HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
Kanalga Telegram’da o‘tish
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
Ko'proq ko'rsatish2 277
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+47 kunlar
+2930 kunlar
Postlar arxiv
🛑ለ12 ዓመታት ደም ይፈሳት የነበረች እናት ታርክ የደም ግብር ፈላጊ ክፉ መናፈስቶች የጬሌ፣ የራሔሎና የአቴተ መናፍስቶች #ethiopia 🙏😰😭🙄
https://youtu.be/dM7cUCOGmrw
🛑ይገርማል! ከአዳልሞቴ፣ ከአመቺሳና ከውቃብ መናፍስት ጋር የተደረገ ትንቅንቅ || በሰኔ ወር የምገበሩ መናፍስቶች #ethiopia #orthodox #eotc 😰😭
https://youtu.be/ma7ryXGwfEw
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የመልእክት ክፍል
“ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።”
[ያዕቆብ 1:14-15]
ጥፋት በሃጢአት ምኞት ይጀምራል.. ያው በሃሳብህ ወይም በልብህ ምኞትህን እየፈጸመኸው ነው.. ከዛ ምኞት በድርጊት ይፈጸማል.. ከዚያም ሞት ይከተላል.. ለዛም ነው በነገራችን ላይ ጌታ ኢየሱስ ሥሩን ሲነካው "ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሯል" ያለን..
ስለዛ ቆንጂትን አይተህ ሰግጠህ ለሌላ ነገር አትመኛት.. ያቺ ምኞትህ ኃጢአትን ጸንሳ ትወልዳለችና.. እንደዚህ ዓይነት አሳብ ከመጣብህና የራስህ ሴት ካልሆነች በቃ ሩጥ ከአካባቢዋ😁😁 እና ጸልይ..
በማንኛውም የሃጢአት ዓይነቶች ላይ ይህንን ተግባራዊ እናድርግ..
መልካም የጌታ ቀን😊🤗
🛑ፍሬያማ ሕይወት መኖር ለምን አቃተን የዲያብሎስ ፈተና መልካም ፍሬ እንዳናፈራ ፍሬያማ ሕይወትን እንዴት እንምራ #ethiopia #orthodox 😭😰🙏
https://youtu.be/o0wZPem5FR0
"የአባታችን የመምህራችን መልዕክት"
በወይን አምባ ማርያም አገልግሎት አቁምያለሁ!
በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
◈ ተወዳጆች ሆይ በእመቤታችን ፍቃድ በወይን አምባ ማርያም ለሁለት ዓመታት በንስሐ እና በቄደር፣ በጥምቀት፣ በቅብዓ ቅዱስ እና በዝክር አብረውኝ ካሉት አገልጋዮች ጋር በሰፊው ስናገለግል ቆይተናል፡፡
◈ በዚህም አገልግሎት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ንስሐ ገብተዋል ቄደር ተጠምቀዋል፡፡ በቁጥር የማናውቃቸው ምዕመናን ጸበል ተጠምቀው፣ ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው ከክፉ መናፍስት እና ከተለያዩ ደዌያት ድነዋል፡፡
◈ በቦታው ላይ በምንዘክራቸው በተለያዩ የቅዱሳንን ዝክር በልተው በቃል-ኪዳኑ በነፍሳቸው፤ በዝክሩ በረከት በሥጋቸው ድነዋል፡፡ ሥራ ያጡ ሥራ አግኝተዋል፣ መካን ሆነው ልጅ ያጡ ልጅ ወልደዋል፣ የተጨነቁት ተጽናንተዋል፣ ብቻ ቦታው ላይ ወለላይቱ እመቤት ብዙ ገቢረ ተአምራት ለልጆቿ እድርጋለች፡፡
◈ በዚህ አገልግሎት እኔ እና አብረውኝ የሚያገለግሉት ምክንያት እንጂ ልጆቿችን በነፍስ በሥጋ ስትፈውስ ስታድን የነበረችው እመቤታችን ናትና ክብሩን እሷ ትውሰድ፡፡
◈ ነገር ግን ለሁለት ዓመታት በቦታው ላይ ስሰጥ የነበረውን አገልግሎት ለእናንተ ይህ ነው በማልላው ምክንያት አቁምያለሁ፡፡ በቅርቡ በሌላ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ስለምጀምር አሳውቃቹኃለሁ፡፡
◈ በተለይ የ ‹‹ወለላይቱ እመቤት›› ማህበርተኞቼ እና በተለያዩ ሀገራት ያላችሁ የእመቤታችን ልጆች በሙሉ ወይን አምባ ማርያም ቤተ ክርስቲያኗ በዕዳ በተያዘችበት ጊዜ፤ ለቤተ ክርቲያኗ የማስፋፊያ ቦታ ለመግዛት፤ ለቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ ንዋየ ቅድሳት እና ለውጭ ለአገልግሎት የሚያስፈልጉንን ነገሮች በሙሉ ካላችሁ እና ከሌላችሁ ላይ ቀንሳችሁ
◈ በገንዘባችሁ ቤተ ክርስቲያኗን ስለረዳችሁ በእውነት ነው የምላችሁ በማገለግላት፣ ስሟን ለመጥራት ከብዶኝ ‹‹ወለላይቱ እመቤት›› በምላት በድንግል ማርያም ስም አመሰግናቹኃለሁ፡፡ ለቤተ ክርስቲያኗ ስላደርጋችሁት በጎ ነገር ወለላይቱ እመቤት ያሰባችሁትን ትፈጽምላችሁ፣ በሕይወታችሁ የተቋጠረውን ትፍታላችሁ፡፡
◈ ሌላው "ለዝክር ነው በዚህ አካውንት አስገቡ" እያሉ በስሜ ከሚነግዱ እና በቤተ ክርስቲያኗ ስም የግል አካውንት እየሰጡ ገንዘብ አስገቡ ከሚሉ እራሳችሁን ጠብቁ!
