uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 951 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 316-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 234-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 951 obunachiga ega bo‘ldi.

21 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 408 ga, so‘nggi 24 soatda esa 1 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.79% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.92% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 113 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 742 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 29 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 22 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 951
Obunachilar
+124 soatlar
+1627 kun
+40830 kun
Postlar arxiv
#እንኳን_ለኅዳር_21_ታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_አደረሰን_አደረሳችሁ፡፡ ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/ share እና like ያድርጉ #ኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የምናከብርበት_ምክንያት_፤ ፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6) ፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23) ፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት ፥ በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/ ፬ኛ. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/ ፭ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....) ፮ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡ ፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላ በአንበሳ ውድምና፤ ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡ ፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡ ፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን (ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ቢሆንም) ቅዳሴ ቤት የተከበረበት በመሆኑ፡፡ ———— #ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ድንግል_ማርያም_፤ ፠ ታቦተ ጽዮንን፤ ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤ ✤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡ ፠ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች ፥ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/ ፥ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/ ፥ ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት የቈራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/ ፥ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/ ፥ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/ ፥ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/ ፥ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/ ፥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡ ✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት) በንጽሕናና (በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር) በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7/ ፠ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች ✤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች ናት፡፡ ፠ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነች፤ ✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/ ——- **** በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ምሥጢሩን ከምሥጢር አመሳጥሮ፤ እንደ ሸማ አንከባሎ፥ እንደ ወርቅ ከብልሎ እንዲህ አስቀምጥታል፤ «ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤ ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡ አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤ ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤ ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡ ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ የእመቤታችን ምልጃ አይለየን !ሃገራቸንን ትጠብቅልን አሜን ! #share ያድርጉ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#ኀዳር_17 በዚህች ቀን የዓለም ሁሉ መምህር የሚሆን #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ፍልሰተ_ሥጋው_ሆነ #Share ያድርጉ ፨ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጥሩ ክርስቲያኖች ከነበሩት ከአባቱ #አስፋኒዶስ እና ከእናቱ #አትናስያ ቤ በ347 ዓ.ም ተወለደ፡፡እድሜውም ለት/ት እንደደረሰ ፍልስፍናን የመናገር ክህሎት በአቴና ተማረ፤ በዚህም ከሁሉም በላይ ኾነ፡፡ ከዚህም ቦኃላ በሃይማኖት ተስቦ መንፈሳዊ ት/ትን (ብሉያትንና ሐዲሳትን ፣ ሥርዓተ ቤ/ክርስቲያንን) ተማረ፡፡ ከዚህም ቦኃላ ምንኩስናን ከሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሚሊጢዮስ ተቀበለ በዚህም ጌዜ ገና ወጣት ነበር፡፡ በሄደበትም ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ የገደመበት ስለነበር እርሱንም አገኝው:: ፨በዚህም ገዳም ስሙ ጻድቅ ሲሲኮስ የሚባል ሶርያዊ መነኩሴ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በሚጸልይበት ጌዜ ራእይን አየ ራእዩም ፤ ‹‹ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ቅዱስ ጴጥሮስ መክፈቻን ሲሰጠው ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌልን ሲጠው አየ እንዲህም አሉት እኔ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠን ጴጥሮስ ነኝ ፤በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድር የፈታኸው ደግም በሰማይ የተፈታ ይሆናል ከክብር ባለቤት ከኢየሱስ ክርስቶስ ተልከናል ቅዱስ ዮሐንስም እኔ በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ ወገኖችህን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእሞሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል›› ከዚም ቦኃላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መንፈስ ቅዱስ አድሮበት በዙ መጻሕፍትን ተረጎመ ቅዱስ መልአክም ተግለጦለት በእግዚአብሄር መንግሥት የጸና የብርሃን ዓምድ እንደሚሆን በት/ቱ በዙዎችን እንደሚለውጥና ፣ ስለሚሰጠው የጵጵስና ማዕረግም ነገር፡፡ ፨#በ381 ዓ.ም ዲቁንና ፣ #በ386 ዓ.ም ደግም ቅስናን ተሾመ፡፡ ወንጌልንም ከ386 ዓ.ም እስከ 397 ዓ.ም ድረስ አስተማረ፡፡ በ397 ዓ.ም ኒከታሪዮስ የተባሉት ፓትርያርክ ስላረፉ በንጉሥ #አርቃድዮስ አሳሳቢነት የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ኾኖ ተሾመ፡፡ ፨‹‹ መምህር ወመገሥፅ ዘኢያደሉ ለገጽ ››ማንን የማይፈራ ፊት አይቶም የማያዳላ ፤ ስለነበር ከኤጲስ ቆጰሳት እስከ ነገሥስታት ወገን ይገስጽ ስለነበር በዙ መከራን ተቀብሏል፡፡ የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት የሆነቸው ንግሥት አውዶክሲያን በጥፋቷ ባወገዛት ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጣች ፤ በክፉ ስራቸውም አውግዞ የለያቸውን ኤጲስቆጶሳት በእርሱ ላይ ሰበሰች በአንድ ላይ ሆነው አድራኮስ ወደሞትባል ደሴት አጋዘችው ከዓመታት ቦኃላም ወደ መንበረ ሢመቱ ተመለሰ፡፡ ለሁለተኛም ጊዜ ከመናፍቃን ኤጲስቆጶሳት ጋር በመሆን ወደ አርማንያ ሰደዱት በዚህም ጊዜ ከመንገድ እና ከድካሙ መጽናት የተነሣ #ግንቦት 12 ቀን በ407 ዓ.