uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 042 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 280-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 240-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 042 obunachiga ega bo‘ldi.

29 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 518 ga, so‘nggi 24 soatda esa 1 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.50% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.35% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 090 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 660 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 33 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 30 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 042
Obunachilar
+124 soatlar
+917 kun
+51830 kun
Postlar arxiv
እንኳን ለታላላቆቹ አባቶች ለአቡነ ዓቢየ እግዚእና ለአቡነ ዮሴፍ ዓመታዊ በዓል (ግንቦት 19) በሰላምና በጤና አደሳችሁ፡፡ /#በጻድቃን_ተዓምራት_ማድረግ_ለምትጠራጠሩ፤ #ጻድቃን_ከበዓለ_ዕረፍታቸው_በኋላ_ዛሬም_ከማማለድም_አልፈው_በቃልኪዳናቸው_ተዓምራት_እንደሚያደርጉ_ኑና_እዩ_ተመልከቱ፡፡ ተዓምራትን ማየት ለምትፈልጉ ኹሉ ሂዳችሁ እዩ!!!!!)፡፡ ክብረ በዓላቸው (የአቡነ ዓቢየ እግዚእ በተንቤን መረታ ደብረ መድኃኒት፣ በጎንደር ከተማ ጥንታዊ በኾነው በዓቢየ እግዚእ ኪዳነምሕረት፣ በመቀሌ እንዳ ገብርኤል /እንዳ አቡነ ዓቢየ እግዚእ/፣ በአዲስ አበባ ሞጆ አካባቢ ባለው ቤ.ክ በድምት ይከበራል፡፡) እንዲሁም (የአቡነ ዮሴፍ በላስታ ላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኘውና ወደ ላለበላ የሚጓዝ ኹሉ ሊያየው በሚችል በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና በኢትዮጵያ በከፍታ ከራስ ደጀን ተራራ ቀጥሎ በሚገኘው የዋሻ ገዳማቸው ይከበራል)፡፡ ሁለቱም ቅዱሳን አስካሁን ጊዜ ድረስ የሚታይ ባለ አስደናቂ የቃልኪዳን ተዓምራት አላቸው፤ አቡነ ዮሴፍ ከላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ገዳማቸው ጭላዳ እህል ጠባቂ ሳያሻው እህል እንዳይበላ ገዝተውታል፤ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ቦታ (ለምሳሌ በጎንደር ከተማ) አሁንም ድረስ ጅብ እንስሳቶችን እንዳይበላ ገዝተዋል፡፡ #አቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋቱ (በወሎ ላስታ ሰውንና ዝንጀሮን በቃልኪዳን ያስተሳሰሩ #እስከዛሬ_ድረስ_ዝንጀሮ_እህል_እንዳይበላ_የገዘቱ፤ እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው፤ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑ (እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባና አቡነ ዘርዓ ቡሩክ) ናቸው፤ ገዳማቸው በላሊበላ በቅርበት አቡነ ዮሴፍ ተራራ ተብሎ በሚጠራ ተራራ ቦታ ላይ የዋሻ ቤ.ክ አላቸው፡፡ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ_፤ አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጕመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው:: ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኵሰዋል:: በገዳሙ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር:: ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ:: ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000 በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይህም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል:: ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሰል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይህንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጉዋል:: ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው፥ 3 ሙታንን አስነስተው፥ ብዙ ድውያንን ፈውሰው፥ ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው፥ የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው፥ በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው:: ** አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን:: ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው በ Facebook, Email, Viber, Xender, Bluetooth በማድረስ ይተባበሩ፡፡ ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡ /ሥርዐተ ማኅሌቱን ሳንለጥፍ በማዘግየታችን ይቅርታ፡፡/

መልአከ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ከዘመን መንሱት፤ ከዕለት እኪት አድነን፡፡ መልአኬን አታስቈጡት!!፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በቀረቡ የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠልና …. በሰማን ጊዜ ይህን ጻፍን፡፡ (የዛሬው የደብራችን ውሎ ይህን ይመስላል)፡፡

ንዑ ንሑር ኀበ ደብረ ይባቤ፤ ንዑ ንሑር ኀበ ዉሉደ ያሬድ፡፡ ደብራችንን ጨምሮ በሃገር ውስጥና በውጭ ሲካሄዱ ለነበሩት በግንቦት ወር ለተካሄዱት የ‹‹ዝከረ ቅዱስ ያሬድ›› መርሐ ግብሮች ማጠቃለያ የሚሆነውን መርሐ ግብር እሑድ ግንቦት 18 በደብረ ይባቤ በዉሉደ ያሬድ ሰ/ት/ቤት ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በመገኘት በአንድነት እናክብር፡፡ እግረ መንገዳችንንም የወንድሞቻችንንና እኅቶቻችንን የዉሉደ ያሬድ ሰ/ት/ቤት 50ኛ ዓመት የምሥረታ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አብረን እናከብር፡፡ /ቦታው፤ ጎተራ አጎና ሲኒማ ጋር ነው፡፡/