◈ በሌላ ቤተ ክርስቲያን የምንሰጠውን አገልግሎት በቅርቡ አሳውቃቹኃለሁ፡፡ ወለላይቱ እመቤት በሰፊው አገልግሎት ታገናኘን፡፡
‹‹መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ›› ማቴ 10÷23
ህዳር 1-3-16 ዓ.ም
#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
🛑የተጎዳነው ጠላት የለብኝም ብለን በማሰባችን ነው || ጠላት የለብኝም ብሎ እንደማሰብ ሞኝነት የለም #በማለዳ_ንቁ_2023 #ethiopia #orthodox 😭😰
https://youtu.be/puY9gLj2KVo
🛑ያሳዝናል! የወር አበባን የሚያዛቡ፣ ከባድ የማሕጸን ህመም የሚሆኑ የአተቴ የጬሌ መናፍስቶች || ከባዕድ አምልኮት ሰብሮ መውጣት ያስፈልጋል #ethiopia 😭
https://youtu.be/ibpR85v7l58
🛑በዝሙት መንፈስ መልኩ የሚያጠቁን መናፍስቶች ያላስተዋልነው ከባዱ ጉዳይ የወንድማችን ድንቅ ተሞክሮ ክፍል 21 || የዝሙት አጋንንት #ethiopia
https://youtu.be/zpbwPVGxGi4
😭 የጬሌ መናፍስት ፈተና | ሰይጣንና አጋንንት ማለት የሆነ ሥፍራ ላይ ቆመው የሚያዩን ጠላቶች አይደሉም!
https://youtu.be/3Agzr1UNm38?si=PiYdUt3vIRNcwUKx
🛑ሰዎች በዚህ ዘመን በደመነፍስ ያስባሉ፣ በደመነፍስ ይናገራሉ፣ በደመነፍስ ይንቀሳቀሳሉ ይሄን ተሞክሮ ክፍል 20 አድምጡት በማለዳ ንቁ 2023 😭🙏😭
https://youtu.be/S4gzi7qCyYY
"በቀን 500 እየሰገደች ጠላቷ ዲያብሎስን ያንበረከከች ጠንካራዋ እህታችን የሕይወት ተሞክሮ" https://youtu.be/PCwOZZBDDXo?si=LL0uc6bH8DXqWMJU
🙏 ምዕመናኑ እንዲነቃ እናንተ አልሰማ አላችሁን እንጂ ይሄንን ነበር ስንል የነበረው! እንኳን ከእናንተ አፍ ሰማን ትልቅ ለውጥ ነው!
ይበል ያሰኛል በርቱ!
ሼር አድርጉት!
#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
"ርኩሳን መናፍስትን ለምን ግንባር ላይ ታሰሩ እንላለን? ለሌሎች የመጸልይ ጥበብና በረከት https://youtu.be/DRDGtP92a9A
◈ ንጹሕ ሆነን የረከሰ ምራቅን አለመጠየፍ እንዴት ይቻለናል? ያለ በደል የሚደረግ ውንጀላ እና ግፍንስ "በቃ" አለማለት እንዴት ይሆናልናል? ያለ ጥፋት የሚመጡብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው። እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም። "ተሰሃለኒ እግዚኦ ወበከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" (መዝ 50፥1)
👇👇👇👇
#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
#እንዲህ_እያላችሁ_ስገዱ!
🙏 የተመሰገነ አብ ልዑል ነው (x12)
🙏 የተመሰገነ ወልድም ክቡር ነው (x12)
🙏የተመሰገነ መንፈስቅዱስም ታላቅ ነው። (x12)
◈ እንዲህ እያልን ልዩ ሦስት ለሚሆን አምላክ እንሰግዳለን።
👇👇👇👇
#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
◈ መድኃኔዓለም ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት የሕያው አምላክን ልጅ አሠሩት በቊጣ ጎቱት በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት
ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት
በመኳንንት በሚፈርደው በእርሱ ፈረዱበት።
◈ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን
የእሾህ ዘውድ አቀዳጁት ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው ከፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ እጁን አጽንቶ ፊቱን ጸፋው የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ።
◈ ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው፣ ይህን ያህል ትዕግስት እንደምነ ያለ ትዕግስት ነው፣ ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው፣ ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው።
ቅዳሴ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቊ ፵፮ - ፶፪
👇👇👇👇
#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