ም #አረፈ፡፡ ፨የአርቃዴዎስ ልጅ #ቴዎዶስዮስ በነገሠ #የቅዱስ #ዮሐንስን ሥጋ ከዕረፍቱ ከ35 ዓመት ቦኃላ በመዘመርና በማመስገን ወደ ቊስጥንጥንያ አፍልሶ አስመጣው የዕንቊ ፈርጦች ባሉበት የዕበነበረድ ሣጥን ውስጥ አድርገው ወደ ቤተ መቅድስ አስገቡት ከሥጋውም ታለላቅ ተአምራትን ተገለጡ፡፡ ፨ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የአባቱ ስም አስፋኒዶስ ሲሆን አፈወርቅ የሚለው የተሰጠው ሰያም ከአንደበቱ ታፋጭነት ፣ከሚያተምራቸው ምእመናን ፍቅር ነው እንጂ ---የሐዲስ ኪዳኑ ዳንኤል ፣አፈ ዕንቁ፣ ልሳነ ወርቅ ፣ ጥዑመ ልሳንም በመባል ይጠራል :: ---ከ900 በላይ መጻሕፍትን ፣ ከማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ ወደ 90 ት/ቶችን ፣ ከቅዱስ ዮሐንስም ወደ 80 ት/ትን አስተምሯል:: ---ስለ ሥርዓተ ቤ/ክ እና ዕቅበተ እምነትም እና በረካታ ቅዱሳን መጻሕፍትንም ጽፉል ፡፡ በረከቱ ከአኛ ጋር ይደረ ፣ ምልጃው አይለየን ፣ እንደርሱ ያሉ መምህራንን ያብዛል አሜን ! የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ፡፡ #share ያድርጉ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

**በገባሬ ተዓምርነቱ የሚታወቀው ወጣቱ ሰማዕት #ቅዱስ_ሚናስ ዛሬ ኅዳር 15 በዓለ ዕረፍቱ ነው፨ #ዛሬ_የቅዱስ_ቂርቆስ_በዓለ_ልደቱ_ጭምር_ነው:: #ቅዱስ_ሚናስ በመላው ዓለም በተለይ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእጅጉ የሚወደድ ተአምር አድራጊ ነው:: እናቱ ልጅ ስላልወለደች በእመቤታችን በዓል ዕለት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ በዕንባ መልካም ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላት ተማፀነቻት፤ ያን ጊዜ ከእመቤታችን ሥዕል አሜን የሚል ቃል ተሰማ፡፡ ከዚያም ይኽነን ለባሏ ነገረችው፤ ከዚያም እግዚአብሔር የተባረከውን ልጅ በ285 ዓ.ም ላይ ሰጣት፤ ስሙንም ከእመቤታችን ሥዕል “አሜን” የሚል ቃል ስለተሰማ ርሱንም ሚናስ ብለው ሠይመውታል፡፡ የቤተክርስቲያንን ት/ት ተማረ በ12 ዓመቱ አባቱ አረፈ እናቱም ከሦስት ዓመት ቦኃላ ዓረፈች፤ መኳንንቱም አባቱን ይወዱት ስለነበር በአባቱ ቦታ ሾሙት፡፡ —- ዲዮቅልጥያኖስ ክርስቶስን በካደ ጌዜ ቅዱስ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገብቶ ተጋድሎውን ጀመረ፤ ከዕለታት በአንድ ቀን ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን አክሊልን ሲቀዳጁ ተመለከተ ከዚህ ቦኃላ ወደ ከተማ ተመልሶ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ መኰንኑም ቅዱስ ሚናስ ብዙ ተከታዮች እንዳሉት ስለሚውቅ ብዙ ሹመት እንደሚሰጠው ነገርው ቅዱስ ሚናስ ግን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለይ እንድማይችል ነገርው ከዚህም ቦኃላ ብዙ ስቃይ አድርሶበት ስለሰለቸው ራሱን በሰይፍ እንዲቈጥሩት አዘዘ ኀዳር 15 ቀን ሰማዕትነትን ተቀበለ፤ ሦስት አክሊላትንም ተቀዳጀ አንደኛው ስለ ቅድስናው ሁለተኛው ስለብቸኝነቱ ሦስተኛ ደግም ስለ ሰማዕትነቱ ይህንንም ሲቀብል ከጌታችን ድምጽን እየሰማ ነበር፡፡ —— ከዚህም ቦኃላ ብዙ ተአምራትን አድራጓል ፤ መኰንኑ ሥጋውን ወደ እሳት ሲጨምር እሳቱ ፈጽሞ ሥጋውን ሊነካው አልቻለም፣ አውሬዎች ሥጋውን ሊበሉ ባሉ ጊዜ እሣት አውጥታ አራዊቱን አቃጥላለች፡፡ የመርዮጥ አገር ሰዎች ሥጋውን ይዘው ከእስክንድርያም መመልስ በፈለጉም ጊዜ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ከእነርሱ ጋር ለመውሰድ በግመል በጫኑት ጊዜ ግመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ ሁለተኛም ጊዜ ሌላ ግምል በጫበኑት ጌዜ እርሱም የማይነሣ ሆነ ፤ ስዕሉም ሲሳል እንዚህ ሁለት ግመሎች አብረው ይሳላሉ ፤ ሰዎቹም እግዚአብሔር የፈቀደው ቦታ እንደሆነ አውቀው ሥጋውን በዚያው አኖሩት ፤ታላቅም ቤትክርስቲያን ሰኔ 18 ቀን ታነጸለት በዚህምብዙ ተአምራት አድርጓል:: ሰላም ለከ ሚናስ ኅሩይ፥ ዘታዕካ ሰማይ፥ ዘኀረየከ አዶናይ፨ (አዶናይ አምላክ በሰማይ አዳራሽ የመረጠህ ሚናስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን) **በኢትዮጵያ በአተር ቆሎ ብዙ ገቢረ ተዓምራት የሚያደርገው ገዳሞቹ ደቡብ ጎንደር ከባሕር ዳር ከተማ አጠገብ (ከአቡነ ሐራ ድንግል አቅራቢያ) ጢያ ላይ ይገኛሉ፨ በአ.አ. መርካቶ ራጉኤል ጋር ማኅበሩን የሚጠጡ አሉ፤ በሕመም የምትሰቃዩ ማኅበሩን ፈልጋችሁ የአተር ዝክሩን ቅመሱ፥ በእርግጠኝነት ትፈወሳላችሁ፨ በረከቱ ይደርብን ምልጃው አይለየን! አሜን https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#ጾመ_ነቢያት_ (#የገና_ጾም_) የ2013 ዓ.