cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የገጣሚያን ማኅበር

እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦ 👉መንፈሳዊ ግጥም ፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን 👉መነባነብ 👉ግጥማዊ ትረካ ይቀላቀሉን Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber Group👉 @yegetamianmahiber YouTube https://www.youtube.com/@Poetscoun

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
16 269
Obunachilar
+1024 soatlar
+1667 kunlar
+86430 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
10Loading...
02
የእግዚአብሔር ትልቅነት🔥 (ተፃፌ በደግሰው ደነቀ (@Linurlh_Eskanorkegn)) ክፍል አንድ አንዴ ምን ሆነ መሰላችሁ... ይመስለኛል ሁሌት ወይ አንደኛ አመት ተማሪ እያለሁ ግቢ አከባቢ መብራት ጠፍቶ ልጆች ዶርም አከባቢ በጣም ይጯጯሁ ነበር። እና ብዙ ግዜ እንድህ የማድረግ ልማድ ባይኖረኝም መፅሀፍ ቅዱስ ገልጬ መስኮት አጠገብ ጠረዼዛው ላይ ቁጭ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ። የማነበው ክፍል የማቴዎስ ወንጌልን ነበር። እና ምዕራፍ 25 ላይ ያለውን ቃል አንብቤ በጣም በጣም ከምላችሁ በላይ ስለገረመኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮህኩ። ጌታን የምሬን ነው የምላችሁ😁 አጋጣሚ ሆኖ በተማሪዎች ጩሄት ውስጥ ጮህኩ እንጂ ማንም ባልጮሄበት ጮኬ ቢሆን ወይ ደግሞ ማታ ቢሆን እውነት ለመናገር የሆነ ቅጣትማ ይጠብቀኝ ነበር። እስኪ ምን እንዳስጮሄኝ አብረን እንመልከት። ማሳሰብያ:- ከጮሃችሁ ፀሃፊው ለጩሄታችሁ ተጠያቂ አይደለም።😊 ቃሉን አብረን እንየው... ምንአልባት አሁን ላይገርማችሁ ይችላል በኋላ ላይ ግን በሰፊው እናብራራዋለን። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 25) ---------- 31፤ የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ 32፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ 33፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። 34፤ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ዋናው የምንማማረው ቃል ((🔥ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግስት ውረሱ🔥)) የሚለው ነው። Pls አንዴ ፍቀዱልኝና ከማስረዳቴ በፊት ልጩህ😊 ... ስለዚህ ርዕስ ማውራት ከጀመርኩ ማቆሚያ የለኝም😊 በመጨረሻ የገባው አብሮኝ ይጮሃል ማለት ነው። #1 የእግዚአብሔር ትልቅነት ከምድር ስፋት አንፃር ቃሉን ሳንረሳ ከእኔ ጋር አብረን እንፍሰስ! እኛ የሰው ልጆች ነን። እኛ የሰው ልጆች በመጠን ትልልቆች ነን😁 ከጉንዳን፣ ከቁንጫ፣ ከወፍ፣ ከጭልፊት፣ ከዉሻ፣ ከበግ፣ ከፍየል እና ትናንሽ ፍጡራን አንፃር። እኛ የሰው ልጆች በመጠን በጣም ትናንሾች ነን ከዛፎች፣ ከዳገቶች፣ ከባህሮች፣ ከሰማያትና ከከዋክብቶች አንፃር። ታድያ ግን የምንበልጣቸውም ሆነ የምበልጡን ነገሮች የተፈጠሩት ለእኛው ለራሳችን ነው።❤ የገባኝን ነገር ለማስረዳት ትንሽ ስለ ሳይንስ ላውራችሁ። እኛ የሰው ልጆች የምንኖረው በምድር ላይ ብቻ ነው። ለሰው ልጅ ከምድር (Earth) ውጪ ለኑሮ ተስማሚ የሚባል ቦታ እስካሁን አልተገኘም።(ምናልባት ውሃ እና Oxygen የታሸገበት ምንም አይነት ነፋስ እንዳያስወጣ ተደርጎ ከተሰራ እንጂ)። ታድያ ይህቺ ምድር ወይም መሬት መጠኗ ምን ያህል ነው ካላችሁኝ በጣም ትልቅ ነው። አሁን ነገሩን እያከረርን እንመልከት እስኪ ... እንኪ በኪሎ ሜትር እየለካን እንጀምር። ኪሎ ሜትር የምጀምረው ከእርምጃ ነው። ታድያ አንድ ሰው አንድ ሺ ግዜ ብራመድ አንድ ኪሎ ሜትር ደረሰ ማለት ነው። (አንድ ሺ እርምጃ = 1Km) መሬት ደግሞ ድቡልቡል መሆኗን ሁላችንም እናውቃለን እናምናለንም። ድቡልቡል ነገር ላይ ደግሞ የሆነ መነሻ ይዘን በቀጥታ ወደፊት ከሄድን የተነሳንበት መነሻ ላይ ዞረን እንመጣለን። ያ ማለት አንድ ሰው ሁሌቱን እጆቹን ወደጎን ዘርግቶ ቢቆምና ቀኝ እጁን በዘረጋበት አቅጣጫ ምንም ሳያዛንፍ ቀጥ ብሎ ወደፊት ቢሄድ ግዘውና ሰዓቱ ይረዝማል እንጂ ግራ እጁን በዘረጋበት አቅጣጫ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም። (አደራ በሰማይ በምድር እንዳትሞክሩት😁) ታድያ አንድ ሰው ይሄን ልያደርግ ብወስን ምንያህል ግዜ ልፈጅበት ይችላል? ይሄን ካወቅን የምድር ወገብ ምን ያህል እንደምሰፋ ማወቅ እንችላለን ማለት ነው። የተረጋገጠው የምድር ወገብ ርዝመት በኪሎ ሜትር ሲሰላ 40,075Km ነው።(አርባ ሺ ሰባ አምስት ኪሎ ሜትር ነው።) ታድያ ይሄ ተጓዣ በአንድ ቀን አንድ ሺ ኪሎ ሜትር እየተጓዘ እንኳን ቀኝ እጁን ወደዘረጋበት አቅጣጫ ቢሄድ ከ41 ቀን በኋላበግራ እጁ አቅጣጫ ተመልሶ ይመጣል ማለት ነው። ታድያ መሬት ከሰው ልጅ አንፃር ምን ያህል ትልቅ ነች?🤔 (ያ ማለት መሬትን ብንዘረጋትና ከአንድ ሰው ጋር ብናወዳድራት መሬት ምን ያህል ትበልጠን ይሆን?) (የማይጠየቅ ጥያቄ ነው አይደል? ግድ የላችሁም እስኪ እንየው) የሰው ልጅን ቁመት ከምድር ቁመት ጋር አወዳድሩት እስኪ😁 እስኪ ሁላችንም ሁሌት ሜትር እንረዝማለን ብለን እናስብ😁 የምገርመው ሁሌት ሜትር ብንረዝም እንኳን 1 ኪሎ ሜትር መሙላት የምንችለው 500 ሰዎች አንድ ላይ ስንሆን ነው👨‍🏭😄 የምድር ወገብን ለመክበብ ከፈለግን ደግሞ (500*40,075)=(20,037,500) እና ሃያ ቢልዬን ሰላሳ ሰባት ሺ አምስት መቶ ሰው ማለት ነው።😁 by z way የሰዎች ቁጥር አሁን የዚህ ግማሹ ነው። አሁን ላይ ታድያ በምድር ላይ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አንዱን በአንዱ ላይ ብታቆሙት የተዘረጋችን ምድር የቁመቷን ግማሽ አታክሉም፤ አናክልም! ታድያ ይህን ያህል ለምናንስ ለእኛ የሄን ያህል ምድር የፈጠረልን አምላክ በፈጠራቸው እጆች መታዘዙና ለታዘዘላቸው ነፍሶች መሞቱ አይገርምም?😣 #ትልቅነው! ያም ብቻ አይደለም'ኮ የምገርመው። አሁን ባለንበት የዩንቨርስ ክፍልፋይ በሆነው ጋላክሲ ውስጥ 8 ፕላኔቶች አሉ ይባላል እነሱም:- 1. Mercury 2. Venus 3. Earth 4. Mars 5. Jupiter 6. Saturn 7. Uranus ና 8. Neptune ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ትንሿ mercuey (4879 km ስፋት ያላት) ስትሆን ትልቁ ደግሞJupiter ነው ስፋቱም ወደ 139,822km ነው ይህም ከምድር እስከ አራት እጥፍ እንድበልጥ ያደርገዋል። እና እነዚህን ፕላኔቶች ከፀሃይ ቀጥሎ በተቀመጡበት order ነው ከላይ ያስቀመጥኩላችሁ። እስኪ ከፀሃይ ምን ያህል እንደምርቁ በቁጥር እንመልከት። እኛ ራሱ ከፀሃይ አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሚልዬን ስድስት መቶ ሺ(149,600,000Km) ኪሎ ሜትር እንደምንርቅ ታውቃላችሁ?😁 እንግድህ ከዛ ርቀት ነው ምትሞቀን እግዜር ያሳያችሁ😊... ይሄው እስከ ፀሃይ ያላቸው ርቀት:- 1. ከMercury:-  57.9 million km 2. ከVenus: 108.2 million km 3. ከEarth: 149.6 million km 4. ከMars: 227.9 million km 5. ከJupiter: 778.5 million km 6. ከSaturn: 1.43 billion km 7. ከUranus: 2.88 billion km 8. ከNeptune: 4.5 billion km በነገራችን ላይ Pluto ከፕላኔትነት ተሰርዛለች አሁን አሉ የሚባሉት ፕላኔቶች 8 ብቻ ናቸው። የመጨረሻዋ ፕላኔት ግን ከፀሃይ ምን ያህል እንደምትርቅ 😯 (እስከ 7.4 billion ኪሎ ሜትር) ልትርቅ ትችላለች። ከፍጥረቱ እስከ ፍጥረቱ ይህን ያህል ከራቀ ፈጣሪው ምንኛ ትልቅ ይሆን?😯 አቤቱ ትልቅ ነህ እኮ🔥🔥🔥 ከሁሉም በጣም የሚገርመውን ቆይ ላሳያችሁ። ይሄኛው እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ከምያስገርመኝ ነገር መሃል አንዱ ነው። እና ሳይንስ ተብዬው ሰውዬ "አላውቅም" ከምል ብሎ ያስቀመጠውን ቁጥር እንመልከት እስኪ። ጥያቄ:- ዩኒቨርስ ወይም ይሄ አልም ምን ያህል ሰፊ ነው? የሳይንስ መልስ:- 93 ቢልዬን የብርሃን አመት😯 ክፍል ሁለት ይቀጥላል React❤️❤️
1053Loading...
03
❌የውሸት ማስታወቅያ አይደለም❌ ለመንፈሳዊ ህይወታቹ ጠቃሚ የሆኑ የቴሌግራም ቻናሎችን ልጋብዛቹ። ♥️ስለምወዳቹ ጋብዤአቹሃለው። ተቀላቀሉ በርግጠኝነት ትጠቀሙበታላቹ👍🏼 🟢Join🟢 የሚለውን በመጫን አሁኑኑ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
2742Loading...
04
በጣም ስከፋችሁ ምንድነው የምታደርጉት🥹🥹
4552Loading...
05
መንፈሳዊ ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN ይበሉ ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇 https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk wave ለመግባት👉 @wunuye_bot
2441Loading...
06
ማስፈለጌ ገርሞኝ ሆሳዕና ይሉታል ይህንን ልዩ ቀን ሰው በሰው ላይ ወቷል ሊሆን አንድ ነገር አሳዳጊዎቼም ተጣድፈው ወተዋል ንጉሡን ለማየት እጅጉን ጓጉተዋል ገና ከመንጋቱ ይህን ወሬ ሰምተው ምንጣፍ አሰናዱ ዘንባባውን ቆርጠው ለእሱ ሊያነጥፉለት እናያለን ብለው እኔን ግን እኔን ግን ያስታወሰኝ የለም ልሂድ ልቅር ብሎ የጠየቀኝ አንድም እዛው ከጓሮዬ አስረውኝ ሄደዋል ብጮህም ብጣራም የሚሰማኝ ታጥቷል ምንም የአህያ ልጅ ውርንጭላ ብሆን ንጉስን ለማየት እጅጉን ጓጓሁኝ ግን ለተስፋም የሚሆን ኮሽታም አጣሁኝ ግና ግና ከብዙ ሴኮንዶች ከደቂቃ ኋላ ጩኸትም ይሰማል በትልቁ እልልታ በዚህ መሃል ነበር ቤቴ የተንኳኳው በተከታዮቹ እኔው ተወስጄ ምሆነውን አጣው አላፊ አግዳሚው ደሞም ተሳታፊው ስለኔ ይጠይቃል አንዲት የአህያ ልጅ ምን ያደርግለታል ህዝቡ ይባባላል ደቀመዛሙርቱ እኔን ሲጠየቁ ትንሽነቴንም እነሱ ሳይንቁ ለአምላክ ማስፈለጌን ራሱ አወቁ በሄድኩበት ሁሉ ታስፈልገዋለች እያሉ አሳወቁ ሲገርም ላየው የጓጓሁኝ እየሱስ ጌታዬን በእኔው ሊሳፈር ሊቀመጥ መሆኑን ከጎኔ ሰማሁኝ ንጉሥ ተቀመጠ ክብር ሆነ ለኔ ትልቁን ተዓምር አየሁኝ በአይኔ ከማየትም በላይ በእጆቹ ዳበሰኝ እንደማስፈልገው በተግባር አሳየኝ ያለች ይመስለኛል ይቺ ውርንጭላ በእሷ ውስጥ እኔን ልታሳየኝ ወዳ ለንጉሡ እሷ እንዲህ ካስፈለገች የእኔ ምን ሊሆን ነው ድርሻዬን አሰብኩት በእራሱ አምሳል ሙሉ አርጎ ፈጥሮኝ በአዳም በሰራሁት በደሙ አጥቦልኝ በራሴው በደል መስዋዕት ልኮልኝ ለማይገባኝ ለኔ ህይወት የሚሆነኝ እስትንፋሱን ሰቶኝ እንደሚፈልገኝ እንዲህ አሳይቶኝ ታዲያ ታዲያ ታዲያ ለንጉሤ ምን ባደርግለት ነው የሚሆነው መልሴ በሙሉ ህይወቴን ልስጥህ ይኸው እንካ ለራሴ የምለው የምቆርሰው ጊዜ ከእኔ ይትጣ አንተን ብቻ ላውራ አንተን ብቻ ልኑር መላ ሰውነቴ ላንተ ብቻ ይሁን አንተ ብቻ ክበር ላከበርከኝ ላንተ ክብር ነው ምላሼ ይገባሃል ንጉሥ ምስጋና ውዳሴ ለፈለከኝ ላንተ ይሄ ነው ምላሼ ሙሉ እኔነቴን ላንተ ለምስጋና እንዲሆን መስጠቴ ይሄ ነው  ምላሼ።                                               ✍️ ብፅዕት ዘነበ React❤️❤️ Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
7598Loading...
