሃኪም ራሱ እርምጃ ስለሚወሰድበት ዐማራ በይፋ ህክምና መከልከሉ ነው ነው የተነገረው። የሃገሬው ሰው ባለ ሃገር ነህ የተባለው ኦሮሞው ሰብዓዊነት ተሰምቶት ለዐማራ ወንድሙ አዝኖ ቢገኝ እንኳ እሱ ራሱ የዐማራ ዕጣ ነው የሚደርስበት። ይገደላል። የዐማራ የሆነው ንብረት በሙሉ ይዘረፋል። ይቃጠላል። ከብቱ እንስሳው እንደ ጉድ ይነዳበታል። ደግሞም የክፋቱ ክፋት ሸሽቶ ከወለጋ ወደ ዐማራም ሆነ ወደ ሌሎች ክልል እንዲሰደድ አይፈቀድለትም። መሰደድም አይችልም። አይፈቀድለትም። ክልክል ነው። ዘግናኝ ነው። … እንደሚታየው አዲሱ የዐቢይ አሕመድ መንግሥት ለአፍቃሬ ኦነጎች፣ ለኦነግ አመራሮች፣ ለፀረ ዐማራና ለፀረ ኦርቶዶክስ ኃይሎች በክልሎችም በፌደራልም ሥልጣን አድሎ በአዲስ መልክ ሥራ ጀምሯል። ኦነግ ሸኔ የኦህዴድኦነግ የኦሮሚያ ብልጽግና ኢ-መደበኛ ጦር ሲሆን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ደግሞ መደበኛው የዐቢይ ሽመልስ ጦር ነው። ሁለቱም ጦሮች አሁን በግላጭ ዐማሮቹን ከክልሉ በሃላል እያጸዳ ነው የሚገኙት። የሽመልስ አብዲሳው የኦሮሚያ ክልል ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ከሆን ሌሎች ክልሎች እንኳ ገብተው እንዲረዱት እንዲያግዙት ማድረግ ይችል ነበር። ነገር ግን ይህን ማድረግ አይፈልጉም። የግፍ ዜናውም ወጥቶ ዓለም እንዲያውቀውና እንዲሰማውም አይፈልጉም። … ዐማራ በተለየ ሁኔታ ውስብስብ ባልሆነ ዘዴ በቀላል ቀመር ከምድረ ኢትዮጵያ በመኖሪያ ቀዬውም፣ ከመኖሪያ ቀዬው ውጪም በግልፅ በጅምላ እየተጨፈጨፈ ነው። ይሄን የሚናገርና የሚያወግዝ ሰው አታገኝም። የዐማራ ቴሌቭዥን ሰሜን ጎንደር ጭና ተክለሃይማኖት ትግሬዎቹ በዐማሮቹ ላይ ፈጸሙ ያሉትን ጭፍጨፋ ትናንት አይቼው ስታመም ነው ውዬ ያደርኩት። አሁን በትግሬዎቹ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የሰሜን ወሎ ዐማራ በምን ዓይነት ሁናቴ ላይ እንዳለ አይታወቅም። በራብ… በበሽታ… በጦርነት ዐማራው እየረገፈ ነው። ከላይ ትህነግ… ከጎን ሱዳን… በመሃል ደግሞ የዐቢይ ሽመልስ ኢ-መደበኛ ጦር ዐማሮቹን እየፈጇቸው ነው። … ከጥቃት ቀጠናው ውጪ ያለው ዐማራ ደግሞ የሚያደርግ የሚሠራው ጠፍቶታል። የዐማራ ብልጽግና ተብዬው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን እየዞረ ሲጎበኝ ይውላል። ዳያስጶራ ዐማራው ገሚሱ ለዐቢይ አሕመድ በአለ ሲመት ደሙን ይሰጣል። ገሚሱ ደግሞ ተወዛግቦ ዝም ጭጭ ብሏል። የሚገርመው ደግሞ እስከ ምርጫው ድረስ ዋይዋይ ብለው በዐማራው ስም ሥልጣን ያገኙት ጀማሪ ፖለቲከኞች በሙሉ (ዐብን) ሳይቀር ውሾን ያነሣ ዓይነት ዝምታን መርጠዋል። ለዐማራ ከፈጣሪ በቀር ከዚህ እልቂት የሚታደገው ያለም አልመስልህ እያለኝ መጥቷል። • በቀጣይ በወለጋ ዐማሮቹ በምን ዓይነት ሁናቴ እንደሚገደሉ ከሥፍራው የደረሰኝን እጽፍላችኋለሁ። ይሄን ጭካኔ ሰይጣን ራሱ በፍፁም እንደማያውቀው ግን አፌን ሞልቼ መከራከር ሁላ እችላለሁ። ከምታስቡት በላይ ዘግናኝ ነው። ምን ቢሆን ትላላችሁ። እስቲ ሃሳባችሁን አካፍሉን። • እግዚአብሔር ይድረስላችሁ ወገኖቼ። ኡፍፍፍፍ…
Hammasini ko'rsatish...