የሐምሌ 25 መርቆሬዎስ፤ የ2ቱ አባቶቻችን ዕርቅ ቀን፤ የደስታችን ቀን ትውስታ፡፡ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ይመስገን፡፡

#130ኛ_ሳምንት_የዐርብ_ጕባኤና_የኪዳነ_ምሕረት_ማኅበር #ዐርብ_ግንቦት_16/፳፻፲፩ዓ.ም. ከ፲፪-፪ ሰዓት፤ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል:: ትምህርት ይሰጣል፤ ጠበል ጠዲቅም በየወሩ እንደሚደረገው ይደረጋል፡፡

ዜና ዕረፍት የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜንና ደቡብ ቀይ ባሕር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የ76ት ዓመቱ አረጋዊ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ዐርብ በአሥመራ ዐርፈውሥርዓተ ቀብራቸው ማክሰኞ በአስመራ ርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የገዳማት አበምኔቶች፣ የደብር አለቆች፣ መነኰሳት፣ ካህናት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ቊጥራቸው በርካታ የሆነ ምዕመናን በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡ በረከታቸው ይድረሰን፡፡

#130ኛ_ሳምንት_የዐርብ_ጕባኤና_የኪዳነ_ምሕረት_ማኅበር #ዐርብ_ግንቦት_16/፳፻፲፩ዓ.ም. ከ፲፪-፪ ሰዓት፤ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል:: ትምህርት ይሰጣል፤ ጠበል ጠዲቅም በየወሩ እንደሚደረገው ይደረጋል፡፡

‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በግንቦት ፰/፳፻፲፩ ዓ.ም. ጋብቻሽን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም የፈጸምሽው የሰ/ት/ቤታችን አባል እኅታችን፤ #ሕሊና_ግዛቸው_ከኢዮብ ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

፪ኛ. የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን የሚደረገው ይህ ርክበ ካህናት ነው፡፡ በዚህ ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያደርገው ጕባኤ የሚተላለፉ መመሪያዎችና የሚጸድቁ ውሳኔዎች ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት፣ ለምእመናን አንድነት፣ ለአገር ሰላምና ደኅንነት የሚጠቅሙ ይሆኑ ዘንድ ሁላችንም በጾም በጸሎት እግዚአብሔርን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ አምላካችን ቤተ ክርስቲያናችንንና አባቶቻችንን ይጠብቅልን፤ እኛንም ለአባቶች የሚታዘዝ ልቡና፣ ሓላፊነታችንን የምንወጣበትን ጥበብና ማስተዋሉን ያድለን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ይህንን ታላቅ ጕባኤ ይባርክ ይመራ፤ እኛንም ይጎብኘን፡፡ /ምንጭ፤ የቃል ትምህርት በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ላይ የተደረጉ ትምህርቶች ዝክረ ቅዱሳን የፌስ ቡክ ገጽ የማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ ሐመር መጽሔት/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

