ru
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 367 подписчиков, занимая 5 600 место в категории Религия и духовность и 2 189 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 367 подписчиков.

Согласно последним данным от 26 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 2, а за последние 24 часа — 2, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 20.69%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.92% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 180 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 679 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 18.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 27 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 367
Подписчики
+224 часа
Нет данных7 дней
+230 день
Архив постов
እንኳን ለጥቅምት መድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤ ፤ ስብስብ 1፤ ✤መቅደላ መድኀኔዓለም ✤ባሕር ዳር ድባንቄ መድኄኔዓለም ✤አዴት መድኃኔዓለም ✤አዲስ አምባ መድኃኔዓለም ከ1600 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው በግብፃዊው ጻድቅ አቡነ ሙሴ የተፈለፈለ የዋሻ ገዳም ✤በቅሎ አግት / ዝንጀሮ አስጨብጭብ/ ጨጨሆ መድኃኔዓለም ገዳም ✤ወንጪት መድኃኔዓለም በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግስት ተመስርቶ እስካሁን ድረስ ነብር በቤተ መቅደሱ እየኖረ በሚጠብቀው በታላቁ ወይን እንጨት ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ውስጥ የተሰራ ✤መቀሌ መድኃኔዓለም ✤አድግራት መድኃኔዓለም ወቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ብዙ ድንቅ ታሪክ ያለው ✤ደባርቅ መድኃኔዓለም ✤የሽረት መድኃኔዓለም እጅግ ተደንቀውና ተደምመው ምስጋናዎ ኢምንት ሆናብዎት የሚመለሱበት ✤ኮሶ በር መድኃኔዓለም ✤ሐረር መድኃኔዓለም ✤ምስካበ ቅዱሳን ጻድቃኔ ዋሻ መድኃኔዓለም ገዳም ✤እመኪና መድኃኔዓለም ገዳም በመናኔው ጻድቅ ንጉሥ በአጼ ካሌብ ልጅ በጻድቁ ንጉሥ በአጼ ገብረ መስቀል በ6ኛው መ.ክ.ዘ. የተመሰረተ ታሪካዊ ገዳም ✤በሬ አገር መድኃኔዓለም ገዳም 1000 ሜትር ፍልፍል ዋሻ ገዳም ✤ደብረ ታቦር መድኃኔ ዓለም ✤ደብረ ዘይት መድኀኔ ዓለም ቤ.ክ፤ ደብረ ዘይት ከተማ፤ ባቦጋያ አጠገብ ✤ ናዝሬት መድኃኔዓለም ✤ተከዜ መድኃኔዓለም ገዳም በ11ኛው መ.ክ.ዘ. የላስታ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም /ታላቁ ሐርቤይ/ ደቀመዝሙር እንደነ ነቢዩ ኤልያስና ወንጌላዊው ቅ.ዮሐንስም ሞትን ሳያይ እስከ ምጽዓተ ሐሳዊ መሲህ /ዳግም ምጽአተ ክርስቶስ ዋዜማ/ ድረስ የተሰወረው ጻድቁ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ከሰማይ ተቀብሎ የመሰረተው ንዑድ ክቡር የሆነ መካነ ጸሎት ወአርምሞ ወትኅርምት ✤ሬማ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፦ በ1414 በአባ ኖብ የተመሰረተና የብዙ ቅዱሳን መካነ ጸሎት የነበረ በዘመነ ሱስንዮስ ሰማእትነትን የተቀበለቺው ጻድቅት ወሰማእት ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አጽሟ ያለበትና የከበረና የማይሻር ቃልኪዳኑን ከአምላከ ቅዱሳን የተቀበለችበት እፁብ ድንቅ ሥፍራ ሲሆን የሰማእቷን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን አጽማቸው የሚገኝበት ጥንታዊ ገዳም ______ በኢትዮጵያ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ ፤ 1. ✤ዋሻ መድኃኔ ዓለም አቡነ ሙሴ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም 2. ✤አርብዓሐራ ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም(ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም)፦ ደመ ክርስቶስን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል የተቀበለበትን የብርሃን ጽዋ የሚያጥኑና ሌሎችንም ቅዱሳንን አጽም በንሥር አሞራ የተመሰለ የጌታ መልአክ በቀስተ ደመና ተከብቦ በቀን የሚያመጣበት እልፍ ታሪክና ብዙ የብዙም ብዙ ገቢረ ተአምራት የሚፈጸሙበት ለተፈቀደላቸውና እንደሚገባ ሆነው በቦታው ላይ በበጎ ኅሊና ለሚጸልዩ ምዕመናን ሥውራኑ እየተገለጡ ጥያቄያቸውን የሚመልሱበት ግርማ ያለው ክቡር ንዑድ የ40ዎቹ ቅዱሳን ሰማእታት መካነ ጸሎት የአቡነ ሐራ ግብፃዊ የቃልኪዳን ሥፍራ 3. ✤ጨጨሆ መድኀኔዓለም፤ ወሎና ጎንደር ድንበር ላይ 4. ✤በደሌ ደብረ ሣህል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ ከ100 ዓመት በላይን ያስቈጠረ ጥንታዊ ቤ.ክ. 5. ✤ደሴ መድኃኔዓለም 6. ✤ወዘም ባሕታዊ መድኃኔዓለም፣ ፍቼ አጠገብ ሰሜን ሸዋ ———————————— ✤ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ቤ.ክ ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምወደ.ት. ቅ. ገብርኤል ቤ.ክ ✤ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔዓለም፤ (ታቦተ ሕጉ ባይወጣም በሰዐታትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡)፤ 6 ኪሎ ✤አቃቂ ጋራው መድኀኔዓለም፤ ✤ረጲ መካነ ጎልጎታ መድኀኔዓለም፤ረጲ ✤መንበረ ሕይወት መድኀኔዓለም፤ አቃቂ ክ/ከተማ ✤ደብረ ቅዱስ ደብረ ቀራሜሎስ ካራአሎ መድኀኔዓለም ወአቡነ ገሪማ፤ የካ ክ/ከተማ ✤መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም፤ የካ ክ/ከተማ ✤ቦሌ ቡልቡላ ደብረ ገነት መድኀኔ ዓለም፤ቦሌ ቡልቡላ ✤ድልበር መድኀኔዓለም፤ ጉለሌ (ቶታል) ✤ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ.ክ ልደታ ሜክሲኮ ✤ደብረ ሳሌም ቦሌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን (የመድኀኔዓም ታቦት በድርብነት ይገኛል)፤ ቦሌ ✤ምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኀኔዓም ቤተክርስቲያን፤ቀበና ✤አያት መድኃኔዓለም፤ አያት ✤ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔዓለም፤ደቡባዊ አ.አ ✤ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡ ✤ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል ፡፡ ጎተራ ✤የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ወኢሉጣ ቤ.ክ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፤ ለገሃር ✤ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡ ✤ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም ቤ.ክ (የመድኀኔዓለምና የመብዓ ጽዮን ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ.ክ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ ኮተቤ(ሲምሲ) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል) ---------------------------------- በኢትዮጵያና በአሜሪካ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 7፤ 1. ✤ላፍቶ ሌንቃ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ 2. ✤መድኃኔዓለም ቤ.ክ፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ 3. ✤የቲሊሊ ደብረ ገነት መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን 4. ✤ሚዛን ተፈሪ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን 5. ✤ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም 6. ✤ኒውዮርክ መድኀኔ ዓለም _______