10.04 KB
መመሎ ለሃ ከተማ፣ በፕሮቴስታንቶቹ ባለሥልጣናት ትእዛዝ ከባሕረ ጥምቀቱ ስፍራ ተነቅሎ በፖሊስ ጣቢያ ከመጸዳጃ ቤት ደጃፍ የተጣለው የክርስቶስ መስቀል ነው። ይሄም ይመዝገብ።
Hammasini ko'rsatish...
“ባለቤቴን አርደው በደሙ ታጠቡ” የሻሸመኔ ግፍ ነው *~★★★~* • በዚህ ጉዳይ በኋላ በደንብ አድምተን እናወራበታል። ጠብቁኝ። #ETHIOPIA | ~ በደቡብ ክልል በጋሙጎፋ በመሎለሃ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች የፕሮቴስታንት ባለሥልጣናት በጅምላ አስረው ወደ ዘብጥያ እያወረዱዋቸው ነው። በኋላ በሰፊው እናወጋለን። ••• ይህ አጸያፊ፣ ነውረኛና ዘግናኝ ግፍ የተፈጸመው ጥንት አይደለም። በሌላ ክፍለ ዓለምም አይደለም። እዚያው በሀገረ ኢትዮጵያ፣ ዓለም አቀፍ ኃያላን ሃገራት ሙሉ ድጋፋቸውን በሚሰጡት፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ይቀጣም ዘንድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው ፈርኦኑ፣ ልበደንዳናው፣ አፈ ቅቤ ልበ ጩቤው እና ናቡከደነጾሩ የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በሚመራት ኢትዮጵያ፣ ኦሮሚያ በተባለች ጀርመናዊ ስም በሰጣት ክፍለ ሃገር ሻሸመኔ በተባለ ከተማ ውስጥ ሰኔ243/2012 ዓም የተፈጸመ ድርጊት ነው። ( ለዘንዶው ግብር መሆኑ ነው) ••• እኚህ ባላቸውን ፊታቸው አርደው በባላቸው ደም አራጆቹ ሲታጠቡ ያዩት እናት ይህን ምስክርነታቸውን የሰጡት ትናንት መስከረም 24/2012 ዓም በዚያው በሻሸመኔ ከተማ በታቦተ ሕጉ ፊት፣ በሊቃነ ጳጳሳቱና በጉባኤው ሁሉ ፊት ነበር። የሚገርመው መሄጃም መድረሻም የላቸውም። በገዛ ሃገራቸው የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በሽመልስ አብዲሳ አስተዳደር በኩል፣ በለማ መገርሳ ጦር ፊት የፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት ነው። ( አምላክ ሆይ አፎቱን ወደ ራሳቸው መልስ፣ እንዴት እንደሚዘገንን በቤታቸው አሳያቸው።) አሜን። ••• አሁን እንደማየው ከሆነ ኦርቶዶክሳዊነት ዓለም አቀፍ ዘመቻና ከመናፍስቱ ዓለም ኃይለኛ ጦርነት እንደተከፈተበት ነው። የግብጽ ኦርቶዶክስ መከራዋን ማየት ከጀመረች ትንሽ ቆየች። ከካቶሊኮቹ ጋር መሞዳመድ ከጀመረች በኋላ ግን አሁን ለጥቂት ጊዜ ያረፈች ይመስላል። ዱላውም ቀንሶላታል። የሶሪያ ኦርቶዶክስ ወድማለች። ጳጳሳቶቿ፣ ካህናቶቿና ምእመናኖቿ ከነ አብያተ ክርስቲያናቶቻቸው ወድመዋል፣ ታርደዋል፣ በእሳትምተቃጥለዋል፣ ተሰደዋል። የህንድ ኦርቶዶክስም እንደዚሁ ፍዳዋን እየበላች ነው። ••• የተቀሩት የአርመንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ። የኤርትራ ኦርቶዶክስ አዲስ ገቢ ናት። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአርመንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሶሪያና ከግብጽ አንጻር በአንጻራዊነት ምንም እንኳ መከራ ቢኖርባቸውም እግዚአብሔር ይመስገን የሚባልለት ሰላምም ነበራቸው። የግራኝ ኢትዮጵያን፣ የቱርክ አርመንያን ማውደምም ሳይዘነጋ ማለት ነው። ••• አሁን ግን የአርመኒያ ቤተ ክርስቲያንም ፈተና ላይ ናት። ከእሳላማዊው የአዘርባጃን መንግሥት ጋር ጦርነት ላይ ናት። ከሁለቱም ወገን ከአንድ ሺ ሰው በላይ ተገድሏል። የአርመንያ መንግሥት በሃገሪቱ ወንድ የሆነና ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሁሉ ሃገሩን ከእስላማዊው ወረራ ለማዳን በተጠንቀቅ ይቁም ብሏል። ዜናው ግን በአውሬው ዓለም አይዘገብም። ምክንያቱም የሚገደሉት አርመኖች ሃይማኖታቸው ኦርቶዶክስ ነውና። ••• በኢትዮጵያም ዳግማዊ ግራኝ የተሰኘው ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የአገዛዙን