ም. የገና (የነቢያት) ጾም፤ ፠ #ጾሙ_ኅዳር_15_ይጀምራል_!! #Share l ፠ ከ7ቱ አጽዋማት (ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ፍልሠታ፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌ ና ጾመ ገሃድ) መካከል አንዱ ነው፡፡ ፠ ኅዳር 15 ቀን ተጀምሮ እስከ ልደት ለአርባ ሦስት ቀናት የሚጾም ጾም ነው፡፡ ፠ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤ † ፩. #ጾመ_አዳም_፤ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡ † ፪. #ጾመ_ነቢያት_፤ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል:: † ፫. #ጾመ_ሐዋርያት_፤ ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡ † ፬. #ጾመ_ማርያም_፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡ † ፭. #ጾመ_ፊልጶስ_፤ ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡ † ፮. #ጾመ_ስብከት_፤ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡ † ፯. #ጾመ_ልደት_፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡ ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#አንኳን_ለቅዱስ_አግዚአብሔር አብ በዓልና_ለአእላፍ_መላእክት_በዓለ_ሢመት እንዲሁም #ቅዱስ_ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 ጀምሮ እስከ 13 ድረስ ከአምላኩ ምሕረትን ለሚለምንበት) በዓል በሰላም አደረሳቹህ፡፡ ፨ ፨ ፨ #ኀዳር_13 ቀን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሊቃውንት #አእላፍ መላእክት እየተባለ ይጠራል ፤ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከብሩብት ቀን ነው እንዚህም ሥጋ የሌለቸው ረቂቃንና ለዓለም ሁሉ የሚማልዱ ናቸው ፡፡ #Share ያድርጉ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ 100 በክፍለ ነገድ 10 አድርጓቸዋል ፡፡ በ3 ሰማያትና በ10 ዓለማት ላይም ይገኛሉ፡፡ መላእክት ያሉባቸው ከተሞች #ኢዮር #ራማ #ኤረር ይባላሉ ፡፡ አሥሩ ነገዶች ከነአለቆቻቸው አንዲህ ናቸው 1. #አጋዕዝት (ቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል የነበረ ፤ አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ስር ናቸው) 2. #ኪሩቤል (አለቃቸው ቅዱስ #ኪሩብ ፤ ለበለጠ ኀዳር 7 የጻፍነውን ይመልከቱ) 3. #ሱራፌል (አለቃችወ ቅዱስ #ሲራፊ ፤ ለበለጠ ኀዳር 24 ይጠብቁን) 4. #ኃይላት (አለቃቸው ቅዱስ #ሚካኤል ) 5. #አርባብ (አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ) 6. #መናብርት (አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል) 7. #ሥልጣናት (አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ) 8. #መኳንንት (አለቃቸው ቅዱስ ሰዳካኤል ) 9. #ሊቃናት (አለቃቸው ቅዱስ ሰላታኤል) 10. #መላእክት (አለቃቸው ቅድስ አናንኤል) ናችው፡፡ ከእነዚህም ፨ አጋዕዝት ፣ኪሩቤል ፣ ሱራፌልና ኃይላት መኖርያቸው በኢዮር(3ኛው ሰማይ ) ነው ፡፡ ፨አርባብ ፣መናብርትን ሥልጣናት መኖርያቸው በራማ ነው ፡፡ ፨መኳንንት ፣ሊቃናት ፣ መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር ነው (1ኛው ሰማይ ) ———- (ከእልፍ አእላፋት አለቃዎች ስሞች በጥቂቱ)፡፡ ጸሎትነ ትብጻሕ (ሰላም ለክሙ) ለመላእክተ ምሕረት፤ #ሚካኤል_ወገብርኤል፥ #ሱራፌልወኪሩቤል/፬ቱ እንስሳ/፥ #ዑር(ራ)ኤል_ወሩፋኤል /፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ/፥ #ሱርያል_ወፋኑኤል፥ #አፍኒን_ወራጕኤል፥ #ሳቁኤል_ወአቅናኤል፥ #ብርናኤል_ወሱባኤል፥ #ፍናኤል_ወሰላታኤል፥ #ሰዳካኤል_ወኤልናኤል፥ #አናንኤል_ወኢየሩማኤል፥ #ግርማኤል_ወድርማኤል ፥ #ድማህኤል_ወአድማኤል፥ #ሙራኤል_/ምናቴር_አብያቴር/፥ #ሱታ(ስቱ)ኤል_ወሱርያል፤ ……. ፨ ፨ ፨ ፨ የመላእክት ተፈጥሮ እመኀበ አልቦ ኀበ ቦ (ካለመኖር ወደመኖር ) ነው ፡፡ አይራቡም አይጠሙም ፤አይዋለደሙ ፣ አይሞቱም ፣ ዕረፍት የላቸውም ፤ምስጋናቸው እረፍታቸው ፤እረፍታቸው ምስጋናችው ነው አንጂ(አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ) እንዲል፡፡ ተፈጥሯቸው እጅግ ረቂቅ ነው፡፡ ተግባረቸውም ዘውተር እግዚአብሄርን ማመስገን ነው፡፡ —— #መላአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም ፤ ለመዓትም ይላካሉ፡፡ ምሕረትን ያወረዳሉ ፡፡ ልመናን ያሳርጋሉ ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ አንዲዚሁም ሁሉ ወቅትንም የሚቆጣጠሩ አሉ ፤ ስለ ሰው ልጆች ይማልዳሉ (ዘካ 1÷12 ) ምሥጢርም የሚገልፁም አሉ(ዳን 9÷21) መላእክት ተራዳኢም ናቸው (ኢያ 5÷13)፣ እነዳንሰናክል ይጠብቁናል (መዝ 90÷11 ) ፣ያድናሉ ( መዝ 33÷7 ) ፣የፀጋ ስግደትም ይገባቸዋል (መሳ 13÷20) በፍርድ ቀንም ኀጥአንን ከጻድቃን ያለያያሉ (ማቴ 25 ÷31) እነሆ እግዚአብሄር ይፈርድዘንድ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል እንዲል ፡፡ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ፨፨፨ እልፍ አእላፋት ወትእልፊት ቅዱሳን ንጹሐን መላእክት ቆሙ በአገልግሎት ጸንተው በአንድነት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አምላክ በማለት፡፡ ምልጃቸው እና ጠብቆታቸው አይለየን አሜን ፡፡ —————— ኀዳር 13 ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ቦታዎች ጥቂቶቹ፤ ከፎቶ ጋር …. 1. ግሸን ደብረ ከርቤ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (መስቀሉ የሚገኝበት)፤ 2. ጠዳ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (ጎንደር፤ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ)፤ 3. ጎርዶማ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን (በሰሜን ሸዋ)፤ 4. ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (አዲስ አበባ)፤ 5. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) 6. ቦሌ ቡኒ ደብረ ቤቴል ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ #Share ያድርጉ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

በመዲና ከተማችን የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል የሚከብርባቸው ገዳማትና አድባራትን እንጠቁማችሁ፡፡ /ፎቷቸውን ያልለጠፍናቸውና ስማቸውን ያልጠቀስናቸውን እንድትልኩልን በሊቀ መልአኩ ስም እንጠይቃለን) 1) *የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ሾላ፤ መገናኛ) 2) *አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል /ጭቁኑ/፤ ፈረንሳይ 3) *ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል (አዲሱ ሚካኤል)፤ አውቶብስ ተራ 4) *ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል፤ /ቦሌ/ 5) *ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ /ላፍቶ/ 6) *ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል፤ (መካኒሣ) 7) *ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲምሲ) 8) *ደብረ ምሕረት ሚካኤል (ቀድሞ ወህኒ ቤት ሚካኤል) 9) *መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል 10) *ገነተ አምባ ቅዱስ ሚካኤል 11) *ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል 12) *ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ 13) *ሐያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት) 14) *መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም /ኋላ ወቅድስት አርሴማ በሚል እየተጠራ የሚገኝ/፤ (በቀጨኔ በአዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ጉብታ ላይ የሚገኝ) እንዲሁም በድርብነት 15) *እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት 16) *መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (ስድስትኪሎ) 17) *ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ (መስቀል አደባባይ) 18) *ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ቤ.ክ (ኋላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል በሚል እየተጠራ የሚገኘው)፤ (ኢምግሬሽን አጠገብ) 19) *ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ (ኋላ ወመካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም በሚል እየተጠራ የሚገኝ)