የመጽሐፍ ዳሰሳ የሚዳሰሰው መጽሐፍ ፤ መልክአ መድኀኔዓለም ዘኢረከቡ እና እሰግድ ከ 12፡30 – 2፡30 በፍኖተ ሕይወት ቤተ-መጻሕፍት #orthodox_book_review
የመጽሐፍ ዳሰሳ የሚዳሰሰው መጽሐፍ ፤ መልክአ መድኀኔዓለም ዘኢረከቡ እና እሰግድ ከ 12፡30 – 2፡30 በፍኖተ ሕይወት ቤተ-መጻሕፍት #orthodox_book_review

#ጥቅምት_20_በዓለ_ልደቱ_ለኤልሳዕ_ነቢይ #በዓሉ በእንጦጦ ራጉኤል ይከብራል። ኤልሳዕ የስሙ ትርጒም “እግዚአብሔር ደኅንነት ነው” ማለት ነው፡፡ነቢዩ ኤልሳዕ እጅግ ባለጠጋ የሆነ ሰው ነበር። ከዕለታት በአንደኛ ዕለት በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። የኤልያስ መንፈስ እጥፍ ድርብ ሆኖ አድሮበት ለረጅም ጊዜ እግዚአብሔርን አገለገለ፣ ብዙ ተአምራትንም አደረገ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ኢያሪኮ ከተማ በሚገባበት ጊዜ በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎች ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ እንደመጣ ባዩ ጊዜ “የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው ውኃው ግን ክፉ ነው ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች” አሉት፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ይህን ልመና ለኤልሳዕ ያቀረቡት እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ነገርን ሁሉ መለወጥ እንደሚችል ይታመኑ ስለነበር ነው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሰዎቹን ችግር ከተረዳ በኋላ የከተማውን ሰዎች አዲስ ማሰሮ እና ጨው እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡ ሰዎቹም ኤልሳዕ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አዲስ ማሰሮ በውስጡ ጨው አድርገው አመጡለት፤ ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ ውሃው ምንጭ ወደ አለበት ስፍራ መጥቶ ጨው ጣለበት እና “እግዚብሔር እንዲህ ይላል ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፉ አይሆንበትም” ብሎ ለከተማው ሰዎች ተናገረ፡፡ ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ከዛ ጊዜ ጀምሮ ንጹሕ ውሃ መጠጣት ጀመሩ፡፡ የምድሪቱንም ፍሬ ተመገቡ፡፡ እግዚአብሔር በነቢዩ አልሳዕ ድንቅ ነገር ሰለአደረገላቸው ዘወትር ያመሰግኑ ነበር፡፡ እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች። ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነቢይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት19 ላይ በስፋት ተጽፏል ጥቅምት 20 ልደቱ ሲሆን ሰኔ 20 ቀን ደግሞ በዓለ እረፍቱ ነው።