ቅቡልነት ለማረጋገጥ ሲል በቅድሚያ የወሰደው እርምጃ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አጋድሞ በማረድ ለአለቆቹ መስዋዕት አድርጎ ማቅረብን ነበር። በዘመነ ዐቢይ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፣ ካህናትና ምእመናን ታረዱ፣ ሃብት ንብረታቸውም እንዲወድም ተደረገ። ተሰደዱ፣ ተፈናቀሉ። የወሐቢይ እስላሞችና አክራሪ ፕሮዎች ደስታና ፈንጠዚያ ላይም ናቸው። ይሄም ታሪክ ነውና ተጽፏል። ••• መከራው ቀጥሏል። በዘመነ ዐቢይ አሕመድ የአደባባይ በዓላት ተከልክለዋል። በኦሮሚያ ክልል ሙስሊምና ፕሮቴስታንት የዋቄፈታም አማኝ የሆኑ ባለሥልጣናት የኦርቶዶክሳውያንን የአደባባይ በዓላት በይፋ ከልክለዋል። የመስቀልና የጥምቀት ማክበሪያ አደባባዮቻችንንም በይፋ መውረስ ጀምረዋል። ድርጊቱን የሚቃወሙ ምእመናንም በገንዘብና የረጅም ጊዜ እስርም ማከናነብ ጀምረዋል። ደቡብና ኦሮሚያ ፕሮቴስታንቶች ክልላቸውን ከኦርቶዶክሳውያን ነጻ ያደርጉ ዘንድ ከማዕከላዊው መንግሥት ያልተጻፈ ዓዋጅ ወጥቶ በግልጽ ተፈጻሚ እየሆነ መጥቷል። ከፕሮሙስሊሙ ዐቢይ አሕመድ እውቅና ውጪ አንዳች እንዳይደርግ ሁሉም ይወቅ። ••• ቀጣዩ ጃንሜዳ ነው። መስቀል አደባባይ በኢሬቻ፣ በዋቀ ጉራቻ እንዲዋጥ ተደርጓል። የታቦታት ማደሪያ የሆነው ጃንሜዳም በሰገራ፣ በሽንት፣ በመጥፎ ጠረን እንዲግማማ፣ እንዲጨቀይ ተደርጓል። ይሄም የሆነው በዐቢይ አሕመድ ትእዛዝ፣ በታከለ ኡማ አስፈጻሚነት ነበር። ታኬ ሲሄድ አዴ የየክታለች። መቼም በዚህ ዘመን እንደ ኦርቶዶክሳዊነት የተናቀ ማንም የለም። ••• እና እኛስ ምን እናድርግ? እስቲ ወደ ኋላ ላይ እንተለመደው በተለመደው ሰዓት … በኢትዮጵያ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በጀርመን ከምሽቱ 18:00 ሰዓት በዱባይ ከምሽቱ 8:00 ሰዓት በአማሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ የሰዓት አቆጣጠር ልክ ከቀኑ 12:00 ሰዓት ላይ ምሳ ሰዓት ሲሆን ማለት ነው በተለመደው እና :https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele በተሰኘው የዩቲዩብ ቻናሌ በኩል “ከብዙ ቁጭት፣ እልህና የምስራችም ጋር” ከተፍ ብዬ ልመጣ ነኝ። እናም ጎዶኞቼ፣ ወዳጆቼም ሁላችሁ ተዘጋጅታችሁ፣ ሰንዳ፣ ሰንዳም፣ ሰብሰብም ብላችሁ ጠብቁኝ። ••• ነጭጯንማ ሳንሳቀቅ እናዋጋለን። ••• ሻሎም ! ሰላም ! ዘመድኩን በቀለ ነኝ። መስከረም 25/2013 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ።
Hammasini ko'rsatish...

በ4 ደቂቃ ተሳክቷል። አ ከ ተ መ *~★★~* • ሃይ አቦ ምንድነው ሳ! በፌስቡክህ #SHARE አድርገዋ ሃይ። ምን አፍጠህ ታየኛለህ። እንደ ጅብራ ከፊቴ አትገተርብኛ። ሃይ ተንቀሳቀስ አቦ። #ETHIOPIA | ~ ልክ እንደ ቴሌግራሙም ዩቲዩብም ሪከርዱ ተሰብሯል። • በዜግነት ኢትዮጵያዊ፣ በሃይማኖት ኦርቶዶክሳዊ መሆን ጥቅሙ ይሄው ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊም ኦርቶዶክሳዊም ከሆንክ ታሸንፋለህ። ከኑመጋ ዱቢን። ••• ይህ የሆነው በ4 ደቂቃ ብቻ ነው። ይህን ያደረገው ደግሞ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እኔም እየሆነ ባለው ነገር እጄን በአፌ ጭኜ ጮጋ ከማለት በቀር ሌላ ምንም ቃላት የለኝም። ••• ኦቦሌሶ በዩቲዩብ ገቢ ማግኘት ለመጀመር እችል ዘንድ በYouTube Monetization ከሚያስፈልጉኝ ማጣርያዎች መካከል አንዱ 1ሺ ሰብስክራይበርን ማግኘት ነው አሉ። እሱ ነገሩ ነው አድካሚም ይባላል። ለዚህ ነው ብዙ ሰዎች ሰብስክራይብ አድርጉን፣ በማርያም፣ በሚካኤል፣ በገብርኤል እያሉ ዋይዋይ ሲሉ የሚውሉት። ••• ኦቦሌሶ እኔ ዘመዴ የድንግል አሽከር፣ ባለማዕተቡ ግን ይሄን በዩቲዩቡ ዓለም አድካሚና