07
🎁ዳጎስ ያለ ካርድ የሚያሸልም መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ ውድድር ሊጀመር ስለሆነ በፍጥነት ይቀላቀሉ እንዳያመልጣችሁ🎁👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
2610Loading...
08
ገጣሚያን እንዴት ናቹ የተወደዳችሁ
7661Loading...
09
አንዲት ሀሳብ ላካፍላችሁና አብረን እናውራ እስኪ.... ከዛ በፊት ግን ይህቺን ግጥም ልጋብዛችሁና በዚህች ግጥም ሀሳብ ተመርኩዘን እናወራለን። ...ሀዘንና ደስታ.... (ግጥም) አንድ አባት ነበሩ እጅግ የከበሩ ከልጆቹም መሀል አንዱ ይጠይቃል ቦታዎች በሙሉ 'ያባቱን ቤት መስሎት ድርሻው እንዲሰጠው 'ባጸንኦት ጠይቆት ነፍሱ መሄድ መርጣ 'ካባቱ ቤት ወጣ አባቱም አዘነ የምያስበው ሁሉ ስለ ልጁ ሆነ . . ከእለታት ባንዷ ቀን ያ .. ኮብላዩ ምስኪን ልጅነትን ትቶ በውጪ ከመኖር ባርነትን መርጦ ከጌታው ጋር መኖር እንደምሻል ገብቶት ከልቡ ተረድቶት እርምጃውን ሁሉ የኋሊት አ'ረገው አባት ከሩቅ አይቶ እጅጉን ደስ አለው ፍሪዳ አርዶለት ልብሱን ቀየረለት ይሄው ስለሆኔ በሰው አለም እውነት ስያጡ እያዘኑ ስያገኙ መደሰት . . ጌታ ሆይ 🤔🤔🤔🤔..... በእግዜር አለም ??? . . ዸጥሮስ ንሰሀ ገብቶ ይሁዳ ስከዳህ አንቴን ምን ተሰማህ?? ስለ ይሁዳ ሀዘኔታ . ወይስ . ስለ ዸጥሮስ ደስታ አንቴ ' ኮ ትልቅ ነህ!!!! በዚህ ምድር ከምገመኝ ነገር መሃል አንዱ የእግዚአብሔር እግዚአብሔርነቱ ውስጥ ሁሉን ቻይነቱ ነው። ከሁሉን ቻይነቱ ውስጥ ደግሞ የዚህን ሁሉ ፍጥረት ስሜት አንድ ላይ ማስተናገዱ ነው። ... በነገራችን ላይ በሰው ፊት ከምያወራው ሰው ይልቅ በሰው ፊት ዝም ያለው ሰው ነው ለእግዚአብሔር ብዙ የምያወራው። ያ ማለት ይሄ ሁሉ ሰው ከእግዚአብሔር ጋራ ያወራል ማለት ነው። አሁን ይሄን ስታነቡት እንኳን ሁላችሁም የሚሰማችሁ ስሜት አንድ አይነት አይደለም። ሁላችንም አሁን ሚሰማንን አውጥተን ብናወራ የስሜት መዋዤቅ ያገኘናል። ምክንያቱም የሁሉም ስሜት አንድ ስላልሆነ። ታድያ ይሄ ጌታ የሁላችንንም ስሜን አንድ ላይ ስሰማ የምሰማው ስሜት ምን ሊሆን እንደምችል አስባችሁታል? እና ይሄ ጌታ ትልቅ የሚል ቃል ብቻ ይገልፀዋል?🤔 ደግሞ'ኮ የምገርመው የእግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ስልጣን መስማት ብቻ አለመሆኑ ነው። ስንቶቻችን ነን በተሰጠን ሰውነት ውስጥ እንድንሰራ የተሰጠን አንድ ነገር ብቻ እንደሆነ የምናውቅ? እሱም ማሰብ ብቻ ነው። ሰው ሀሳብን ብቻ ስራው አድርጎ ተቀብሎ ይሄን ያህል ጭንቀትን ካተረፈ አስቡት እስኪ ... የልብ ትሪታችን ሪትም እኛ እንድንቆጣጠር ቢሰጠን። ምግብ ሲፈጭ  manager ቢንሆን😁 ልብን ደም ቅዳ ደም መልስ ብንለው? የአይን እርግብግቢት.. የሳንባ አየር ቁጥጥር ተላልፎ ለእኛ ቢሰጠን ምን እንሆን ነበር? እግዚአብሔር የራቀ የመሰለን ሰዎች ካለን በህይወት የመኖራችን ጉዳይ ራሱ ትልቅ ማሳያ ነው። እንግድህ ይሄን ሁሉ ነገር በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ሰርቶ ስሜታችንንም ይችለዋል። ሀሌሉያ🔥 ይሄ ታድያ የሰው ብቻ ነው። ወደ እንስሳት ስንሄድ ደግሞ ማሰብያውንም ይረከባል😁 አይ ጌታ.... ክርስቶስን ነው ምላችሁ ይሄን ሁላ ፅፌ ገና ምጀምር ምጀምር ነው እየመሰለኝ ያለው። ለዛሬ እዝህች ጋ ላብቃ .. እስኪ ስለ እግዚአብሔር ትልቅነት እናውራ ጥያቀዬ ይህቺ ናት "ከእግዚአብሔር እግዚአብሔርነቱ ምኑ ይገርማችኋል?" ተባርካችኋል🔥 ተፃፈ በደግሰው (@Linurlh_Eskanorkegn) Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
8103Loading...
10
ራእይ 22 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ። ² በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ። ³ ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥
6771Loading...
11
🎉🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎉 🤱እኔ በተወለድኩበት ወር ብቻ ከተወለዳቹ አሪፍ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ😃 🤰እናንተ በየትኛው ወር ነው ወደዚች ምድር የመጣቹት🤱  ወይም የተወለዳቹ? 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
3190Loading...
12
Repost
7120Loading...
13
የእምነት አባቶች ትላንትና ነበር : ከትላንትም ወድያ የጀግኖቹ ታሪክ : የግብግብ ውጊያ የጨለማው ዘመን : ማይፋቅ አሻራ አንዳንዱ ሚያሳዝን : ታሪክ የሚያኮራ:: የእምነትአባቶች: እግዚአብሔርን ይዘው ከፊት ከፊታቸው : እሱን አስቀድመው እውነት ሳይገለጥ : ሳይታወቅ ንጋት ኑሮንም መቀጠል : ቀንበር በህግጋት:: ሆኖም ድል ሰርተዋል : ብዙ ተጋድለዋል የገደለን ገለው : በድንጋይ ወግረዋል ቁጣ የሚበርደው : በቁጣ መሆኑን ወደው እኮ አይደለም:ፈልገው በቀሉን :: አስደናቂዎቹ : እነ ሙሴ እያሱ አብርሀምና ይስሀቅ : ያቆብም እራሱ ስንቱ ይነገራል : ኧረ ስንቱ ይወራል ህይወታቸው ዛሬም : ይሄው ይነበባል:: የእምነት አባቶች : ጌታን ሲያስቀድሙ የጠላታቸው ሀይል : መሬት ሲጋደሙ ድልን ሲቀዳጁ : አልፈው ሲሻገሩ በድንቅ በታምራት : በጌታ ሲመሩ:: ዛሬ ማን ነው ታዲያ : የወንጌል አርበኛ በአዲሱ ኪዳን : ተነሺ ተረኛ ብርሀኑን ይዞ : በአለም ሚያበራ የወንጌሉን ጥሪ : መንገዱን ሚመራ:: ኧረ ማን እሱ : ዛሬ ማያቅማማ የየሱስን ሀይል : ክብሩን የተተማ እውነተኛ አርበኛ : እሆናለሁ ያለ ይስጠው ማንነቱን እግዚአብሔር አለ::
7027Loading...
