የስንኝ ቋጠሮ
Kanalga Telegram’da o‘tish
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Ko'proq ko'rsatish2 046
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
2 046
ምክንያቴ
ድንገት እነሳና ሀዘን እቀዝፋለው፤
ፍርሀት ይሞላኝ እና እርበደበዳለው፤
ጭ……ን…ቅ ይለኛል፤
ጥ……ብ…ብ ይለኛል፤
ሰው የመሆን ጣዕሜን አጣለው፤
ሰው አስቀይማለው ልብን እሰብራለው፤
ግድ የለሽ ሆኜ ወንድሜን ገፋለው፤
#ምክንያቴም_አንድ_ነው።
አንተን ሳላዋራህ ውዬ ያደርኩ ቀን እንዲህ እሆናለው፤
#አባብዬ_ያለ_ህልውናህ_እንዴት_እኖራለው?!
✍…ፂ…የኢየሱስ ልጅ
@abel_gizaw share for us
2 046
" የአባቴ ብልጠት"
አንድ ቀን ወደ ትምህርት ቤት እየሄድኩኝ መንገድ ላይ አስገራሚና አስተማሪ ነገር ገጠመኝ ለሊቱን ዘንቦ ስለ ነበረ(የድሬ ዝናብ) መሬቱ አሸዋማ ቢሆንም አልፎ አልፎ ከጭቃ ጋር እየታገልኩ ስሄድ ሁለት ጎልማሳ ሰዎች ከፊት ለፊቴ ይሄዱ ነበር ። አንደኛው ሁለት ትንንሽ ልጆች ይዛል ልጆቹም ከፊት እየሮጡ አስቸገሩ አባታቸው "ተው ትወድቃላችሁ እኔ ልያዛችሁ" ቢላቸውም አሻፈረኝ አሉ ከዚያ አባትየው ትንሽ አሰላስሎ ለጋደኛው "አሁን እንዴት እደምይዛቸው ተመልከት" አለው ከዚያ አባትየው እየተንገዳገደ "ልወድቅ ነው ልጆቼ ያዙኝ" ብሎ ጭኸ ልጆቹም በፍጥነት አንዱ የግራ እጁን ሌላኛው የቀኝ እጁን ያዙት እርሱም ጠበቅ አርጎ ያዛቸውና ልጆቼ እንዳልወድቅ እጄን አትልቀቁኝ አላቸው እነርሱም እሺ አባዬ አሉት ይሄኔ አባትየው ዞር ብሎ ለጓደኛው አየህ እንዴት እንደያዝኩቸው ትወድቃላችሁ ልያዛችሁ ብላቸው አንወድቅም ብለው ይወድቃሉ ያዙኝ ብላቸው ግን እንይዘዋለን ብለው ይያዛሉ አለው ልያዛችሁ ብዬ ከማልይዛቸው ያዙን ብዬ ብይዛቸው ይሻልል አለው።
በጣም ገረመኝ የአባትየው ብልጠት የሰማዩ አባቴን አስታወሰኝ የልጆቹ መረዳት አባታቸውን መያዛቸው ነው እውነቱ ግን እነሱ በአባታቸው መያዛቸው ነው። አገልግሉኝ ያለን ለካ ሊያገለግለን ፈልጎ ነው! ዘምሩልኝ ያለን ለካ ሊባርከን ፈለጎ ነው! ስጡኝ ያለን ለካ ሊሰጠን ፈልጎ ነው! እንጂማ የትኛውን ጉድለቱን ልንሟላ የትኛውን ደካሙን ለናግዝ " እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።"
(የሐዋርያት ሥራ 17:25) ለካ የሳምራዊቷን ሴት ውሃ አጠጪን ያላት እንደተጠማች አውቆ የህይወትን ውሀ ሊያጠጣት ነው ለካ "ውሀ አጠጪን ብሎ ውሃ የሚጠጣ የአባት ብልጠት" " ኢየሱስ መልሶ።... ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።"
(የዮሐንስ ወንጌል 4:10) እሷማ ምንታርግ ምድራዊ ውሃ የሚለምን ሰማያዊ ውሃ ያጠጣኛል ብላ እንዴት ትጠርጥር የአባቷ ብልጠት አልገባትም "ሊያጠጣ ሲፈልጎ አጠጡኝ እንደሚል "
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡን ከባርነት ቤት ሲያወጣ ያለውን ተመልከቱ " እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው። ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።"(ኦሪት ዘጸአት 8:1) የእውነት ግን እስራኤል ነው እግዚአብሔርን ያገለገለው ወይስ እግዚአብሔር ነው የእስራኤልን ያገለገለው? ማነው መና ከሰማይ ያወረደው? ማነው ደመና ጋርዶ የእሳት አምድ ዘርግቶ ያገለገለው? ማነው በምድረ በዳ ከነክፉ አመላቸው እንደ ንስር በክንፍ የተሸከማቸው? እግዚአብሔር ነው። እነሱማ አስመረሩት እንኩዋን ሊያገለግሉት። ታገለግሉኛላችሁ ብሎ አውጥጦ እራሱ አገለገላቸው ።
የአባቴ ብልጠት አገልግሉኝ እያለ ማገልገሉ፤ አክብሩኝ ያለ ማክበሩ፤ ስጡኝ እያለ መስጠቱ ነው። እኔ በአባቴ ብልጠት ተገርሚያለሁ እናንተስ?
@bamatub

መሆን የምትፈልገውን ሰው ለመሆን እራስህን ሁልጊዜም በተስፋ ሙላው ።
አንተ መሆን የምትፈልገውን ሰው ለማንም ብታስረዳው ማንም ስለማይረዳህ እራስህን ለሰዋች ከማስረዳት ይልቅ ለመሆን ጣር።ሁሉም ሰው መሆን በሚፈልገው ሰው ምክኒያት ሲጣደፍ በሙሉ ልብ የሚሰማህ አይኖርም መሆን ከቻልክ ግን ሳታወራ ይረዱታል ሳትናገር ይፈልጉሀል።
Its not personal !!
When people ignore you or when people don't seems like they don't care about your dreams .....its that you have to be it , for them to believe in it....
You have to believe in yourself...
አንተ በራስህ ልትተማመን እና ህልምህን መሆን እንደምትችል ማመን አለብህ።
አንተ ካላመንከው ማንም አያምነውም
አንተ ካመንከው ግን ሁሉም ያየዋል!።
@bamatub
@bamatub
@bamatub
#እንሞክር
2 046
ኦ ጌታ ሆይ ለውጥ ይምጣ በህይወቴ
አልደግም የትናንቱን ይራገፍ ኮተቴ
ብዙ ተጉዣለው ከጉስቁልናዬ
ይለወጥ ውስጠቴ ግባ ከጓዳዬ
ዲግሪ ማስተርሱን phd ብጨርስ
የሰው ፍየል ሆኜ ሲጋራውንም ባጨስ
ምንስ ይጠቅመኛል ከሱስ ካላወጣ
ወረቀት ብቻ ነው ለውጥ ከላይ ካልመጣ
የአለም ምሁራን የፃፉትን ባነብ
ገንዘቡም ቢበዛ ዙሪያዬንም ቢከብ
ገንዘብ አልጋን እንጂ እንቅልፍን አይገዛ
ሰማያዊ ለውጥ በህይወታችን ይብዛ
መምህር ከመሆን መለወጥ ይቀድማል
ለመለወጥ ደግሞ ማዳመጥ ይበጃል
ቃሉን በማዳመጥ ውስጥን ሲያደርግ ነካ
ቃሉ ቀዳሚ ነው ለመለወጥ ለካ።