እንደ ራስደጀን፣ ኪሊማንጃሮና ሂማልያ ተራራ የሚቆጠረውን የየዩቲዩብ መንደር መንገድ እኔ ዘመዴ የድንግል አሽከር በ4 ደቂቃ ውስጥ አሟልቼ ከተራራው አናት ላይ ተቀምጫለሁ። ይሄ ሁሉ የሆነው ታዲያ በማን ይመስልሃል? በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በድንግል ማርያም አማላጅነት፣ በእናንተ በባለ ማዕተቦቹ የእምዬ ተዋሕዶ ልጆች መልካም ፈቃድና ትብብር ነው። ኢንዴዢያ ነው። አሁን ለእኔ 2350 SUBSCRIBE ያደረጉ ባለማዕተብ የእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ይታዩኛል። ደግሞ ለሰብስክራይብ ቱ ሞተናታላ !! ገና ሚልዮኖች ይከታተሉናል። ይሄ እንግዲህ ገና መጀመሪያው ነው። ገና ገና ምኑ ተነካና ይቀጥላል። ••• https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele/?sub_confirmation=1 ሰብስክራይብ የማድረጉ ቻሌንጅም ይቀጥላል። ••• ዛሬ ሰኔ 6 በዓለ ኢየሱስና ቅድስት አርሴማም አይደሉ? አዎ እየቆየሁ እያየሁ የጎደለ ካለ እጨምርላችኋለሁ። እስከዚያው ••• ሻሎም ! ሰላም ! ዘመድኩን በቀለ ነኝ። ሰኔ 6/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ።
Hammasini ko'rsatish...

ግራአጋቢው የኮሮና ጠባይ !! *~★★~* #ETHIOPIA | ~ እኔምለው ጤፍ ግን ስንት ገባ ? ••• ቀደም ባለው ወራት አንድ በኮሮና የተያዘ ሰው ተገኘ ተብሎ ዜናው ወሬው ከተሰማ ሀገር ሙሉ ዝግ ይሆን ነበር። በሰማይም፣ በየብስም፣ በባህርም እንቅስቃሴ አይኖርም ነበር። ጦር ሰራዊት አየር ሀይል፣ ምድር ጦር በተጠንቀቅ ይቆም ነበር። ነበር ነው ያልኩት። ••• የሰው ልጅ ከቤቱ እንዳይወጣ፣ በአደባባይ እንዳይታይ፣ እጁን በሳሙና እንዲታጠብ፣ ሳኒታይዘር እንደ እምነት እንዲቀባ፣ እንዲተሻሽ ይደረግም ነበር። በግድም፣ በዱላ በጥፊም ከቤቱ ይቀመጥ ዘንድ ይታዘዝ ነበር። አፍህን ሸፍን፣ ርቀትህንም ጠብቅ ትእዛዙ ገራሚ ነበር። ••• ትምህርት ቤቶች ይዘጉ፣ ትራንስፖርት ይጠረቀም፣ ሆተል፣ ኪዮስክ፣ መዝናኛ፣ መገናኛው ሁሉ ይጠረቀም ነበር። ( በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤት እስከአሁን ዝግ ነው። ቡናቤት ግን ለአዲስአበባ ፖሊስ የቀን ገቢውን በጉቦ መልክ እያካፈለ እስከአሁን ክፍት ናቸው አሉ። ፖሊሶች የአዲስ አበባ ቡናቤቶችን በየወረዳው ተከፋፍለው የቀን ገቢ ይከፋፈላሉ አሉ። ደካማ መንግሥት መገለጫው ፖሊሱ ሌባና ያገኘውን ወጋሪ፣ ቀማኛ ይሆናል። ) ••• በቀደመው ወራት የኮሮና ሟቾች የዜናቸው ብዛት ለሰሚው ያስደነግጥ ነበር። የሟቾች ቀብራቸው ባይታይም የሟቾቹ ቁጥራቸውግን አስደንጋጭ ነበር። የኦሎምፒክ ውድድር ይመስል ነበር። ቻይና አንደኛ፣ ጣልያን አንደኛ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ አንደኛ 50 ሺ፣ መቶ፣ ሺ ሲባል ለሰሚው ያስደነግጥ ነበር። በሽታው አለ። የሞቱም፣ የታመሙም፣ የዳኑም አሉ። ነገር ግን ኡን ምንተገኝቶ ይሆን? ቀዝቀዝ ያሉት እነ አማሪካ። ••• ጸሎቱም ልዩ ነበር። እንባ የተቀላቀለበት፣ መንበርከክ ያለበት፣ ደረት እየተደቃ፣ እየወደቀ እየተነሣ ጸሎት ይደረግ ነበር። ቴሌቭዥን ሬድዮኑ ሁሉ ጸሎት፣ ንስሐ ያውጅ ነበር። ቤተሰብ ከመኝታ በፊት አደግድጎ ለጸሎት ይቆም ነበር። ያው ነበር ነው እንግዲህ። አሁንስ? ••• በአማሪካ ሰዉ ከቤቱ ተቀምጦ ይነገር የነበረው የሞት መርዶ አሁን ሰዉ ለሰልፍ ከቤት ወደ ደጅ ወጠቶ በደጅ ውሎ እያደረ፣ ከፖሊስ ጋር ሲተሻሽ፣ ሲተቃቀፍ ውሎ እያደረ፣ የሟች ዜና መጥፋቱ፣ የኮሮና ዜና ቁጥሩ መቀነሱ፣ ጭራሽ ዜናው ያለመኖሩን ስታይ የሆነ ነገር ጠርጥር ጠርጥር ያሰኝሃል። መድኃኒቱ ሰልፍ ነበር እንዴ? ሆሆይ!! ••• በኢትዮጵያም እንደዚያው ነው። የቀደመው ፍርሃት ጠፍቷል። የቀደመውም የሚድያ የጸሎት መርሀግብርም በወሀቢይ እስላም ድንቁርናና ጥጋብ ሌሎች ሃይማኖቶችን በስብከት ስም በመሳደቡ ምክንያት አሁን ቆሟል፣ ተቋርጧል። ይቅርታም አልጠይቅም ብሎ ሁሉን ነገር እኔ ከሞትክ ሰርዶ አይብቀል ብሎ አፈር ከደቼ አብልቶታል። ••• በኮሮና የተያዙ ሰዎች የሞት ቁጥር በዜና ሲነገር እያየን ነው። ቁጥሩ በአዲስ አበባ ከፍ ብሏል። አሻቅቧል። ሟቾቹ በቁማቸው ሳይመረመሩ አስከሬናቸው እየተመረመረ በኮሮና የመያዛቸው ዜና መነገሩ ደግሞ የበለጠ አስቂኝ፣ አስገራሚም ነገር ሆኗል። ይታያችሁ አስከሬን መርምረህ ሀገር ምድሩን ስታሸማቅቅ። በቁም ሳትመረምር አስከሬን እየመረመረች መርዶ የምታረዳ ብቸኛ የምድራችን ጉደኛ ሀገርም ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አትቀርም። ••• ደግሞም ደግሞ የታከለ ኡማን አፉን ሳይሸፍን በድፍረት በከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ ስታይ፣ የዐቢይ አሕመድን 5ቢልዮን ችግኝ ትከሉ ማለትን ስታይ፣ የህወሓትን ማንአባቱ ያገባዋል? ምርጫ በክልሌ አደርጋለሁ የምን ኮረና ነው ማለቷን፣ እስቲ የሚናገረኝን አያለሁ ማለቷን ስታይ፣ ( ለምርጫ መስፈጸሚያ ብሩ እንኳን አላት። አይቸግራትም። በኮንቴነር አይደል እንዴ የምታስቀምጠው። ብሩ ከተቀየረ ነው ህወሓት የምትከስረው። እንጂ አሁን እንኳ በፈረንካ በኩል ችግር የለባትም።) እናም ይሄን ይሄን ስታይ ኮረና የለም እንዴ? ትልና ጠርጥር ጠርጥር ያሰኝሃል። ••• እዚህ ባለሁበት በሀገረ ጀርመን ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በቀር ሁሉ ነገር እንደ ድሮው ነው። መስክ የሚደረገው እንኳ ትራንስፖርትና ሱፐር ማርኬት ሲገባ ብቻ ነው። በባለፈው ሳምንት ከአንድ ጓደኛዬ ጋር በምንኖርበት ከተማ ወደ አንዲት ፒዛ ቤት ገብተን ነበር። እናም ሁሉም ነገር እንደድሮው ነው። ወይ ኮሮና። ••• ለማንኛውም በአማሪካ፣ በአውሮጳ፣ በካናዳ ከባድ ሰልፎች ተደርገዋል። በአሜሪካ እስከአሁንም ሰልፉ አልቆመም። የኮሮና ዜና ግን ቆሟል? በኢትዮጵያ በኮሮና የሚያዘው ሰው ዜና ከፍ ብሏል። በኢትዮጵያ ሟቾች በኮሮና መሞታቸው የሚታወቀው አስከሬን ሲመረመር ብቻ ነው። እንደ ዜናው አዲስ አበባ የኮሮና ማከፋፈያ ሳትሆን አልቀረችም። ••• እስቲ የዛሬውን የአዲስ አበባ የኮሮና ዜና እንመልከት። ደግሞ የሟቾች ስም አይነገርም። ዕድሜና ጾታ ብቻ ነው። እንዴት እንደሚቀበሩም አይታወቅም መሰለኝ። በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 47 ደረሰ! ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰባት (7) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል። ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ 1. የ75 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ። 2. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው። 3. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው። 4. የ29 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት። 5. የ48 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት። 6. የ85 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው። 7. የ21 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት። • ለማንኛውም፦ • ጸሎቱ አይቋረጥ። • ንስሐ እንግባ • እጃችንን በሳሙና እንታጠብ • ርቀታችንን እንጠብቅ • አፋችንን እንሸፍን። ፈ ቀ ቅ ታ !! ••• ሻሎም ! ሰላም ! ዘመድኩን በቀለ ነኝ። ሰኔ 5/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ።
Hammasini ko'rsatish...