14
Repost
6870Loading...
15
ግሩም ነው ግሩም የሆነ ብርቱ አምላክ ነው እንደ አሱ ያለ አረ ማነው በስራውም ድንቅ እንከን የሌለው ሀያል እግዚአብሔር እሱ ብቻ ነው ሰማይን የሰራ ምድርን ያበጀው ተራራው ሚዳውን ያቃናው እሱ እግዚአብሔር ድንቅ እኮ ነው ምስጋናም የሚገባው ለሱ ነው ያዋፋቱ ዜማ የወንዙ አወራረድ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ሁሉ የሱ ፍቃድ የአንበሳው ጀግንነት የጦጣ አዘላለሉ ሁሉንም የሰራ እግዚአብሔር ድንቅ ነው ሀያሉ ግሩም ነው ጌታ አለምን የገዛ በል ዘመኔን ህይወቴን ይግዛ ግሩም አባት ነው ድንቅ መካን ሀያል ሁሉን የፈጠረ እግዚአብሔር ይበልጣል @dreamgirl127
7671Loading...
16
#የዓለም_ብርሃን ዓለምን በሙሉ ጨለማ ሲወርሰው ብርሃን ተሸፍኖ ሃጢያት ሲጋርደው፤ ዓለም በዕውርነት ብርሃንዋ ጨልሞ በህወት ጎዳና ለሊቱ ዕጅግ ረዝሞ፤ ድቅድቁ ቢጨልም ጀንበር ስታበቃ ፍጥረት ሲያጣጥር ተይዞ በሲቃ፤ ጥያቄዋም ግሎእንቆቅልሽ በዝቶ ቃጠሮዋ ገኖ ህይወት ጣዕም አጥቶ፤ እግዜር ራሱን ላከ ስጋን ተላበሰ ለጨለማው ተስፋ ማለዳ እየሆነ፤ ህሊናዬ ነቅቶ ሲሆን እንደ ዋላ ጨለማውን ገፎ ልቤን ብርሃን ሞላ፡፡ #I_AM_A_WITNESS #እኔምስክርነኝ React❤️❤️ Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
8872Loading...
17
መንፈሳዊ ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN ይበሉ ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇 https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk wave ለመግባት👉 @wunuye_bot
2950Loading...
18
ሠላም ቅዱሳን እንዴት ናችሁ😍🙌 እስቲ ይሄን ወንድማችንን አበረታቱ የሚትፈልጉትን ነገር ከእርሱ ጋር ተነጋገሩ።እግዚአብሔር ይባርካችሁ በማስታወቂያ መሠረት ሁሉንም ስራዎች በጥራት እና በታማኝነት እንደፍላጎትዎ አሳምሮ ይሰራል። ስልክ፦ +251936903841
1 0260Loading...
19
💚እጅግ ተወዳጅነት ያገኙ 🙏ለመንፈሳዊ ህይወታችን ጠቃሚ የሆኑ 📲በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን 💁🏻‍♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹ 🙋🏻‍♀እኔ ተቀላቅያለው ስለምወዳቹ ጋብዤአቹሃለው🎁 የምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
2990Loading...
20
ለምን ዩቲዩብ ቻኔላችንን Subscribe አታደርጉም ቆይ🥹🥹 እስቲ አንዴ Subscribe ያላደረጋችሁ ሄዳችሁ አድርጉ አድርጉ🥰🙏🙏🙏🙏 LINK https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394 Subscribe ያደረጋችሁ ተባረኩ እችን 👉❤️ ግጩ
9650Loading...
21
➪ ክርስትና ቀሎ      ክርስትና ቀሎ  ክርስትያን ነኝ ማለት ታዲያ ምን ያደርጋል ኖሮ ካልታዬበት ወገነ ሀይ ስማኝ ክርስትና ቀሎ ከታየህ መኖር  ቀርቶብህ  ዋጋው ከቀለለህ እና ምኑ ጋር ነው ክርስትያን ነኝ ያልከው     ስከፈል የመስቀል ውለታ     አዋርዳ የአለሙን ገታ እንዲህ ነው የመጣው ክርስትና ተብሎ በእኛ ዘንድ የታየው በአለሙ ቀሎ     አይ ክርስትና ............. ወንድም በወንድሙ ላይ እጅን ካነሳበት ክርስትና ቀሮቶ ሰይፍ ከሸመተበት ቆይ🤔 ምኑጋ ነው ክርስትያን ነኝ ማለት   አስታራቅ ተብየው ስታይ በማጣላት   አክባር ተብየው ስገኝ በሀመት ትዕብት ወርሳ ፍቅርን ስያጠፍት     በምነኛም ምዛን ክርስትያን ምያስኘን አስተውል ወገን አስተውል ወደጅ የምትራመድበትን መንገድ ለይ የተጠራህበትን አለማ እወቅ የዘመኑ አውረ እንዳይበላህ ተጠንቀቅ አትገኝ ፍሬ በማይገኝበት አትገኝ ፈቅር በለለበት የመስቀሉ ፍቅር ገብቶን ፈቅር ካላሳየን ክርስትያን ነኝ ማለት ቀሎ ከታየብን ስም ብቻ ዋጋ  የለው ኖሬን ካላሳዬን   እራሳችንን እንፈትሽ ከዝህ ክፍ ግዜ እንሽሽ            እስትይ ልጠይቃችሁ ከዝህ ጣጣ           እንደት ልውጣ ላላችሁ ልመሊስላችሁ መልሰንም ልስላችሁ ልባችሁን በፍቅር ማልታችሁ ሀሳበች ይሁን ልክ እንደ ህፂን ተንካል ቀርቶ ገታን ከመሰልን ያነ ያነ ክርስትያኖች ሆንን    ክርስትያን እንሁን ✍✍Dibora wegene✍✍✍ 2013 /3 React Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
1 07713Loading...
22
🎤አዳዲስ መዝሙሮች እና አልበሞች እየተለቀቁ ስለሆነ የምትፈልጉት ዘማሪ ስም በመንካት መሉ አልበም እና አዳዲስ ዝማሬዎችን ያገኙበታል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
2290Loading...
23
🎁 መሸለም ልንጀምር ነው 🎁 ይሄ መልዕክት ከ20 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል ቀድመው እነዚን ቻናል ለተቀላቀሉ 20 ሰዎች የ500 ብር ካርድ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን ለመለሱ ዳጎስ ያለ ሽልማት እንሸልማለን ፈጥነው ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
630Loading...
24
Media files
10Loading...
25
Media files
10Loading...
26
ጉርብትና...💔 አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል። ‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ የግድግዳ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም። ‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለ ና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ። ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ።የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው። በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል። አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው? አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ። በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ። አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው። የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አስክሬን ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹም ይራመዱ ጀመር። የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው? የማንን አስክሬን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው። ‹‹አባታችን ጠዋት ሙቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይጓደል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት ጀናዛ የተሸከሙ ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።
1 08115Loading...
27
እጅግ በጣም ደስ የሚል ዜና ቅዱሳን🥰 እውነተኛ እና የተረጋገጠ ነው የምትፈልጉ ሰዎች ይሄን ዕድል ተጠቀሙ። ስለ Process  የተጣራ መረጃ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ። 95% ይሳካል።እኔ ወንድማችሁ ሶለን Process ጅማሮ እስከ መጨረሻ እመራችኃለሁ።🤓😊 The Great Opportunity who wants to study in Italia Full funded scholarship Program in 2024 Full Funded Scholarship Includes: 1 Accommodation 2 Sponsored meals 3 Free transport service 4 Pocket Money more than 7500 Euro per Years Remember: No Pre payment before Acceptance letter. Passport ያላችሁ ብቻ በተሰጠው አድራሻ ማናገር ትችላላችሁ። ሙሉ መረጃ ለማግኘት 👉 @S_o_L_e_N_y አናግሩኝ በስልክ 0955305109 ደውሉ። አመሰግናለሁ 🙏🙏❤️
1 15910Loading...
28
✍️✍️ምን ይጠቅማኛል ✍️✍️ አመት ጠብቄ ስቃይህን ብያስብ                 ጊዜው ስደርስ ጥቅስ ብሰበስብ የአመቱን በአል ልዘክር ብዘጋጅ                  ለምግብ ለመጠጡ ከጎረቤቴ ብወደጅ          ምን ይጠቅመኛል? የአመቱን አርብ ጠብቄ ግርፋትህ ከዝያም ስቀጥል ስቅለትህን በአመት አንዴ ብያስብ ብያብሰለስል ምን ያደርግልኛል?   ህመማት እየልኩ በቸርኬ ብጓዝ ለprofile ጥቅስ ብመዝ Add storien በደምና በምስማር posten በመስቀሉ ብያሰምር            ምን ይጠቅማል? ለማስመሰል ነዉ እንጂ አመት ጠብቄ መቀየሬ የFb,የTG,የimo profile ማሳመሬ ምን ያደርግልኛል ከንቱ ስም ብቻ ህይወት ነዉ profile የአምለኬ መቀመጫ  profilሌ ኑሮዬ ነዉ የአምለክ ማኖሪያ          አመት ጠብቆ ማይቀየር የክብሩ ማደሪያ             profilሌ ህይወቴ ነው የመስቀሉ  መታያ! 🙏🙏🙏BY BETTY🙏🙏❤                      በየቀኑ ሰቃዩን,ስቅለቱን,ሞቱንና ትንሳኤዉን እንድነሳይ ጌታ ይርደን🙏አሜን እንኳን አደረሳችሁ መልካም ትንሳኤ❤🙏🙏🙏🙏 Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
1 1989Loading...
29
መንፈሳዊ ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN ይበሉ ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇 https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk wave ለመግባት👉 @wunuye_bot
3251Loading...
30
ያ የሮማ ጅራፍ ጀርባህን ያረሰው ጽድቅን የጻፍክበት ብዕር ነው REACT ❤️ ✍ዘማሪ ሀዋዝ ተገኝ
1 3050Loading...
31
.        ❓የመዝሙር ጥያቄ❓     💿ይህ መዝሙር የማነው?💿                        👇 🎶ተመስገን ተመስገን🎶 🎶ተመስገን ልበልህ ደግሜ🎶 🎶ከሃጢያት በሽታ🎶 🎶ተፈውሼ በአንተ ታክሜ...🎶 ይህን ጥያቄ በትክክል ከመለሳቹ ጠቃሚ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ።
2390Loading...
32
⚓️👑 #አውራ_ፍቅር 👑⚓️ -------------------------------------- ከመታወቅ በሚያልፈው        በመውደዱ ተወድጄ አለው ቤቱ        በአውራ ፍቅሩ ተረትቼ የእርሱስ ፍቅር                ልኬት የለሽ                ወረት አልባ ለወገሩት ለሰቀሉት ለተፉበት                 የሚያነባ። የጠሉትን ከጠላቸው የሚናጠቅ ለአላወቁት የሚዋደቅ ንፁ ደሙን እስከማፍሰስ ነፍሱን ለሞት እስከመስጠት                       እንዲያው ሚወድ ሰው ከናቀው ከተጠላው በህግ በወግ ከጎደፈው                       ዘንድ የሚዛመድ ያላወቁት እስኪያውቁት የማያምኑት እስኪያምኑት ያልዳኑበት እስኪድኑ                  ስለሁሉም የታገሰ ዮናሶችን ከተርሴስ የኤማሆሶቹን ከመንገድ ጴጥሮሶችን ከታንኳቸው                    የመለሰ። #አውራ_ፍቅር የማይናድ                 በዘመናት ሁሉ የጸና በፍቅር እጦት የጎበጠን                 እንደመላው የሚያቀና። Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
1 48815Loading...
33
ትላንትና በኔ ስህተት ነው እንጂ አሸናፊው ብሩክ ሳይሆን አክሊሉ ነው🤗🤗🤗🤗👏👏👏👏🥳🥳🥳🥳🥳 ሌሎቻችሁም ተሳተፉ አሸንፉ ሽልማት ውሰዱ🙏👏🙏🙏🙏🙏
1 2331Loading...
34
🎁 መሸለም ልንጀምር ነው 🎁 ይሄ መልዕክት ከ20 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል ቀድመው እነዚን ቻናል ለተቀላቀሉ 20 ሰዎች የ500 ብር ካርድ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን ለመለሱ ዳጎስ ያለ ሽልማት እንሸልማለን ፈጥነው ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk
3240Loading...
35
👆👆👆👆 No reaction There is No post ☹️
1 1860Loading...
36
#ሰው_ጠፍቶ_ከመንገድ ለይምሰል ሰው ሆነው:ገብቷቸው ካልኖሩ የሰውነት ዋጋ:የመኖርን ሚስጥር:በልብ ካላሰሩ ምኑ ተኑሮ:እረ ምኑ ታይቶ:በህይወት ዘመን የሰው ልጅ ረክሶ:ሰውነቱን ትቶ:በጥፋት ሲመዘን ወደየት ከወዴት :ጉዞ:የሌለን ሊያመጣ ስጋውን ገፍትሮ:ወዳጁን በድሎ:አስጨንቆ ገድሎ ራሱን ረስቶ:አጋንንት ሰፍሮበት:ከቀየው ኮብልሎ በጥፋቱ መንገድ:መገስገስ ጀምሯል ሰይጣናዊ ስራው:ይባሱን ጨምሯል አይ ሰው:ሰውማ:በአምላኩ ሲፈጠር ለጌታው ቃል ፈቃድ:ተገዝቶ እንዲኖር አደራ ተሰጥቶት:እንዲሰራ በምድር እርሱ ግን  ዘንግቶ:ሌላ ሀሳብ ይዟል እጅና እግሮቹ:ለጥፋት ውለዋል የበላበት ወጪት:ተጥሎ ተሰብሯል ወንድሙን ወዳጁን:ከአምላክ የተሰጠው የሀሳብ ልዩነት:የልቡን ቃል ሀሳብ:ከልብ ሳያደምጠው ደሙን አፈሰሰ:ሽቅቡን ወረደ:ከመኝታ ስፍራው እ ህ ህ...ታመናል:ታሞአል:አበደ:የሰው ዘር አንድነትን ትቶ:ልዩነትን ይዞ:በከተማው ሲዞር መንገድ የጠፋበት:ምስኪን ከንቱ ፍጥረት እግዜሩ እንዲያየው:ልቦና እንዲሰጠው:በፀሎት አስቡት                               👉ክብር_ሰፈር                                      ታሜ🔥🔥                                    15/10/2014
1 2924Loading...
37
ከምትፈልገው ነገር በላይ፣ ለሚያስፈልግህ ነገር ዋጋ ክፈል።           🔱 @Sela3m @worlds_light @worlds_light join & share
1 0530Loading...