#ርክብ_ካህናት (#ዕለተ_ጥብርያዶስ፤ #ዳግሚት_ዕለተ_አግብኦተ_ግብር፤ የሃገራችን የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ ቀን)፤ ግንቦት 14 /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ ርክበ ካህናት የሁለት ቃላት ጥምረት ሲኾን እነዚህም፤ **1ኛ. ረክብ የሚለው ቃል ተራከበ ተገናኘ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጕሙም ማግኛ፣ መገኛ፣ መገናኛ ማለት ነው፡፡ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፰፴፩/፡፡ **2ኛ. ክህነት የሚለው ቃል ከዲቁና ጀምሮ እስከ ከጵጵስና ድረስ ያሉትን መዓርጋት (በጥቅሉ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትንም ኾነ ጳጳሳትን) የሚያጠቃልል ስያሜ ነው፤ ካህን (ነጠላ ቍጥር) ሲኾን ካህናት ደግሞ (ብዙ ቍጥር) ነው፤ ብዙ ጊዜ ግን ይህን ባለማወቅ ካህናት የሚለውን ለቀሳውስት ብቻ መጠሪያ ሲኾን እናያለን፤ አለማወቅ ነው (ለምሳሌ በቅዳሴ መጨረሻ ጊዜ ዲያቆኑ በእደ … ካህን ይባርከነ ቢል ለኹሉም ያስኬዳል ሰዋስዉም ያዛል ሥርዐቱም ይኸው ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ዛሬ በእደ … ካህን ይባርከነ በማለት ፈንታ በእደ ብፁዕ ፓትርያርክ፣ በእደ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ፣ በእደ ቆሞስ…. ሲባል ይታያል፤ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ነው፡፡) ርክበ ካህናት ማለትም የአባቶች ካህናት (ማለትም በጵጵስና ማዕረግ ያሉ /ኤጲስ ቆጶሳት፣ ጳጳሳት፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስን ያጠቃለለ (የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት) ጕባኤ፤ የካህናት መገኛ መገናኛ ጉባኤ (መሰባሰቢያ፣ መወያያ) ማለት ነው፡፡ በዓሉ በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን ሁልጊዜ በዕለተ ረቡዕ ይውላል፤ ወሩና የሚውልበት ቀን ግን በኢየዓርግና በኢይወርድ (በባሕረ ሓሳብ የበዓላትንና የአጽዋማትን ቀመር ተከትሎ) የሚወጣ ስለኾነ ከፍና ዝቅ ይላል፡፡ የአጽዋማትና የበዓላት ቀመር በቅዱስ ድሜጥሮስ አማካኝነት ከመዘጋጀቱ በፊት (ዐቢይ ጾም ሰኞ፣ ስቅለት ዓርብ፣ ትንሣኤ እሑድ፣ ርክበ ካህናት ረቡዕ፣ ዕርገት ሐሙስ፣ ጰራቅሊጦስ እሑድ እንዲሆን ከመደረጉ በፊት) ርክበ ካህናት በየዓመቱ ግንቦት ፳፩ ቀን ይውል ነበር /መጽሐፈ ግጻዌ ግንቦት ፳፩/፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በየጸጋቸው መጠን እየተገለጠ ያጽናናቸው፥ ያጸናቸው፥ ያስተምራቸው፥ ይባርካቸውም ነበር፤ ጌታችን እስከ ዕርገቱ ባሉ ፵ ቀናትም መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትምህርተ ኅቡዓትን፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን አስተምሯቸዋል፤ በልቡናቸውም አሳድርድሮባቸዋል:: በመጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል ከዕርገቱ አስቀድሞ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ፫ ጊዜ በጕባኤ መገለጡ ተዘግቦ ይገኛል፡፡ እነዚህም፤ 1. የትንሳኤ (ዮሐ. 20፥19) 2. የአግብኦተ ግብር (ዳግም ትንሳኤ) /ዮሐ. 20፥:26/ 3. የጥብርያዶስ፤ (ዮሐ. 21፥1) ለድንግል ማርያም ግን በኹሉም እለታት መገለጡን አበው ያስተምራሉ፡፡ በጥብርያዶስ ባሕርም ከዐሥራ አንዱ ቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ምሳ በልቷል፡፡ የርክበ ካህናት በዓል መነሻም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከተገለጠበት ከጥብርያዶስ ባሕር ካለው ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በዚህች ዕለት በቅዱስ ዼጥሮስ መሪነት ሐዋርያቱ ወደ ጥብርያዶስ ባሕር ሔዱ፡፡ አሶችን ሊያጠምዱም በብዙ ደከሙ፤ ነገር ግን ጌታችን በረድኤት አብሯቸው አልነበረምና አንዳች አሣ በመረባቸው ሊገባ አልቻለም፡፡ ማጥመድ (አስተምሮ ከክህደት ወደ ሃይማኖት፤ ከኀጢአት ወደ ጽድቅ መመለስ) የሚቻለው በረድኤተ እግዚአብሔር እንጂ በእውቀት ብዛት ወይም በአንደበተ ርቱዕነት ብቻ አይደለምና፡፡ ሲነጋ ግን መድኀኒታችን ወደ ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ መጣ፤ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻም ቆሞ ታያቸው፤ ከሚወደው ደቀ መዝሙሩ ከቅዱስ_ዮሐንስ በቀር የለየው ግን አልነበረም፡፡ ቸሩ አባት "ልጆቼ! አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁ?" ሲል ጠየቀ፤ "ጌታ ሆይ! የለም" አሉት፡፡ "የለንም" ብሎ የሌለንን ነገር በጌታ ፊት ማመኑ እጅግ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ያጣነውን ነገር ያን ጊዜ ሊጠቁመን ቸርነቱ ብዙ ነውና፡፡ ያን ጊዜ ሐዋርያቱን መረባቸው በመርከብ ቀኝ እንዲጥሉ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም በደስታ ጣሉ፤ በአግራሞት እስኪሞሉ ድረስ መረባቸውን መሳብ አቅቷቸው ሊቀደድ እስኪደርስ ድረስ 153 ዓሦች ተያዙላቸው፡፡ ያን ጊዜም የሚወደው ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችን መኾኑን ለቅዱስ ዼጥሮስ "ጌታ እኮ ነው" አለው፤ ሽማግሌው ቅዱስ ግን ራቁቱን ነበርና ወደ ባሕሩ ተወረወረ፡፡ ከአፍታ በኋላም ጌታችን ከሐዋርያቱ ጋር በድጋሚ (ለ፪ኛ ጊዜ) ለምሳ ተቀመጠ፤ ባርኮ ሰጥቶ ልባቸውን ሊያጸና አብሯቸው በላ፡፡ በዚያች ሰዓት ቅዱስ ዼጥሮስን ፫ ጊዜ "ትወደኛለህን?" ሲል ጠየቀው፤ ቅዱሱ አረጋዊም እየደጋገመ "ለሊከ ተአምር ከመ አነ አፈቅረከ (እንድወድህ አንተ ታውቃለህ)" ሲል መለሰ፡፡ ጌታም በበጐች ሐዋርያት (ካህናት)፤ በጠቦቶች አርድእት (ዲያቆናት)፤ በአባግዕት ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት (ምዕመናን ወምዕመናት) ላይ ሁሉ እረኛ እንዲሆን ሾመው፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው ጌታችን ሐዋርያትን፣ ሰብዐ አርድእትንና ሠላሳ ስድስቱን ቅዱሳት አንስት በአጠቃላይ መቶ ሃያውን ቤተሰብእ እንዲጠብቅና እንዲከባከብ ቅዱስ ጴጥሮስን ማስጠንቀቁን፤ ፍጻሜው ግን የቤተ ክርስቲያን አባቶች (ጳጳሳት) መምህራንንና መላው ሕዝበ ክርስቲያንን እንዲጠብቁና እንዲያስተዳድሩ በእግዚአብሔር መሾማቸውን የሚያስረዳ ትርጕም አለው /ዮሐ.፳፩፥፩-፲፯ (አንድምታ ትርጓሜ)/፡፡ ቀጥሎም የቅዱስ ጴጥሮስን የሰማዕትነቱን ምሥጢር ገልጦለት "ተከተለኝ" (ለጊዜው በእግር፤ በኋላ ግን በግብር ምሰለኝ) ብሎታል፡፡ ወልደ ነጐድጓድ ወፍቊረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስም ሞትን እንደማይቀምስ እንዲሁ ተናግሮለታል:: ጌታ ለሐዋርያት በአንድነት የተገለጠባትን ይህች ቀን እነዚህ ሁሉ ተግባራት የተከናወኑባት ናትና (የትንሣኤ በዓል ፳፭ኛ ቀን) መሠረት በማድረግ፤ የኋላ ሊቃውንት በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን ዐራቱ ሊቃነ ጳጳሳት የሚሰበሰቡበት የካህናት መገናኛ ቀን ርክበ ካህናት ይሁን ብለው ወስነዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ርክበ ካህናት በዓለ ትንሣኤ በዋለ በ፳፭ኛው ቀን፣ በበዓለ ሃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ ይዘከራል፤ በያዝነው ዓመት በ፳፻፲፩ ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ከተከበረበት ዕለት (ሚያዝያ፳ ቀን) ጀምሮ ብንቈጥር ፳፭ኛው ቀን ግንቦት ፲፬ ቀን ይኾናል፡፡ በመኾኑም የዘንድሮው ርክበ ካህናት ሚያዝያ ፳፬ ቀን በዕለተ ረቡዕ ይውላል ማለት ነው፡፡ ይህ በዓል ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የቆዩ አባቶቻችን ጌታንና ደቀ መዛሙርቱን አብነት በማድረግ በጋራ በመሰባሰብ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተቀላጠፈ አገልግሎት እንደዚሁም ለምእመናን አንድነትና መንፈሳዊ ዕድገት የሚበጁ መንፈሳውያን መመሪያዎችን የሚያስተላልፉበት እለት ነው፡፡ ይህንን የጌታችን ትእዛዝና የሐዋርያትን ሥልጣነ ክህነት መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ጉባኤ ያደርጋል፤ ፩ኛ. የመጀመሪያው ጉባኤ ጥቅምት ፲፪ ቀን (የቅዱስ ማቴዎስ በዓለ ዕረፍት) ሲሆን፣