ዜና ማዕዶት *~★~* • ለወዳጆቻችን ሁሉ ይህን ዜና #SHARE አድርጉት። #ETHIOPIA | ~ ሥራ ላይ ነን። ••• “ ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የትናንቱን ለነገ ” ማኅበራችን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የማኅበሩ የቦርድ አባላት ትናንት ባደረጉት ስብሰባ ለማኅበሩ ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሾመዋል። በዚሁ መሠረት ዋነኛው፣ እግዚአብሔር ለዚህ ታላቅ የኢትዮጵያ ትንሣኤ አብሣሪ ሠራዊት ሥራአስኪያጅ ባለ ማዕተብ እስኪመጣ ድረስ በሁላችሁ ዘንድ የሚወደደው የአየር ጤና ኪዳነምህረቱ ፍሬ ወንድማችን ዮኒ ፓፒ ጊዜያዊ የማዕዶታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ማኅበሩን እንዲመራ በቦርዱ በሙሉ ድምጽ ተመርጧል። ••• ዮናስ ወንድማችን ይህ ማኅበር እዚህ እንዲደርስ ከእኔ ጋር በመመካከር ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ሥራውን በድሎ በእጅጉ የለፋ ወንድማችን ነው። እኔ በርቀት ስላለሁ ሁሉን የሰበሰበ፣ ያገናኘ፣ ያስማም በእውነት ወንድማችን ዮኒ ነው። ዮኒ ከመንግሥትም ሆነ ከአባቶቻችን ጋር መልካም ግኑኝነት ያለው ለፍቶ አዳሪ ወንድማችንም ነው። ዮኒ የተማረ ፊደል የቆጠረም ባለማዕተብ ወንድማችንም ነው። ለዚህ ማኅበር እዚህ መድረስ ሲል ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ እንኳ በማኅበሩ ጉዳይ ሲወያይ የሚነጋበት ትጉህና ንቁ ወንድማችን ነው። እናም ዋነኛው ባለማዕተብ እስኪመጣ ዮኒ በጀመረበት መልኩ ማኅበሩን ይመራዋል። መልካም የሥራ ዘመን ይሆንለት ዘንድ ተመኙለት። ••• በሌላም በኩል ከአባቶች በመጣ ማስተካከያ መሠረት የቦርዱ አባላት ቁጥር ከ13 ወደ 11 ዝቅ እንዲል ተደርጓል። የ11ም የቦርድ አባለት ስም ዝርዝራቸውም በቀጣይ እንዲሁ ይፋ ይደረጋል። ••• በሌላም በኩል ማኅበሩ እንግሊዝኛና አማርኛ መጻፍ፣ ቃለ ጉባኤዎችን መጻፍ፣ ማደራጀት የምትችል አንዲት ባለማዕተብ የጽሕፈት ቤት ሠራተኛም ይፈልግ ነበርና እሱንም አንዲት በውጭ ድርጅት ውስጥ ትሠራ የነበረች ባለማዕተብ እህት መልካም ፈቃዷ ተጠይቆ ለጥቂት ወራት ያለምንም ክፍያ አገለግላለሁ በማለቷ ማኅበራችን የጽፈት ቤት ሠራተኛም አግኝቷል ማለት ነው። ••• የሚቀረው አንድ እንደሌሎቹ ሁሉ በጎፈቃደኛ የሆነና ፈረንካ ላይ የማያተኩር ከሂሳብ ጋር የተያያዘ የፋይናንስ ሹም ባለማዕተብ ሲሆን እሱም ከዚህ ዜና በኋላ ከተፍ ማለቱ አይቀርም። ማነህ አንተ ባለማዕተብ፣ የተዋሕዶ የሊቃውንቱ ወዳጅ? እኔ ባለማዕተቡ አለሁ በል። ካለህበት ከተደበቅህበት ሥፍራ ውጣ ተገለጥ። ኣ ? ••• አሁን መሬት እየረገጥን ነው። በዓለም ላይ ያሉ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ የማኅበሩን ዕውን መሆነረ በጉጉት እየጠበቁ ነው። • የአይቲው ግሩፕ ተአምር ለመሥራት ጣጣውን ጨርሷል። • በፕሮፌሰር ዶክተር ባለ ማዕተቦች የሚመራው የኢኮኖሚስቶቹ ግሩፕ ሰነድ ጭምር አዘጋጅቷል። • የሕክምናው፣ የሕግ፣ የአርክቴክቶቹና የመሐንዲስ የሠዓልያኑ ግሩፕም እንዲሁ ወጥረው ይዘዋል። • ማኅበሩ ሕጋዊ ወረቀቱን ሲያገኝ ይፋ የሚሆኑት ባለ 105 ቁጥር አባላት የያዙት አንድ አሁን ላይ ስማቸውን የማልገልጻቸው ባለ ማዕተቦችም የሚደንቅ መሰባሰብ እየፈጠሩ ነው። በቴሌግራም እያገኘኋቸው ነው። • ራሱን የቻለ የአድሚኖች ስብስብም ተፈጥሯል። በቴሌግራም ተደባልቀው ገብተው መርዝ የሚረጩ መርዘኞችን የሚያጠሩ፣ የሚያስወግዱ የአይቲ ምሩቃን በነፃ የአድሚን ግሩፕ በመፍጠር ተአምር በመሥራት ላይ ይገኛሉ። ማዕዶት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂው መስክ የተነጠቅነውን የመሪነት ሥፍራ መልሶ ይይዛል ማለት ነው። • በምን ልታዘዝ ድራማ ደራሲ፣ ፕሮዲዩሰርና ዳይሬክተሩ “ ዋጄ ” አማካኝነት የተሟላ የኤዲቲንግ፣ የካሜራና የመሰል ሙያ ላይ የተሰማሩ ወደ ሰባት ባለሙያዎች ራሳቸውን አደራጅተው ለቀረጻ ሥራ ዝግጁ ሆነው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ገዙፍ የቴሌቭዥን ቻናል፣ ግሩም የሆኑ ኦርቶዶክሳዊ የመንፈሳዊ ፊልሞች፣ ድራማዎችና ጭውውቶች በቀጣይ መንገድ ላይ ናቸው። ••• ኦቦሌሶ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የመጪዋን ዘመን የኢትዮጵያ ትንሣኤ አብሣሪ ሠራዊቶችን ከያሉበት በወረንጦ፣ በወስፌ፣ በመርፌም እየለቀመ እየሰበሰበ ነው። እናም አንተም ተዘጋጅ። የመጸለይ ፀጋ ያለህ በጸሎትህ፣ ገንዘብ ያለህ በገንዘብህ፣ ዕውቀት ያለህ በዕውቀትህ፣ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፣ ሙያም ያለህ በሙያህ መጪውን የኢትዮጵያ ትንሣኤ ለመረጋገጥ ተዘጋጅ። አከተመ። ••• እኔ ዘመዴም፣ ጓደኞቼም ሥራ ላይ ነን። በቀላሉ እጅ መስጠት ብሎ ነገር የለም። ስለ ጨለመ አይነጋም ማለት አይደለም። ይነጋል። ክረምቱም ያልፋል። እጅ መስጠት ብሎ ነገር ግን አይታሰብም። እኔ ዘመዴ ከነከስኩ ሳላደማ፣ የነብርን ጅራት ከያዝኩ መልቀቅ ብሎ ነገር አላውቅም። ወጥር ዘመዴ። ••• ገድለ ጊዮርጊስን፣ ገድለ ሰማዕታት ወሐዋርያትን፣ ስንክሳሩን ሳነብ፣ ስሰማ፣ ሲተረክልኝ፣ ስሳለመው፣ ስባረክበት ኖሬማ በቀላሉ እጅ አልሰጥም። የዚህ ዘመን ወጣት ዋነኛው ችግሩ፣ በተሎ መካዱ፣ እጅ መስጠቱ የመጣው ከገድለ ሰማዕታት በመራቁ ነው። የሆሊዉድና የቦልዊድ ፊልም ሲያይ፣ አስር በቀላሉ ሴትን ልጅ የመጥበስ ጥበብ የሚል መጽሐፍ ሲሸምት የሚውል ጠጃም ጠባሽ ትውልድ ሃይማኖቱን ለሴት ቀሚስ፣ለጭን ሲል፣ ለገንዘብ ለሆዱ ሲል በቀላሉ ሃይማኖትን ባይክድ ነው የሚገርመው። እኔና ጓደኞቼ ግን ሃይማኖት እንደ አባቶቻችን፣ ጥበብ እንደዘመናችን አሰናስለን፣ አስማምተን፣ ኦርቶዶክሳዊ ሆነን፣ ተወልደን፣ ኦርቶዶክሳዊ ሆነን አድገን፣ ኦርቶዶክሳዊ ሆነን እንሞታለን። አከተመ። ••• ካነሰ እያየሁ እጨምርላችኋለሁ። ••• ሻሎም ! ሰላም ! ዘመድኩን በቀለ ነኝ። ሰኔ 5/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ
Hammasini ko'rsatish...
