cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

መዝሙር ግጥሞች ቤት

ይህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የምንማማርበት Channel ነው !  ወደ ቻናላችን በመቀላቀል 👇 ➲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መፅሐፍትን በPDF ➲ስንክሳር ትምህርቶች ➲ መዝሙራትን በግጥሞች ➲ ኪነ-ጥበብ ➲ ጥያቄዎችን በሐይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ"   ( 2ኛቆሮ -13 ፥ 5)👇 Group ገጽ👇👇 https://t.me/Orthodoxs_Tewahdo_menfeswi_group

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
15 751
Obunachilar
+9424 soatlar
+7367 kunlar
+2 26430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🕊 †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  † 🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊 [ †  እንኩዋን ለሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ዓመታዊ የቅዳሴ ቤት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ] 🕊 † ቅዱስ ሚናስ ምዕመን ሰማዕት † 🕊 ቅዱስ ሚናስ [ ማር_ሚና ] በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም:: ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው:: ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር ፹ [80] ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው:: አባቶቻችንና እናቶቻችን ኢትዮዽያውያን ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው:: ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ [ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው] :- - በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ - በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ - በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ - ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ - በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው:: እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል:: የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ:: በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም:: ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: ቅዱስ ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል:: አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን:: 🕊 [ †  ሰኔ ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ሚናስ [ማር ሚና] ሰማዕት [ቅዳሴ ቤቱ] [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ ፪. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [አፈ በረከት] ፫. ቅድስት እንባ መሪና ፬. ቅድስት ክርስጢና " ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይሕን እጽፍልሃለሁ:: ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ:: ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔርንም የመምሠል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው:: " [፩ጢሞ.፫፥፲፬] (3:14) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
[ ስንክሳር ሰኔ - ፲፭ - ] .mp34.34 MB
●✥ የቤተ ክርስቲያን የጸሎት መፅሐፍ በመባል የሚታወቀው የትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው❓✥●
Hammasini ko'rsatish...
⚪️ሀ. ትንቢተ ኢሳያስ
⚫️ለ. መዝሙረ ዳዊት
🔴ሐ. የሉቃስ ወንጌል
🔵መ. የዮሐንስ ራእይ
📓#አንድጥያቄ ✟ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአብርሃም ድንኳን ለኖህ መርከብ ለያዕቆብ መሰላል ለአዳም ምኑ ናት? ✟
Hammasini ko'rsatish...
⚫️ሀ. ሔዋን
🔴ለ. ቅርበት
🔵ሐ. ተስፋ
⚪️መ. ገነት
Photo unavailableShow in Telegram
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊 ▷  " የዋሃን እነማን ናቸው ! " [   " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! "   ] [                        🕊                        ] ----------------------------------------------- ❝ እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ ፥ ምሕረትን ፥ ርኅራኄን ፥ ቸርነትን ፥ ትህትናን ፥ የዋህነትን ፥ ትዕግሥትን ልበሱ። ❞ [ ቆላስ . ፫ ፥ ፲፪ ] 🕊                        💖                     🕊                              👇
Hammasini ko'rsatish...
[ የዋሃን እነማን ናቸው ! ] .mp35.26 MB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.