38
ሰላም👋 እስኪ ወደ telegram ቢዝነስ ጎራ በሉ ስለ 💰crypto እና 🪂Airdrop (Notcoin,Tapswap,Hotcoin...) ሙሉ መረጃ ከፈለጋቹ ይህን ቻናል አሁኑኑ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/cryptofarmers https://t.me/cryptofarmers
492Loading...
39
ፕሮግራማችንን ጨርሰናል ክብር በሰማይ ለእግዚአብሔር በረከት በምድር ለሰው ልጆች አስከ አለም ፍጻሜ ይሁን አሜን 🙏🙏🙏🙏 ስትሳተፉ እና ስታገለግሉ የቆያችሁ ዘመናችሁ በተድላ ዕድሚያችሁ በልምላሜ በጌታ ቤት ይልቅ ጌታ ረጅም ዕድሜና ፍጹም ጠና ይስጣችሁ ተባረኩ ዘራቹ የጠላትን ደጅ ይውረስ
1 2160Loading...
40
አሸናፊው 🏆🏆🏆🏅🏅🏅🏅 biruk new😳👏👏👏👏👏👏
1 1011Loading...
Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
Hammasini ko'rsatish...
የእግዚአብሔር ትልቅነት🔥 (ተፃፌ በደግሰው ደነቀ (@Linurlh_Eskanorkegn)) ክፍል አንድ አንዴ ምን ሆነ መሰላችሁ... ይመስለኛል ሁሌት ወይ አንደኛ አመት ተማሪ እያለሁ ግቢ አከባቢ መብራት ጠፍቶ ልጆች ዶርም አከባቢ በጣም ይጯጯሁ ነበር። እና ብዙ ግዜ እንድህ የማድረግ ልማድ ባይኖረኝም መፅሀፍ ቅዱስ ገልጬ መስኮት አጠገብ ጠረዼዛው ላይ ቁጭ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ። የማነበው ክፍል የማቴዎስ ወንጌልን ነበር። እና ምዕራፍ 25 ላይ ያለውን ቃል አንብቤ በጣም በጣም ከምላችሁ በላይ ስለገረመኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮህኩ። ጌታን የምሬን ነው የምላችሁ😁 አጋጣሚ ሆኖ በተማሪዎች ጩሄት ውስጥ ጮህኩ እንጂ ማንም ባልጮሄበት ጮኬ ቢሆን ወይ ደግሞ ማታ ቢሆን እውነት ለመናገር የሆነ ቅጣትማ ይጠብቀኝ ነበር። እስኪ ምን እንዳስጮሄኝ አብረን እንመልከት። ማሳሰብያ:- ከጮሃችሁ ፀሃፊው ለጩሄታችሁ ተጠያቂ አይደለም።😊 ቃሉን አብረን እንየው... ምንአልባት አሁን ላይገርማችሁ ይችላል በኋላ ላይ ግን በሰፊው እናብራራዋለን። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 25) ---------- 31፤ የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ 32፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ 33፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። 34፤ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ዋናው የምንማማረው ቃል ((🔥ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግስት ውረሱ🔥)) የሚለው ነው። Pls አንዴ ፍቀዱልኝና ከማስረዳቴ በፊት ልጩህ😊 ... ስለዚህ ርዕስ ማውራት ከጀመርኩ ማቆሚያ የለኝም😊 በመጨረሻ የገባው አብሮኝ ይጮሃል ማለት ነው። #1 የእግዚአብሔር ትልቅነት ከምድር ስፋት አንፃር ቃሉን ሳንረሳ ከእኔ ጋር አብረን እንፍሰስ! እኛ የሰው ልጆች ነን። እኛ የሰው ልጆች በመጠን ትልልቆች ነን😁 ከጉንዳን፣ ከቁንጫ፣ ከወፍ፣ ከጭልፊት፣ ከዉሻ፣ ከበግ፣ ከፍየል እና ትናንሽ ፍጡራን አንፃር። እኛ የሰው ልጆች በመጠን በጣም ትናንሾች ነን ከዛፎች፣ ከዳገቶች፣ ከባህሮች፣ ከሰማያትና ከከዋክብቶች አንፃር። ታድያ ግን የምንበልጣቸውም ሆነ የምበልጡን ነገሮች የተፈጠሩት ለእኛው ለራሳችን ነው።❤ የገባኝን ነገር ለማስረዳት ትንሽ ስለ ሳይንስ ላውራችሁ። እኛ የሰው ልጆች የምንኖረው በምድር ላይ ብቻ ነው። ለሰው ልጅ ከምድር (Earth) ውጪ ለኑሮ ተስማሚ የሚባል ቦታ እስካሁን አልተገኘም።(ምናልባት ውሃ እና Oxygen የታሸገበት ምንም አይነት ነፋስ እንዳያስወጣ ተደርጎ ከተሰራ እንጂ)። ታድያ ይህቺ ምድር ወይም መሬት መጠኗ ምን ያህል ነው ካላችሁኝ በጣም ትልቅ ነው። አሁን ነገሩን እያከረርን እንመልከት እስኪ ... እንኪ በኪሎ ሜትር እየለካን እንጀምር። ኪሎ ሜትር የምጀምረው ከእርምጃ ነው። ታድያ አንድ ሰው አንድ ሺ ግዜ ብራመድ አንድ ኪሎ ሜትር ደረሰ ማለት ነው። (አንድ ሺ እርምጃ = 1Km) መሬት ደግሞ ድቡልቡል መሆኗን ሁላችንም እናውቃለን እናምናለንም። ድቡልቡል ነገር ላይ ደግሞ የሆነ መነሻ ይዘን በቀጥታ ወደፊት ከሄድን የተነሳንበት መነሻ ላይ ዞረን እንመጣለን። ያ ማለት አንድ ሰው ሁሌቱን እጆቹን ወደጎን ዘርግቶ ቢቆምና ቀኝ እጁን በዘረጋበት አቅጣጫ ምንም ሳያዛንፍ ቀጥ ብሎ ወደፊት ቢሄድ ግዘውና ሰዓቱ ይረዝማል እንጂ ግራ እጁን በዘረጋበት አቅጣጫ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም። (አደራ በሰማይ በምድር እንዳትሞክሩት😁) ታድያ አንድ ሰው ይሄን ልያደርግ ብወስን ምንያህል ግዜ ልፈጅበት ይችላል? ይሄን ካወቅን የምድር ወገብ ምን ያህል እንደምሰፋ ማወቅ እንችላለን ማለት ነው። የተረጋገጠው የምድር ወገብ ርዝመት በኪሎ ሜትር ሲሰላ 40,075Km ነው።(አርባ ሺ ሰባ አምስት ኪሎ ሜትር ነው።) ታድያ ይሄ ተጓዣ በአንድ ቀን አንድ ሺ ኪሎ ሜትር እየተጓዘ እንኳን ቀኝ እጁን ወደዘረጋበት አቅጣጫ ቢሄድ ከ41 ቀን በኋላበግራ እጁ አቅጣጫ ተመልሶ ይመጣል ማለት ነው። ታድያ መሬት ከሰው ልጅ አንፃር ምን ያህል ትልቅ ነች?🤔 (ያ ማለት መሬትን ብንዘረጋትና ከአንድ ሰው ጋር ብናወዳድራት መሬት ምን ያህል ትበልጠን ይሆን?) (የማይጠየቅ ጥያቄ ነው አይደል? ግድ የላችሁም እስኪ እንየው) የሰው ልጅን ቁመት ከምድር ቁመት ጋር አወዳድሩት እስኪ😁 እስኪ ሁላችንም ሁሌት ሜትር እንረዝማለን ብለን እናስብ😁 የምገርመው ሁሌት ሜትር ብንረዝም እንኳን 1 ኪሎ ሜትር መሙላት የምንችለው 500 ሰዎች አንድ ላይ ስንሆን ነው👨‍🏭😄 የምድር ወገብን ለመክበብ ከፈለግን ደግሞ (500*40,075)=(20,037,500) እና ሃያ ቢልዬን ሰላሳ ሰባት ሺ አምስት መቶ ሰው ማለት ነው።😁 by z way የሰዎች ቁጥር አሁን የዚህ ግማሹ ነው። አሁን ላይ ታድያ በምድር ላይ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አንዱን በአንዱ ላይ ብታቆሙት የተዘረጋችን ምድር የቁመቷን ግማሽ አታክሉም፤ አናክልም! ታድያ ይህን ያህል ለምናንስ ለእኛ የሄን ያህል ምድር የፈጠረልን አምላክ በፈጠራቸው እጆች መታዘዙና ለታዘዘላቸው ነፍሶች መሞቱ አይገርምም?😣 #ትልቅነው! ያም ብቻ አይደለም'ኮ የምገርመው። አሁን ባለንበት የዩንቨርስ ክፍልፋይ በሆነው ጋላክሲ ውስጥ 8 ፕላኔቶች አሉ ይባላል እነሱም:- 1. Mercury 2. Venus 3. Earth 4. Mars 5. Jupiter 6. Saturn 7. Uranus ና 8. Neptune ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ትንሿ mercuey (4879 km ስፋት ያላት) ስትሆን ትልቁ ደግሞJupiter ነው ስፋቱም ወደ 139,822km ነው ይህም ከምድር እስከ አራት እጥፍ እንድበልጥ ያደርገዋል። እና እነዚህን ፕላኔቶች ከፀሃይ ቀጥሎ በተቀመጡበት order ነው ከላይ ያስቀመጥኩላችሁ። እስኪ ከፀሃይ ምን ያህል እንደምርቁ በቁጥር እንመልከት። እኛ ራሱ ከፀሃይ አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሚልዬን ስድስት መቶ ሺ(149,600,000Km) ኪሎ ሜትር እንደምንርቅ ታውቃላችሁ?😁 እንግድህ ከዛ ርቀት ነው ምትሞቀን እግዜር ያሳያችሁ😊... ይሄው እስከ ፀሃይ ያላቸው ርቀት:- 1. ከMercury:-  57.9 million km 2. ከVenus: 108.2 million km 3. ከEarth: 149.6 million km 4. ከMars: 227.9 million km 5. ከJupiter: 778.5 million km 6. ከSaturn: 1.43 billion km 7. ከUranus: 2.88 billion km 8. ከNeptune: 4.5 billion km በነገራችን ላይ Pluto ከፕላኔትነት ተሰርዛለች አሁን አሉ የሚባሉት ፕላኔቶች 8 ብቻ ናቸው። የመጨረሻዋ ፕላኔት ግን ከፀሃይ ምን ያህል እንደምትርቅ 😯 (እስከ 7.4 billion ኪሎ ሜትር) ልትርቅ ትችላለች። ከፍጥረቱ እስከ ፍጥረቱ ይህን ያህል ከራቀ ፈጣሪው ምንኛ ትልቅ ይሆን?😯 አቤቱ ትልቅ ነህ እኮ🔥🔥🔥 ከሁሉም በጣም የሚገርመውን ቆይ ላሳያችሁ። ይሄኛው እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ከምያስገርመኝ ነገር መሃል አንዱ ነው። እና ሳይንስ ተብዬው ሰውዬ "አላውቅም" ከምል ብሎ ያስቀመጠውን ቁጥር እንመልከት እስኪ። ጥያቄ:- ዩኒቨርስ ወይም ይሄ አልም ምን ያህል ሰፊ ነው? የሳይንስ መልስ:- 93 ቢልዬን የብርሃን አመት😯 ክፍል ሁለት ይቀጥላል React❤️❤️
Hammasini ko'rsatish...
4🔥 2👍 1
❌የውሸት ማስታወቅያ አይደለም❌ ለመንፈሳዊ ህይወታቹ ጠቃሚ የሆኑ የቴሌግራም ቻናሎችን ልጋብዛቹ። ♥️ስለምወዳቹ ጋብዤአቹሃለው። ተቀላቀሉ በርግጠኝነት ትጠቀሙበታላቹ👍🏼 🟢Join🟢 የሚለውን በመጫን አሁኑኑ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
🟢Join🟢
በጣም ስከፋችሁ ምንድነው የምታደርጉት🥹🥹
Hammasini ko'rsatish...
💊 7
Photo unavailableShow in Telegram
መንፈሳዊ ፊልም የሚመቻችሁ ከሆነ አሁኑኑ JOIN ይበሉ ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇 https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk https://t.me/addlist/RTZLA-fPJHEyOTFk wave ለመግባት👉 @wunuye_bot
Hammasini ko'rsatish...
🎬መንፈሳዊ ፊልሞች🎬
🎬ተከታታይ መንፈሳዊ ፊልሞች🎬
🎬 የኢንግሊዘኛ ፊልሞች 🎬
🎬የአማርኛ ፊልሞች🎬
🎬የኢንግሊዘኛ ፊልም በትርጉም🎬
🎬አስተማሪ መንፈሳዊ ፊልሞች🎬
🎬አዳዲስ መንፈሳዊ ፊልሞች🎬
🎬የቆዩ መንፈሳዊ ፊልሞች🎬
🎬ልብ አንጠልጣይ መንፈሳዊ ፊልሞች🎬
🎬🎬አሁኑኑ ይቀላቀሉ🎬🎬
ማስፈለጌ ገርሞኝ ሆሳዕና ይሉታል ይህንን ልዩ ቀን ሰው በሰው ላይ ወቷል ሊሆን አንድ ነገር አሳዳጊዎቼም ተጣድፈው ወተዋል ንጉሡን ለማየት እጅጉን ጓጉተዋል ገና ከመንጋቱ ይህን ወሬ ሰምተው ምንጣፍ አሰናዱ ዘንባባውን ቆርጠው ለእሱ ሊያነጥፉለት እናያለን ብለው እኔን ግን እኔን ግን ያስታወሰኝ የለም ልሂድ ልቅር ብሎ የጠየቀኝ አንድም እዛው ከጓሮዬ አስረውኝ ሄደዋል ብጮህም ብጣራም የሚሰማኝ ታጥቷል ምንም የአህያ ልጅ ውርንጭላ ብሆን ንጉስን ለማየት እጅጉን ጓጓሁኝ ግን ለተስፋም የሚሆን ኮሽታም አጣሁኝ ግና ግና ከብዙ ሴኮንዶች ከደቂቃ ኋላ ጩኸትም ይሰማል በትልቁ እልልታ በዚህ መሃል ነበር ቤቴ የተንኳኳው በተከታዮቹ እኔው ተወስጄ ምሆነውን አጣው አላፊ አግዳሚው ደሞም ተሳታፊው ስለኔ ይጠይቃል አንዲት የአህያ ልጅ ምን ያደርግለታል ህዝቡ ይባባላል ደቀመዛሙርቱ እኔን ሲጠየቁ ትንሽነቴንም እነሱ ሳይንቁ ለአምላክ ማስፈለጌን ራሱ አወቁ በሄድኩበት ሁሉ ታስፈልገዋለች እያሉ አሳወቁ ሲገርም ላየው የጓጓሁኝ እየሱስ ጌታዬን በእኔው ሊሳፈር ሊቀመጥ መሆኑን ከጎኔ ሰማሁኝ ንጉሥ ተቀመጠ ክብር ሆነ ለኔ ትልቁን ተዓምር አየሁኝ በአይኔ ከማየትም በላይ በእጆቹ ዳበሰኝ እንደማስፈልገው በተግባር አሳየኝ ያለች ይመስለኛል ይቺ ውርንጭላ በእሷ ውስጥ እኔን ልታሳየኝ ወዳ ለንጉሡ እሷ እንዲህ ካስፈለገች የእኔ ምን ሊሆን ነው ድርሻዬን አሰብኩት በእራሱ አምሳል ሙሉ አርጎ ፈጥሮኝ በአዳም በሰራሁት በደሙ አጥቦልኝ በራሴው በደል መስዋዕት ልኮልኝ ለማይገባኝ ለኔ ህይወት የሚሆነኝ እስትንፋሱን ሰቶኝ እንደሚፈልገኝ እንዲህ አሳይቶኝ ታዲያ ታዲያ ታዲያ ለንጉሤ ምን ባደርግለት ነው የሚሆነው መልሴ በሙሉ ህይወቴን ልስጥህ ይኸው እንካ ለራሴ የምለው የምቆርሰው ጊዜ ከእኔ ይትጣ አንተን ብቻ ላውራ አንተን ብቻ ልኑር መላ ሰውነቴ ላንተ ብቻ ይሁን አንተ ብቻ ክበር ላከበርከኝ ላንተ ክብር ነው ምላሼ ይገባሃል ንጉሥ ምስጋና ውዳሴ ለፈለከኝ ላንተ ይሄ ነው ምላሼ ሙሉ እኔነቴን ላንተ ለምስጋና እንዲሆን መስጠቴ ይሄ ነው  ምላሼ።                                               ✍️ ብፅዕት ዘነበ React❤️❤️ Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
Hammasini ko'rsatish...