የዛሬው ውሎዬ *~★★~* • በፌስቡክ #SHARE አድርጉት። እስቲ ባለማዕተቦች ፈታ በሉ። #ETHIOPIA | ~ ብዙ የሚያግዙኝ ወንድም እህቶችን ስላገኘሁ ከምር ደስ ብሎኛል። እግዚአብሔር ይመስገን። ••• እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዛሬ ወሀቢዮች በኃይለኛው ተሰባስበው ነበር። የስብሰባቸውም ዋነኛ ምክንያት እኔ በምኖርበት ሀገር በሀገረ ጀርመን እኔኑ ዘመዴን እንዴት እንደሚከሱኝ በሚመክሩበት ጉባኤ ላይ ነው ተጋብዤ የገባሁት። ደግሞም ለክሱም የሚሆኑ የወንጀል ዓይነቶችን ሲያማርጡ፣ ሲወያዩና ሲከራከሩ ቁጭ ብዬ ስከታተላቸው ነው የዋልኩት፣ ያመሸሁት። ••• ደስ የሚለው ደግሞ ከአወያዮቹ መካከል የጥንታዊው እስልምና ወንድሞቼ ስለነበሩበት ዘመዴ ና ጉድህን ስማ ብለው ጥርተውኝ ነበር በታዛቢነት የተገኘሁት። በክሱ ጉዳይ ወንጀል ቢፈልጉ ስላጡ እኔ ራሴ የሆነ ነገር ፈጥሬ ልሰጣቸው ሁላ ፈልጌም ነበር። አሳዘኑኝ ግን። መጨረሻ ላይ ያው ለክሱ ገንዘብ ያስፈልጋልና ገንዘብ እናዋጣ ሲሉ አይ የወሀቢይ ነገር ብዬ በጊዜ ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ። [ እንደ ዘመድኩን አይነት ማኅበር እንመስርት የተባለውን ምክር ስሰማ ግን የክሴ ምክንያት ወለል ብሎ ታየኝ። ] ወይ ማዕዶት ዘኦረረቶዶክስ ገና ተአምር ታሳዪኛለሽ። ከሳሾቹ ያላወቁት ነገር ጀርመን ሙከጡሪ፣ ወይም እናርጅ እናውጋ፣ ወይም እዳጋ ሀሙስ፣ ወይም አላባ ጠምባሮ ወዘተ አለመሆኑን ነው። ከዚህ በፊት በጀማ ከሰውኝ ልካቸውን አይተውባታል። ዚስ ኢዝ ጀርመኒ አለ ሙለር። ••• የጴንጤ ፓስተሮች የደቡብ ኢትዮጵያን ህዝብ አፈር ከደቼ ካጋጡት በኋላ ሰሞኑን ደግሞ ወንዱም ፓስተርና ሴቷም ፓስተሪት እስልምናን ተቀበልን ብለው አንድም መድረሳ ቤት ሳይገቡ፣ ከየትኛውም ሼክ ዘንድ ቁርዓን ሳይቀሩ በአንድ ጊዜ ኡስታዚት ሆነው መስበክ ጀምረዋል። ሲያሳዝኑ። ወይ ፓስተርና ፓስተሪት መቼም የማትገቡበት የለም? ፈዛዛ ስታገኙ ማጃጃሉንና ማለቡን መቼም ታውቁበታላችሁ። አይ ብልጦ። በነገራችን ላይ ወሀቢም ያው የእስላም መናፍቅ ማለት እኮ ነው። አንድ ናቸው። የፓስተር ኡስታዝ ሰምቼም አላውቅ። የእኛ የአይቲ ቡድን አባላትም አኩርተውኛል። ይሄ ነው አምበሶቼ። እስከአሁን የተኛንበት ዘመን ይበቃል። ••• ሌላው ያሳቀኝ ደግሞ የመርካቶ ራጉኤሉ፣ የበጎ አድራጊው የዘኪ፣ የዘካርያስ ኪሮስንም ስም ከእኔ ጋር አንስተው ሲወቅጡት መዋላቸው አስቆኛል። ዘኪ የእማማ ዝናሽን ህይወት የለወጠ ምርጥ ወንድሜ ነው። ዘኪ ጀግና ነው። ዘኪ የታቦተ ጽዮን ፍሬ ነው። ዘኪ የመርካቶ ልጅ የቅዱስ ራጉኤል ፍሬ ነው። ወዳጄ እሱ ሥራ ላይ ነው። ለማንኛውም ወንድሜ ዘኪን በፌስቡኩ ተከታተሉት። የእማማ ዝናሽ ምርቃት ራሱ ይበቃዋል ወዳጄ። https://www.facebook.com/asemarch.deberu ••• እንዲያውም አሁን ዩቲዩቤን ስጀምር ከዩቲዩብ በማገኘው ገንዘብ ለዘካርያስ በመላክ ነው በደንብ ድሆችን የምረዳው። ዘኪ ጸልይልኝ። ጸልይልኝ በጣም ጸልይልኝ። የእኔን ጦማር ፖስት ስላደረገ እኮ ነው የሚንበጫበጩበት። ወለበል አቦ። ••• ስብሰባ ሲኖር እንዲሁ እየተሳተፍኩ እጽፍላችኋለሁ። የሚገርመው በእኛ የቴሌግራም ቻናል ላይ አብዛኛውን ስፍራ የያዙት ወሀቢዮቹ ናቸው። እናም የማኅበራችን አድሚኖቹች የሴት እስላም ስም ያላቸውንና ኡስታዞቹን ትተው ወንድ ወንዱን ከቻናላችን ላይ እንዲያጸዱዋቸው ትእዛዝ ሰጥቻለሁ። ••• አሁን ደግሞ ስም ቀይሬ ሌላ የወሀቢይ ስብሰባ ላይ እንድገባ እስላሟ እህቴ ፎ ጋብዛኝ ልገባ ነው። በሉ ደህና እደሩልኝ። ••• ሻሎም ! ሰላም ! ዘመድኩን በቀለ ነኝ። ሰኔ 4/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ።
Hammasini ko'rsatish...
Zekaryas Kiros

Zekaryas Kiros is on Facebook. Join Facebook to connect with Zekaryas Kiros and others you may know. Facebook gives people the power to share and makes the world more open and connected.

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.