🔥 8 3👍 1
🎁ዳጎስ ያለ ካርድ የሚያሸልም መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ ውድድር ሊጀመር ስለሆነ በፍጥነት ይቀላቀሉ እንዳያመልጣችሁ🎁👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
🎁ጀምር🎁
🎁Start🎁
ገጣሚያን እንዴት ናቹ የተወደዳችሁ
Hammasini ko'rsatish...
🥰 6 2
አንዲት ሀሳብ ላካፍላችሁና አብረን እናውራ እስኪ.... ከዛ በፊት ግን ይህቺን ግጥም ልጋብዛችሁና በዚህች ግጥም ሀሳብ ተመርኩዘን እናወራለን። ...ሀዘንና ደስታ.... (ግጥም) አንድ አባት ነበሩ እጅግ የከበሩ ከልጆቹም መሀል አንዱ ይጠይቃል ቦታዎች በሙሉ 'ያባቱን ቤት መስሎት ድርሻው እንዲሰጠው 'ባጸንኦት ጠይቆት ነፍሱ መሄድ መርጣ 'ካባቱ ቤት ወጣ አባቱም አዘነ የምያስበው ሁሉ ስለ ልጁ ሆነ . . ከእለታት ባንዷ ቀን ያ .. ኮብላዩ ምስኪን ልጅነትን ትቶ በውጪ ከመኖር ባርነትን መርጦ ከጌታው ጋር መኖር እንደምሻል ገብቶት ከልቡ ተረድቶት እርምጃውን ሁሉ የኋሊት አ'ረገው አባት ከሩቅ አይቶ እጅጉን ደስ አለው ፍሪዳ አርዶለት ልብሱን ቀየረለት ይሄው ስለሆኔ በሰው አለም እውነት ስያጡ እያዘኑ ስያገኙ መደሰት . . ጌታ ሆይ 🤔🤔🤔🤔..... በእግዜር አለም ??? . . ዸጥሮስ ንሰሀ ገብቶ ይሁዳ ስከዳህ አንቴን ምን ተሰማህ?? ስለ ይሁዳ ሀዘኔታ . ወይስ . ስለ ዸጥሮስ ደስታ አንቴ ' ኮ ትልቅ ነህ!!!! በዚህ ምድር ከምገመኝ ነገር መሃል አንዱ የእግዚአብሔር እግዚአብሔርነቱ ውስጥ ሁሉን ቻይነቱ ነው። ከሁሉን ቻይነቱ ውስጥ ደግሞ የዚህን ሁሉ ፍጥረት ስሜት አንድ ላይ ማስተናገዱ ነው። ... በነገራችን ላይ በሰው ፊት ከምያወራው ሰው ይልቅ በሰው ፊት ዝም ያለው ሰው ነው ለእግዚአብሔር ብዙ የምያወራው። ያ ማለት ይሄ ሁሉ ሰው ከእግዚአብሔር ጋራ ያወራል ማለት ነው። አሁን ይሄን ስታነቡት እንኳን ሁላችሁም የሚሰማችሁ ስሜት አንድ አይነት አይደለም። ሁላችንም አሁን ሚሰማንን አውጥተን ብናወራ የስሜት መዋዤቅ ያገኘናል። ምክንያቱም የሁሉም ስሜት አንድ ስላልሆነ። ታድያ ይሄ ጌታ የሁላችንንም ስሜን አንድ ላይ ስሰማ የምሰማው ስሜት ምን ሊሆን እንደምችል አስባችሁታል? እና ይሄ ጌታ ትልቅ የሚል ቃል ብቻ ይገልፀዋል?🤔 ደግሞ'ኮ የምገርመው የእግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ስልጣን መስማት ብቻ አለመሆኑ ነው። ስንቶቻችን ነን በተሰጠን ሰውነት ውስጥ እንድንሰራ የተሰጠን አንድ ነገር ብቻ እንደሆነ የምናውቅ? እሱም ማሰብ ብቻ ነው። ሰው ሀሳብን ብቻ ስራው አድርጎ ተቀብሎ ይሄን ያህል ጭንቀትን ካተረፈ አስቡት እስኪ ... የልብ ትሪታችን ሪትም እኛ እንድንቆጣጠር ቢሰጠን። ምግብ ሲፈጭ  manager ቢንሆን😁 ልብን ደም ቅዳ ደም መልስ ብንለው? የአይን እርግብግቢት.. የሳንባ አየር ቁጥጥር ተላልፎ ለእኛ ቢሰጠን ምን እንሆን ነበር? እግዚአብሔር የራቀ የመሰለን ሰዎች ካለን በህይወት የመኖራችን ጉዳይ ራሱ ትልቅ ማሳያ ነው። እንግድህ ይሄን ሁሉ ነገር በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ሰርቶ ስሜታችንንም ይችለዋል። ሀሌሉያ🔥 ይሄ ታድያ የሰው ብቻ ነው። ወደ እንስሳት ስንሄድ ደግሞ ማሰብያውንም ይረከባል😁 አይ ጌታ.... ክርስቶስን ነው ምላችሁ ይሄን ሁላ ፅፌ ገና ምጀምር ምጀምር ነው እየመሰለኝ ያለው። ለዛሬ እዝህች ጋ ላብቃ .. እስኪ ስለ እግዚአብሔር ትልቅነት እናውራ ጥያቀዬ ይህቺ ናት "ከእግዚአብሔር እግዚአብሔርነቱ ምኑ ይገርማችኋል?" ተባርካችኋል🔥 ተፃፈ በደግሰው (@Linurlh_Eskanorkegn) Subscribe Our YouTube Channel https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
Hammasini ko'rsatish...
6🥰 3👍 2

8🥰 4